
12/24/2020
ሀብታሙ አያሌው
መንግስታዊ ነውር - እንዲህ ተጋልጧል !
****************
ጠቅላይ ሚንስትሩ በመተከል ባደረጉት ስብሰባ … ይህ በፎቶ የሚታየው ሰው … በአሻድሊ መልማይነትና አቅራቢነት በጠቅላይ ሚንስትሩ ይሆንታ በአዳራሹ ከ30 ደቂቃ በላይ አደገኛ የጥላቻ መልዕክት አስተላለፈ። እንዲናገር የተደረገውም ጋቢ ለብሶ የአገር ሽማግሌ በሚል ስም ነው።
ሰውዬው አቶ ሰብስቤ ንጻጼ ይባላል … ቀደም ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበረ፤ ከዚያ ቀደም ብሎ የክልሉ ውሃ ሃብት ቢሮ ኃላፊ ሆኖ የሰራ ቅልጥ ያለ የህወሓት ስሪት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ካድሬ የነበረ፤ አሁን የነሽመልስ አብዲሳ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆኖ የብልፅግና ጋቢ የለበሰ ነው ።
በተመደበበት መድረክ ሽማግሌ መስሎ ተውኖ ብቃቱን አሳይቷል። ባልደረባዬ ኤርሚያስ ለገሰ Ermias Legesse Wakjira በኢትዮ 360 የዛሬ ምናለ ፕሮግራም ስለ ሰውዬው ንግግር እና አንድምታው በዝርዝር አንስቶ ይህ ሰው ለመድረኩ ዓላማ ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ጋቢ አልብሰው ቢያቀርቡትም የአገር ሽማግሌ ብሎ መውሰድ አይቻልም ሲል ጥርጣሬውን ገልፆ ነበር።
ባልደረባዬ ብሩክ ይባስ Biruk Yibas በነበረው መረጃ ሰውዬው የቤንሻንጉል ክልል ምክርቤት አባል የነበረ መሆኑን ጠቁሟል። በመድረኩ ያንን አደገኛ ጥላቻ ሲዘራ ጠቅላይ ሚንስትሩም ከማስተካከል ይልቅ በዝምታ ያለፉት የአገር ሽማግሌ መስሎ የተወነው ሰው በመጨረሻም ጋቢው ተገልጦ እንዲህ ተጋልጧል።