TGEthiopianTelevision

TGEthiopianTelevision TG Ethiopian Television is dedicated to provide accurate information to all Ethiopians around the globe.

Ethiopian media

Mission: TG Ethiopian Television is dedicated to provide accurate information to all Ethiopians around the globe.

06/08/2019

እድገት በህብረት ዘመቻ...
ተማሪዎች ወደ እድገት በህብረት ዘመቻ ሲሄዱ ከ40 ዓመት በፊት የተነሳ ቪዲዮ ነው። Ethiopiawinet በሚል የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው ያገኘሁት። ከእናታችንን ጋር ሆነን ታላቅ ወንድማችንን ስንሸኝ አየሁ…በጣም አስገራሚ ቪዲዮ!

06/06/2019

መንግስትን እንቃወማለን እያላችሁ ሀገራችንን በሚጎዳ መንገድ የምትዋሹ እግዚአብሔር ልቡን ይስጣችሁ፡፡ የህዳሴ ግድቡ አልቆመም! የፋና ቲቪ ዜናን ያንብቡ.....

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር ሳይንስን ተከትሎ እንዲሰራና ከፓለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲላቀቅ መደረጉ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር ሳይንስን ተከትሎ እንዲሰራ እና ከፓለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲላቀቅ መደረጉ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ኢንጂነር አብርሃም በላይ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የስራ እንቅስቃሴ ያለበትን ሁኔታ ጎበኝተዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሥራ እንቅስቃሴ ከጎበኙ በኋላ እንደገለፁት፥ ግድቡን ከገጠመው የስራ መቀዛቀዝ ማላቀቅና ያጋጠሙ ችግሮችን በፍጥነት መፍታት የተቋሙ ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

ግድቡ በህዝብ ተሳትፎ የሚገነባ መሆኑን ያነሱት ዶክተር አብርሃም፥ በአሁኑ ወቅት ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር ሳይንስን ተከትሎ እንዲሰራ መደረጉንና ከፓለቲካ ጣልቃ ገብነት መላቀቁን ጠቁመዋል።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስራ እንቅሰቃሴ በየወሩ ያለበትን ደረጃ ለመከታታልና የሚጠበቁ ድጋፎችን ለማድረግ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ፕሮጀክቱ ሙያዊ እይታ እና አመራር እንዲኖረው ከመደረጉም ባለፈ ያጋጠሙ ችግሮችን በጥናት በመለየት ምላሽ እንዲያገኝ መደረጉንም ዋና ስራ አስፈፃሚው አንስተዋል።

በተለያዩ አካላት ፕሮጀክቱ ቆሟል በሚል አፍራሽ አሉባልታዎች እየተናፈሱ እንደሆነ የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ እውነታውን እያወቁ የሚሸፋፍኑና የሚሰራውን ስራም እንዳልተሰራ አድርገው በማህበረሰቡ ውስጥ ውዥንብር ለመፍጠርና ፖለቲካዊ ገፅታ ለማላበስ የሚንቀሳቀሱ አካላት ምኞት ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ፕሮጀክቱ ከነበረበት ችግር ተላቆና ሳይንሳዊ መፍትሄ አግኝቶ በየጊዜው ስራዎች በስፋትና በጥራት እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል።

ከዚህ አይነት ጨዋታ በመውጣት እውነትን መሸሸግ የፈለጉ አካላትን ማሸነፍ የሚቻለው እውነተኛ መረጃ ለህዝቡ በማቅረብና በተፋጠነ መንገድ በግድቡ ግንባታ ላይ አተኩረን በመስራት ነው ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚው።

በመሆኑም ግድቡን በተያዘለት መርሃ ግብር ለማጠናቀቅ ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ቀደም ሲል ለሲቪል ስራው መጓተት ምክንያት የነበረው የሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸርና የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎችን በጥልቀት በመፈተሸ በርካታ የጥራትና የጊዜ መጓተት ችግሮች በመኖራቸው የነበረው ውል እንዲቋረጥ መደረጉን ዶክተር አብርሃም አስታውሰዋል።

አሁን ግን በዘርፉ ላይ ብቃትና ልምድ ካላቸው ተቋራጮች ጋር የኮንትራት ማሻሻያ በመፈፀም የፋብሪካና ተከላ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

የፕሮጀክቱ ስራ አንድም ቀን አለመቋረጡን ማንም ሰው በቦታዉ ተገኝቶ ማረጋገጥ ይችላል ነው ያሉት ዶክተር አብርሃም።

ፕሮጅክቱ የሀገርም የመንግስትም ቀዳሚ የትኩረት ማዕከል በመሆኑ ከፋይናንስ እስከ ግንባታ ክትትል ድረስ ቅደሚያ አግኝቶ እየተመራ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፋፃሚው፥ በየወሩ የስራ እንቅስቃሴውን በመስክ ምልከታ ክትትል እና ቁጥጥር የሚያደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአሁኑ ጉብኝታቸው በአራት ወራት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቁመዋል።

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ከነበሩበት ችግሮች ተላቆ ትክክለኛ መስመር ላይ የሚገኝ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት የወሰደው እርምጃም አሁን ለሚታየው የሥራ ለውጥ መሰረት መሆኑን ነው የተናገሩት።

06/06/2019

የነቀምቴ ከተማው ተጫዋች ወንድወሰን ዮሐንስ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ህይወቱ አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የነቀምቴ ከተማው ተጫዋች ወንድወሰን ዮሐንስ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ህይወቱ አለፈ።

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ እየተወዳደረ የሚገኘው የነቀምቴ ከተማ ተጫዋች የሆነው ወንድወሰን ዮሐንስ በትላንትናው ዕለት በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት ህይዎቱ አልፏል።

በነቀምቴ ከተማ ፋክት በተሰኘ ሆቴል በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ከደረሰው የሞት አደጋ በተጨማሪ ሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማው ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ጥቃቱን የፈጸሙት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጿል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ሰዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል።
‎ምንጭ -ፋና ቲቪ

አቶ ተወልደ ገብረማርያም የዓለም አቀፉ አየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) የ...
06/06/2019

አቶ ተወልደ ገብረማርያም የዓለም አቀፉ አየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) የቦርድ አባል ሆነው እንደገና ተመርጠዋል። IATA በዓለም ላይ ከሚገኙት አየር መንገዶች ውስጥ 290 አየር መንገዶችን (82% total air traffic) የሚወክል ድርጅት ነው።
በዓለም ላይ ካሉት ታላላቅ የአየር መንገድ ሃላፊዎች የተካተቱበት የቦርድ አባሎች የሚከተሉት ናቸው።

Chair of the Board

1. Mr Carsten Spohr
Chairman and
Chief Executive Officer
LUFTHANSA

Members
2. Mr Vitaly Saveliev
Director General and CEO
AEROFLOT

3. Mr Calin Rovinescu
President and
Chief Executive Officer
AIR CANADA

4. Ms María José Hidalgo
Gutiérrez
Chief Executive Officer
AIR EUROPA

5. Mr Benjamin Smith
Chief Executive OfficerAIR
FRANCE / KLM

6. Mr Yuji Hirako
President and Chief Executive Officer
ALL NIPPON AIRWAYS

7. Mr Douglas Parker
Chairman and Chief Executive Officer
AMERICAN AIRLINES

8. Mr Rupert Hogg
Chief Executive Officer
CATHAY PACIFIC

9. Mr Liu Shaoyong
Chairman
CHINA EASTERN AIRLINES

10. Mr Wang Changshun
Chairman
CHINA SOUTHERN AIRLINES

11. Mr Pedro Heilbron
Executive President and Chief Executive Officer
COPA AIRLINES

12. Mr Ahmed Adel
Chairman and Chief Executive Officer
Egyptair Holding Co (representing EGYPTAIR)

13. Mr Tewolde GebreMariam
Group Chief Executive Officer
ETHIOPIAN AIRLINES

14. Mr Donald F. Colleran
President and Chief Executive Officer
FEDEX EXPRESS

15. Ms Christine Ourmières-Widener
Chief Executive Officer
FLYBE LIMITED

16. Mr Luis Gallego MartÍn
Chief Executive Officer
IBERIA

17. Mr Yuji Akasaka
President
JAPAN AIRLINES

18. Mr Robin Hayes
Chief Executive Officer
JETBLUE AIRWAYS

19. Mr Sebastian Mikosz
Group Managing Director and Chief Executive Officer
KENYA AIRWAYS

20. Mr Walter Cho
Chairman and CEO
KOREAN AIR

21. Mr Enrique Cueto
Chief Executive Officer
LATAM AIRLINES

22. Mr Mohamad El-Hout
Chairman and Director General
MIDDLE EAST AIRLINES

23. Mr Mehmet Tevfik Nane
Chief Executive Officer
PEGASUS AIR

24. Mr Alan Joyce
Chief Executive Officer
QANTAS

25. Mr Akbar Al Baker
Chief Executive Office
QATAR AIRWAYS

26. Mr Rickard Gustafson
President and Chief Executive Officer
SAS

27. Mr Saleh Nasser Al Jasser
Director General
SAUDI ARABIAN AIRLINES

28. Mr Goh Choon Phong
CEO
SINGAPORE AIRLINES

29. Mr Ajay Singh
Chairman and Managing Director
SPICEJET

30. Mr Oscar Munoz
Chief Executive Officer
UNITED AIRLINES

06/04/2019

Let's Poll Tamagne Beyene
ታማኝ በየነ የፈለገውን ያህል ጥሩ ሰው ቢሆን፣ የፈለገውን ያህል ጀግና ነው ብትሉትም በእኔም ሆነ በቤተሰቤ ላይ ዓይን ያወጣ ውሸት ሲዋሽ ሕግን ተመርኩዘን መልስ ከመስጠት ወደኋላ አንልም። እኔ በታማኝ በየነ ላይ ጥሩ አመለካከት ኖረኝ አልኖረኝ አንድ ግለሰብ ነኝ። አብዛኛው ሕዝብስ ሰለታማኝ በየነ በአጠቃላይ ያላው አመለካከት ምን ይመስላል? በዚህ በማያዳላው የፈስኩክ POLL ድምጻችሁን ስጡ። ይህ POLL በምንም ዓይነት መንገድ ለማንም የማያዳላና ታማኝ በየነን ለሚደግፉትም ሆነ ለሚቃወሙት ሁሉ ክፍት ነው። ለአርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በአጠቃላይ ያላችሁ አመለካከት ጥሩ ነው? ጥሩ አይደለም?

06/04/2019
Ethiopian Broadcasting Corporation

ኢድ ሙባረክ

#etv የኢድ በዓል ሲከበር አንድነትን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑሙር እንድሪስ ገለፁ
1440ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል ተከበረ

06/02/2019

በወርቅ ፍለጋ ፕሮጀክት ላይ ጥቃት ተፈጸመ

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ቱሉ ካፒ በተሰኘ ሥፍራ የሚገኘው ከፊ ሚኒራል በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ሥር የሚተዳደረው የወርቅ ፍለጋ ፕሮጀክት፣ የጦር መሣሪያ በታጠቁ ግለሰቦች ጥቃት ደረሰበት፡፡

ኩባንያው ከአራት ዓመት በፊት የወርቅ ማዕድን ለማምረት ፈቃድ አግኝቶ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ጥቃቱ የደረሰው እሑድ ግንቦት 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ማለዳ ላይ መሆኑን፣ የከፊ ሚኒራልስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሐሪ አዳምስ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከኩባንያው ሠራተኞች አብዛኞቹ ቤተ ክርስቲያን መሄዳቸውን ጠብቀው ወደ ኩባንያው ቅጥር ግቢ ገብተዋል ብለዋል፡፡

ጥቃት ፈጻሚዎቹ በፕሮጀክቱ ግቢ ውስጥ የተለያዩ የማዕድን ፍለጋ መሣሪያዎች ያሉበትን ቤት ማቃጠላቸውን፣ በውስጡም ያገኙትን የጂፒኤስ መሣሪያዎችና ማይክሮስኮፖች መዝረፋቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ቢሮዎች ውስጥ በመግባት የኩባንያው መገልገያ ዕቃዎችንና ፋይሎችን አተራምሰዋል ብለዋል፡፡ ‹‹ይህ ዓይነት ዘረፋና ንብረት ማውደም በአካባቢው ከዚህ ቀደም ተከስቶ ቢያውቅም፣ እኛ ላይ ሲፈጸም ግን የመጀመርያው ነው፤›› ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

በኩባንያው ሥር የሚገኘው የወርቅ ማምረቻ በዓመት እስከ 1.2 ሚሊዮን ቶን የወርቅ አፈር በማጣራት ከ2,650 እስከ 2,800 ኪሎ ግራም ወርቅ የማምረት አቅም ሲኖረው፣ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ገንጂ ወረዳ ቱሉ ካፒ የሚገኘው የወርቅ ማውጫ ይዞታ ሰባት ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት አለው፡፡ ኩባንያው የወርቅ ማምረቻውን ለመገንባት 120 ሚሊዮን ዶላር ወጪ መድቦ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ይታወሳል፡፡

‹‹የአሁኑ ጥቃት እኛንም ሆነ የአካባቢውን ማኅበረሰብ አስደንግጧል፤›› ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ‹‹በኩባንያችን ያለውን ጥበቃ ማጠናከር እንዳለብን ትምህርት ሰጥቶናል፤›› ብለዋል፡፡

ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የተወሰኑ ግለሰቦች መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጥቃት ፈጻሚዎቹ የፈለጉትን ካደረጉ በኋላ የኩባንያውን ሾፌር በማስገደድ፣ ከኩባንያው አሥር ኪሎ ሜትር ያህል ርቀው ይዘው መጓዛቸው ታውቋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠውን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡

ይህን የመሰለ ጥቃት በተለይ በምዕራብ ወለጋ ዞን ሲከሰት ሁለተኛው ሲሆን፣ ከወራት በፊት አምስት የወርቅ ማዕድን ፍለጋ ኩባንያ ሠራተኞች በታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ይታወሳል፡፡ ከተገደሉትም ውስጥ አንድ የጃፓንና አንድ የህንድ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች እንደነበሩበት ይታወሳል።

ምንጭ፡ ኢትዮጵያን ሪፖርተር

05/27/2019

መኪና ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ለምትፈልጉ በቅድሚያ ይህን ይወቁ…

የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን
=====================================
ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባ ቀረጥና ታክስ የሚታሰበው የተሸከርካሪዉን ሲሲ መሰረት በማድረግ CIF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡ ተሽከርካሪው ያገለገለ ከሆነ ከተመረተበት አንድ ዓመት ጊዜ ጀምሮ ከFOB ዋጋዉ ላይ በየዓመቱ 10% በመቀነስ በጠቅላላዉ እስከ 3 አመት ወይም 30% ድረስ የእርጅና ቅናሽ ካለዉ በማስላት የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ በማባዛት ቀረጥና ታክሱን ማወቅ ይቻላል፡፡
የተሽከርካሪው የፈረስ ጉልበት ማለትም ሲሲው 1300 ከሆነ 125% ሲሆን 1301ሲሲ እስከ 2500 ሲሲ ደግሞ ከ176.24% እስከ 244.55% ባሉት የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ ይሰላል፡፡ ለሰው ማጓጓዣ የሚያገለግሉ ሌሎች ተሸከርካሪዎች ሲሆን ደግሞ በሌላ ስፍራ ያልተጠቀሰ ከሆነ የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ 125.00075% ሲሆን ሹፌሩን ጨምሮ አስር ወይም ከዛ በላይ ሰዎችን ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ ተሸከርካሪዎች ከ15 ተጓዦች ያነሰ መቀመጫ ያላቸው ተሸከርካሪዎች 58.25% እንዲሁም 15 እና ከዚያ በላይ ሰው የሚይዝ መቀመጫ ያላቸው የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔው 29.50% ነው፡፡
የተሽከርካሪው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡ የተሸከርካሪ ቀረጥና ታክስ ለመወሰን አምስት የሰሌት ደረጃዎችን(ማለትም የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይስ ታክስ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣ ሱር ታክስ እና ዊዝሆልዲንግ ታክስ) እንከተላለን፡፡ የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት እንደሚታሰብ በምሳሌ እንመልከት፡፡
የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 70000፣ የሲሊንደር አቅሙ 1280 የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ሲገባ:-
በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 70,000 X 35% =24,500 ይሆናል፡፡
ቀጥሎ ኤክሳይስ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (70,000 + 24,500) 30%=28,350 ይሆናል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350) 15% = 18,427.5 ብር ይሆናል፡፡
በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350 +18,427.5)10%= 14,127.75 ብር ይሆናል፡፡
በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 70,000 X 3%= 2,100 ብር ይሆናል፡፡
በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት
24,500 + 28,350 + 18,427.5 + 14,127.75 + 2,100= 87,505.25 ብር ይሆናል፡፡

Address

P. O. Box 11061
Alexandria, VA
22312

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TGEthiopianTelevision posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to TGEthiopianTelevision:

Videos

Nearby media companies


Other Broadcasting & media production in Alexandria

Show All