Ethiopia2day

Ethiopia2day world News
(1)

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ -ሳወት
02/17/2020

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ -ሳወት

ብምኽንያት ለካቲት 11 ካብ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ዝተውሃበ መግለፂ

ጅግና ህዝቢ ትግራይ፣ እንኳዕ ንታሪኻዊት ዕለት ለካቲት 11 ኣብፀሓካ!

ህዝቢ ትግራይ ግዝኣታዊ ሓድነቱ፣ ብሄራዊ መንነቱን ረብሕኡን ንምዉሓስ ምስ ደጋዊን ዉሽጣዊን ተፃባእቲ ሓይልታት ንዘበናት ተቓሊሱ እናሰዓረ ዝመፀ ጅግና ህዝቢ እዩ። ህዝቢ ትግራይ ፊደልን ስርዓተ-ፅሕፈትን ዝፈልሰፈ፣ ቅኒተ-ዜማ ዝፈጠረ፣ ከዉሒ ነዲሉን ፀሪቡን ዝተፈላለዩ ሓወልቲታን ኣብያተ-እምነታትን ብምስራሕ ብመዳይ ስነ-ህንፃ ብራኽኡ ዘመስከረ፣ ከተማታት ዝሰረተ፣ ናይ ባዕሉ ምሕደራን ስርዓተ-መንግስቲን ዝተኸለ፣ ንኻልኦት እውን ዘምሀረ ህዝቢ እዩ፡፡ ስለዝኾነ እውን ንዉድቀት መንግስቲ ኣኽሱም ስዒቦም ንዝመፁ ተፃብኦታት ኢዱ ኣይሃበን። ህዝቢ ትግራይ መሪር ወፅዓ ዘየሰኩኖ፣ ትካቦ ዘየስድዖ፣ ብታሪኹን ጅግንነቱን ዘይዕበ፣ ዕጉስ ህዝቢ እዩ። ወሎዶታት እናተቐባበልዎም ዝፀንሑ ዉርስታት ናፅነት፣ ሓርነት፣ ሓቦ፣ ርትዓዊነት፣ ጅግንነት፣ ፍቕሪ ዓድን ህዝብን፣ ወያነነት ገና ብጊሓቱ ዝማዕበሉ ክብርታት ተጋሩ እዮም። እዞም ክብርታት በቢእዋኑ ንዝተፈጠሩ ፀረ-ረብሓታት ህዝቢ ትግራይ ማለት እዉን ህልዉና ህዝብና፣ ግዝኣታዊን ብሄራዊን ሓድነትና ንዝተፃብኡ ሓይልታት ክስዕሮምን ክሳገሮምን ዓንዲ ሑቐ ኮይኖሞ እዮም። ስለዝኾነ ድማ ነዛ ለካቲት 11 እንትነኽብር እውን ነዞም ክብርታት እዚኦም ብምዕጣቕን ብምዕቃብን እዩ፡፡

ለካቲት 11 ህዝቢ ትግራይ ብርቱዕ መንግስቲ ንምትካል ንዘበናት ከካይዶም ዝፀንሐ ቃልስታትን እቲ ን17 ዓመታት ንብሄራዊ ሓርነት ዝተኻየደ መሪር ህዝባዊ ተጋድሎን እትልቁም ታሪኻዊት ገመድ እያ። ህዝቢ ትግራይ ብሄራዊ ዕላማታት ተሓንጊጡ፣ ሰንኮፍ ለዉጥን ምዕባለን ንዝነበረ ድሑር ስርዓት ብሓይሊ ንምውጋድ፣ ሽግ ሓርነት ወሊዑ ዕጥቃዊ ቃልሲ ዝጀመረላ መዓልቲ እያ። ነዚ ስዒቡ ህዝብና ኣብ ትግራይ ሰላም፣ ሓርነት፣ ልዕልና ሕጊ፣ ዴሞክራሲ፣ ኩሉ ተጠቃሚ ዝገብር ልምዓት፣ ፍትሒ፣ መሰል ዓርሰ ዉሳነን ግዝኣታዊ ሓድነቱን ብዘተኣማምን ደረጃ ንምርግጋፅ ከቢድን መሪርን መስዋእቲ ኸፊሉ እዩ። ብሓፈሻ ህዝባዊ ቃልስና እቲ ንዘበናት ዝዘለቐ ሕሉፍ ተዉፃዕ በቲ ሓደ ወገን፤ በቲ ካልእ ሸነኽ ህልዉና ብሄራት ዝጭፍልቕ ኣሃዳዊ ህንፀት ሃገረ መንግስቲ ኢትየጵያ ብምስዓር ሓዱሽ ስርዓት ክምሰረት ኣሰሩ ዘንበረላ መዓልቲ እዉን እያ።

በዚ መሰረት ውድብና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ /ሳወት/ ለካቲት 11 እንትነኽብር ህዝብና ዝተቓለሰሎምን ኩለመዳያዊ መስዋእቲ ዝኸፈለሎምን መሰረታዊ ዕላማታት ኣብ ግብሪ ብምዉዓል፣ ክብርታትን ፀጋታትን ህዝብና ብምዕቃብን ብምድንፋዕን ክኸዉን ይግባእ ኢሉ ይኣምን። ብተወሳኺ ለካቲት 11 ኣብ ዙርያ እቶም ህዝብና ዝተቓለሰሎም ግን ከዓ ዛጊድ ዘይተረጋገፁ መሰረታዊ ሕቶታትን ጠለባትን ንምምላስ ኣብ እንገብሮ ቃልሲ ዝያዳ ወነን መንፈስን ንዕጠቐሉ ዕለት ጌርና ንወስዶ። ውድብና ሳወት እዛ ታሪኻዊት ዕለት ዘለኣለማዊን ዘይሃስስን ድምቀት ዝህልዋ፤ ብሄራዊ ረብሓታት ትግራይ ምሉእ ዘይጎደሎ እንትረጋገፁ ጥራሕ እዩ ኢሉ ይኣምን፡፡

ሳወት ኣቦታትን ኣደታትን ተጋሩ ንዘበናት ዘካየድዎም ቃልሲታት ብሓፈሻ፤ ለካቲት 11 ዝፈለመ ህዝባዊ ቃልሲ ድማ ብፍሉይ እምነ ኩርናዕ ታሪኽና ጌሩ እዩ ዝርድኦ። ውድብና ሳወት ኣብቲ ናይ 17 ዓመት ዕጥቃዊ ቃልሲ ህዝብና ንዝኸፈሎ ኩለመዳያዊ መስዋእቲን መጉዳእቲን ዓብዪ ክብሪ ኣለዎ። ውደብና እቲ ህዝባዊ ቃልሲ ዘማዕበሎምን ዘጥረዮምን ክብርታት ማለት'ውን ዉፍይነት፣ ሓቦ፣ ፅንዓት፣ ጥቡቕ ስነ-ስርዓትን ስምረትን፣ ብፃይነት፣ ጅግንነት፣ ህዝባዉንትን ተኣማንነትን ካብ ወሎዶ ናብ ወሎዶ ክሰጋገሩ ዝግበኦም ዓበይቲ ዉርስታት እዮም ኢሉ ይኣምን ።

ውድብና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ንመላእ ህዝቢ ትግራይ፣
እንኳዕ ንመበል 45 ዓመት ምጅማር ህዝባዊ ቃልስካ ለካቲት 11 ኣብፀሓካ ክብል ይፈቱ።

ክብርን ሞጎስን ንሰማእታትና!
ብሄራዊ ረብሓታት ተዓጢቕና ንዘላቒ ዓወትን ሓድነትን!

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ
ለካቲት 2012 ዓ/ም
መቐለ፣ ትግራይ

02/10/2020
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ -ሳወት

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ -ሳወት

ኣባልነት
---------

ኣባል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ነዚ ዝስዕብ ረቛሓታት ዘማልአት/ዘማልአ ውልቀ ሰብ ወይ ኣካል ጥራሕ ይኸውን፡፡

1. ንመደብ(ፕሮግራም) ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ኣሚና/ኑ ዝተቐበለትን/ን ተተግብር/ዘተግብር

2. ፅቡቕ ስነምግባር ዘለዋ/ዎ፣ ኣብ ዝነብረሉ ሕ/ሰብ ፅቡቕ ተቐባልነት ዘለዋ/ዎ

3. ንህዝቢ ብማዕረ ዝተገልግል/ዘገልግል፣ ካብ ኣተሓሳስባ ግዕዝይና ዝረሓቐት/ዝርሓቐ፣ ረብሓ ትግራይ ንምርግጋፅ ድሌት ዘለዋ/ዎ

4. ትሕቲ ትግራዋይነት ዘሎ ፖለቲካዊ ኣወዳድባ ዘይትቅበል/ዘይቕበል

5. ዕድሜኣ/ኡ 18 ዓመትን ልዕሉኡን ዝኾነት/ነ

6. ኣብ ፖለቲካ ከይትሳተፍ/ከይሳተፍ ብሕጊ ዘይተኣገደት/ደ

7. ኣባል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ንምዃን ፍቓደኛ ዝኾነት/ነ

8. ናይ ኣባልነት ክፍሊት ትኸፍል/ዝኸፍል

9. ኣባል ካሊእ ፖለቲካዊ ውድብ ዘይኮነት/ነ

10. እቲ ውድብ ዝህቦ ናይ ዓቕሚ ህንፀት ስልጠና ፕሮግራም ክትወስድ ትኽእል/ዝኽእል

*ካብ ስሪት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ዝተወስደ

ዋና ቤት ፅሕፈት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፣ መቐለ!
06/19/2019

ዋና ቤት ፅሕፈት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፣ መቐለ!

ዘሕጉስ ዜና
--------------
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ምስ ህዝቡ ንምርካብ ቀዋሚ ኣድራሻ ኣብ ምእላሽ ዕውት ስራሕ ሰሪሑ እንሆ ዋና ቤትፅሕፈት ኣብ ዓይኒ ትግራይና መቐለ ከፊቱ ኣሎ።

እቲ ቤትፅሕፈት ዝርከበሉ ፍሉይ ከባቢ ድማ ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ ፊትንፊት ቀዳማይ ወያነ ፖሊስ ጣብያ ኣብ ዘሎ ህንፃ ካልኣዋይ ደብሪ እዩ።

ናብ ቤትፅሕፈትና ክትመፁ ስለትግራይና ድማ ክንዝትዪ ብኽብሪ ንዕድመኹም።

ሻላ ውፉይነት ኣባላትና ኣብዚ በፂሕና ኣለና።

ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሀገሪቱ የተወሰኑ አከባቢዎች የዜጎች ህይወት በማለፉ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡መንግሥት ጉዳዩን የሚያጣራ ግብረ ኃይል ማቋቋሙንና የማጣራቱ ሂደት ...
12/17/2017

ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሀገሪቱ የተወሰኑ አከባቢዎች የዜጎች ህይወት በማለፉ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡
መንግሥት ጉዳዩን የሚያጣራ ግብረ ኃይል ማቋቋሙንና የማጣራቱ ሂደት እንደተጠናቀቀም አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወሰድና የማጣራት ሂደቱን ውጤት ለሕዝቡ በዝርዝር እንደሚገለጽ ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ተናግረዋል፡፡
የጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡

-----

የተከበራችሁ የአገራችን ሕዝቦች- እንደምን አመሻችሁ
በቅርቡ በተለያዩ የሐገራችን አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት የሐገራችንን ሰላም እና መረጋጋት የሚያውኩ ችግሮች ታይተዋል፡፡ በተከሰቱት ግጭቶች ምክንያት የሰው ህይወት ጠፍቷል፡፡ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ የህዝብ ሐብት እና ንብረት ወድሟል፡፡ እጅግ የምሳሳለትን የሰላም፤ የልማት እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግባንታ ሥራችንን የሚጎዱ ችግሮች ተከስተዋል፡፡ በተለይም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት መከሰቱ ይታወቃል፡፡ የፈዴራል መንግሥት ከሁለቱ የክልል መንግሥታት ጋር በቅርበት በመሥራት ችግሩ እንዲቀረፍ ያለሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ጉዳዩ እልባት ወደ ሚያገኝበት ምዕራፍ በመሸጋገር ላይ ነበር፡፡ ሆኖም በቅርቡ ግጭቱ እንደገና ያገረሸ ሲሆን በነጹሀን ዜጎቻችን ላይ የሞት፣ የአካል ጉዳትና የሐብትና ንብረት ውድመት በማስከተል ላይ ይገኛል፡፡ በምዕራብ ሐረርጌ በድሮሎቢ ወረዳ በጋድሌ ቀበሌ ለደህንነታቸው ሲባል በአካባቢው በአቅራቢያ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ተጠልለው በነበሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች የጅምላ ግዲያ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በራሴና በፌዴራል መንግሥት ስም በንጹሐን ዜጎች ላይ በደረሰው አዳጋ የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽኩ ለተጎጅዎቹ ቤተሰቦች፣ ዘመድ አዝማድና ለመላው የአገራችን ህዝቦች መጽናናትን እመኛለሁ፡፡መንግሥት ድርጊቱን እያወገዘ ጉዳዩን የሚያጣራ ግብረ ኃይል ያቋቋመ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ የማጣራቱ ሂደት እንደተጠናቀቀም አስፈላጊውን እርምጃ የሚወሰድ ሲሆን የማጣራት ሂደቱን ውጤት ለሕዝቡ በዝርዝር እንደምንገልጽ ከወዲሁ ለማሳወቅ እፈልጋለሁ፡፡ በተመሳሳይም በጨለንቆና ሌሎች አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ በአካቢው በሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ አጋጥሟል፡፡

በድጋሚ በመንግሥትና በራሴ ስም በዜጎቻችን ህልፈተ ሕይወት ምክንያት የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽኩ ለተጎጂዎቹ ቤተሰቦች፣ ዘመድ አዝማድና ለመላ የአገራችን ህዝቦች መጽናናትን እመኛለሁ፡፡ የጸጥታ ኃይሎቻችን መንግሥት ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ሰላምን እንዲያረጋግጡ ተልዕኮ ሰጥቷቸው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ የጨለንቆን ግጭት ጨምሮ ተልዕኳቸውን እየፈጸሙ ባሉበት ወቅት ያጋጠሙ ክፍተቶች ካሉ አሰራሩን ተከትሎ መንግሥት የሚጣራ ሲሆን፣ የማጣራቱ ሂደት እንደተጠናቀቀም ውጤቱን ለሕዝቡ በዝርዝር ይፋ የምናደርግ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
በተጨማሪም በአማራ፣ በትግራይ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ አንዳንድ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፤ እንዲሁም በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ክቡር የሰው ህይወት መጥፋቱ፤ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው እና የዜጎች ሐብት እና ንብረት መውደሙ ብቻ ሳይሆን፤ ችግሩ በፍጥነት ካልተወገደ እንደ ሐገር አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ሊጥለን የሚችል ነው፡፡
በመሆኑም፤ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በቦረና፣ በጉጂና በባሌ የተለያዩ አካባቢዎች እና በቅርቡም ጨለንቆ አካባቢ በተከሰተው ግጭት፤ እንዲሁም በአዲግራት፣ በወለጋ፣ በደብረ ታቦር፣ በወልድያ፣ በባህርዳር፣ በጎንደር እና በአምቦ ዩኒቨርስቲዎች በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ በተማሪዎች የአካል ጉዳት መድረሱ እና በአንዳንዶቹም የሰው ህይወት መጥፋቱ በእጅጉ አሳዛኝ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ህይወታቸውን ባጡ ተማሪዎች የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽኩ ለተማሪ ወላጆችም መጽናናትን እመኛለሁ፡፡

ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ትምህርትን በፍትሐዊነት ለማዳረስ እና የተማሩ ዜጎችን ቁጥር ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ከ50 በላይ ዩኒቨርስቲዎች ተገንብተው፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ትምህርታቸውን መከታተል የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ እነዚህ የሐገር ተስፋ ተደርገው የሚታዩ የትምህርት ተቋማት የሚታዩ አስተዳደራዊ ችግሮችን እና ተማሪዎች የሚያነሷቸውን ሌሎች ችግሮችን በማዳመጥ መፍትሔ ለማስቀመጥ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በተጠቀሱት ዩኒቨርስቲዎች ተከስቶ የነበረው ችግር የክልል እና የፌዴራል መንግስታት፤ እንዲሁም የየዩኒቨርስቲዎች አመራሮች እና የየአካባቢው የመስተዳድር አካላት፤ ከተማሪዎች፣ ከሐገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት መሪዎች እና የጸጥታ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ችግሩ ተወግዶ፤ ሁኔታዎች ተረጋግተው የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቀጥል ለማድረግ ተችሏል፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈጠረውን ይህን ችግር ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ ችግር በተፈጠረባቸው የትምህርት ተቋማት በተማሪዎች ዘንድ የተፈጠረውን የደህንነት ሥጋት ለማስወገድ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በተቋማቱ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲኖር፣ የተቋማቱን ሰላም ለማስከበር የጸጥታ ኃይሎች ጥበቃ እንዲኖር ተደርጓል፡፡
በአጠቃላይ በክፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የጸጥታ መደፍረስ ችግር አንዳይኖር፤ የዜጎች ህይወት ዋስትና እንዲያገኝ እና በዜጎች ሐብት እና ንብረት ላይ የሚደርስ ውድመት እንዳይኖር ለማድረግ አስፈላጊው ሁሉ ይደረጋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱት ግጭቶች የሰላም፣ የልማት እና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ትግላችንን የሚጎዱ፤ ሐገረችንን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ውስጥ የሚከቱ እና በመራራ ትግል የተገኘውን ብሩህ ተስፋ የሚያጨናግፉ ክስተቶች ናቸው፡፡ ለዘመናት የቆየ የአብሮ መኖር እሴቶቻችን የሚጎዱ ችግሮች በመሆናቸው መንግስት ከሕዝቡ ጋር በመሆን ችግሮቹን በማያዳግም ሁኔታ ለመፍታት በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡

ለዘመናት በድህነት የኖረውን ህዝባችንን ከድህነት አረንቋ ለማውጣት እና ከኋላ ቀርነት ለማለቀቅ፤ እንዲሁም የሰላም፣ የልማት እና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጥረታችን ለማጠናከር በማሰብ፤ በከፍተኛ ወጪ በተለያዩ የሐገሪቱ አካባቢዎች የተገነቡት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤ የሐገራችንን ህዝብ ችግር ለመፍታት በጥናት እና ምርምር ዘርፍ ተሰልፈው የበኩላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ ታስበው ከፍተኛ ገንዘብ ፈሶባቸው የተቋቋሙ ናቸው፡፡ በመሆኑም በእነዚህ ተቋማት ገብተው የሚማሩ እና ሐገሪቱ በከፍተኛ ተስፋ የምትጠብቃቸው ተማሪዎች ምክንያታዊ አስተሳሰብን በመከተል፣ ከግጭት በመራቅ ለሐገራቸው ተስፋ ይሆኑ ዘንድ ለትምህርታቸው ልዩ ትኩረት ሰጥተው ጠንክረው መማር ይኖርባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል፤ መረጃን በማሰራጨት ተግባር የተሰማሩ የተለያዩ አካላት የሚያሰራጯቸውን መረጃዎች ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት መስጠት እና በኃላፊነት መንፈስ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በተጨማሪም ህዝቡ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች የሚያገኛቸውን መረጃዎች ትክክለኛነት ለማረጋገጥና መረጃዎቹን በተለያየ አግባብ ለማጣራት የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በመደበኛው የሚዲያ ዘርፍም ሆነ በሌሎች የመረጃ ማሰራጫ አግባቦች በመጠቀም መረጃን የሚያሰራጩ ተቋማት ህግን አክብረው ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡ ሐሰተኛ እና የተጋነኑ መረጃዎችን በማሰራጨት የህዝቡን ሰላም፣ ደህንነት እና አኩሪ የአብሮ መኖር እሴቶች የሚንዱ እና ህግን በሚያስተላልፉ የግልም ሆነ የህዝብ የመገናኛ ብዙሃን ከዚህ መሰል ተግባራት መራቅ ይኖርባቸዋል፡፡ መንግስት እንዲህ ያሉ ችግሮችን በሚፈጽሙት ላይ ተከታትሎ እርምጃ የሚወስድ መሆኑም በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥትና ገዢው ፓርቲ በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች እያጋጠሙ ያሉትን ግጭቶች መሰረታዊ መንስኤን በመለየት ችግሩን ከሥር መሰረቱ የሚፈታ እርምጃ የሚወስድ ሲሆን መላ የአገራችን ሕዝቦችም እንደ ወትሮው ከመንግሥት ጎን በመቆም ያልተቆጠበ ድጋፋችሁን እንዲትቸሩን በመንግሥትና በራሴ ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡ በተለይም ግጭቱ በሚከሰትባቸው የኦሮሚያና የኢትዮጰያ ሶማሌ ክልል ነዋሪ የሆኑት ወንድማማች ሕዝቦች ለሰላምና ለወንድማማችነት ቅድሚያ በመስጠትና ለግጭት ጥሪዎች ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት በጋራ በመንቀሳቀስ ሰላማቸውን እንዲያስከብሩ በኢፌዴሪ መንግሥት ስም ጥሪዬን እያቀረብኩ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥታት በቅንጅት ችግሩን ለመቅረፍ በመረባረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
በድጋሚ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠሙ ግጭቶች ሳቢያ በዜጎቻችን ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማኝን መራር ሐዘን እየገለጽኩ፣ ለመላ ቤተሰቦቻቸው፣ ዘመድ አዝማዶቻቸውና ለአገራችን ሕዝቦች መጽናናትን እመኛለሁ፡፡

12/11/2017

አማራጭ የፖለቲካ ስርዓት

ክፍል አንድ

ሀ/መነሻ

ለአገሪቱ ፖለቲካዊ ችግሮች በብዙ ወገኖች የሚሰጡትን የመፍትሄ አስተያየቶች በሁለት መክፈል ይቻላል፡፡ አንደኛው ወገን ስርዓቱ አንዳለ ሆኖ የስርዓቱን አንቀሳቃሾች መለወጥና ማስተካከል ነው፡፡ ይህ ከኢህአዴግ በኩልና ከለዘብተኛ ተቃዋሚዎች የሚሰጥ አስተያየት ነው፡፡ አንደ ኢህአዴግ እምነት ስርዓቱ ችግር የለበትም፡፡ ችግሩ ያለው ስርዓቱ አንቀሳቃሾች ላይ ስለሆነ ማስተካከል ያለብን ይህንኑ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ በየገዚው ድርጅታዊ ተሀድሶ እና የአመራር ግምገማ እያደረገ ቢመጣም የስርዓቱ ችግር እስከአሁን አልተፈታም፡፡ ይህ የኢህአዴግ መፍትሄ ችግር አንደማከባለል ነው፡፡ ችግሩን እንደ ኳስ አድርገህ ብታስብ ኳሷ በተንከባለለች ቁጥር ሌላኛውን የኳሷን ክፍል ልታይ ትችላለህ፡፡ ግን መልኳን ለወጠች አንጂ አንድ ኳስ ናት፡፡ ፖለቲካ ችግራችን እንደ ኳሷ ነው፡፡ ችግሩ ቢንከባለልም አሁንም ወደፊትም ያለነው ችግሩ ላይ ነው፡፡ የኢህአዴግ መፍትሄ ችግር ችግር አንደማንከባለል ነው፡፡ እሱ የለመደው ችግር ባልተለመደ ችግር ሲተካ መፍትሄ ይመስለዋል፡፡ ግን አይደለም፡፡ ስለዚህ አየመራር ግምገማና ድርጅታዊ ተሀድሶ ችግርን በችግር የመተካት ያህል አንጂ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ይህ አሳብ ወደ ሁለተኛው መፍትሄ ያመራናል፡፡

ለአገሪቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚሰጠው ሁለተኛው አማራጭ የስርዓት ለውጥ ነው፡፡ የስርዓት ለውጥን አንደ መፍትሄ የሚያነሱ ወገኖች ግን የተሻለ የስርዓት አማራጭ የላቸውም፡፡ ምን አይነት ስርዓት ሲባሉ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይላሉ፡፡ ይህ ማለት ተመሳሳይ ስርዓቶችን አርስ በእርስ መተካት አይቻልም፡፡ ዴሞክራሲዊ ስርዓት ስርዓትን አፍርሶ በሌላ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመተካት መታገል ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም መፍትሄ አይሆኑም፡፡ ስለዚህ መፍትሄው ምንድን ነው ? ከዴሞክራሲ ውጪ ሌላ የተሻለ የፖለቲካ ስርዓት መመስረት ብቻ ነው፡፡

ለ/ የዴሞክራሲ ችግር

ፊሎክራሲ የተሻለ የፖለቲካ ስርዓት የመሆኑን ምክንያቶች ከማንሳታችን በፊት አሁን ላይ ተግባራዊ እያደረግነው ያለነው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ችግሮችን ማየት እንዳለብን ይሰማኛል፡፡ ዴሞክራሲ ላይ ትኩረት የምናደርገው ሌሎች የፖለቲካ ስርዓቶች ስሌሉ ሳይሆን አሁን ላይ በስፋት ተቀባይነት ያለው ስርዓት ዴሞክራሲ በመሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ የዘውዳዊ ስርዓት ፣ አምባገነን ስርዓት ወዘተ የሚባሉ የፖለቲካ ስርዓቶች ቢኖሩም ጊዘያቸው ያለፈባቸው በመሆናቸው እኛ ባንተቻቸውም አሁን ተፈላጊ አይደሉም፡፡ ስለዚህ መነሳት ያለብን ወቅታዊ ተቀባይነት ካለው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ችግሮች ነው፡፡

አሁን ላይ ያሉትን የዴሞክራሲ አይነቶች በሁለት ሊከፈሉ የሚችሉ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሊበራል ዴሞክራሲ ነው፡፡ ይህ የሊበራል ዴሞክራሲ የመንጋ ስርዓት ነው፡፡ ሁለተኛው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሲሆን ይህ የሥልጣን ስርዓት ነው፡፡ ሁለቱም አይነት የዴሞክራሲ አይነቶች ችግር የሚወራረሱ በመሆናቸው በጥቅሉ ከዴሞክራሲ አንፃር ሊታዩ የሚችሉ ቢሆንም ለአንባቢ ግንዛቤ አመቺ የሚሆነው ሁለቱም ያለባቸውን ችግሮች በተናጠል ማየት ነው፡፡ ስለዚህ ከሊበራል ዴሞክራሲ አንጀምራለን፡፡

ሐ/ ሊበራል ዴሞክራሲ

ሊበራል ዴሞክራሲ የግለሰቦችን ልቅ ነፃነት የሚፈቅድ በመሆኑ ያልተገራ የመንጋ ተሳትፎን የሚጋብዝ ነው፡፡ በዚህ ያልተገራ የመንጋ ተሳትፎ የአገር መሰረት የሆነው የፖለቲካ ሰርዓት የፈረሰባቸው ፣ ለአምባገነን ስርዓት መተካት እድል ያመቻቹ የሊበራል ስርዓቶችን እንደ አብነት መውሰድ አንችላለን፡፡ በጀርመን የናዚ አምባገነናዊ ስርዓት የተመሰረተው ሊበራል ዴሞክራሲ በፈጠረው ፖለቲካዊ ክፍተት ነው፡፡ ራስልና ፑፐር የናዚን አነሳስ ከፕሌቶ ዩቱዮጵያኒዝም ጋር በማያያዝ ፊሎክራን የተቹ ቢሆንም የወቅቱን የጀርመን ፖለቲካ እንደ አቶ መለስ ዜናዊ የተረዳው የለም፡፡ እኔም የመለስን ትንታኔ አንደምደግፈው በጀርመን የናዚ አምባገነን ስርዓት እንዲመሰረት እድሉን ያመቻቸው ልቅ የሆነ የመንጋ ተሳትፎን ያራምድ የነበረው የሊበራል ዴሞክራሲ ነው፡፡ ከዚያም ወዲህ በታዩ የሊበራል ታሪኮች ውስጥ በጣሊያን የሰርቪዮ ቤርሌስኮኒ ፣ በአሜሪካ የዶናልድ ትራምፕን አይነት ብቃት የሌለው የፖለቲካ መሪ የመጣው የሊበራልን ያልተገራ ተሳትፎ ተገን በማድረግ ነው፡፡ በአገራችንም ተመሳሳይ ችግር ማየት ይቻላል፡፡

በአገራችን የዴሞክራሲ ጥያቄ እየጎለበተ በሄደባቸው የ60ዎቹ የወጣቶች ንቅናቄ እንደተጠበቀው ያልተሳካው የሊበራል ዴሞክራሲ አይነት የፖለቲካ ትግልን በመከተሉ ነው፡፤ በወቅቱ እነ-መለስን የትጥቅ ትግል አንዲጀምሩ ያስገደዳቸው አብይ ምክንያቱም የ60ዎቹ የወጣቶች ዴሞክራሲያዊ ትግል ያልተገራ የመንጋ ትግል በመሆኑ ደርግን የመሰለ አምባገነን ስርዓት እንዲመሰረት በማድረጉ ነበር፡፡ ደርግ አንደ ኢህአዴግ የራሱን መስመር ተከትሎ በትግል የተፈጠረ ስርዓት ሳይሆን የወጣቶቹን ዝርክርክ የዴሞክራሲ ትግል የፈጠረለትን እድል በመጠቀም ስልጣንን የተቆጣጠረ እና በአገሪቱ ላይ 17 ሙሉ የቀለደ የአጋጣሚ ክስተት የወለደው ጥገኛ የአምባገነን ስርዓት ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ትግል በራሱ በፈጠረው አምባገነናዊ ስርዓት የተነሳ እንደ መኢሶንና የመሳሰሉ የዴሞክራሲ ትግልን የመረጡ የለውጥ አራማጆች የተጨፈለቁበት ፣ ኢህአፓንና ኢህአዴግን የመሳሰሉ ሀይሎች የትጥቅ ትግልን አንዲመርጡ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በዚህ የተነሳ ወቅቱ ለአገሪቱ አድገት የሰጠው ምቹ ሁኔታ ረጅም አመታትን ባስቆጠሩ ጦርነቶች ተቀልብሶ በታንክና በመድፍ ስንናጥ ቆይተናል፡፡ ንፁንን ወገኖቻችንን አጥተናል፡፡ አገራዊ እድገታችን ተግድቧል፡፡ ይህ ችግር የተፈጠረው ደርግን የመሰለ አምባገነናዊ ስርዓት በመከሰቱ ሳይሆን ለዚህ አምባገነናዊ ስርዓት መፈጠር ምክንያት የሆነው ያልተገራው ዴሞክራሲያዊ ትግል ነው፡፡ በዛን ወቅት የነበረው ትግል ከሊበራሎቹ ጋር በእጅጉ የሚመሳሰልና በነፃነት ሰበብ ዝርክርክ የፖለቲካ አካሄድን የሚከተል ነበር፡፡

ከዚህ ውጪ ባሉ ታሪካዊ ተሞክሮዎችም የሊበራል ዴሞክራሲ የአፍሪካውያንን እድገት የገደበ ብልሹ የፖለቲካ አካሄድ ነው፡፡ በአፍሪካ አብዛኞቹ አገራት ይህንኑ የመንጋ ስርዓት በመከተላቸው የተነሳ የምዕራባውያኑ የንግድ ተቋት መፈንጫ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ አላገኙም፡፡ የምዕራባውያኑ መንግስታት በአፍሪካ የሊበራል ዴሞክራሲን ካልተከተላችሁ ሞቼ እገኛለሁ የሚለውን ፖለቲካዊ ተፅዕኖው መቋቋም ያልቻሉ አብዛኖቹ አገራት ሳያላምጡ የዋጡትን መልሰው እየተፉት ነው፡፡ ፡ አቶ መለስ በትንታኔያቸው አንዳቀረቡት በአፍሪካ ሊበራል ዴሞክራሲ በተጨባጭ የፈጠረው የሞቱ መንግስታትን ነው፡፡ ከዚህ አልፎ በሊቢያ ፣ በግብፅ ፣ በሶሪያ በየመንና በመሳሰሉት አገራት ለተፈጠረው ችግር መነሻው የሊበራል ዴሞክራሲ የመንጋ ስርዓት ነው፡፡ በእነዚህ አገራት የሊበራል ዴሞክራሲ አቀንቃኞች በፈጠሩት የመንጋ ተፅዕኖ መጀመሪያ የተደረገው የአገር መነሻ የሆነውን የፖለቲካ ስርዓት ማፍረስ ነው፡፡ በዚህ መነሻነት የተማከለ ፖለቲካዊ አስተዳደርን በማዳከም መንግስታት ህግ የበላይነት ማስጠበቅ የሚያስችላቸውን አቅም በምትኩ የመንጋ ስርዓትን ማስፈን ነው፡፡ ስሊዘህ ሊበራል ዴሞክራሲ ሊፈጥር የሚችለው አንድም አምባገነን ስርዓት ይህ ካልሆነ ደግሞ ህግና ስርዓት የሌለበት የመንጋ ስርዓትን ነው፡፡

በዴሞክራሲያዊ መብቶች ወዘተ እያሳበቡ በየጊዜው የሚጨቀጭቁን ምዕራባውያንም ለዘመናት የተዘጋባቸውን አድል በማስከፈት በአገራችን የመንጋ ስርዓት አንዲመሰረት ለማድርግ ነው፡፡ ከፖለቲካ ተቋሞቻቸው የሚደርስብን የፖለቲካ ተፅዕኖም መነሻ ለህዝባችን አስበው ሳይሆን አገራችንን ፖለቲካ አንደፈለጉ ማምታታት የሚችሉበትን የመንጋ ስርዓት ለመመስረት ነው፡፡ እስከአሁን ያየነው የሊበራል ዴሞክራሲን ችግር ነው፡፡ በሚቀጥት ተከታታይ ፖስቶች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ያለበትን ችግሮች በማየት በመጨረሻ ፊሎክራሲ ከሁለቱ የዴሞክራሲ አይነቶች የተሻለ ብቻ ሳይሆን ወቅታዊ የአገሪቷ ፖለቲካዊ ችግር በተጨባጭ መፍታት የሚችልበትን አማራጮች እንመለከታለን፡፡

>>> ይቀጥላል

12/11/2017

.

ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በፍትህ ጋዜጣ ላይ ‹‹የልማቱ ዋጋ ስንት ነው?›› የሚል ጽሁፍ ጽፌ ነበር፡፡ ዛሬ ENN የቴሌቪዥን ጣቢያ አንድ ጋዜጠኛ ከክቡር አንባሳደር ካሳ ተክለብርሀን ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ (በከፊል) ተመልክቼ አስታወስኩት፡፡ በጋዜጠኛው ጉሮሮውን እንደተያዘ ሁሉ፣ የሚያውቀውን ሀቅ አውጥቶ ለመናገር ሲንተፋተፍ ማየት ያሳቅቃል፡፡ አንባሳደሩ በዚህ በየእለቱ የዜጎቻችን ህይወት በሚቀጠፍበት ሁኔታ ውስጥ ሆነን እንኳን ችግሩን የሚመለከቱበት መንገድ ያስደነግጣል፡፡

ጋዜጠኛው በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ችግር ከጠቀሰ በኋላ፣ የሚያቀርበው ጥያቄ ለአንድ ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ለመጣና ጊዜያዊውን ችግር ለታዘበ ቱሪስት እንጂ፣ ለሀያ ስድስት አመት ሀገሪቱን ለመራና አሁን የሚታየው መገዳደል እንደ አንድ ዜጋ ብቻ ሳይሆን፣ እንደአንድ የመንግስት ባለስልጣን በቀጥታ ለሚመለከተው ሰው የሚቀርብ አይመስልም፡፡ በጣም ያበሳጩኝን ሁለት ነጥቦች ልጥቀስ፡፡ ጋዜጠኛው፣ ‹‹አሁን በሀገሪቱ ውስጥ ችግር አለ፤ ሰዎች እየሞቱ ነው፡፡ ይህን ያመጣው ብሄራዊ መግባባት ባለመኖሩ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ብሄራዊ እርቅና መግባባት የለም በማለት ይናገራሉ፡፡ ለምሳሌ የሀገራችን ችግር በሆነው ድህነት ላይ የጋራ መግባባት የለም፡፡ ድህነት ምንድነው በሚለው ላይ ብዙዎች ተመሳሳይ አመለካከት የላቸውም (ቃል በቃል ሳይሆን ሀሳቡ የተወሰደ)፡፡›› ከዚያም አምባሳደሩ የድህነትን ምንነት በመተንተን ይመልሳሉ፡፡ አዎ ጋዜጠኛው ልክ ነው ብሄራዊ እርቅና መግባባት ለሀገራችን አስፈልጓት የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ ለችግራችን ብቸኛው መድሀኒት እሱ ብቻ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ጋዜጠኛው የጀመረው ሀቅ ጉሮሮው ላይ ተወትፎ የቀረበት መንገድ ነው፡፡ ዜጎች እየሞቱ ያሉበትን ሀገራዊ ቀውስ፣ የአንድ ክፍል ተማሪዎች የጽንሰ ሀሳብ አለመግባባት አደረገው፡፡ በመጀመሪያ እንዲህ አይነቱ ሰው ለምን ‹‹ጋዜጠኛ›› ሚድያ ላይ ይወጣል? የህሊናውን እውነት፣ የወገኑን ድምጽ በባዶ ሳሎኑ ውስጥ፣ ጮክ ብሎ (ለራሱ) ለመናገር የማይደፍር ሰው ሚድያ ላይ መውጣት የለበትም፡፡ ለእንዲህ አይነቱ ሰው በእውነት ላይ ሳይሳለቅ፣ የእለት ጉርስና ያመት ልብስ ሊያመጡ የሚችሉ በርካታ ሙያዎች አሉ፡፡

ሌላው ያስገረመኝና መግቢያዬ ላይ የጠቀስኩትን ጽኁፌን ያስታወሰኝ ነጥብ አንባሳደሩ፣ በአሁኑ ሰአት በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ያለውን የዜጎችን ህይወት መጥፋትና መፈናቀል የገለጹበት መንገድ ነው፡፡ ያሉት በግርድፉ እንዲህ ነው፣ ‹‹አሁን በየቦታው የተፈጠረው ችግር የሰው ህይወት ስለሚጠፋበትና መፈናቀል ስለለበት እንጂ ከዚህ የበለጡ ችግሮች አሉ፤›› በማለት ከልማትና ከእድገት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ጠቅሰዋል፡፡ እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ያልተመለሰ ጥያቄዬን አሻሽዬና ደግሜ የጠየቅኩት! ‹‹እውን የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ዋጋ ከልማቱ ዋጋ አይበልጥም?››

***

እባካችሁ! ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሲባል፣ እባካችሁ!

.

የሀገርን ደህንነትና የዜጎችን ህይወት የሚስተካከል ምንም ነገር የለም! የአንድ ወገናችንን ህይወት ከቶም ምንም አያክለውም፡፡ ህዝቦች እየተፈናቀሉ፣ ወጣቶች በየዩኒቨርሲቲውና ስታዲየሙ እየሞቱ ስለልማትና እድገት መጨነቅ እብደት ነው፡፡ ወደፊት ስናድግ፣ ገንዘብ ሲኖረን መንገድ ልንሰራ፣ ባቡር ልንዘረጋ እንችላለን፡፡ የአንድ ዜጋ ህይወት ግን ልንመልስ አንችልም፡፡

አሁን ጊዜው የሚጠይቀው ብቸኛ መንገድ ብሄራዊ እርቅ ነው፡፡ የኦሮሚያ፣ የአማራና የቤንሻንጉል ክልላዊ አመራሮች የጀመሩት ብሬራዊ የመግባባት ስሜት በሁሉም የሀገሪቱ ህዝቦች መካከል ሳይውል ሳያድር መደረግ አለበት፡፡ የኢህአዴግ ሀላፊነት ችግር በገጠመ ቁጥር እየተሰበሰበ ‹‹ድክመቴን አንጥሬ ተገማግሜያለሁ፤ እገሌን በእገሌ ተክቻለው›› የሚል የግምገማ ራፖር ማቅረብ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ መንግስት እንደመሆኑ እያንዳንዱ የአስተዳደርና የጸጥታ ችግር በቀጥታ የሚመለከተው እሱን ነው፡፡ እሱ በዘረጋው የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ ያለ አንድ የዞን ጸሀፊ የስራ አፈጻጸም ችግር የኢህአዴግ ችግር ነው፡፡ አንድ ‹‹በሙስና ተጨማልቄያለሁ፤ በአመራሮች መካከል ያለው ግንኙነት ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን በመተጋገል ላይ የተመሰረተ ነው፤ . . . ›› እያለ እራሱን የገመገመ የንግስት ወይም የመንግስት አካል ስልጣኑን በፈቃዱ ላለመልቀቅ ምን ምክንያት ይኖረዋል!?

ኢህአዴግ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር፣ ኢትዮጵያውያንንም እንደ ህዝብ እንዲቀጥሉ ለአዲስ አስተዳደር ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት፡፡ አንድን ሀሳብ ለመተግበርና ውጤታማ መሆን ያለመሆኑን ለመፈተሽ ሀያ አምስት አመት ከበቂው በላይ ነው፡፡ የኢህአዴግ መንገድ አገራዊ ሰላምን፣ አንድነትንና ልማትን ሊያመጣ አልቻለም፡፡ እዚህ ላይ ልማት ማለት ቁሳዊ የሚመስላቸው ተሳስተዋል፡፡ እውነተኛው ልማት በዜጎች ላይ የሚካሄደው አእምሯዊ ልማት ነው፡፡ የአለምን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ ሁለንተናዊ እድገት ያልለማ አእምሮ፣ የዘመናት ቁሳዊ ልማትን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ አመድነት እንደሚቀይር ተቃጥለው በየመንገዱ ዳር ከቀሩ መኪኖችና በየከተማው ከተሰባበሩ ህንጻዎች መማር አለብን፤ የግድ የመንንና ሊቢያን እስክንሆን መጠበቅ የለብንም፡፡ ኢህአዴግ የልማቱ አስኳል አድርጎ በመላው ሀገሪቱ ከገነባቸው ዩነቨርሲቲዎች ትልቅ ትምህርት መማር አለበት፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በአእምሮ እድገታቸው ከፍ ያሉ፣ የወደፊት የሀገርና የወገን አለኝታ የሆኑ ወጣቶች የሚፈጠሩበት ነው፡፡ ግን አልሆነም! በአንድ የዳር ሀገር ገበሬና በትልቅ ከተማ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚማር ልጁ መካከል ያለው ያስተሳሰብና የድርጊት ልዩነት ምንድነው? እውነት ዩኒቨርሲቲዎቻችን ዩኒቨርሲቲዎች ቢሆኑ ኖሮ፣ ከሱማሌ የተፈናቀሉ ዜጎች ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ልጆቻቸው ዘንድ ይጠለሉ ነበር፡፡ ግን አልሆነም፤ በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚከናወነውን እውቀትና ዘመናዊነት አይገልጸውም፤ ለዚህ ነው የኢህአዴግን የአስተዳደሩን ውድቀት ወጣቶችን አስተምሮ መለወጥ ካልቻለበት ዩኒቨርሲቲ መማር ያለበት፡፡

የኢህአዴግ ባለስልጣናት እባካችሁ ከዚህ ቀውስ ያለተጨማሪ ህይወት መጥፋትና ሀገራዊ ቀውስ እንወጣ ዘንድ፣ ብሄራዊ እርቅን መሰረት ያደረገ ብሄራዊ መግባባት ይመጣ ዘንድ ፈቃዳችሁ ይሁን፡፡ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ ምሁራንንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሳተፈ ሀገራዊ መፍትሄ እንፈልግ፡፡

12/09/2017
12/03/2017
Ethiopia2day

Tigrayan Media Network VOA Tigrigna Tigrayan Media Network ግዕዝ ሚዲያ Geez Media

12/03/2017
Ethiopia2day
12/03/2017

Ethiopia2day

Ethiopia2day's cover photo
12/03/2017

Ethiopia2day's cover photo

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የአቋም መግለጫ------------//--------------የህወሓት/ኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ለላፉት 35 ቀናት ባካሄደው ስብሰባ የድርጅቱ ስትራቴጂካዊ አመራር ክልላ...
11/30/2017
media3.giphy.com

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የአቋም መግለጫ
------------//--------------

የህወሓት/ኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ለላፉት 35 ቀናት ባካሄደው ስብሰባ የድርጅቱ ስትራቴጂካዊ አመራር ክልላዊና ሃገራዊ ተልእኮውን ከመወጣት አንፃር ያለበት ቁመና ለማየት የሚያስችል ስር ነቀል ግምገማ አካሂዷል፡፡ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ከመገንባት፤ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ መዋቅራዊ ለውጥ ከማረጋገጥ፣ የህዝባችንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ከመመለስ አንፃር ያሉበት መሠረታዊ ክፍተቶችንና አዲስቷን ፌዴራላዊት ዴሞክሰራሲያዊት ኢትዮጵያ ከመገንባት አኳያ የተጋረጡ አሳሳቢ አዝማሚያዎች በጥልቀት ገምግሟል፡፡ ይህን መሰረት አድርጎ ባደረገው ሂስና ግለሂስ ተከትሎ የእርምት እርምጃ በመውሰድና የአመራር ሽግሽግ በማድረግ ተጠናቋል፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ ህወሓት የትጥቅ ትግል ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በየደረሰበት የትግል ምእራፍ ውስጥ ሁሉ የሚገጥሙትን ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች በስከነ ሳይነሳዊ ኣመራርና በኣባላቱና በህዝብ የተማላ ተሳትፎ በአስተማማኝ እየመከተ ለድል የበቃ ድርጅት ነው፡፡ የህዝብን ፀረ-ጭቆና፣ ፀረ ኃላቀርነትና ፀረ-ድህነት ትግል ለስኬት ለማብቃት የሚያስችሉ የጠራ መስመር፣ መስመሩን ለማስፈፀም የሚያስችሉ ስትራተጂዎችና ስልቶችን እየቀየሰ ከኣንድ የትግል ምዕራፍ ወደ ሌላው የትግል ምዕራፍ ለመሸጋገር የቻለበት ምስጢር ግልፅ ነው፡፡ ህዝባዊ ወገንተኝነቱ አስተማማኝ የሆነ፣ ፈተናዎች በገጠሙት ቁጥር ራሱን በሚገባ እየፈተሸና ወቅቱ የሚጠብቀውን፤ ማንኛውንም የእርምት እርምጃ እየወሰደ ጥንካሬዎቹን የሚያጎለብት ድክመቶቹ ያለምህረት በማስወገድ በመስዋእትነት የደመቀ ታሪክ መስራት የቻለ ኣመራር ባለቤት በመሆኑ ነው፡፡

ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ከእህትና አጋር ድርጅቶችና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመሆን በከፈሉት እጅግ ከባድ መስዋእትነት አዲሱቷን ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ችለዋል፡፡ በአገራችን ታሪክ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የህዳሴ ምዕራፍ ከፍቷል፡፡

ይሁንና በትጥቅ ትግልም ወቅት ሆነ በልማትና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንቅስቃሴያዎችን እጅግ የሚያኮራ ተግባራትን የፈፀመ ድርጅት ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ከችግር ኣዙሪት መውጣት አቅቶት የሚንገዳገዱበትና ለህዝብ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መስጠት ላይ ሰፊ ድክመት እያሳየ የመጣበት ሁኔታ ተፈጥረዋል፡፡ በተለይም ካለፉት ጥቂት ኣመታት ወዲህ ስትራቴጂካዊ ኣመራሩ እየተዳከመ ተልእኮውን ለመወጣት የሚያስችል ቁመና፣ ኣመለካከትና ኣደረጃጀቱ በየጊዜው እየተሸረሸረ፣ ህዝባዊነቱ እየቀነሰ፣ የህዝብን ችግር በማያወለዳ መልኩ ሳይፈታ በትንንሽ ድሎች የሚረካ ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት የመፍትሔ አካል ከመሆን ይልቅ የችግር ምንጭ መሆን የጀመረበት ሁኔታ በስፋት መታየት ከጀመረ ውሎ ኣድራል፡፡ ይህንን ቁመና ይዞ መስመሩንና የመለስን ለጋሲ ማስቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ እንደሌለ በግልፅ አይቷል፡፡

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ማእከላዊ ኮሚቴው ከገባባት ኣዙሪት ለመውጣት ያለው ብቸኛ አማራጭ በድርጅት የቆየ ሳይንሳዊ የትግል ባህልና ታሪክ መሰረት በቁጭት ተነሳስቶ ጥልቀት ያለው የአመራር ግምገማ ማድረግ ብቻ እንደሆነ በማመን በኣፅንኦት መክራል፡፡ ያጋጠሙትን ፈተናዎች በጥሞና መርምሮ ድርጅቱን በማያዳግም ሁኔታ ወደ ትክክለኛው መስመሩና ህዝባዊ ወገንተኝነቱ ለመመለስ በሚያስችለው መልኩ ራሱን በጥልቀት ፈትሿል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ስደረጉ ከነበሩት የይስሙላ ግምገማዎች በዓይነቱና መልኩ በተለየ ችግሮቹን በሚገባ ለመለየት ያስቻሉት መተጋገል አካሂዷል፡፡

ወደ ግምገማ ሲገባ አሁን በስራ ላይ ያለውና ተተኪው አመራር በጋራ ትኩረት ሰጥቶ ያየው ጉዳይ ከገባበት የአመራር አዙሪት ውስጥ ለመውጣት በተለመደው መንገድ መሄድ በፍፁም የማያዋጣ መሆኑን በመገንዘብ ከተለመደው ግምገማ ለመውጣት ያስችላል ተብሎ የታመነበትና ስፋትና ጥልቀት ያለው ክርክር የጋበዘ የድርጅቱን ኣጠቃላይ ሁኔታና የኣመራሩን ድክመት በሚገባ የፈተሸ ሰነድ ለኣመራሩ ቀርቦ ሰፊ ውይይትና ክርክር ተደርጎበታል፡፡

በዚህ መድረክ በቀረበዉ ሰነድ ላይ ተመስርቶ በተደረገ ጥልቅ ዉይይት የህዝባችንና የመላው አባላችንን ተደጋጋሚ ጥያቄ ለመመለስ ያልተቻለው በዋናነት ስትራቴጂክ አመራሩ ከገባበት አዙሪት ውስጥ መውጣት አቅቶት ሲዳክር በመቆየቱ መሆኑን የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አረጋግጧል፡፡
አመራሩ የሃሳብና የተግባር አንድነት የጎደለው፣ ፀረ ዴሞክራቲክ ተግባርና አስተሳሰብ ውስጥ በስፋት የተነከረ፣ በተልዕኮ ዙርያ በመተጋገልና በመርህ ላይ የተመሰረተ አመራር የማይሰጥ፣ ህዝብንና አላማን ከማስቀደም ይልቅ የራሱን ክብርንና ጥቅም የሚያስቀድም መሆኑ ታይቷል፡፡ ለህዝብ ያለው ወገንተኝነት እየተሸረሸረ፣ ከአገልጋይነት ይልቅ ራሱን እንደ ተገልጋይ እየቆጠረ፤ መዋቅራዊ ለውጥ በሚያመጡ ስኬታማ የህዝብ ዙርያ መለስ እንቅስቃሴ ከመጠመድ ይልቅ በተደማሪ ለውጦች የሚረካና በውሸት ሪፖርት ራሱን መሸለም የሚቃጣው አመራር እየሆነ በአጠቃላይ ራሱን ወደ ጥገኛ ገዢ መደብ የመሸጋገር አዝማሚያ የተጠናወተው መሆኑን በትክክል አስቀምጧል፡፡

ይህ የስትራተጂካዊ አመራር ድክመት በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግቦቻችን አፈፃፀም ላይ እጅግ ከባድ ተፅእኖዎች ፈጥረዋል፡፡ በህዝብ ዙርያ መለስ ተሳትፎና በጠራ መስመር ማስመዝገብ የጀመርናቸውን በርካታ ለውጦች ማስቀጠል ያልተቻለበት አንዳንዴም ወደሃላ መመለስ የጀመሩበት ሁኔታ እንደነበረ በጥልቀት ታይታል፡፡ ሁሉንም የልማት ሃይሎች በተደራጀ መልኩ በመምራት ረገድ የነበረውን ሰፊ ክፍተትንም ኣይቷል፡፡ ወጣቶች ፣ ምሁራን፣ ሴቶችና ሌሎችም የሞያ የማሕበራትና መሰል ኣደረጃጀቶች የለውጥ ባለቤት ሆነው የሚውጡበትን ዕድል በማምከን ድርጅቱን በቀጣይነት የሚመራ ብቁ ሃይል እንዳይፈጠር እንቅፋት የሆነ ኣመራር መሆኑንም በሚገባ ተረድቷል፡፡ ህዝቡ በድርጅቱ ላይ የነበረዉን እምነት እንዲሸረሸርም ትልቅ አስተዋፅኦ ኣድርጓል፡፡

በአመራሩ ዘንድ የታየው ድክመት በህዝብ ዘንድ ካስከተለው ከፍተኛ የአመኔታ መሸርሸር ችግር በተጨማሪ በከተማም በገጠርም በጀመርናቸው ትራንስፎርሜሽንና ዘላቂ ልማትን የማረጋገጥ ሰራዎቻችን ለአደጋ ያጋለጠ እንደነበረ ማእከላዊ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡ በገጠርም በከተማም የቀረፅናቸው ፖሊስዎችና የቀየስናቸው ስትራተጅዎች ትክክለኝነት ላይ የሚያጠራጥር ነገር ባይኖርም ኣፈፃፀማችን የደረሰበት ደረጃ ባቀድነው ልክ ኣስተማማኝ መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ በህዝባችን ዘንድ ተገቢ ጥርጣሬ እንዲያድርበት ማድረጉም በትክክል ለይቷል፡፡ በገጠር የእርሻ ትራንስፎርሜሽን፣ በከተማ የኣነስተኛና ጥቃቅን ልማት፣ የከተሞች እድገት፣ የወጣቶች እና ሴቶች ስራ ፈጠራ እንዲሁም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዕድገት ባቀድነዉ ልክ ላለመመዝገቡ የስትራተጂክ አመራሩ ድክመት ዋናውን ድርሻ እንደሚወስድ ገምግሟል፡፡

የችግሩን ጥልቀትና የኣመራሩን ሁኔታ በስፋት ከገመገመ በኃላ ማእከላይ ኮሚቴው ለተፈጠረው የአመራር ችግር ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት በማመን ቀጥሎ ያከናወነው በመላው የማእከላይ ኮሚቴው ኣባላት የሚደረግ የሰላ ሂስና ግለሂስ ነው፡፡ ለተፈጠረው ችግር ማእከላዊ ኮሚቴው በአጠቃላይ ተጠያቂ ቢሆንም የችግሩ የከፋ መገለጫ የህወሓት ስራ ኣስፈፃሚ ኮሚቴ እንደ አካልም ሆነ እንደ ግለሰብ አመራሩ መሆኑን በመውሰድ ጥልቅ የሂስና ግለ ሂስ መድረክ ኣካናውኗል፡፡ የሂስና ግለሂስ መድረኩ አላማ በግለሰብ ኣመራር አባላት ላይ ያተኮረ ሳይሆን ድርጅቱ ካለዉ ስትራተጂካዊ ፖለቲካዊ ተልእኮ አንፃር እያንዳንዱ አመራር ሃላፊነቱን የተወጣበትን ደረጃ እና ልክ በትክክል ለመገንዘብ እና አስፈላጊዉን የእርምት እርምጃ ለመዉሰድ ያለመ ነበር፡፡ ሂደቱም በግልፅነት፣ በሙሉ ተሳትፎና በቁጭት መንፈስ የተከናወነ ሲሆን በመጨረሻም መላዉ አመራር ዘንድ በተደረሰበት ድምዳሜ ዙርያ የጋራ መግባባት የተያዘበት ሁኔታ ተፈጥራል፡፡

ማእከላይ ኮሚቴዉ የሂስና ግለሂስ ሂደቱን ካከናወነ በኃላ በድርጅቱ ስትራቴጂክ አመራር ዘንድ በስፋት ይስተዋል የነበረዉን የሃሳብና የተግባር አንድነት ችግር ስር ነቀል በሆነ መልኩ ለመፍታት የሚያስችል መግባባት ላይ የተደረሰበት የአመራር ሽግሽግ በማድረግ የተሃድሶው ስትራቴጂክ አመራር ተጠናክሮ የወጣበት የተመቻቸ ሁኔታ ፈጥሯል ፡፡

የተከበራችሁ የድርጅታችን አባላት፣ አርሶ አደሮችና የከተማ ነዋሪዎች።

ህወሓት የትግራይ ህዝብ የትግል ውጤት እና መሪ ድርጅት ነው፡፡ ጥንካሬው ለህዝቡ ካለው ታማኝነትና ወገንተኝነት የሚመነጭ ነው፡፡ ህወሓት ፈተናዎች ባጋጠሙት ቁጥር ከህዝብና አባላቱ ጋር በመሆን ችግሩን እየፈታ ለበርካታ አስርት ዓመታ ዘልቋል፡፡ ባለፉት ዓመታት ጥያቄዎችህን በመፍታት ረገድ የህወሓት አመራር ከፍተኛ ድክመት አሳይቶም ጭምር በትዕግስት እና በተስፋ መጠበቃችሁ ድርጅቱ ይገነዘባል፡፡ ማእከላይ ኮሚቴው ችግሩን በሚገባ ተረድቶ የናንተን ጥያቄዎችንና ፍላጎቶች ለመፍታት፣ በህዝብ ዘንድ በብዙ መልኩ ተሸርሽሮ የነበረውን አመኔታ ለማሳደስ የሚተጋ፣ በሃገር ኣቀፍ ደረጃ ሊኖረን የሚገባውን ገንቢ ሚና ለማስቀጠል ዝግጅነቱ ፣ ተኣማኒነቱና ፅናቱ ያለው፤ ስኬቶቻችንን ለማስቀጠል የቆረጠና ቀጣዩን ጉባኤ ኣሳታፊ በሆነ መልኩ ለማከናወን የሚያስችል ስራዎችን የሚሰራ ኣመራር እንደሚሆን ኣንጠራጠርም፡፡ አመራሩ በጊዜ የለም መንፈስ ከመላው አባላችንና ህዝባችን ጋር በሚደርገው ጥልቅ ውይይት ያስቀመጣቸው ኣቅጣጫዎች በበለጠ ለማበልፀግ የሚያስችል ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡
የጉባኤ ዝግጅታችን መላው አባላችን፣ ምሁራን፣ ወጣቶች ፣ ሴቶችና ብዙሃን ማሕበራትን በነፃነት ባሳተፈ መልኩ እንዲካሄድና በተመረጡ የህዝብ አጀንዳዎች ላይ አተኩሮ ለማካሄድ የሚያስችል ዙርያ መለሽ ዝግጅት የሚደረግ ይሆናል፡፡ እንደተለመደው ሁሉ አሁንም ከጎናችን ቁማቹህ ለጥቅማቹህ መረጋጥ እንድትታገሉ ድርጅታቹ ህወሓት ጥሪውን ያቀርባል።

የተከበራችሁ የክልላችን ምሁራንና ልማታዊ ባለሃብቶች።

የህወሓት/ኢህአዴግ አመራር በሚፈለገው ደረጃ የተመቻቸ ሁኔታ ባለመፍጠሩ ምክንያት በክልላችሁና በሃገራችሁ ጉዳይ ላይ በሚገባው ደረጃ ያላሳተፍናችሁ መሆኑን ተገንዝቧል። በመሆኑም ጥያቄያችሁን ለመመለስ የራሳችሁን የተሟላ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ህወሓት/ኢህአዴግ ምሁሩና ባለሃብቱ በመሰላችሁ አደረጃጀት ውስጥ ሆናችሁ ተዋናይ የምትሆኑበት ተቋማዊ መሰረት በማስቀመጥ ከልቡ የሚሰራ ይሆናል፡፡ በጥናትና ምርምርም ሆነ በልማት የክልላችንም ሆነ የሃገራችን ልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ባለቤት የምትሆኑበት ሁኔታ ይመቻቻል ፡፡

የተከበራችሁ የክልላችን ወጣቶችና ሴቶች።

በክልላችን ልማትም ሆነ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያላችሁ ተሳትፎ ለሃገራችን ዕድገትና ህዳሴ መረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡ ከምንም በላይ የተጠቃሚነትና የተሳታፊነት ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚንቀሳቀስ ድርጅታችሁ ህወሓት/ኢህአዴግ ቃል ይገባል፤ እናንተን በፅሞና ለማዳመጥና ለማታገል የሚያስችሉ መድረኮችንም ያመቻቻል ፡፡

ዉድ የኢህአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶች።

በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙርያ ህዝባችን ለከፍተኛ ምሬት የዳረጉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በኣመራሩ ድክመት የተፈጠሩ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጅታችን ህወሓት/ ኢህአዴግ በአገር ደረጃ በሚደረጉ የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎቻችን በማሳካት ረገድ ሲጫወት በመጣው ሚና ላይ ኣሉታዊ ተፅእኖ መፍጠሩንም በሚገነባ ይገነዘባል፡፡ የኣመራር ድክመት በህወሓት ውስጥም ሆነ በክልላችን በሚደረጉ የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጥረቶች ላይ ጉዳት ከማድረሱ በተጨማሪ በእህትና በአጋር ድርጅቶች መካከል ለበርካታ ኣስርት ኣመታት የነበረውን በመርህ እና በትግል ላይ የተመሰረተ ውህደት፣ ለዙርያ መለሽ ስኬት ያበቃን የአመለካከትና የተግባር ኣንድነት በየጊዜው እየተሸረሸረ እንዲመጣና በጋራ ዓለማ ዙርያ በአንድ ልብና መንፈስ ከመንቀሳቀስ ይልቅ በንትርክና በጥርጣሬ መተያየት ያጠላበት እንዲሆን በማድረግ በኩል የራሱን ኣሉታዊ ኣስተዋፅኦ እንደደረገ በትክክል ኣስቀምጣል፡፡

ሁሉንም አቅሞቻችን፣ የህዝባችንን ፍትሓዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ የጠሩ ፖሊሲዎቻችን ሲኬታማ ኣፈፃፀም ላይ ከማድረግ ይልቅ የፌዴራል ስርዓት ጠላቶች ባጠመዱልን ወጥመድ ውስጥ ገብተን የሃገራችንን ኢትዮጵያ ህልውና ፈተና ላይ እንዲወድቅ በማድረግ ረገድ በህወሓት ኣመራር ዘንድ የታየው ድክመት የማይናቅ ሚና እንደነበረው በግልፅ ይረዳል፡፡ የፈዴራል ስርዓቱን ለመናድ ከውስጥም ከውጭም የተሰባሰቡ ጥገኛ ሃይሎችን በጋራ የመመከት ኣቅማችን እየተመናመነ በተመሳሳይ ፕሮግራምና ልማታዊ መስመር ዙርያ የተሰለፉ ሃይሎች የጋራ ትግላቸዉ መደነቃቀፍ የጀመረበት ሁኔታ ተፈጥራል፡፡ በኢህኣዴግ ኣባል ድርጅቶች ውስጥ ለሚታዩ ችግሮች ዋነኛው ተጠያቂነት ለየድርጅቱ ኣመራር የሚተው ቢሆንም በህወሓት ኣመራር ውስጥ ይታዩ የነበሩ ኣዝማሚያዎች ለብዙ ኣስርተ ዓመታት በእሳት ጭምር ተፈትኖ የመጣውንና ለሃገራችን ኢትዮጵያ ልማትና ዴሞክራሲ እውን መሆን ምክንያት የሆነው አብዬታዊና ዲሞክራሲያዊ አንድነት በመሸርሸር ረገድ የማይናቅ ድርሻ እንዳነበረው ማእከላዊ ኮሚቴው ባደረገው ግምግማ ኣረጋግጧል፡፡

ህወሓት ከእህት እና አጋር ድርጅቶች ያለውን ግንኝነት በመርህና በመተጋገል ላይ በመመስረት የሚታደስበት የነበሩ የርስ በርስ መጠራጠሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ኣቅጣጫዎችን የሚከተል ይሆናል፡፡

ዉድ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች፣ ላብአደሮች፣ ልማታዊ ባለሃብቶች።

ህወሓትና የትግራይ ህዘብ ከሌሎች እህትና ኣጋር ድርጅቶች እንዲሁም ከመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመሆን ለእኩልነትና ለፍትሓዊ ተጠቃሚነት የከፈሉት እጅግ ከፍተኛ መስዋዕትነት ሳይበቃውና ተከታታይ ገዢዎች ያሲረፉበት ቁስል በወጉ ሳያገግም ለሌላ የተቀናጀ ጥቃት የሚጋለጥበት ሁኔታ ከመፍጠር ኣንፃር የህወሓት ኣመራር ውስጥ የታየው ድክመት የማይናቅ ኣስተዋፅኦ ኣድርጓል፡፡

አሁንም ቢሆን ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን ያመጣቸዉን ትሩፋቶች ጠብቆ የተሻለ ብልፅግና የሰፈነባት እና ህዳሴዋ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን እዉን ለማድረግ በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ዉስጥ ድርሻዉን ኣጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከዉጭም ከዉስጥም የሚቃጡብንን አፍራሽ ጥቃቶች ለመመከት ከመላዉ የሃገራችን ህዝቦች ጋር በቅርበት ይሰራል፡፡ በአሁኑ ሰአት በየአካባቢዉ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትና የህዝቦች የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የልማት ጥያቄ በተገቢዉ መንገድ ለመመለስ በሚደረገዉ ርብርብ ዉስጥ ድርሻዉን ለማበርከት ዝግጅነቱን ይገልፃል፡፡ ህወሓት/ኢህኣዴግ የጋራ ሃገራችንን በሆነችው ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ የተጫወተውን ገንቢ ሚና ኣጠናክሮ ለመወጣት የሚያስችለውን ኣቅጣጫዎች ከህዝቦች ጋር በመመካከር የሚያከናውን ይሆናል፡፡ ዲሞክራሲያዊ አንድነታችሁን አጠናክራችሁ አፍራሽ አጀንዳዎቻችውን ለማሳካት ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚዳክሩ ጠላቶችን በጋራ እንድንመክት ጥሪውን ያቀርባል።

የህወሓት ማ/ኮሚቴ
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማእታት
ህዳር 21/2010 ዓ.ም

Address

5405 Duke Street
Alexandria, VA
22304

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia2day posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopia2day:

Videos

Nearby media companies


Comments

ስም ያልተገኘለት ፌክ ኢህአዴግ ፓርቲው አመርቂ ለውጥ አምጥተዋል!? "አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ ስለሌለ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ጥሩ ሆኖዋል።" የኢህአዴግ መንግስት/ህወሓት መር/ የሌቦችና የሙሰኞች ስብስብ ነበረ። ጨቋኝና አፋኝም ነበረ። የሚጨቁነው ለ(አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ለጋዜጠኞችና ጦማርያን፣ አንዳንዴም ለምሁራን…ወዘተ) ነበረ። የኢኮነሚያዊ ጭፍለቃም ነበረ። የቀረው ሰፊው ህዝብ ግና በዕለታዊ ኑሮው ደፋቀና ከማለት በመድረኮችም ሆነ በሌላ ዕለታዊ የኑሮ መስተጋብሩ እምብዛም የሚያስተውለውና ትልቅ ችግር የሆነበት ነገር አልነበረም። ለማለት የፈለኩት;- በአንድ ከተማ ወይም ገጠር ያሉት የአንድ ማ/ሰብ አባላት በብሄራቸው ወይም በፖለቲካዊ አመለካከታቸው ምክንያት የህይወትም ሆነ የአካል ጉዳት አይደርስባቸውም ነበር። በኢህአዴግ/ህወሓት ዘመን ኢህአዴግ/ህወሓት የምትቃወም ከሆነ ብቻ የመንግስት አካላት ያጠቁሀል እንጂ ህዝብ ምንም አይልም ነበረ። ኢህአዴግ/ህወሓት አንድ ግለሰው ወይም የአንድ ብሄር ተወላጆች በአደባባይ በህዝብ የደቦ ፍርድ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ይጠብቅ ነበረ። በስልጣኑ ከመጣህበት እርምጃ የሚወስድብህ ቢሆንም ሰው ለሰው በብሄር አመክንዮ መገዳደል ያስጀመሩት ግን #ቲም ለማ የተባሉት ቡድን አባላት ናቸው። አሁን ግን ሁለቱም የለም። አንደኛ ይህ ስሙ ያልታወቀ ፌክ ኢህአዴግ በስልጣኑ ከመጣህበት አይምርህም። አልተደመርኩም ካልክ ራሱ #ፀረ ለውጥ፣ ተሸናፊው ሀይል፣ ጥቅመኛው ቡድን፣ የተባረረው ሀይል፣ ለውጥ አደናቃፊ" ወዘተ ብሎ ያጠምቅህና ባለ ስልጣን ወይም ኢህአዴግ አባል ከነበርክ "በቀድሞ ከለውጥ በፊት የዜጎች ሰብአዊ መብት የገፈፈ፣ የህዝብ ሀብት አለቅጥ ያባከነ" ብሎ ይፈርጃል። ከምኑ ኢህዴግ ቤት ካልነበርክም ግን አሁን የተደመርክ ካልሆነ "ከቀድሞ ባለስልጣናት በመመሳጠር" ብሎ ይፈርጀሀል። ሁለተኛ ይህ የለውጥ የተባለው ምናባዊ ለውጥ መሪ ቡድን ባትቃወምም የአንድ ብሄር ተወላጅ/አባል በመሆንህ ብቻ ከአንድ ብሄር አባላት ለሚደርስህ ጥቃት፥ ወይም አንድ ብሄር በሌላ ብሄር ለሚያደርሰው ግድያ፣ ማፈናቀል፣ የልውረር የሚልፉከራና ቻዛ ከለላም ዋስትናም አይሰጥም። በአሁኑ ሰዓት ጠቅላዩን ጨምሮ ከጥቃት ስጋት ነፃ የሆነ አንድ ሰውም ሆነ ብሄር የለም። በፊት መንግስትን ከሚቀናቀኑ ጥቂት የፖለቲካ አቃላጣፊዎች በቀር ሁሉም ያለስጋት ከፍርሀት ነፃ ሆኖ ይኖር ነበር። በጣም የገረመኝ ቢኖር የዓለም ህዝብ በሙሉ ለውጥ እያለ ሲለገልፍ ነው። ፖለቲከኞች "በአሁን ለውጡ አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ ስለሌለ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ጥሩ ነው።" ሲሉ እሰማሎህ። ይህ ስህተት የሆነ አገላለፅ ነው። ምክንያቱም "አንድ የታሰረ ጋዜጠኛ ስለሌለ የፖለቲካ ምህዳሩ ጥሩ ነው" ማለት #ጋዜጠኞች ምንም ህግ ቢጥሱም መከሰስ መታሰር የለባቸውም የሚል ወይም ደግሞ ጋዜጠኞች ሁሉ ብፁኣን ስለሆኑ ህግ አይተላለፉም" የሚል ትርጉም የሚሰጥ ነው። ጋዜጠኛ አለመታሰር የዴሞክራሲ ምህዳር ስለመስፋቱ እንዴት ሊገልፅ ይችላል? ጋዜጠኞችም ጦማርያንም አክቲቪስቶችም ቢሆኑ ህግ ቢተላለፉስ መታሰር እንዴት የለባቸዉም? በነፃ ፕረስ ስም ማንም ተነስቶ ጥላቻና የዘር ዕልቂት ሲሰብክ የህትሕ ስርዓቱ ዝም ብሎ ሲመለከት እንዴት የነፃነት መብት ሊሆን ይችላል? የማልረሳውና መቼም ይቅር የማልልበት #እስክንድር_ነጋ አንድ ወቅት #በሰንደቅ_ጋዜጣ ላይ እንዲህ ብሎ ፅፊ ነበር። "ኑ ከናዚዎች ጀግንነትን እንማር፥ ነቀርሳ የሆነ አንድ ብሄር፥ ዘር ወይም ማህበረሰብ ይመንጠር። እንክርዳድ ይነቀል።" (ይመንጠር የተባለው የትግራይ ህዝብ መሆኑ ነው) ይህ አገላለፅ የናዚ ታሪክ ለሚያውቅ አስደንጋጭ ነው። የትግራይ ህዝብም ቢልዮኖች ከሰረቁ ይልቅ ይህ ዓይነት አክቲቪስት የህልውናው አደጋ ስለሆነ በቀላሉ የሚያልፈው አይደለም። እንዲህ ዓይነቶቹ ጋዜጠኞች በህግ አለመጠየቅ የፕሬስ ነፃነት የዴሞክራሲ ምህዳር መስፋት ሳይሆን ግልፅ የህግ ጥሰት ነው። የመድረክ ስዎች እኔ ከተመቸኝ ምን አገባኝ እያሉ ነው። ይህ ደግሞ ረዥም ርቀት የማያስኬድ በመሆኑ ለማናችንም አይጠቅምም። በአሁኑ ሰዓት በሀገረ ኢትዮጵያ የምግብና ቁሳቁስ እርዳታ የሚደረግላቸው #ከ9ሚልዮን በላይ ተፈናቃዮች አሉ። #ጌዴኦዎች ብቻ ከ1.4 ሚልዮን ህዝብ በላይ በአስቸኳይ #የአልሚ_ምግብ እርዳታ እየተደገፈ ይገባል። ሌሎችም በሶማሌ ክልል፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ በደቡብ፣ በቤንሻንጉልና በደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በትግራይ ክልልም ከሌሎች ክልሎች የተፈናቀሉ ተጋሩ በእርዳታ እየኖሩ ነው። እስከዛሬ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ችግርና ችጋር አይታ አታውቅም። ምን እስከምንሆን እያየን ይሆን! መቶ ሚልዮን ህዝቡ እስከሚፈናቀል ወይም እልቂት እስኪመጣ! "ኢትዮጵያም ሆነ ለውጡ ችግር ላይ ነው የሚባለውስ ከዚህ በላይ ምን ስንሆን ነው? #መከላከያ ተልዕኮው መንግስትን መጠበቅ ነው ወይስ ህዝብና ሀገር? ይህ የለውጥ ሀይል የተባለው ቡድን እንቅስቃሴ ከጀመረ ከ2008ዓ/ም ጀምሮ የስንት ዜጎች ህይወት እየበላ መጥተዋል። የብሄር ተኮር ጥቃትም አስጀምረዋል። ኢህአዴግ/ህወሓትም የተሻለ ነገር እንዲመጣ በመጠበቅ ስልጣኑን ጠቅልሎ አስረክቦታል። ነገር ግን ሰላም ከመምጣት ይልቅ ትርምስና ነውጥ በዝተዋል። የዜጎች ደህንነት ስጋት ላይ ወድቀዋል። ህዝቡ ስጋት ላይ ነው ያለው። ህግና ስርዓት ፍርስርስ ብሎ በዜጎች ሀይል መጠቀም አማራጭ ከሆነ ሰንብተዋል። እንደሚባለው #መከላከያ የሀገር ጠባቂ ከሆነ ሀገሪቱን ማዳን ይኖርበታል። መከላከያ የመንግስት ጠባቂ መሆኑ ብናውቅም! ይህ #ለውጥ የተሰኘው በኢህአዴግ ስም የሚነግደው ድርጅት በድክመትም ይሁን በሌላ ሀገር ማስተዳደር አቅቶት መከላከያም ሀገሪቱ ከመዳን ይልቅ የዚህ ደካማ ቡድን ጠባቂ ሆኖ መቅረት እውነትም ያሳዝናል። ከአንድ መቶ ሚልዮን ህዝብ 10 ሚልዮን (10%) ተፈባቅለዋል። ቀሪው 90%ትም በስጋት ላይ ነው። የዚህን መንግስት ህልውና ምን በጀን!? መከላከያ ሀገሪቱን ተረክቪ ለሽግግር መንግስት ማስረከብ አለበት! #ፍትሕ_ለጌዴኦ_ህዝብ! ፍትሕ ለሁሉም ተፈናቃይ ወገን
አጫሽ በአሜሪካ
[ምርጥ ዘፈን] አቡሽ ዘለቀ ~ "አንቺ ልጅ ተይ እንተሎ "
Addi Abeba
Amazing VIDEO Great #Ethiopian Run 2017 in Addis Ababa, Ethiopia #ETHIO #Ethiopia #GreatEthiopianRun
Mekelle FC VS Jimma FC
ደወል ፩ የኢትዮጵያ ሃገራችን ዋና ችግር ኢህአዲግ ነው ካልን ፣ ኣዎ! ልክ ነን ኣልተሳሳትንም! ህወሓት ነው ካልን! ኣዎ! ነው ኣልተሳሳትንም! ዳሩ ስህተት የሚሆነው ትርጉምና ኣተረጓጎም ላይ ሲሆን ፣ትልቁ ስህተትም በትግሉ ኣቅጣጫ ተሳስተናል ብቻ ሳይሆን ተለያይተናል በጣም ተራርቀናልም። ኢህአዲግ ማለት ህወሓት ጠፍጥፎ የሰራው ፓርቲ ነው…ህወሓት ከፈረሰች ኢህአዲግ ይፈርሳል የሚል ብሂል ሞኝነት ነው። እንደው ወደር ያልተገኘለት ቂልነት! እንደኔ እይታ… በኢህአዲግ ውስጥ ህወሓት ፣ ኢህአፓ ፣ መኢሶን፣ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ህግሓኤ ፣ መኣህድ፣ ኢህዴን ፣ ግገሓት ወዘተረፈ ኮለል ብሎው ይታዩኛል። የሃገራችን መሰረታዊ ችግር የነዚህ ደም የወለዳቸው የስልሳዎቹ የእርግማን ዘሮች ድምር ውጤት እንጂ ኣንዱን ቀድሶ ኣንዱን ውጉዝ ከመ ኣርዮስ ማለት ኣይቻልም። እነዚህ ሃይሎች ፣ ድርጅቶች ፣ ብዱኖችና ግለሰቦች የስልጣን ጥማት እንጂ ህዝባዊነት ከቶ የላቸው። ቆራጦች እንጂ ፈሪሃ እግዚኣቢሔር ከቶ ኣልፈጠረባቸውም። እልቂትና ደም መፋሰስ እንጂ ፍቅርና ምህረት ኣልታደሉትም። ፋኖነትና ጦረኝነት እንጂ ለትህትና ቦታ የላቸውም! ሌላም ሌላም! ኣንተ ጅል! ማዶ ተጎልተህ ህወሓት ይውደም ኣትበልብኝ! ስለህወሓት እኔ ወንድምህ ኣለሁልህ! ህወሓት እንዴትና በምን እንደምጥለው ራሴ ጠንቅቄ ኣውቃለሁ። ቁም ነገሩ ከህወሓት ውድቀት ወድያ ማዶ ያለ ዝባዝንኪና ዝርክርክ ነገር ነው። ለደፈረሰች የነገይቱ ኢትዮጵያ ዛሬ ኣላማስልልህም! ዓላማችን ፣ ራእያችን፣ የትግላችን ግብና ኣቅጣጫ ተመሳሳይና ተመጋጋቢ ሲሆን ነው ትግሉ ኣመርቂ የሚሆኖው። ለመታገል ብቻ ዘው ተብሎ ትግል ውስጥ ኣይገባም! ውጤት የሚሉት ኣለ ትልቅና ኣሳሪ ነገር! ያንተ ወሮበሎች ብጉያህ ሸሽገህ ኣድማስ ተሻግረህ ኣታማስል። ትግል በጥበብ እንጂ በስሜት ኣይመራም! የችግሩ ምንጭ በውል ካልለዩ ትግል ባይጀምሩ። ኦህዲድ ፣ ብአዲን/እህዲን፣ ደኢህዴን ና ህወሓት ሁሉም ያው የሌቦች መፈንጫና ማድለብያ ድርጅቶች ናቸው። ትግራይ ውስጥ ያለ ጅብ ካልታገልኩ ፣ ኦሮሞ ባለው ከርከረ ብጨነቅ ምኑ ጋ ነው ያተረፍኩት? ኣማራ ክልል ያለ የጥፋት ኣውልያ በሃገሬው ሰው ለዛውም በወጣቱ ካልተፈለፈለ ፣ ወደ ሌላ ጣት መቀሰሩ ፣ ተያይዘን እንጥፋ የሚል ቁንፁል ኣመለካከት ካልሆነ በስተቀር ምንም! ሁሉም ሌቦች! ሁሉም! ፍትህ ኣጉዳዮች! ሁሉም ደም ኣፍሳሾችና ኣፋሳሾች! ሁሉም ኣግላዮች! ሁሉም ውድቀታችን የሚያፋጥኑልን እንጂ ማነው ህወሓት ጭራቅ ብሎ ብአዲን መልኣክ ነው የሚለኝ? ማን ነውሳ ኦህዲድ ፃድቅ ነው የሚለኝ? ደኢህዲንም ጅቦች የሚያደልብ የጅቦች ድርጅት እንጂ ከየት ኣምጥቶት ነው ልማት የሚያፋጥነው? እንዴ! ኣንተ ማነህ!? እዛ ማዶ? ቢቻል ቢቻል! ኣዲሱ ትውልድ ሙሉ በሙሉ ከስልሳዎች የፖለቲካ ኣዙሪትና ተፅዕኖ መላቀቅ መቻል ኣለበት። ከደሙ ንፁህ የሆነ የኔ ትውልድ ፣ ስለምንድን ነው ወደ ስልሳዎቹ የጦረኝነትና ፋኖነት የጅሎች ፖለቲካ የሚሯሯጠው? ያራሱ ኣጀንዳ ሳይቀርፅ ፣ከዛሬ 40ና 50 ዓመት የተቀረፀለትን ኣጀንዳ ይዞ እንደ ጅራፍ ያስጭኋል እንዴ!? ና'ማ! ተከተለኝ! ኣባይ ፀሃዬ ለትግራይ ያልጠቀመ ኦሮምያን ይጠቅማል ብዬ ኣልገምትም ኣላስበውም! ስለዚ ኣባይ ፀሃዬ ሃገር ኣጢፍ ነው ካልኩኝ ፣ ኦሮምያን ድምጥማጥዋን ያጠፋትና ቀረጣጥፎ የበላት ያለ ማወላወል ኣባ ዱላ ገመዳ መሆኑን ላስምርልህ። በተመሳሳይ ኣማራ ክልልን ወደ ጥፋት ኣሮንቋ እየጎተተ ከናት ኢትዮጵያ ሊለያት እትብትዋን እየቆረጠ ያለው ገዱ እንዳርጋቸው መሆኑን እወቅ። እዛ ታገል! መቐለ ላለው ኣባይ ወልዱ ፣ መቐለ ያለ እሳት የላሰ ወጣት ታጋይ ተውለት! ቤትህ ኣፅዳ ቤቴዬን ላፅዳ! በማያገባህ ገብተህ ኣትፈትፍት። የትግራይ ህዝብ ዝም ማለቱ ኣይድነቅህ! ስለ ደላው እንዳይ መስልህ! የሰላም ዋጋ ምን ያህል ውድ መሆኑን በወሬ ሳይሆን ከኣንድ ቤት ኣራት ኣምስት ብርቅዬ ልጆቹ ገብሮ መኩሮት እንጂ። ኣራት ኣምስት ልጆችዋን ቀብራ ፣ ልጆችዋን የተውላት ቲኒሽዬ ሰላም ተጠቅማ ትለምናለች እንጂ የልጆችዋን የደም ካሳ ኣልጠየቀችም። ከሁሉም በላይ ሰላም ግን ኣሁንም ትፈልጋታለች! ይቀጥላል………… ሰላም! ወዲ ገረብ ፃና!