
02/10/2025
አሰብ የማን ናት?
ኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤት ከአደረጓት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1434 − 1468) ጀምሮ፣ የቀድሞዎቹ “ታሪካዊ የባሕር በር ባለቤትነትዋን አስከብረው ቢያልፉም፤ ይኽ ትውልድ ግን የተረከበውን አደራ መጠበቅ አልቻለም። የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር ማካለልን በተመለከተ ብያኔ የተካኼደበት የአልጀርሱ ስምምነት መሠረት የአደረገው የኢትዮ ጣልያን የቅኝ ግዛትን ስምምነት ነው። በኢትዮጵያ ላይ በፍጥነት የተሠራውን ሸፍጥም “የባሕር በርን የሚዘጋ፣ ባድመን፣ ኢሮብን፣ ጾረናን፣ ከፊል አፋርንና ሌሎችም የኢትዮጵያ ግዛቶችን ለኤርትራ አሳልፎ የሚሰጥ ውዝግብ በ285 ቀናት ውስጥ መጠናቀቁ የጊዜ ሰሌዳውን አጠያያቂ ያደርገዋል።
ለኢትዮጵያ የወደብ አስፈላጊነት በጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም።