Yonas Tade

Yonas Tade ይህ ቻናል መንፈሳዊ መልእክቶች እና ዝማሬዎች ይተላለፉበታል:

08/23/2026

አንድ ወደ ላጤ ለገና በዓል ሰው ሁሉ ቤት ዶሮና በግ ሲገዛ አይቶ እርሱም ቅርጫ ገባና ስጋውን በዘንቢል ይዞ ወደ ቤት ተመለሰ፡፡ ለጥብስ የሚሆን ይመርጥ ዘንድ ሙዳ ሥጋውን ጎትቶ መክተፊያ ላይ አስቀምጦ ቢላዋ ሊዋስ አከራዩ ቤት በሄደበት ድመት ገብታ ሥጋውን ጎትታ ትወጣለች፡፡ ሲደርስ ድምቷን ተመልክቶ በንዴት ይከተላት ጀመር፡፡ ድመቷም ሙዳዋን ላለማጣት ፈጥና ጢሻ ውስጥ ገባች፡፡ በንዴት ስሩ እንደተገተረ ወደ ቤት ሲመለስ ቤቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተደርምሶ ጣሪያው ቤቱ ላይ ወድቆ ተመለከተ፡፡ በዚያ ሰዓት ቤት ውስጥ ሆኖ ቢሆን ሟች እንደነበር ተረዳ፡፡ እግዚአብሔር ሊያተርፈው ትንሽ ድመት እንደላከለት ሲመለከት ተመስገን ብሎ ወደ ልቡ ተመለሰ፡፡ ተወዳጆች ሆይ፡ -በአስቸጋሪ ህይወታችሁ ውስጥ እግዚአብሔር የሚያመጣውን ትርፍ ታያላችሁና አትቸኩሉ፡፡ ኑሃሚን በብዙ ኪሳራዋ ውስጥ ቆንጆዋን ሩትን አትርፋለች፡፡ ጎደለኝ፣ አልተሳካም፣ መከራ በዛብኝ፣ ተፈተንኩ፣ ትግልና ተግዳሮት በዛብኝ የምትሉ ሆይ አምላካችሁ በዚህ ውስጥ የሚሰጣችሁ ውብ ስጦታ አለ፡፡ የሚሆነውን አታውቁም እና ዝም በሉ፡፡ ኑሃሚን በረከቷን ሩትን ይዛ ቤተልሔም ስትደርስ እግዚአብሔር አስመረረኝ እያለች ጌታዋን ትወቅስ ነበር፡፡ ለማኝ ሆና የምትቀር መስሏት ነበር፡፡ ይህን ያለችው እርሷ እንጂ እግዚአብሔር አልነበረም፡፡ ቆይቶ ሩት ጸሐይ ሆና ወጣችላት፡፡ የትልቅና የሃብታም ቤተሰብ አያት ለመሆን በቃች፡፡ እግዚአብሔር እንደዚህ ነው፡፡
ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም

08/23/2026

ተጉዘን ከመጣነው መንገድ የሚቀረን ወሳኝ ነውና ጉዞአችንን አናቋርጥ ተስፋም አንቁረጥ ወደፊት ብቻ::
እግዚአብሔር አምላክ በመንገዳችን ይቅደምልን::

ይህ ምስል የ21ኛው ክፍለዘመን ዘመናዊ አለም ቢሆንም ከስማርት ስልክ ነፃ ነው። ይህ የአንባብያኑ የሩስያውያን ምድር ነው። ሩስያውያን አሁንም አንገታቸውን ወደ መፅሀፍ እንዳቀረቀሩ ነው። መኮ...
08/23/2026

ይህ ምስል የ21ኛው ክፍለዘመን ዘመናዊ አለም ቢሆንም ከስማርት ስልክ ነፃ ነው። ይህ የአንባብያኑ የሩስያውያን ምድር ነው። ሩስያውያን አሁንም አንገታቸውን ወደ መፅሀፍ እንዳቀረቀሩ ነው። መኮረጅ ካለብን ይሄን ነው!!!

✝️መስቀል አምላክ ሰውን ወዶ እጁን የዘረጋበት የፍቅር ዙፋን ነው።✝️ሞትን በሞት ሽሮ ነፃነትን ያስገኘ መሣሪያ ነው።✝️የትህትና ምሳሌ፡ አምላክ ራሱን አዋርዶ ለፍጥረቱ ሕይወቱን የሰጠበት ጥ...
08/20/2026

✝️መስቀል አምላክ ሰውን ወዶ እጁን የዘረጋበት የፍቅር ዙፋን ነው።

✝️ሞትን በሞት ሽሮ ነፃነትን ያስገኘ መሣሪያ ነው።

✝️የትህትና ምሳሌ፡ አምላክ ራሱን አዋርዶ ለፍጥረቱ ሕይወቱን የሰጠበት ጥግ ነው።

08/19/2026

በራስ ፅድቅ መተማመን የእግዚአብሔርን ቸርነት የመስቀሉን ስራ ያስረሳል::

ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው አበይት በዓላት አንዱ ደብረ ታቦርን ነው፡፡ ደብር ተራራ ማለት ሲሆን፤ የታቦር ተራራ ማለት ነው ሲተረጎም፡፡ ቀኑ በዓለ ኢየሱስ ነው፡፡ በእርግጥም ጌትነቱ የሚነገ...
08/19/2026

ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው አበይት በዓላት አንዱ ደብረ ታቦርን ነው፡፡ ደብር ተራራ ማለት ሲሆን፤ የታቦር ተራራ ማለት ነው ሲተረጎም፡፡ ቀኑ በዓለ ኢየሱስ ነው፡፡ በእርግጥም ጌትነቱ የሚነገርበት ቀን ነው፡፡ጎልጎታ መድኃኒትነቱና ሰው በመሆን ቤዛ መሆኑን ያሳየበት ተራራ ሲሆን፣ ታቦር ጌትነቱ የታየበት ተራራ ነው፡፡ ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ይዞ ተራራ መውጣቱ ጌትነቱን ያሳያል፡፡ የእግዚአብሔር ክብር በተራራ ሲገለጥ ኖሯል፡፡ በብሉይ ኪዳን በኮሬብ፣ በቀርሜሎስ፣ በሞርያ እንዲሁ በአዲስ ኪዳን በቆሮንቶስ፣ በደብረ ዘይት፣ በጽዮን፣ በታቦር ተራራ ከፍ ያለ ጌትነቱን ሲያሳይ ኖሯል፡፡ ዛሬም እጃቸውን ይዞ እንዲኖር ለሚፈቅዱ ወደ ከፍታ ተራራ ህይወታቸውን ይዞ ይወጣል፡፡ ፊቱ እንደ ጸሐይ ማንጸባረቁ ማንም በማይቀርበው ብርሃን የሚኖር ጌታ መሆኑን ያሳየበት መገለጥ ነበር፡፡ ልብሱ እንደ መብረቅ በሆነ ጊዜ ብርሃን የለበሰ የብርሃናት አዛዥ፣ የመላእክት አዛዥ እርሱ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ከሙታን መሃል ሙሴን፣ ሳይሞቱ ከተነጠቁ ቅዱሳን ኤልያስ አጠገቡ ቆመው በታዩ ጌዜ፤ በእርግጥም ኢየሱስ የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ሳይሆን የህያዋንና የሙታን ጌታ እንደሆነ ታወቀ፡፡ እነ ቅዱስ ጴጥሮስ በድንጋጤ እንደ ሞተ ሰው በሆኑ ጊዜ ዳስሶ ተነሱ ማለቱ ወደ ፊት ከሙታን የሚጠራን ትሳኤያችን እንደሆነ ታየ፡፡ በክብር ደመና ውስጥ አብ የምወደው ልጄ በማለቱ የዮሴፍ ልጅ ሳይሆን ጌታ የሆነው የአብ ልጅ እርሱም ጌታ እንደሆነ ሰማን፡፡ ደመና ወርዶ የሚከበው፣ በደመና መሃል የሚራመድ የልዑል ልጅ ኢየሱስ በታቦር ተራራ ጫፍ ቆሞ ታየ፡፡ የዛሬ በዓል ለዓለም ሁሉ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ሲናገር ይውላል፡፡ በዓመታት መካከልም ይህን ሲመሰክር ይኖራል፡፡ እንኳን አደረሳችሁ፡፡
ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም

Address

Atlanta, GA

Telephone

+14047865011

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yonas Tade posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yonas Tade:

Shortcuts

Share