ሃያ ሰባት ሚዲያ

ሃያ ሰባት ሚዲያ ፳፯
(1)

07/11/2025

❤️ ገብር መንፈስ ቅዱስ ርዕሰ ባህታዊ ❤️






























.

ቤተ ክርስቲያንና ሆስፒታልን ምን አገናኛቸው?ሕሙማንን በአንድ ቦታ አስቀምጦ ማስታመምና ማከም ከቅዱስ ባስልዮስ ከተማ ቀመስ ገዳማዊ ሆስፒታል ከባዚልያድ የተገኘ ፅንሰ ሃሳብ ነው:: ገዳማውያን...
07/10/2025

ቤተ ክርስቲያንና ሆስፒታልን ምን አገናኛቸው?

ሕሙማንን በአንድ ቦታ አስቀምጦ ማስታመምና ማከም ከቅዱስ ባስልዮስ ከተማ ቀመስ ገዳማዊ ሆስፒታል ከባዚልያድ የተገኘ ፅንሰ ሃሳብ ነው:: ገዳማውያንም ከዓለም አይደሉም እንጂ በዓለም ውስጥ ናቸው:: ለማኅበረሰቡ የማይገዳቸው የራሳቸውን ደሴት ፈጥረው የሚኖሩም አይደሉም:: በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ብዙ ቅዱሳን አበው መነኮሳት በወረርሽኝ ዘመን ሕሙማንን ሲያስታምሙ በሽታውን ተጋርተው እንደ ሰማዕታት ሆነው ያረፉ አሉ::
ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳንና ጉባኤ ቤታቸው ይህንን የአበው አሠረ ፍኖት የተከተለ የሆስፒታል ግንባታ ዕቅድ ይፋ አድርገዋል:: ቤተ ክርስቲያን የሕሙማን መጠጊያ የድሆች ማረፊያና የአረጋውያን መጦሪያ የሆነች የማኅበራዊ አገልግሎቶች ሁሉ እመቤት ናት:: ይህንን በዘመናዊ መንገድ የማሳየት ታሪካዊ ዕቅድ ላይ ሁላችንም እንሳተፍ::

“አቤቱ ድውይ ነኝና ፈውሰኝ”መዝ ፮፥፪ በሚል መሪ ቃል ፈውስ መንፈሳዊ ዘጣና ቅዱስ ቂርቆስ በዓይነቱ ልዩ የሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት ተነስተናል። እርሶም ለዚህ ፕሮጀክት ከታች በተቀመጡት የባንክ አማራጮች አበርክቶ በማድረግ አሻራዎትን ያሳርፉ።

ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምሥክር ጉባኤ ቤት

TANA KIDUS KIRKOS YE-ABATOCH ENA YE-ENATOCH ANDNET GEDAM YE-ARATU GUBAYAT METSAHIFT MISKIR GUBAE BET

1000680619488 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
219553568 አቢሲኒያ ባንክ
2011111181981013 አባይ ባንክ
0068829811701 አሐዱ ባንክ
5020827358011 ዳሸን ባንክ

ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር
+251 982333444
+251 983333444
+251 984333444 ይደውሉ።

07/08/2025

😭 አባ ገብረ ኪዳን በእንባ ያስተላለፉት መልእክት 😭






























.

07/07/2025

❤️መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ♥️






























.

††† ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝ †††††† ✝እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ✝ †††††† ✝ቅዱስ ዮሐንስ መ...
07/06/2025

††† ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝ †††

††† ✝እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ✝ †††

††† ✝ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ✝ †††

=>ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

+የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

+ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

+የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

=>መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
+የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
+በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
+በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
+እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
+የጌታችንን መንገድ የጠረገ
+ጌታውን ያጠመቀና
+ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::

+ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::

+" አባ ጌራን ሕንዳዊ "+

=>ዳግመኛ በዚህች ቀን ሕንድ ካፈራቻቸው ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ጻድቁ አባ ጌራን ይታሰባሉ:: የእኒህ ቅዱስ ታሪክ አሳዛኝ ነው:: ቅዱሱ በሕንድ ተወልደው: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድገው: ገና በወጣትነታቸው መንነው: ደሴት ውስጥ ወደሚገኝ አንድ በርሃ ገብተዋል:: ከገድላቸው ጽናት: ከቅድስናቸውም ብዛት የተነሳ በሃገረ ሕንድ ሰይጣን እንዳይገባ: ጠብ ክርክር እንዲጠፋ: ሰው ሁሉ በፍቅርና በሰላም እንዲኖር ማድረግ ችለው በጣም ተወዳጅ ነበሩ::

+በዚህ የተበሳጨ ሰይጣን ግን ባልጠረጠሩት መንገድ መጣባቸው:: አንዲት ሴት ወደ እርሳቸው መጥታ (የንጉሡ ልጅ ነኝ በሚል) አስጠግተዋት ነበር:: አንድ ሌሊት ላይ ግን አውሬ ያባረራት በመምሰል ሩጣ ወደ ቤታቸው ገብታ አቀፈቻቸው:: በዚያ ቅጽበት ፍጡር ደካማ ነውና ታላቁ አባ ጌራን ተሰነካከሉ:: ከአፍታ በሁዋላ የሆነውን ሲያውቁ ደም አለቀሱ::

+ልብሳቸውን ቀደው: እንባቸው እንደ ዥረት እየፈሰሰ አለቀሱ:: ራሳቸውን በትልቅ ድንጋይ እየቀጠቀጡት የጭንቅላታቸውና የደረታቸው አጥንቶች ተሰባበሩ:: እርሱ እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ይቅር ብሎ: የቅድስና ስም ሰጥቶ በዚሕች ቀን ወደ ገነት አሳርጉዋቸዋል:: ለዚህ ነው መጽሐፉ "ጻድቅ 7 ጊዜ ይወድቃልና: ይነሣማል" ያለው:: (ምሳ. 24:16)

=>አምላካችን ከቅዱሱ ቤተሰብና ከጻድቁ አባ ጌራን በረከት ይክፈለን::

=>ሰኔ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ልደቱ)
2.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ (ወላጆቹ)
3.አባ ጌራን መስተጋድል (ሕንዳዊ)
4.ቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት-የአልዓዛር እህቶች)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

=>+"+ ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ:: መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና:: እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ:: ይሕም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው:: +"+ (ሉቃ. 1:76)

>

07/05/2025

እግዚአብሔር አምላክ ለአባታችን እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን የተጀመረውን ለፍጻሜ ያብቃልን
❤❤❤❤❤❤❤❤





























.

07/04/2025

ቤት ክርስቲያንንን መጠበቅ ማለት ሰይፍ እና ጦር ማንገብ አይደለም !
❤❤❤❤❤❤❤❤





























.

“በሥላሴሁ ሐነፀ ጥቅማ ለማርያም፤ ሰመየ ስማ ቤተ ማርያም” ቅዱስ ያሬድእንኳን ለበዓለ ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !
06/28/2025

“በሥላሴሁ ሐነፀ ጥቅማ ለማርያም፤ ሰመየ ስማ ቤተ ማርያም” ቅዱስ ያሬድእንኳን ለበዓለ ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !

06/21/2025

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
❤❤❤❤❤❤❤❤





























ለኔ የደረሰ ቅዱስ ሚካኤል ለናንተም ይድረስላችሁ ❤️🥰🥰ይለይብኛል ሚካኤል🥰💥🧡🧡🧡📸 𝙥𝙞𝙘 𝙤𝙛 𝙩𝙝𝙚 𝙙𝙖𝙮🔆:::
06/18/2025

ለኔ የደረሰ ቅዱስ ሚካኤል ለናንተም ይድረስላችሁ ❤️
🥰🥰ይለይብኛል ሚካኤል🥰💥
🧡🧡🧡
📸 𝙥𝙞𝙘 𝙤𝙛 𝙩𝙝𝙚 𝙙𝙖𝙮🔆
:
:
:





























Address

Broomfield, CO

Telephone

+17204420683

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሃያ ሰባት ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share