
07/18/2025
የትግራይም ሆነ የኤርትራ ህዝብ እንደ ማነኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ጥንትም አሁንም ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ 1.3 ሚሊየን ኪ.ሜ² ግዙፍ ምድር የእሱም ጭምር ነው ። ኢትዮጵያ የኤርትራ ክፍለ ሃገርን ጨምሮ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት እውነታው ይህ ነው ።
ሲቸገሩ፣ ሲያጡ ፣ ሲደሰቱም ሁሉም የሚመጣው የሚሰደደው ወደ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ነው በአለፉት 7ዓመታት ብቻ ወደ እናት ኢትዮጵያ የተሰደዱ ከ 1 ሚሊየን በላይ ኤርትራዊያን በኢትዮጵያ ዜግነት ተቀብለው ይኖራሉ ፣ ከዛ በፊት " ኤርትራዊ ናችሁ ተገንጠሉ" ተብለው ኢትዮጵያ የቀሩትን ቤት ይቁጠረው ፣ ከመላው ኢትዮጵያ የተዳቀለው የኤርትራ ክፍለ ሀገር ህዝብም በፖለቲካ ድራመኞች ጥረት ሀገር ለመሆን ሞክሮ ተነጥሎ ሀገር አልባ የሆነውም ለዚህ ነው።
የትግራይ ክልል ህዝብም ጉዳይ ከዚህ የተለየ አይደለም፤ "ሀገረ ትግራይ" ሚባል ነገር ቅዥት ነው፣ የህውሃትና ሻዕቢያ የደም ነጋዴ ቡድን በነ ስብሃት ዲዛይን ኤርትራን በግድ የገነጠለውና ኤርትራን ሃገር ያረገው ትግራይን የኢትዮጵያ ድምበር አርጎ ለማስገንጠል እንዲመች ነበር ፣ ነገር ግን ከዛ እልቂት በውሃላ እንኳን ትግራይ ሀገር ልትሆን ኤርትራም የተራ ክልል ቁመና መያዝ ተስኗት አረፈችው ።
ህዝብ ህዝብ ነው ፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከየትኛውም ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ምዕራብ ፣ምስራቅ ያለ ኢትዮጵያዊ ጋር ተዋልዶ ተዋዶ ነው እየኖረ ያለው። በመሆኑ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተናቦ እነዛን የነ ስብሃትና ኢሳያስ የውጭ ተላላኪ የኢትዮጵያን ታሪክ ያጠቆሩ ባንዶች ስብስብ ላይ ከተነሳ የኢትዮጵያ ችግር 99 ከመቶ ይፈታል።
ህዝባችንን የከፋፈሉት፣ የገነጣጠሉት፣ ለዘመናት ያባሉት የሻዕቢያ ህውሃት 100 ማይሞሉ አስመራና መቀሌ የከተሙ አዛውንቶች ላይ በቋንቋ በሰፈር ሳይከፋፈል ጥላቻን ጥሎ ...ሆ... ብሎ ለመነሳት ከዘመናት መተላለቅ ነፃ ለመሆንና አብሮ ታሪክ ለመቀየር ቁርጡ ግዜ አሁን ነው ።
በተረፈ እኛ ኢትዮጵያዊያን እውነታውንና ማንነታቸውን ከማስረዳት ባለፈ ግን የማይቀር የሆነው ኢትዮጵያ በድራማ የተነጠቀችውን የቀይ ባህር ድምበሯን በቅርቡ ወደ ራሷ ታካልላለች። ...ከዛ ከምፅዋ ወዲያ ሀገር ነኝ ሚል ካለ መንገዱን ስፖንጅ ያርግለት እንለዋለን ።
ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet