Fetan Zena - ፈጣን ዜና

Fetan Zena - ፈጣን ዜና Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fetan Zena - ፈጣን ዜና, Dallas, TX.

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በሙሉ ጤንነት ላይ ናቸው! ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ በካርል አደባባይ አካባቢ ድንገተኛ የመኪ...
06/30/2025

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በሙሉ ጤንነት ላይ ናቸው!

ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ በካርል አደባባይ አካባቢ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ቢደርስባቸውም፣ ሚኒስትሩ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ተወስደው ተገቢውን ህክምና አግኝተዋል፡፡ አሁን በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ከተወሰነ የእረፍት ጊዜ በኋላ ወደ መደበኛ ስራቸው ይመለሳሉ፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩ መሰረተ ቢስ መረጃዎችን እንዳትመኑ፣ እውነተኛውን መረጃ ለማወቅ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን መግለጫ ይከታተሉ፡፡

በትግራይ እና ኤርትራ ህዝቦች መካከል እየተፈጠረ ያለው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እሰራለሁ” - ህወሓት “ተመሳሳይ ግንኙነቶች ከሌሎች ጎረቤት ህዝቦች ጋር እንዲኖርም እጥራ...
06/23/2025

በትግራይ እና ኤርትራ ህዝቦች መካከል እየተፈጠረ ያለው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እሰራለሁ” - ህወሓት

“ተመሳሳይ ግንኙነቶች ከሌሎች ጎረቤት ህዝቦች ጋር እንዲኖርም እጥራለሁ” ብሏል

በትግራይ እና ኤርትራ ህዝቦች መካከል እየተፈጠረ ያለው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል” እንሰራለን ሲሉ በቅርቡ ህጋዊ ሰውነቱ በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ገለፁ። ደብረጺዮን፤ “ተመሳሳይ ግንኙነቶች ከሌሎች ጎረቤት ህዝቦች ጋር እንዲፈጸም ለማድረግ ትኩረት ሰጥተን አስፈላጊውን ጥረት እንደምናደርግ ልናረጋግጥ እንወዳለን” ብለዋል።

የህወሓት ሊመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ይህንን የተናገሩት የክልሉ ሰማዕታት ለ37ኛ ጊዜ ለማሰብ በሐውዜን ከተማ በተካሄደው ስነስርአት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

ሊቀመንበሩ ደብረጺዮን በተጨማሪም በመልዕክታቸው “የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት በርካታ ጉዳዮች አልተፈጸሙም ብቻ ሳይሆን ስምምነቱ ጠቅልሎ የሚፈርስበት እንቅስቃሴዎች ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ እየሄደ ይገኛል” ሲሉም አሳስበዋል።

🛑 ለጥንቃቄ      በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በአንዱ ካፌ አንድ ዝንጅብል ሻይ 629 ብር ይሸጣል ቢባል አትከራከሩ ።ካፌው አማረ ብላችሁ  ሻይ ቡና ልበል ብላችሁ ገብታችሁ ጉድ እንዳት...
06/21/2025

🛑 ለጥንቃቄ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በአንዱ ካፌ አንድ ዝንጅብል ሻይ 629 ብር ይሸጣል ቢባል አትከራከሩ ።
ካፌው አማረ ብላችሁ ሻይ ቡና ልበል ብላችሁ ገብታችሁ ጉድ እንዳትሆኑ።

ሰናይ ቅዳሜ ሰንበት

ከነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓም

መልካም የአባቶች ቀን ❤️
06/15/2025

መልካም የአባቶች ቀን ❤️

የቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወላይታ ግዙፍ ሎጅ ሊገነቡ ነውየቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወላይታ ዞን፣ በበሌ አዋሳ ከተማ ግዙፍ የቱሪስት ሎጅ ለመገንባት በይ...
06/10/2025

የቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወላይታ ግዙፍ ሎጅ ሊገነቡ ነው

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወላይታ ዞን፣ በበሌ አዋሳ ከተማ ግዙፍ የቱሪስት ሎጅ ለመገንባት በይፋ ማስጀመራቸው ተዘግቧል። ይህ ፕሮጀክት በ"ኃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን" አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን፣ ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ደረጃ ግዙፍ ከሚባሉት የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዱ እንደሚሆን ተገልጿል።

አቶ ኃይለማርያም በቦታው የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት፣ ሎጁ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን አስታውቀዋል። ይህ ሎጅ በቴክኖሎጂ እገዛ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ሲሆን፣ ሲጠናቀቅም ለአካባቢው ወጣቶች በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ታውቋል።

ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉበምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ እና በባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ በርካታ የኮ...
05/29/2025

ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ እና በባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ በርካታ የኮንትሮባንድ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ከተያዙት ዕቃዎች መካከል የቦንዳ አልባሳት እና የተሽከርካሪ ጎማዎች ይገኙበታል።

በምስራቅ ሀረርጌ የተያዙ ኮንትሮባንዶች

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ፣ በተለይም በዋራና መልከ ራፉ ቀበሌዎች በተደረገ ፍተሻ፣ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ቁሳቁሶች ተይዘዋል። የዞኑ ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ እንዳስታወቁት፣ በራፉ ቀበሌ ብቻ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ዕቃዎች ተይዘዋል። ከእነዚህም መካከል ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም የተያዘው ኮድ 3 81635 ኦሮ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ከጃርሶ ወረዳ ሲጋራዎችን እና የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ይጠቀሳል።

በተጨማሪም በኮምቦልቻ ወረዳ ዋሬ ቀበሌ ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ውሏል። እነዚህ የተያዙ ቁሳቁሶች ለሀረር ጉምሩክ ጽሕፈት ቤት ገቢ የተደረጉ ሲሆን፣ ተጠርጣሪ ግለሰቦችም ምርመራቸው ተጠናቆ ለሚመለከተው አካል እንደሚላኩ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ ገልፀዋል።

በባሌ ዞን የተያዙ የቦንዳ አልባሳት

በሌላ በኩል፣ በባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ፣ መነሻውን ከበርበሬ ወረዳ ያደረገ ካሶኒ የጭነት ተሽከርካሪ ተይዟል። ተሽከርካሪው የዋጋ ግምቱ 16 ሚሊዮን 126 ሺህ 600 ብር የሚያወጡ 188 የተለያዩ የቦንዳ አልባሳት ይዞ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ከሀረር ጉምሩክ ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በመባ ወርቅነህ

05/26/2025

ይህ ወጣት ዲያቆን ለሃይማኖቱ እያደረገ ያለው ነገር ሊበረታታና ትልቅ ድጋፍ ሊሰጠው የሚገባ ነው።

ዲያቆን ፈለገ አትናቴዎስ ብዙ ከመስመር የሳቱ ወጣቶችን በትህትና እና በመልካም አስተምህሮ ወደ ቀልባቸው እንዲመለሱ እያደረገ ያለ ታታሪ አገልጋይ ነው።

በርታ ዲያቆን! እረጅም እድሜ ከጤና ጋር እንመኝልሃለን።

Via: ጉርሻ

በአዲስ አበባ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ባለቤት ለማድረግ ስምምነት ተፈረመበአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈረመ። ስም...
05/24/2025

በአዲስ አበባ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ባለቤት ለማድረግ ስምምነት ተፈረመ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱን የፈረሙት የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ናቸው።

ይህ ስምምነት መምህራንን ጨምሮ በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል። ስምምነቱ በአነስተኛ የወለድ መጠን በ25/75 የብድር መርሃ ግብር የሚከናወን ይሆናል።

ቀደም ሲል ተደራጅተው በመጠባበቅ ላይ ለነበሩ ቤት ፈላጊ መምህራን በዚህ መርሃ ግብር ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ተብራርቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ቤት ፈላጊ ሠራተኞች በዝቅተኛ የወለድ መጠንና በ20 ዓመት የሚከፈል ብድር ማመቻቸቱን አስታውቋል።

በከተማዋ የሚገኙ ከ40 ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ፋና ዘግቧል።

በትግራይ ክልል የተጋነነ የነዳጅ እጥረት በመኖሩ ተዘዋውሮ ለመስራት መቸገሩን የእምባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅጫፍ ፅህፈት ቤት ተናገረ፡፡ከተቋሙ እንደሰማነው በጥቁር ገበያ ነዳጅ ከመደበኛ ዋጋው...
04/28/2025

በትግራይ ክልል የተጋነነ የነዳጅ እጥረት በመኖሩ ተዘዋውሮ ለመስራት መቸገሩን የእምባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅጫፍ ፅህፈት ቤት ተናገረ፡፡

ከተቋሙ እንደሰማነው በጥቁር ገበያ ነዳጅ ከመደበኛ ዋጋው እስከ ሁለት እጥፍ ይሸጣል፤ሌሎች ተቋማት እንዲሁም ነዋሪው ለመንቀሳቀስ ተቸግሯል ተብሏል፡፡

በትግራይ ክልል ያለው እየተባባሰ መምጣቱን የሚናገረው ፅህፈት ቤቱ ይህ ችግር በክልሉ ተዘዋውሮ ለመስራት እንቅፋት ሆኖብኛል ብሎናል፡፡

ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ ባሉ ማደያዎች ነዳድ ማግኘት ብር እሆነ ነው፤ነዳጅ ሰወር ብሎ በጥቁር ገበያ ከመደበኛ ዋጋው እስከ ሁለት እጥፍ እየተሸጠ ነው፤የትራንስፖርት ዋጋውም በዚያው የሚጠየቀው ከነበረው በ1እና2 እጥፍ ሆኗል፤ እኛ የፌድራል ተቋም እንደመሆናችን ሂሳብ የምናወራርደው በመደበኛ ዋጋው ነው፤የግድ ስራውን መስራት ስላለብን ለትራንስፖርት የምናወታው በእጥፍ ነው ያሉን የቅርጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፀሃዬ እምባዬ ናቸው፡፡

አርቲስት ሳምሶን ታደሰ፡ የትዳር ታማኝነቴሳምሶን ታደሰ ለሚስቱና ለልጆቹ ታማኝ መሆኑን አጥብቆ ተናግሯል። በሶሻል ሚዲያ የሚናፈሰው - ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት አለው ወይም ሌላ ሴት አግብቷል...
04/27/2025

አርቲስት ሳምሶን ታደሰ፡ የትዳር ታማኝነቴ

ሳምሶን ታደሰ ለሚስቱና ለልጆቹ ታማኝ መሆኑን አጥብቆ ተናግሯል። በሶሻል ሚዲያ የሚናፈሰው - ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት አለው ወይም ሌላ ሴት አግብቷል የሚለው - ሙሉ በሙሉ ውሸት መሆኑን አረጋግጧል። አሜሪካ የሄደው ለእረፍት እንጂ ለሌላ ምክንያት አለመሆኑን ገልጿል። በቤት ውስጥ ሁሌም የሚረዳ፣ ልጆቹን የሚንከባከብና ጥሩ ባል እንደነበር አስምሮበታል። ለልጆቹም አሁንም የሚያስፈልጋቸውን እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

ደብረፂዮን "በትግራይ ጦርነት ወቅት ለተፈፀመው ወንጀልለ ፍትህ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ይሁንና በአገር ውስጥ ይህንን ፍትህ ማግኘት አይቻልም፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ዓለም አቀፋዊ እንደመሆኑ አጥ...
04/27/2025

ደብረፂዮን

"በትግራይ ጦርነት ወቅት ለተፈፀመው ወንጀልለ ፍትህ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ይሁንና በአገር ውስጥ ይህንን ፍትህ ማግኘት አይቻልም፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ዓለም አቀፋዊ እንደመሆኑ አጥፊዎች እንዲቀጡና ተጎጂዎች ፍትህ እንዲያገኙ ጉዳዩ በዓለም አቀፍ ደረጃ መዳኘት አለበት። ይህ ካልሆነ ዘላቂ ሰላም ይመጣል የሚል እምነት የለኝም።"

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለዲደብሊው ከሰጡት ቃለምልልስ የተወሰደ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለሩሲያው መሪ ፑቲን አስተያየት አሰጡበሮም የተካሄደው የሊቀ ጳጳሱ ቀብር ስነ-ስርዓት ዶናልድ ትራምፕና ዩክሬኑ መሪ ዜሌንስኪ አብረው የመገናኘት እድል ፈጥሮላቸ...
04/27/2025

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለሩሲያው መሪ ፑቲን አስተያየት አሰጡ

በሮም የተካሄደው የሊቀ ጳጳሱ ቀብር ስነ-ስርዓት ዶናልድ ትራምፕና ዩክሬኑ መሪ ዜሌንስኪ አብረው የመገናኘት እድል ፈጥሮላቸዋል። በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስትያን ውስጥ መጠነኛ ጊዜ አብረው በማሳለፍ ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸው ታይቷል።

ከሮም ከተለዩ በኋላ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው በፑቲን ላይ ጠንካራ አስተያየት ሰጥተዋል። በሰላማዊ ዜጎች ላይ ሚሳኤል መተኮስ ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው "እያታለለኝ ሳይሆን አይቀርም" የሚል አስተያየት አቅርበዋል።

ዋይት ሀውስ የሁለቱን መሪዎች የ15 ደቂቃ ውይይት "በጣም ውጤታማ" ሲል ገልጾታል። በዚህ ረገድ ዜሌንስኪም ውይይታቸውን "ታሪካዊ" ሲሉ አወድሰውታል።

በትሩዝ መድረክ ላይ ትራምፕ ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች ላይ የፈጸመችውን ጥቃት አይተው፣ ፑቲን ጦርነቱን ማቆም አለመፈለጉን የሚጠረጥሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ምናልባትም በባንክ ወይም በሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ መስተናገድ እንዳለበት ጠቁመዋል።

ይህ የሁለቱ መሪዎች ሁለተኛ ግንኙነት ነው። ከዚህ ቀደም በዋይት ሀውስ የነበራቸው ውይይት በተለያዩ አቋሞች ምክንያት ውጤታማ አልነበረም። አሁን በሮም ሊያገኙት የበቁት እድል ግን ከዚህ ከሁለት ሳምንት በፊት ዊትኮፍ ከሩሲያ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ተመስርቶ የቀጠለ ነው።

Address

Dallas, TX

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fetan Zena - ፈጣን ዜና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share