Ethio Media Network

Ethio Media Network Ethio Media Network(EMN) is an Ethiopian media and entertainment media outlet serving the Ethiopian c

07/12/2025

እነሱ ባይኖሩ ኖሮ ክረምቱም አይገፋም ነበር 😆

🩸 የአዲስ አበባው ታላቅ 'የማፊያ ስራ'!*****************************************************አራት ኪሎ የሚገኘው 'አምባሳደር ህንፃ ላይ ይገኝ የነበረው የድር...
06/02/2025

🩸 የአዲስ አበባው ታላቅ 'የማፊያ ስራ'!
*****************************************************
አራት ኪሎ የሚገኘው 'አምባሳደር ህንፃ ላይ ይገኝ የነበረው የድርጅቱ ቢሮ ውስጥ ሲገባ በመጀመርያ ቀልብን የሚስበው በብዙ የመንግስት ቢሮዎች ውስጥ እንደሚደረገው በትልቁ ታትሞ እና በፍሬም ተዘጋጅቶ የተሰቀለው የጠ/ሚር አብይ አህመድ እና የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ፎቶ ነው።

ድርጅቱ ቢሮው ብቻ ሳይሆን ማስታወቂያውም ቀልቢ ሳቢ ነበር።
"ልጄ ውጭ ሀገር ሄዳ ነው ትምህርቷን መከታተል የምትፈልገው፣ አገሯን የምታስጠራ ምሁር እንድትሆንልኝ እፈልጋለሁ" ትላለች ዝነኛዋ የማስታወቂያ ባለሙያ ሙሉአለም ታደሰ ከሌላኛዋ ታዋቂ የሚድያ ሰው ዳናይት መክብብ ጋር በመሆን በጋራ የሰሩት የዚህ ድርጅት ማስታወቂያ።

ይህ ዛሬ የምናቀርብላችሁ የከባድ ማጭበርበር ድርጊት ዋና ተዋናይ ቀላል ሰውም አይደለችም። ከጥቂት አመታት በፊት በአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ላይ ከ 'ተስፋ ሰጪ' 'እና 'ስራ ፈጣሪ' አምስት የሀገራችን ግለሰቦች አንዷ ሆና ቀርባለች፣ በተጨማሪም ከሴቶች እና ህፃናት ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጌጎ ተስፋዬ ልዩ ሽልማት ተበርክቶላታል።

ግለሰቧ ቤተልሄም ታደሰ ይማም ትባላለች፣ ታድያ ተሸላሚ ያረጋት ስራዋ ምን ይሆን? ድርጅቷ ከ120 ሚልዮን በላይ ብርስ ከህዝብ እንዴት ማጭበርበር ቻለ?

ከቅርብ ግዜ ወዲህ ለስራ ወይም ለትምህርት ወደ ውጪ ሀገር ሰው እንልካለን በማለት ገንዘብ የሚሰበስቡ ድርጅቶች መብዛታቸውን ብዙ ሰው ታዝቧል፣ ከነዚህም አንዱ Aim Ultra Consultancy የተባለው ድርጅት ነው።

"እኔ Aim Ultra ን ለደቂቃ እንኳን አልተጠራጠርኩም። ማስታወቂያውን ታዋቂ ሰዎች በቲቪ እና በሶሻል ሚድያ ሲሰሩ ስላየሁ እውነት ይሆናል ብዬ ከቤተሰብ ያገኘሁት ገንዘብ ላይ ከብድር እና ቁጠባ ተጨማሪ በመበደር 520,000 ብር ከፈልኩ" ብሎ ለሚድያችን የተናገረው የማጭበርበር ድርጊቱ ሰለባ የሆነ ወጣት ነው።

መሠረት ሚድያ ለምርመራ ዘገባው ለበርካታ ቀናት ሲያሰባስብ የነበረው መረጃ እንደሚጠቁመው ይህ ድርጅት ከ600 በላይ ከሆኑ ሰዎች ከትንሹ 40 ሺህ ብር እስከ ከፍተኛው 680,000 ብር ተቀብሎ አሁን ቢሮውን ዘግቶ ጠፍቷል። እነዚህ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ድርጅቱ በትንሹ 120 ሚልዮን ብር ገደማ ከህዝብ ሰብስቦ ተሰውሯል።

ይህ Aim Ultra የተባለ ድርጅት 'ካባ ሆልዲንግ' በሚል ስም በህጋዊ መንገድ ከተቋቋመ እና በስሩ ቢያንስ አስራ ሁለት ከሚሆኑ ሌሎች ድርጅቶች አንዱ ነው።

ባለፉት ሁለት አመታት እንደ አርቲስቶች ሙሉአለም ታደሰ፣ ዳናዊት መክብብ፣ ሩታ መንግስተአብ፣ ቲክቶከሮች ዩቲ ናስ፣ ፊዮና ወዘተ ያሉትን በህዝብ ዘንድ የሚታወቁ ግለሰቦችን በመጠቀም ባሰራጨው ማስታወቂያ የተታለሉ ብዙዎች ህይወታቸው ተመሰቃቅሏል።

ሚድያችን የደረሰው የተረጋገጠ መረጃ እንደሚጠቁመው ስማቸው አይጠቀስ የተባሉ ህይወታቸውን ያጠፉ ወጣቶች አሉ፣ ከክፍለ ሀገር በራሳቸው እና በቤተሰባቸው በኩል ተበድረው አዲስ አበባ መጥተው ከተጭበረበሩ በኋላ ወደመጡበት መመለስ ፈርተው እና አፍረው በመዲናዋ በሴት አዳሪነት የተሰማሩ ሴቶች ይገኛሉ፣ 'ምን ብዬ ወላጆቼ ጋር ልመለስ?' ብለው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚያድሩ እንዳሉም ደርሰንበታል።

Aim Untra ምን ቃል ገባ፣ የቱንስ ቃል አጠፈ?
ድርጅቱ የዱቤ እና የሙሉ ክፍያ አሰራርን በመተግበር ሰዎችን ለትምህርት እንደ ሩማንያ፣ ፖላንድ እና ሀንጋሪ ያሉ ሀገራት እንደሚልክ በስፋት ማስታወቂያ ሲያስነግር ቆይቷል።

እስከ 680,000 ብር ከፍለው የሚመዘገቡ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው እና ኬዛቸው አልቆ ትኬት በአራት ወር ግዜ ውስጥ እንደሚረከቡ እና እንደሚጓዙ ይነገራቸዋል። ሙሉ መክፈል ያልቻሉ ደግሞ ከ10 ፐርሰንት ጀምሮ እየከፈሉ በሂደት የሚቀርባቸውን ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ስራ ከጀመሩ በኋላ እንደሚከፍሉ ውል ይፈርማሉ።

"የግፋቸው ብዛት አንዳንዶቻችንን ይባስ ቪዛው መጥቷል፣ የትኬት ክፈሉ ብለው የሙሉ የአውሮፕላን ትኬት ጭምር አስከፍለውናል" የሚለው አንድ የድርጊቱ ሰለባ ወጣት ነው።
ከዛሬ አራት ወር ወዲህ ግን ድርጅቱ ቢሮውን መዝጋቱን፣ የድርጅቱ ሀላፊ ቤተልሄም ታደሰ እና ገሊላ በለጠ የተባለች የቢሮው ሀላፊ ስልክ ማንሳት እንዳቆሙ ተበዳዮች ይናገራሉ።

"እስካሁን አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ፌደራል ፖሊስ እና በፍትህ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት እና አቃቤ ህግ ቢሮ ሄደን አቤት ብለናል" ብለው ለመሠረት ሚድያ ቃላቸውን የሰጡ ተበዳዮች ተጠርጣሪዋ በወቅቱ እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ እያለች ለምን እንዳልተያዘች ስንጠይቅ የሚሰጡን መልስ አስገራሚ ነበር ይላሉ።

"አንዴ ወንጀሉ ውስብስብ ነው ይሉናል፣ ሌላ ግዜ ሀገር ውስጥ የለችም ይላሉ። በጣም ያስገረመን አንዴ ደግሞ 'በቦዲጋርድ' ታጅባ ስለምትሄድ ነው አሉን። በቦዲጋር ታጅቦ የሚሄድ ወንጀለኛ አይያዝም ማለት ነው?" ብለው የሚጠይቁት እነዚህ ወጣቶች 'ምርጥ ስራ ፈጣሪ' ተብላ የተሸለመች እና በህጋዊ መንገድ ፈቃድ አውጥታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጭበረበረች ግለሰብ የፀጥታ አካላት እንዴት ማግኘት እንዳልቻሉ ይጠይቃሉ።

ከአራት ቀናት በፊት ግን ይህ ለምን እንደሆነ መሠረት ሚድያ መረጃ ከፖሊስ አካላት ፍንጭ ደርሶታል፣ ይህም ጉዳዩ ላይ ክትትል የሚያደርጉ ፖሊሶች ስራቸው እንዳይሰሩ እና ግለሰቧን እንዳይዙ "ጫና አለ" ብለው ነግረውናል፣ ነገር ግን ጫናው ከየት እንደሆነ ከመናገር ተቆጥበዋል።

ተጠርጣሪዋ ቤተልሄም 'Ethio Airs' የተባለ እና የአዲስ አበባ መስተዳድር የከንቲባ ቢሮን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ቢሮዎችን በማፅዳት እና የተባይ ቁጥጥር በማድረግ የሚታወቅ ድርጅት ባለቤት ናት። ግለሰቧ በዚህ እና በሌሎች ድርጅቶቿ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር ትስስር እንዳላት የቀድሞው የድርጅቱ ሰራተኞች ይናገራሉ።

"አሁን አድራሻዋ ከመጥፋቱ በፊት ወደ ክስ እንሄዳለን ስንላት መልሷ 'የትም ብትሄዱ አያዋጣችሁም፣ ራሳችሁ ትጎዳላችሁ' ብላ ማስፈራርያ ትሰጠን ነበር" የሚሉት ከሳሾች በመጨረሻ የሄዱት ወደ ፍትህ ሚኒስቴር እንደነበር ያስረዳሉ።

እዛ ያገኟቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዴኤታ ፀሀፊ ጉዳዩን ለዴኤታው ካስተላለፉ በምላሹ "ጉዳዩን ወደ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ዳይሬክቶሬት ውሰዱ" እንዳሏቸው እና ወደ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ሀላፊ ሲሄዱ ደግሞ "ወንጀሉ ውስብስብ ነው" ብለው እንደመለሷቸው በተስፋ መቁረጥ ይናገራሉ።

በ Aim Ultra ለተጭበረበረው እና ስሜ አይጠቀስ ላለው ወጣት የደረሰው የአበዳሪው የአዋጭ የገንዘብ ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ማስጠንቀቂያ እንዲህ ይላል: "ውዝፍ እዳዎትን የማያስተካክሉ ከሆነ እርሶንም ዋሶትንም በገቡት ውል መሰረት ውዝፍ ዕዳውን በህግ አግባብ ለማስመለስ እየተዘጋጀን መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።"
ወጣቱ ገንዘቡን እንዴት እንደሚመልሰው አያውቅም፣ የ Aim Ultra ቢሮም ተዘግቷል፣ ስልክ እንኳን የሚመልስ የለም።

"በብድርም ሆነ ንብረት ሽጠን መክፈል የቻልን የጠየቀችንን ገንዘብ በሙሉ ብንከፍልም መጨረሻ ላይ 'አልተሳካም' አለችን። እኔ በግሌ በ Aim Ultra 586,000 ብር ከፍያለሁ። ምንም ቪዛ ባልተመታበት ሁኔታ የአየር ቲኬት፣ የኮቴ እናም የትራቭል ኢንሹራንስ በሙሉ አስከፍላናለች። ለአንድ ዓመት ያክል ፕሮሰሱን ስከታተል የነበረው ደግሞ ከክፍለ ሀገር በአውሮፕላን (በጦርነት ምክንያት የየብስ ትራንስፖርት ዝግ ስለነበር) እየተመላለስኩ ነበር። በዚህም ለፕሌን እናም ለአልጋ ከ120,000 ብር በላይ አውጥቻለሁ" የሚለው ሌላኛው የማጭበርበር ድርጊቱ ሰለባ ነው።

በዚህ የማጭበርበር ተግባር ምክንያት የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ ትዳር ፈርሷል፣ ቤተሰብ ተበትኗል የብዙ ወጣቶች ህይወት ሲኦል ሁኗል የሚለው ይህ ወጣት እሱ ፕሮሰሱን ሲጀምር ቢያንስ 200,000 ብሩ የራሱ ገንዘብ እንደነበር ያስረዳል።

"ሌላው በተለያየ መንገድ የተቀበልኩት የቤተሰብ፣ የጓደኛ፣ ብሎም የእቁብ ብር ስለነበር ይሄንን መመለስ ባለመቻሌም ከቤት የመውጣት ሞራል አጣሁ። ስለእውነት አሁን ላይ ሙሉ ገንዘቤን ብትመልስልኝ እንኳን የማልሸፍነው እዳ ውስጥ ገብቻለሁ። ብዙ ነገር አጥቻለሁ። ከቤተሰብ ጋር ተቆራርጫለሁ። ገንዘብ በሰጡኝ ሰዎች ፊት አንገቴን ለመድፋት ተገድጃለሁ! ከአልጋ ላይ የምነሳበት ሞራል እያጣሁ ብዙ ቀኖችን አልጋዬ ላይ እያሳለፍኩ አለሁ! ጉዳዩ ከተበላሸ ጀምሮ ንጋትን እየፈራሁ አለሁ! ሁሉም ነገር ያደክማል! ከማስታወሻዬ ውጭ ለቅርብ ቤተሰቤ እንኳን አውርቼው የማላውቀውን ችግሬን እና መከፋቴን ሁሉ [ለቤተልሄም ታደሰ] በዝርዝር ነግሬያት ነበር እንኳንስ አዝና ገንዘቤን ልትመልስልኝ ለመልዕክቴ እንኳን መልስ አልሰጠችኝም" በማለት የደረሰበትን ፅፏል።

አክሎም "ሴትዮዋን ተከታትሎ ለመያዝም ሆነ ለማስያዝ ከባድ ያደረገው ሌላው ጉዳይ በተለያዩ የቤተሰብ አባል ፍቃድ ማውጣቷ ነው። መኖሪያ አድራሻም ስለምትቀያይር ማግኘት አልቻልንም። አንድ ድርጅት ትከፍት እና እሱን ትዘጋ እና በሌላ ሰው ስም በአዲስ ፈቃድ በአዲስ ስም ትመለሳለች እንዲህ እያለች ትቀጥላለች። በእርግጠኝነት ይቺ ሴትዮ በጊዜ በህግ ቁጥጥር ውስጥ ካልዋለች ገና ብዙ ግፍ እናም ማጭበርበሮች እንሰማለን" ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) እና ፋና ሬድዮ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የድርጅቱን ስም ብቻ በመጥቀስ የተበዳዮችን መረጃዎች እንዳጋሩ የተመለከትን ሲሆን ከዛ ወዲህ ምንም ለውጥ እንደሌለ እና ተጠርጣሪዋ አሁን ውጭ ሀገር (ምናልባትም ዱባይ) እንደምትገኝ ግምቶች ተሰጥተዋል።

ቤተልሄም በምትዘውራቸው ተቋማት ውስጥ ቁልፍ ሰዎች እንደሆኑ የተጠቆሙት በአብዛኛው የቤተብ አባል እና ጓደኛ የሆኑት ገሊላ በለጠ፣ በለጠ ሳህሉ፣ አቤል ተስፋዬ፣ ሩት መኮንን፣ ዳዊት በለጠ እና እዮሲያስ ታደሰ የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸው ታውቋል።
መሠረት ሚድያ ቤተልሄም ታደሰ ይማምን በተለያዩ መንገዶች ለማነጋገር እና ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ምላሽ ባለመስጠቷ አልተሳካም

መሀል አዲስ አበባ ላይ ፈቃድ አውጥተው ወጣቶችን ወደ አውሮፓ እንልካለን ብለው ገንዘብ ከተቀበሉ በኋላ ቢሯቸውን ዘግተው ከሚጠፉት ድርጅቶች በአንዱ ላይ ያሰናዳናው ዘገባ በዚህ ይጠናቀቃል።
ምንጭ: መሰረት ሚድያ

05/24/2025

በስምምነት ለምን የ 'ፓስተር' ዮናታን አክሊሉን ስም #ጥቁር ጉንዳን አንለውም :)

🔴 የጤና ባለሙያዎች የዳቦ ጥያቄ እና ከመከላከያ ሚንስትር ያፈተለከ የሚመስለው መግለጫ...........⤵️*****************************************  በዶ/ር መቅደስ ...
05/15/2025

🔴 የጤና ባለሙያዎች የዳቦ ጥያቄ እና ከመከላከያ ሚንስትር ያፈተለከ የሚመስለው መግለጫ...........⤵️
*****************************************
በዶ/ር መቅደስ ዳባ የሚመራው ጤና ሚኒስትር ዛሬ በህክምና ባለሙያዎች ጥያቄ ዙሪያ መግለጫ ሰጠ። መግለጫው እንደወረደ ይኸው፦

"መቼምና በምንም ሁኔታ መቋረጥ ከሌለባቸው ማኅበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የጤና አገልግሎት መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ በጥቂት የማስተማሪያ የጤና ኮሌጆች/ተቋማት በመደበኛ የሥራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የተወሰኑ ባለሞያዎች እንዳሉ መረጃዎች ደርሰውናል። ከእነዚህ የጤና ባለሞያዎች መካከል ብዙዎቹ በሐሰተኛ መረጃ የተወናበዱ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ ጥፋትን ዓላማቸው ያደረጉ ናቸው።

"ከሕግ አኳያም የጤና ሞያ የሥራ ማቆም አድማ ከማይደረጉባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑ በግልጽ ተደንግጓል። የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ እንኳን ቢኖራቸው በሥራ ገበታቸው ተገኝተው መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ ጉዳያቸውን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

በመሆኑም እነዚህ የጤና ባለሞያዎች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው ማኅበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ያቀርባል።

"መንግሥት በሆደ ሰፊነት ችግሩን ለመፍታት ያሳየውን ትዕግሥት ወደጎን በመተው በሥራ ገበታቸው ላይ ባልተገኙ እንዲሁም በጤና ተቋሙም ሆነ ከጤና ተቋሙ ውጭ ሆነው ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩት ላይ አስፈላጊ የሆነ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ቀድመን እናሳውቃለን።"

በመግለጫው ላይ ያላችሁ አስተያየት ምንድን ነው?

የጤና ባለሙያዎች የሰራ ማቋም አድሚያ እያደረጉ ነው::ለወራት በጭዋ እና በተማረ ደንብ ድምፃቸውን ለሚመለከተው አካል ሲያስሙ የነበሩት የጤና ባለሙያዎች የሚመለከተው አካልም ለጥያቄዎቻቸው ምን...
05/13/2025

የጤና ባለሙያዎች የሰራ ማቋም አድሚያ እያደረጉ ነው::

ለወራት በጭዋ እና በተማረ ደንብ ድምፃቸውን ለሚመለከተው አካል ሲያስሙ የነበሩት የጤና ባለሙያዎች

የሚመለከተው አካልም ለጥያቄዎቻቸው ምንም አይነት አጥጋቢ የሆነ መልስ ባለመሰጠቱ በከፊል የሰራ ማቆም አድሚያ አያደረጉ ሲሆን ብዙዎችም ዛሬ ስራ ገበታ ላይ እንዳልተገኙ ታውቋል::

በዚህም ሆስፒታሎች እና የጤና ተቋም መግለጫ እያወጡ ሲሆን

የጤና ባለሙያዎች ጥያቄዎቻቸው ካልተመለሱ ብዙ የህብረተሠብ ክፍል ይጎዳል

የሚመለከተው አካል አሁንም አረፈደም እና ብዙ ጉዳት ሳይደርስ ጥያቄዎቻቸውን ቢመልስ ይሻላል::

Ethiopian Healthcare Professionals Go On Strike

A strike is currently underway.

For months, healthcare professionals have been presenting their concerns to the responsible authorities in a peaceful and organized manner.

However, these authorities have failed to provide any meaningful or appropriate response to their demands, leading many to participate in a partial or full work stoppage today.

Hospitals and health institutions have begun issuing public notices regarding the situation.

If the concerns of healthcare professionals are not addressed, large segments of the population could be negatively affected.

It is still not too late for the authorities to act — responding to the demands now would help prevent further harm.



🙏🙏🙏

‹‹አገሪቱ መክፈል አትችልም ከማለት ይልቅ በጋራ መፍትሄው ላይ ማተኮሩ የተሻለ ነው›› ሲሉ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ ባለሙያዎቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ግንቦት 3 ቀን 2017 በ...
05/12/2025

‹‹አገሪቱ መክፈል አትችልም ከማለት ይልቅ በጋራ መፍትሄው ላይ ማተኮሩ የተሻለ ነው›› ሲሉ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ ባለሙያዎቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ግንቦት 3 ቀን 2017 በጽሑፍ ባሰራጩት መግለጫ ‹‹የኢትጵያ ጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ከማንኛውም የፖለቲካ ሀይል ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ወይንም እገዛ የሌለው መሆኑን ስለማሳወቅ›› በሚል ርዕስ ጀምሯል፡፡

ሲቀጥልም ‹‹የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ኑሮ በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ህዝባቸውን በቅንነት ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ አሁንም እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በባለሙያዎች የተነሱት መሰረታዊ ጥያቄዎች በኢትዮጵያ መንግስት መመለስ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ያምናል›› ብሏል፡፡

እንደገለፀውም ጥያቄዎቹ፡
🔴 ቤት ለተቸገሩ ባለሙያዎች ቤት ሊሰሩበት የሚችል መሬት መስጠት፣
🔴 የትራንስፖርት ክፍያ ለተቸገሩ ባለሙያዎች ነፃ ትራንስፖርት ማመቻቸት፣
🔴ባለሙያው ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ፣
🔴ባለሙያዎች ለስራቸው የሚመጥን ክፍያ መክፈልና
🔴 የተጋላጭነት ክፍያን ማስተካከልና የባለሙያውን ደህንነት ማረጋገጥ መሆናቸውን ገልፆ፡ መፍትሄውም የጤና ሚኒስትርን ከሲቪል ሰርቪስ በማውጣት በቦርድ እንዲተዳደር ማድረግና ባለሙያው የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች ቀነ ገደብ በማስቀመጥ መመለስ እንዲቻል ማድረግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የጽሁፍ ማብራሪያው ሲቀጥልም ‹‹እነዚህ ጥያቄዎች በኢትዮጵያ መንግስት መመለስ የሚችሉና የቅንጦት ያልሆኑ ናቸው›› ካለ በኋላ አገሪቱ መክፈል አትችልም ከማለት ይልቅ መፍትሄው ላይ ማተኮሩ የተሻለና ጥሩ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል አስረድቷል፡፡
የጤና ባለሙያዎችን ከማሰር፣ ከማሳደድና ከማስፈራራት ይልቅ ቀረብ ብሎ በባለሙያው የተነሱትን ጥያቄዎች መመለስና ባለሙያውን ማናገር የላቀ ጠቀሜታ እንዳለውም አሳስቧል፡፡

🔴 በጥያቄዎቹ ዙሪያ አስተያየታችሁን ስጡበት። ተወያዩበት።

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ዛሬ በጻፉት "ማስታወሻ" እንዲህ ብለዋል።******************************************************"ፀረ-ዕዉቀት...
05/09/2025

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ዛሬ በጻፉት "ማስታወሻ" እንዲህ ብለዋል።
******************************************************
"ፀረ-ዕዉቀት ቁማርተኞች ዛሬም እዉነቱን አልተረዱም። ስለኮሪደር፣ ስለሪዞርትና ስለፓርክ እያወሩ ለመኖር የተቸገረዉን ለማታለል ሲሞክሩ አያፍሩም። ኢትዮጵያ እኮ የቄስ ሞገሴና የመሬት ደላላ ብቻ አይደለችም። እኛ በልቶ ማደር፣ የኤሌክትሪክ ታሪፍ መክፈል፣ ልብስ መቀየርና ልሎች የህይወት ጉዳዮች የቸገረን የኢትዮጵያ ሀኪሞች፣ መምህራን፣ ወታደሮች፣ ሠራተኞችና የከተማ/ገጠር ነዋሪዎች የደቦ እንጂ የመዝናኛ ጥያቄ የለንም ። ስለዚህም የፓርክና የኮሪደር ቁንጅና አያምረንም።

ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይና አመራሮች በተለይ ከሀኪሞቻችን እንማር። ከብሔር፣ ከሀይማኖትና ከአከባቢ አጥር ወጥተን በነፃነት፣ በፍትህ፣ በሠላምና በወንድማማችነት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለጋራ እናተኩር። ችግሩ ለሁላችንም የህልውና አደጋ ነዉና በመርህ እንተባበር!"
በታዬ ጽሑፍ ላይ ያላችሁ አስተያየት ምንድን ነው?








04/26/2025

ጀግንነት በደማችን ነው!

ደጃዝማች አያሌው ብሩ ከጦር ሰራዊቶቻቸው ጋር በዳባት አረደጃን ቤተመንግሥታቸው ውስጥ ሆነው የተቀረጹት ቪዲዮ፤ (በ 1916 ዓ.ም)

ወታደራዊ አዛዡ ተማርኳል።መረጃ ሸዋየአብይ አህመድ መከላከያ ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ጫኔ ለገሰ አሊ በቁጥጥር ስር ውሏል።
04/21/2025

ወታደራዊ አዛዡ ተማርኳል።

መረጃ ሸዋ
የአብይ አህመድ መከላከያ ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ጫኔ ለገሰ አሊ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በዘመቻ አንድነት ሕይወቱን ያጣው የብ/ጄኔራል ሰይፈ ኢንጊ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል። ፋኖ ይችላል!
04/06/2025

በዘመቻ አንድነት ሕይወቱን ያጣው የብ/ጄኔራል ሰይፈ ኢንጊ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል። ፋኖ ይችላል!

04/05/2025

በጣም በቅርብ ግዜ ነፍሰ ገዳዩ የብልፅግና ስርአት ተዋርዶ እና ተቀጥቅጦ ከአራት ኪሎ ተጠራርጎ ይወጣል። Mark my Words!

04/02/2025

ሸዋ #ፋኖ

Address

Denver, CO

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Media Network:

Share