D.Mekuria Gugsa

D.Mekuria Gugsa preacher poet & script writer
(1)

12/20/2022
ተጠየቁ ???
12/02/2021

ተጠየቁ ???

የዝማሬ ድብቅ ጦር  ‼️   ሀገራችን የገጠማት ፈተና በሁሉ ዘርፍ ሰልፍ ያስፈልገዋል እንደ እግዚአብሔር ልጆች ጸሎታችንን ለሰከንድ አናቋርጥም ። እንሆ በሙዚቃው ዓለም አንጋፋ የነበሩት አቦነ...
11/25/2021

የዝማሬ ድብቅ ጦር ‼️

ሀገራችን የገጠማት ፈተና በሁሉ ዘርፍ ሰልፍ ያስፈልገዋል እንደ እግዚአብሔር ልጆች ጸሎታችንን ለሰከንድ አናቋርጥም ። እንሆ በሙዚቃው ዓለም አንጋፋ የነበሩት አቦነሽ አድነውና ማርታ አሻጋሪ ስለሃገራቸው በዝማሬ ጸሎት ማልደዋል !!
ነገ ማታ ይጠብቁን ‼️

“ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡት በአሞንና በሞዓብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ድብቅ ጦርን አመጣባቸው፤ እነርሱም ተመቱ።” 2 ዜና 20፥22

ኢትዮጵያን ቀኝህ ላይ ... ‼️

ጥበብህ የመላት ያንተ ጸጋ ክብር
የብሉይ የኦሪት የአዲስ ኪዳን ምድር
እንኳን ሰው ይቅርና መሬቷ ያመነህ
የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ወዴት ነህ ?
ከደም ላይ ትነሳ ንቀል አጋጎቿን
በእሳት በነበልባል እጠረው ድንበሯን
ሄሎሄ ሄሎሄ ኢብኖዲ ናይናን
....

ባንዳ ገና ይዋረዳል ... ‼️         በእልፍኛችሁ የምትመክሩብንን በአደባባይ                  የሚገልጥልን የታመነ ነው ‼️                         2ኛ ነገ 6...
11/24/2021

ባንዳ ገና ይዋረዳል ... ‼️

በእልፍኛችሁ የምትመክሩብንን በአደባባይ
የሚገልጥልን የታመነ ነው ‼️
2ኛ ነገ 6÷11

የእሥራኤልን ንጉሥ ለመግደል በድብቅ ያሴረው የሶሪያ ንጉሥ በተደጋጋሚ ሊያገኘው አልቻለምና ልቡ ታውኮ
ባሪያዎቹንም ጠርቶ፦ ከእኛ ዘንድ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ አትነግሩኝምን? አላቸው።
ከባሪያዎቹም አንዱ፦ ጌታዬ ሆይ፥ እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል አለው።
ይሄን የነብዩን የኤልሣዕን ብቃት አይቶ ልቡን ያልመለሰው ንጉሥ የመጨረሻው ውርደት ክፍሉን እንብባችሁ ስትጨርሱ ታገኙታላችሁ !!
በኢትዮጵያ ላይ በጓዳቸው ተደብቀው የሚመክሩባትን የአጋንንት ልጆች እግዚአብሔር በአደባባይ አጋልጦ አዋርዷል ።
እንደ ንጹህ ሰው ቤቴ ተፈተሸ ብላ እሪሪሪ ስትል የነበረች ባለጌና ዘረኛዋ እሌኒ ገ/መድህን ፣ የእንጨት ሽበታሙ የሽማግሌ ሌባ ኤፍሬም ይስሐቅ ፣ ከዋናው የጅንታ ክንፍ ብርሃነ እና ከጋላቢዎቻቸው ጋር ቁጭ ብለው የመከሩብንን የምናመልከው አምላክ አሳልፎ ሰጥቶናል !!

የምንዋጋችሁ እየጸለይን እንጂ እያሴርን አይደለም !!

ቤተክርስቲያንን አትችሏትም ‼️        ብትገድሏቸውም አይገርመንም ‼️         እናንት የአጋንንት ልጆች ርጉማን ሆይ የፈለጋችሁትን ነገር ሁሉ ብታደርጉ ቤተክርስቲያንን ፈጽሞ አትችሏት...
11/09/2021

ቤተክርስቲያንን አትችሏትም ‼️

ብትገድሏቸውም አይገርመንም ‼️

እናንት የአጋንንት ልጆች ርጉማን ሆይ የፈለጋችሁትን ነገር ሁሉ ብታደርጉ ቤተክርስቲያንን ፈጽሞ አትችሏትም ‼️ ያለበደሏ ሃገር አቅንታ ታቦት አዝምታ በታገለች፣ ከፋሽሽት ኢጣሊያ ጋር ተፋልማ በአርበኝነት በተዋደቀች፣ ከጫካ ጀምራችሁ አሴራችሁባት ፣ ነከሳችኃት ፣ ወነጀላችኃት ፣ ገዳሞቿን በካድሬ ሞልታችሁ አላገጣችሁባት አልበቃችሁ ብሎ ፓትርያርኳን ከመንበሯ አሳዳችሁ የራሳችሁን ደንበኛ ሾማችሁ ለሁለት ከፍላችኋት ፣ ቀኖናዋን እረገጣችሁባት❗ ቤተክህነቱን መቶ በመቶ ተቆጣጥራችሁ ከቤተክርስቲያኒቱ ሊቀ ጳጳሳት ይልቅ በር ላይ ያቆማችሁት የእናንተን ዘበኛ ባለጊዜ አደረጋችሁባት...‼️ ዘበኛው "ከትግራይ ተወላጆች" ውጪ ያሉትን መነኮሳት አስኬማቸውን ሳይቀር እያስወለቀ እስኪፈትሽ ድረስ አሸማቀቃችኋት ... ‼️ሰደባችዋት ፣ ተፋችሁባት ፣ አዋረዳችኋት ሃብቷን ሙልጭ አድርጋችሁ ከግሽን እስከ አክሱም ፣ ከቁልቢ እስከ አዳዲ ፣ ከቦሌ እስከ ሰላሌ ፣ ከአዲስ አበባ እስከ አላባ ፣ ከወረባቦ እስከ አንቦ ክህነት የሌለውን ሳይቀር እየሾማችሁ በሌብነት የግፍ ግፍ ፈጸማችሁባት ... ‼️
ክርስቶስ ከአይሁድ ተወልዶ አይሁድ እንደሰቀሉት ለክርስትናው ባእድ ባትሆኑም በዘር ፓለቲካችሁ ኦርቶዶክስ ተወህዶን ቀራኒዮ ላይ አወጣችኋት ሃሞትና ከርቤ አጠጣችኋት ... ‼️
አባታችንን እንኳን ማፈናችሁ ይቅርና ብትገድሏቸውም አይገርመንም ‼️ እሳቸው አስቀድመው ለእግዚአብሔር ፍቅር ሞተው በሥጋ የቀረላቸውን እድሜ ለክርስቶስ ሊኖሩት የማሉ ባለ ኪዳን ናቸው ። ‼️
ደማቸውም ሆነ የምትፈጽሙባቸው ግፍ ግን የአቤል ደም መሆኑን ቃዬሎች ሆይ አትርሱ ...
ይጮሃል ... ‼️
እናንተንም በምድር ላይ እንዳቅበዘበዘ ይኖራል ... ‼️

11/05/2021

አንተ ጀግና ህዝብ ነህ ‼️
እንኳንም ካንተ ተፈጠርኩ ‼️

BBC News Amharic
Al Jazeera English
The Economist
Reuters
VOA Amharic
DW News
CNN
እና ሌሎችም ሃያ አራት ሰዓት ስለ ኢትዮጲያ መአት ያወራሉ ፣ ይበጠረቃሉ ፣ ይቦተረፋሉ ፣ ያስፈራራሉ፣ ይዝታሉ ፣ ይተረተራሉ ... ሀበሻ ወይ ፍንክች !! 🤣🤣🤣
ኢንባሲዎች መግለጫ ያወጣሉ፣ ዜጎቻቸውን ያሸሻሉ ያስጠነቅቃሉ ሀበሻ ይሄን ሁሉ መግለጫ:- በልግጫ በርግጫ 😁😁😁
ከሥራው አልቀረ ፣ ክንግዱ እንተነቃነቀ ፣ከቁርጥ ቤትም ከቢራ ቤትም ውልፍች የለም ጮማውን በ CNN እያወራረደ "ባንዳ ና ሞክረኝ "እያለ ይፎክርልሃል !! ዛሬ the Economist ምን ቢያደርግ ጥሩ አይደለም ???
መስሚያችን ጥጥ ነው ስንለው ለፌስ ቡክ የboosting ክፍሎ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ፌስ ቡኩን ሲከፍት እንዲያገኘው እራሱን ስፖንሰር አርጎ አዲስ አበባ ውጥረት ላይ ነች እያለ እሪሪሪሪሪ ይልላችኋል 🤣🤣🤣
አባቴ ሀበሻ ቆቅ ነው አይሸወድልህም ለቂሉ ስታሊንና ዘመዶቹ የዘረፉንን ገንዘብ እየተቀበላችሁ ላሃጫችሁን አዝረክርኩላቸው ።‼️ ይምድሩን ጦርነት በኢትዮጵያውያን ክንድ እንደሚጠናቀቅ ስታውቁት በወሬ ልታተርፉት ?? ከሳምንት በኋላ ታበርዳለህ ወፍ የለም ‼️
እኔን እራሱ ምን ቢሉኝ ጥሩ ነው ባለቤቴና ልጄ ኢትዮጵያ ናቸውና አረ ቶሎ ይምጡ አሜሪካ መግለጫ አውጥታለች ፒሪሪም ፓራራም ሲሉኝ እኔስ ምን ብል ጥሩ ነው " እንኳን ሊመጡ እንደውም ያራዝማሉ " 🤣🤣🤣
ወናፍ አለ መኮንን ላእከ !!!

11/05/2021

እልልልልል እልልልልል ‼️
የኢትዮጵያ ጠላቶች ቋንቋቸው
ድብልቅልቁ ወጥቷል ❤💪💪 ‼️‼️


የሸኔና የሕወሐት ጋብቻ ጫጉላው ሳያልቅ ፈረሰ ‼️
ሕወሐትና ሸኔ በክፉ ባልንጀርነት ገጥመው የጀመሩት የጥፋት ጉዞ ጨፋ ሮቢት ላይ በሕዝብ ተቀጠቀጠ። ንብረታችንን ለሕወሓት አንሰጥም ያለው የከሚሴ ሕዝብ እና ወያኔ አታሎናል ያሉ የሸኔ አባላት ከወያኔ ጋር ከሚሴ ውስጥ ተናንቀዋል‼️
በደዋ ጨፋ የአንጾኪያ ሚሊሻ የኮምቦልቻ ከሚሴን መንገድ ሚላሚሌና ገርቢ ላይ ሙሉ በሙሉ ዘግተውባቸዋል። ወደ ጨፋ ሮቢት ለመሄድ ያቀደው የወያኔና የሸኔ ያልተገባ ጋብቻ ቡድን በጀግናው መከላከያ ኃይል፣ በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ዞን ሚሊሻዎች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ እየተደመሰሰ ነው።
በጨፋ ሮቢት - ጃራ ግራ በኩል የተበተነው ጁንታ በአርጡማ ፉርሲ ሚሊሻ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል‼️
ወደ ማጀቴ የሸሸውና ጋራውን ታክኮ ለመከላከል የሚሞክረው ኃይል ደግሞ በጀግናው መከላከያ እየተደቆሰ ነው። የኦሮሞ ዞንናና የሰሜን ሸዋ ሕዝብ ተባብሮ ጁንታው መፈጠሩን እንዲረግም አድርጎታል‼️

ልጇን መርቁላት                         ( መኩሪያ ጉግሣ)የአፍሪካ ልጆች ኢትዮጵያን ጠይቋት መሪ ዘርቶ ማብቀል ይቻላል ወይ? በሏት አውሮፓ ያልቀባው ያገኛል ወይ ዙፋን ?ያለ አ...
10/04/2021

ልጇን መርቁላት
( መኩሪያ ጉግሣ)

የአፍሪካ ልጆች ኢትዮጵያን ጠይቋት
መሪ ዘርቶ ማብቀል ይቻላል ወይ? በሏት
አውሮፓ ያልቀባው ያገኛል ወይ ዙፋን ?
ያለ አሜሪካ ከየት ይመጣል ስልጣን ?
በሉና ሞግታት
በሻሻው የጣለችው የሰው ፍሬ ቅንጣት
መከራውን አልፎ እንደጎመራላት
ትነግራችኋለች በቅሎ እንዳፈራላት
ይህው ምሥክሯ ልጇን መርቁላት !!

ነገሩ ተገለበጠ                                    መ.አስቴር 4÷9      ገፍተው ገፍተው ከአናት ላይ አወጡኝ እንዳለችው ቂቤ ጨካኞቹ ምስኪኗን በጥፊና በካልቾ ንጠው ን...
10/02/2021

ነገሩ ተገለበጠ
መ.አስቴር 4÷9

ገፍተው ገፍተው ከአናት ላይ አወጡኝ እንዳለችው ቂቤ ጨካኞቹ ምስኪኗን በጥፊና በካልቾ ንጠው ንጠው ወደ ክብሯ አሽቀነጠሯት ። ዛሬ በመላው ዓለም ያለ ወገኗ ሁሉ ሊረዳት፣ ሊያግዛት፣ ሊክሳት ፣ ሊያክማትና እንባዋን ሊያብስላት አድራሻዋን እያሳደደ ይገኛል ። አክቲቪስት የለ ጋዜጠኛ የለ ድብን ብሎ ስለሷ አሯል ። የመንግሥት ሚዲያውን ሳይቀር ተቆጣጥራዋለች ። እስዋ ላይ የተሰራው ግፍ የኢሬቻውን ዳውን ዳውን ሳውንድ ትራክ ሳይቀር ዱቄት አርጎ ዜናው ከአናት ቁጭ ብሏል ። ይብስ ብሎ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን ብትል ጥሩ ነው ??
" ለግለሰቧ መጠለያ እና ህክምና እንድታገኝ የሚመቻች ሲሆን በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ማዕከል ውስጥ ሥራ የምትጀምር ይሆናል።"
ጉድ አትልም ወገን? ደስስ አይልህም? እንባዋ ሲታበስ ?
ወንድሞቹ የተመቀኙት ጉድጓድ ውስጥ ወርውረው የጣሉት ዮሴፍ በግብጽ ምድር በክብር በኃይል በሥልጣን ከፍ ብሎ ጠበቃቸው ። ወንድሞቹን (ጠላቶቹን ) አይቶ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ይለናል ታላቁ መጽሃፍ ። እንባውን ጠራርጎ ተመለሰና እንዲህ አላቸው ...
እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው።” ዘፍ 50÷20
ከድህነቷ እንድታርፍ ፣ ልጆቿ እንዲድኑ እግዚአብሔር የክፉዎችን ሃሳብ ለመልካም ገለበጠው !!

ስልካችሁን ለመብታችሁ ተጠቀሙበት !!           ቪዲዮውን የቀረጸው ምስጋና ይገባዋል !!መንግሥት አረመኔዎቹን ፓሊሶች መያዙን ሰምተናል። የመጨረሻ ፍርዳቸውን ካላሰማን የኢትዮጵያ ነገር ...
10/02/2021

ስልካችሁን ለመብታችሁ ተጠቀሙበት !!

ቪዲዮውን የቀረጸው ምስጋና ይገባዋል !!

መንግሥት አረመኔዎቹን ፓሊሶች መያዙን ሰምተናል። የመጨረሻ ፍርዳቸውን ካላሰማን የኢትዮጵያ ነገር ከወያኔ ወደ ብልጽግና እንዘጭ እንቦጭ እንዳለ እንገነዘባለን ።
ከዛ ውጪ ዜጎች :-
መልበስም መብላትም መጠጣትም በማያኮራበት ደሃና ምስኪን ህዝብ ላይ የስልሳና የሰባ ሺህ ብር ስልክ ይዞ በየኢንስታግራሙ በየቲክታኩ ከመሞላቀቅ እንዲህ ለመብታችሁና ለፍትህ ብትጠቀሙበት ይሻላል ። አሜሪካዊው ጥቁር George Floyd ላይ በነጭ ፖሊስ የተፈጸመበት የዘረኝነት ጭካኔ ግፍ አደባባይ ላይ ወጥቶ ፍትህ ያገኘው ያገባኛል በምትል ዜጋ በተቀረጸ ቪዲዮ ነው ። ይህው ይሄም አረመኔያዊ ድርጊት ከዳር ዳር አንጫጭቶ ቢያንስ መያዛቸውን ያሰማን በመቀረጹ ነው ። ስላልተቀረጸ ነው እንጂ በሺህ የሚቆጠሩ የዚህን እጥፍ የሚበልጡ ግፎች በከተሞች ብቻ በፖሊስ ነን ባይ ዝፍጦች ሲፈጸም ይውላል ። እባካችሁ ካሜራችሁን ተጠቀሙበት ።
ቅረጹ... ቅረጹ... ቅረጹ... !!
በእውነት የነዚህ አረመኔዎች ጭካኔ ፖሊስ ለመሆን መስፈርቱ ደደብነት ነው ወይ? ያስብላል። 😭😭 ለሷ ባያዝኑ እንኳን ለህፃኑ አያዝኑም??? የወለደ ይፍረድ !! እነዚህ ከሰውነት የጎደሉ እርጉሞች ሴቷን እንዲህ የቀጠቀጡ ወንዱንማ አሰቃይተውታል ። የህግ አስከባሪዎች አይደለም ዱላ ቁጣቸው አንጀት ያሳርራል ። ስደት አንሶን እንቅልፍ አጥተን እንደር ???

09/30/2021

ከወያኔ የገላገልከን ጌታ ተመስገንንን !!
መኩሪያ ጉግሣ

* ሀገሬን ከነዚህ ከ*(Tplf) ሰው በላ አረመኔ ጨካኞች እጅ አንዲት ጠጠር ኮሽ ሳትል ከቤተ መንግሥት ማንቁርታቸውን ይዘህ ያስወገክደልኝ የኔ መድኃኒዓለም ምን ከፍዬህ እረካ ይሆን ??
ብቻ ግን ተመስገን... !!!

* ዜግነቴን ነጥቀው ከሰውነት አሳንሰው በዘር ከረጢት ወርውረው ያረከሱኝን አጋንንቶች የተንቤን ጉድጓድ ውስጥ የቀበርክልኝ ጌታ ምን መስዋዕት ባቀርብልህ ደስታዬ ይፈጸም ይሆን ?
ብቻ ግን ተመስገን... !!!
* ቤተ መቅደሴን የካድሬ መፈንጫ ፣ የሜሮኔን ቀንዲል የውስኪ መጠጫ ፣ ታቦቴን ጽላቴን የእግራቸው መረገጫ ያደረጉብኝን ብልጣሶሮች የማኔ ቴቄል ፋሬስ ሰይፍህን መዘህ መንግሥታቸውን ለቆረጥክልኝ እግዚአብሔር ምን ውድ ነገር ባቀርብልህ ፍቅሬን መግለጽ እችል ይሆን ?
ብቻ ግን ተመስገን ... !!!

* ታሪኬን ባህሌን ፣ ቋንቋዬን ሃይማኖቴን፣ ትውፊቴን ዶግማና ቀኖናዬን ቀዳደው የሸኑበትን፣ ሃሞትና ከርቤ ቀላቅለው ያመረሩትን ሉሲፈሮች ብትንትናቸውን ላወጣህልኝ ቅዱስ አማኑኤል ምን ብሰፍርልህ ምንስ ብመዝንልህ አንጀቴን ማራስ እችል ይሆን ??
ብቻ ግን ተመስገን ... !!!

* ጎይቶምን ከመገርሳ ፣ አብነውን ከሌሊሳ፣ ክርስቲያኑን ከሙስሊሙ፣ ተማሪውን ከቀለሙ ፣ መምህሩ ከመንበሩ
ሽማግሌውን ከክብሩ አለያይተው አዋርደው መርዛቸውን የደፉብንን አጋጎች በአደባባይ ለቆራረጠልን ፣ በድንገት ላተነነልን ኢየሱስ ምን ብንገብርለት አንጀታችን ይርስ ይሆን?
ብቻ ግን ተመስገን ...!!!

ሲዖል እንወርዳለን !!                     ገጣሚ (ጌታቸው ረዳ )    ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከጨለማው ገዢ እንዛመዳለን     ከመንጸፈ ደይን ረዳታችን ዘንድ ሲዖል እንወርዳለን  ...
09/28/2021

ሲዖል እንወርዳለን !!
ገጣሚ (ጌታቸው ረዳ )

ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከጨለማው ገዢ እንዛመዳለን
ከመንጸፈ ደይን ረዳታችን ዘንድ ሲዖል እንወርዳለን
ከእጆቹ መዳፍ ፍሙን እያፈስን እሳት እንጭራለን ...
ንጹህ ደም የማፍሰስ ጥበብ እንቀዳለን
በመግደል የመርካትን ጭካኔ እንወርሳለን
ብቻ ...
ኢትዮጵያ ሚሏትን ሀገር ይገላግለን ... !!
ቤልሆር ሉሲፈር ሌጊዎን ሰይጣኑ
አዛዝኤል ጭፍራው ቡኤሉ ጋኔኑ
ለዚህች ሀገር መውደም አብረውን ከሆኑ ...
ምን እንፈልጋለን ... ?
ከኛ ጋር አብረው ኢትዮጵያን ካጠፏት
ቅጥሯን አፈራርሰው ሶርያ ካረጓት
ሸራተናችን ነው ለኛ ጋ'ነም እሳት... ። !!

ሲዖል እንወርዳለን !!!

09/27/2021

ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ
መስቀል አደባባይ
እንካን አደረሳችሁ !!

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ                               (መኩሪያ ጉግሣ)ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ                 ምልክትን ሰጠሃቸው       ...
09/26/2021

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ
(መኩሪያ ጉግሣ)

ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ
ምልክትን ሰጠሃቸው
መዝ 60፥4
ማዕተቤ ትርጉም ነው የክርስትናዬ
ተቀበለኝ ብሎ የሰጠኝ ጌታዬ
በመስቀሉ ፍቅር ሥጋዬን ገድዬ
እሸከመዋለው ምኞቴን ሰቅዬ !!
የማይበጠስ ነው በእምነት የታሰረ
በአምላኬ ፍቅር በደሙ የከበረ
በአንገቴ ላይ ያለው በልቤ ውስጥ ጠልቋል
ማዕተቤን ሊበጥስ ከቶ ማን ይችላል
በቅብዐ ሜሮኑ የተቀደሰ ነው
ዳግመኛ ስወለድ ካህኑ ያሰረው
የእምነቴ ማዕተም አርማዬ ነውን
ይኖራል ባንገቴ እንደ መቅረዝ ፋና

...... ቀሪውን ሊንኩን ተጭናችሁ አዳምጡት
https://m.youtube.com/watch?v=1QY72f9OKdg&feature=share

09/26/2021

ደጺ ደም በእጃችን የሌለ ቅዱሳን ነን
ብሎን እረፈው !!


ገዳይ ... !!
( መኩሪያ ጉግሣ)

ገዳይ ከሟች በላይ ሳያፍር ያለቅሳል
አርዶ እየሰቀለ ለቅሶ ይቀመጣል እዝን ይቀበላል
እጁን በደም ታጥቦ ራሱን ይቀድሳል
ከሟች ደጃፍ ሄዶ ድንኳኑን ይተክላል
ነጠላ አዘቅዝቆ ንፍሮ ይቀቅላል ... iii
ገዳይ ዶሴ ከፍቶ ...
እግዜር ያጽናህ በሉኝ የሞትኩት እኔ ነኝ
እጆቼ አላደፉም ሟች ነው የገደለኝ
ልብሴን ያጨቀየው በደሙ ያጠበኝ ...
እያለ ይከሳል...
ሟችን ይዋቀሳል ...
" አልበደልኩም ብሎ ንጹህ ሰው ነኝ ካለ
መቃብር ፈንቅሎ መምጣት እየቻለ
የገደልኩት ገዳይ ቀብሬ ላይ የታለ" ?
ብሎ ይጠይቃል
ጨክኖ ያለቅሳል
ይገርማል ... !!



.

ህውሃትን ቆርጦ መጣል !!     ሁሌ ልምምጥ የለም !!               ( መኩሪያ ጉግሣ )       የመምህር ዳንኤል ክብረትን ንግግር ከሙሉ ሃሳቡ ሥር ቆራርጦ በመሰንጠቅ  ለመክሰስ...
09/24/2021

ህውሃትን ቆርጦ መጣል !!
ሁሌ ልምምጥ የለም !!
( መኩሪያ ጉግሣ )

የመምህር ዳንኤል ክብረትን ንግግር ከሙሉ ሃሳቡ ሥር ቆራርጦ በመሰንጠቅ ለመክሰስ መሞከር ከመገረም አልፎ ያስቃልም ያሳፍራልም !! እናንት ሌጊዮኖች ይህንን ጠንቅቃችሁ ብታውቁም የፓለቲካ ትርፍ ከተገኝበት እናታችሁንም ስለምታርዱ አይደንቀንም!! ዳኒ መቼ ? የት ? በምን ሁኔታ ? ምን አይነት ንግግር ? ለነማን ? እንደሚቀርብ የምንማርበት ቱባ መጽሃፍ እንጂ ቃላትና ቦታ የሚመርጡለት የወያኔ ዘመን ስንኩል ምሁር አይደለም !!
እንደ ዳንኤል ከቤተ ክህነት እስከ ቤተ መንግሥት ወያኔን ያባበለ፣ የለመነ፣ ያስተማረ ፣ የተለማመጠ ቢፈለግ አይገኝም !!!
እሱ ንግግርን ከክርስቶስ የተማረ ፣ ቋንቋን ከአባቶቹ ጥበብ ሥር የወሰደ ፣ እንኳን ለክፉ ለበጎ እንኳ ዝም ማለትን ከቅዱስ ዳዊት የቀዳ ፣ በአንደበቴ እንዳልስት ለአፌ ጠባቂ መልአክ አኑር "ን የጸለየ የኢትዮጵያ በረከት ነው !!

ሁሌ ግን ልምምጥ የለም !!

ደከመን ሰለቸን እናንተን መለማመጥና ማባበል ...
እናንተ የኢትዮጵያ ምድር "አይሁዶች" እውነትን መስቀል፤ ክርስቶስን መስቀል እንደሆነ ልታውቁ ይገባችኋል ። እናንት ሴሰኝነት ያሰቃያችሁ ረበናት የሶስና አምላክ ዛሬም እንዳለ ልታውቁ ግድ ነው ... !!

ሁሌ ልምምጥ የለም !!

political Correctness, Religious (Spiritual) Correctness, Social life Correctness Need to STOP Right Now !! We want to protect Our Country !!
ኢየሱስ ክርስቶስ አይሁድን እንዳባበለው ነው ዳኒም ሆነ እኛ የኢትዮጵያ ልጆች ያባበልናችሁ በቃንንንንንንንንን !!!
ስትሰቅሉንም፣ ስታርዱንም፣ ስትሸጡንም፣ ስትወጉንም፣ ስትዘርፉንም ስትቀጠቅጡንም ስትሸኑብንም አባበልናችሁ አይበቃም ???
አይሁድ ኢየሱስ ክርስቶስን ሊገድሉ እየፈለጉ የአብርሃም ዘር ነን እያሉ ደሞ ይመጻደቃሉ ጌታም " የአብርሃም ዘር መሆናችሁን አውቃለሁ ልትገድሉኝ ግን ትፈልጋላችሁ "እናንተ ያባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ" ብሎ አበታቸው ማን እንደሆነ ሳይነግራቸው ተዋቹው (አንድ)

ቃሉን እናንተ አንብቡት ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ስምንት ...

እነሱ መች ያፍራሉ አባታችን አብርሃም ነው ለማለት አልተሸማቀቁም ... ጌታም " የአብርሃም ልጆች ብትሆኑ የአብርሃምን ሥራ ባደረጋችሁ ነበር... እናንተ ግን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ ÷ እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ" አላቸው አሁንም አባታቸውን ሳይናገር ዘለለው ... (ሁለት)
ተዋቸው አባበላቸው ...
እነሱ ግን መች ያፍሩና " እኛ ከዝሙት አልተወለድንም አባታችን እግዚአብሔር ነው " ብለው እርፍ !!
ክርስቶስም "እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው ። እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ፣እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ" ብሎ ከግንዱ ላይ ቆርጦ ጣላቸው ... !!
የሙዐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት መንገድም ይህው ነው አባብሎ አባብሎ ፣ ለምኖ ለምኖ ፣ ሸምግሎ ሸምግሎ ፣ ተለማምጦ ተለማምጦ እነዚህ የሰው ደም የማይጠግቡ አጋንንቶችን እንኳን ከሀገራችን ከትውልድ ህሊና እንዲጠፉ ቆርጦ ጣላቸው !!!

ሁሌ ልምምጥ የለም ... !!

ንግግሩ ደግሞ እልልልል የሚያስብል እውነት ነው ። አለቀ ደቀቀ !!
የቤተክርስቲያን ልጆች በመሆናችን ምክንያት እያሸማቀቃችሁ ሀገር ስታሳጡን ዝም ብለን ወያኔንና ጀሌዎቹን ይየምንታገስበት፣ ቃላት የምንመርጥበት የምንራራበት ዘመን አክትሟል ። እናንተ በምድር ያነደዳችሁብን እሳት ስላላጠፋን፤ ሲዖል ድረስ ወርዳችሁ እሳት ልትደፉብን ስትንደፋደፉ ዝም እንድንላችሁ መጽሐፉ አይፈቅድም !!
አናንተ ልታርዱን፣ ልትሰቁሉን ፣ልትሸጡን ፣ ሳትራሩ እኛ ለምናወጣው ቃላት ሚሊዮን ጊዜ ራራንላችሁ አይበቃም? እናንት የህውሃት ዘልዛላ ደጋፊዎች ??? !!

D.Mekuria Gugsa's cover photo
03/10/2021

D.Mekuria Gugsa's cover photo

11/25/2020

ህውሓቶች ያአዶኒቤዜቅ ልጆች !!!

አዶኔቤዜቅም ሸሸ ...
አሳደውም ያዙት ...!! መሳ 1÷6
ህውሓትም ሸሸች ...
ዲያቆን መኩሪያ ጉግሣ

የዚህን ክፉ ሰው ታሪክ በመጽሐፈ መሳፍንት የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ እናገኝዋለን አዶኒቤዜቅ የማረካቸውን ነገሥታት የእጅና የእግር አውራ ጣታቸውን እየቆረጠ ግፍ ይፈጽምባቸው ነበር ። እንደምታውቁት አውራ ጣቱ የተቆረጠ ሰው እንኳን ጦር መወርወር በቀስት መምታት ይቅርና እንጀራ መቁረስ እንኳን አይችልም ። ነገ መልሰው እንዳይዋጉት እያሰበ እጃቸውንም እግራቸውንም አመከነባቸው ። እስኪ ሞክሩት ያለ አውራ ጣታችሁ እንጀራ መቁረስ እንኳ እንዴት ከባድ እንደሆነ ትረዱታላችሁ ፣ ከአንዱ አውራ ጣት ምናለ ሁለቱ የማሃል ጣቶቼ በተቆረጡ እስክትሉ ድረስ ትቸገራላችሁ ... የእግር አውራ ጣትም ከተቆረጠ ችግሩ ብዙ ነው ባላንስ ያሳጣል ሮጦ መቅደም በውጊያ መሰለፍ አያስችልም ...
አዶኔቤዜቅም ሥንት ግብር ያበሉ ሃያላን ነገሥታትን ማርኮ አውራ ጣቶቻቸውን እየቆረጠ የጣለላቸውን ፍርፋሪ እንኳን መብላት ሲያቅታቸው እያየ ይዝናናባቸው ነበር ...
ቃሉ እንዲህ ይላል ...
መሳ 1÷5-7
" አዶኒቤዜቅንም በቤዜቅ አገኙትና ተዋጉት፤ አዶኒቤዜቅም ሸሸ፤ አሳድደውም ያዙት፥ የእጁንና የእግሩንም አውራ ጣት ቈረጡ ።
አዶኒቤዜቅም፦ የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣት የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበር፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ አለ። ወደ ኢየሩሳሌምም አመጡት፥ በዚያም ሞተ
ቀን መጥቶ፣እግዚአብሔር ፈርዶ፣ ነገሩ ወደራሱ ተገልብጦ የሱ ጣቶች ከመቆረጣቸው በፊት እሱ የሰባ ነገሥታቱን ጣቶች እየቆረጠ ከገበታው በታች እንጀራ መቁረስ ሲያቅታቸው እያየ ቲያትር ይመለከትና ያላግጥ ነበር ... ። የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውምና አዶኔቤዜቅም በሰፈረው ቁና እራሱ መልሶ ተሰፈረ " እኔ እንዳደረኩ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ " አለ ። የደሃውን የናቡቴን ደም የጠጣው አክአብ እግዚአብሔር በነብዩ በኤልያስ አማካኝነት"የናቡቴን ደም ውሾች እንደላሱት ያንተንም ደም ውሾች ይልሱታል" ነው ያለው እንዳለውም እንዲሁ ነው የሆነው ...
ህውሓቶች እንደ አዶኒቤዜቅ በአውራ ጣት አልተልከሰከሱም የአውራ ጣት ደም ስለማይበቃቸው አንገት እየቆረጡ ነው ሃያ ሰባት ዓመት ንጹህ ደም የጠጡት ዛሬ እግዚአብሔር ሰይፉን መዞባቸዋል ክእጁስ ማን ያስጥላቸዋል ? ለአንዱ አቤል ደም ቃየልን የተሟገተ " የውንድምህ ደም በፊቴ ይጮሃል" ያለ እግዚአብሔር ዛሬም በዙፋኑ ነው። እውነተኛና ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ዛሬም የሀገራችንን አዶኔቤዜቆች አይምርም የልጆቹን ደም ከእጃቸው ይቀበላል !!
አዶኒቤዜቅ " እኔ እንዳደረኩ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ " አለ እናንተ መቀሌ ገብታችሁ በድሆችና በንጹሃን እናቶች ቀሚስ ሥር የተሸሸጋችሁ እግዚአብሔር የልጆቹን ደም ይቀበላችኋል እናንተ እንዳደረጋችሁት እንዲሁ ያደርግባችኋል !! ከእጅስ ማን ያስጥላችኋል ... !!
ውጊያው የእግዚአብሔር ነው !!

11/15/2020

ፖለቲካ ... !!
ዲያቆን መኩሪያ ጉግሣ

ፖለቲካ ግም ነው ... !!
ገምቶ የተግማማ
የሰው ነፍስ አሲዞ ቆምሮ ሚያዳማ
ሥጋን አበስብሶ ህይወት የሚያቃማ
ምድር የሚያረክስ የሞት አኬልዳማ ... !!
ፖለቲካ ቂም ነው ... !!
የሺህ ዘመን ኃጢያት አምጥቶ ሚከምር
በትናንቱ በደል ፣ ዛሬውን አሲዞ በቀል የሚዘክር
በሰው መቅኔ ሰክሮ ሲተፋ የሚያድር
አምኖናዊ ብክተት እህት የሚያነውር ... !!
ፓለቲካ ርኩስ ነው ... !!
ረክሶ የረከሰ
ትውልድ ያመከነ ፍቅር ያበሰበሰ
የወንድሙን አጥንት ከስክሶ ያጨሰ
በንጹሃን ደም ላይ ራሱን ያነገሰ ... !!
ፖለቲካ ጋቭሮቭ ... !!
ችጋራም ስግብግብ
በቁራ ልብ ክንፍ የሚበር እንደ ርግብ
የቂም የጥላቻ የጥንቆላ አንደርብ
ከሰው ዘር የማነስ የጭንቅላት ሥር ጥንብ ...!!
ፓለቲካ ክህደት ... !!
የውሸቶች ውሸት
ጠቢብና ጥበብ የሚታረዱበት የሚሰቀሉበት
የንጹሃን ሲዖል የጨካኞች ገነት
ክርስቶስን ክዶ ለወንበዴው በርባን የሚቃትቱበት ... !!!
ፖለቲካ ግፍ ነው ... !!
አረመኔ ጨካኝ
" ሚሊዮን ሰው ይርገፍ እኔን እስከደላኝ "
ብለው የማሉበት ... የሞት ቃል ኪዳን ነው
ለዚህ ነው መቶ ዓመት በህመም የኖርነው ... !!!

This is wise decision from Ertirean people and government !! Ethiopian Army more than enough to Capture the criminals ou...
11/14/2020

This is wise decision from Ertirean people and government !!
Ethiopian Army more than enough to Capture the criminals out off Tegre region and all over the country!! Peace and security will be maintained in all regions of the country. It has been lots of killing all over the region caused by TPLF! Jurist must served!! May God bless our Ethiopia and Ertirea !!

11/14/2020

Andualem Buketo Geda እንደፃፈው
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

አንዳንድ ተጋሩ ወዳጆቻችን እና "ሚዛናዊ ኢትዮጵያውያን" የህወሃትን ጠብ አጫሪነት ለምን አታወግዙም ስንላቸው "ጦርነቱን ማን እንደጀመረው አናውቅም!አብይም ራሱ ጀምሮት ይሆናል" ሲሉን ነበር። ይሁን እሺ ብለን ምክንያታቸውን ተቀብለን ቆየን።

ትንሽ ቆይቶ በማይካድራ ከ500 በላይ ወገኖቻችን እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ ተጨፈጨፉ!

"አሁንስ !?"አልናቸው።

አንዳንዶቹ የሟቾቹን ፎቶ እየተነተኑ "ዜናው ሃሰት ነው" ሲሉ የተቀሩት ደግሞ "የሞቱት ሲቪሎች ሳይሆኑ ተዋጊዎች ናቸው ...ግድያውን የምናወግዝበት ምክንያት የለም!" አሉ
እርር እያልን "!ይሁና!" ብለን ተውናቸው

ትላንት የህወሃት ቃል አቀባይ የሆነው ሴኮ ቱሬ በይፋ ወጥቶ ' ጦርነቱን የጀመርነው እኛ ነን ....የሰሜን እዝ ላይ መብረቃዊ እርምጃ ወስደናል!" አለ...

በተመሳሳይ አምነስቲ ኢንተርናሽል "በማይካድራ በአደረኩት ምርመራ(ከሳተላይት ፎቶ በተወሰደ መረጃ እና በአይን ምስክሮች እማኝነትም ጭምር በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች ታርደዋል..ለፍቶ አዳሪ ሰራተኞች ..በማንነታቸው ተለይተው የተገደሉ አማሮች ናቸው!) አለ።

እንግዲህ ህሊና ላለው ማናቸውም ሰው የህወሃትን ክፋት ላለማውገዝ ሩም የቀረለት አይመስለኝም!

የደ.አፍሪካው ዴዝሞንድ ቱቱ እንዳሉት

"If you are neutral in situations of injustice, you have chosen the side of the oppressor!"

(ግፍ ሲፈጸም እያየህ ገለልተኛነትን ከመረጥክ የበዳዩ ወገንን መርጠሃል ..እንደማለት ነው!)

ህዝብ ይታዘባል...ጊዜ ጠብቆ ብይኑን ይሰጣል!

10/26/2020

ፖለቲካ ... !!
ዲያቆን መኩሪያ ጉግሣ

ፖለቲካ ግም ነው ... !!
ገምቶ የተግማማ
የሰው ነፍስ አሲዞ ቆምሮ ሚያዳማ
ሥጋን አበስብሶ ህይወት የሚያቃማ
ምድር የሚያረክስ የሞት አኬልዳማ ... !!
ፖለቲካ ቂም ነው ... !!
የሺህ ዘመን ኃጢያት አምጥቶ ሚከምር
በትናንቱ በደል ፣ ዛሬውን አሲዞ በቀል የሚዘክር
በሰው መቅኔ ሰክሮ ሲተፋ የሚያድር
አምኖናዊ ብክተት እህት የሚያነውር ... !!
ፓለቲካ ርኩስ ነው ... !!!
ረክሶ የረከሰ
ትውልድ ያመከነ ፍቅር ያበሰበሰ
የወንድሙን አጥንት ከስክሶ ያጨሰ
በንጹሃን ደም ላይ ራሱን ያነገሰ ... !!
ፖለቲካ ጋቭሮቭ ...
ችጋራም ስግብግብ
በቁራ ልብ ክንፍ የሚበር እንደ ርግብ
የቂም የጥላቻ የጥንቆላ አንደርብ
ከሰው ዘር የማነስ የጭንቅላት ሥር ጥንብ ...!!
ፓለቲካ ክህደት ...
የውሸቶች ውሸት
ጠቢብና ጥበብ የሚታረዱበት የሚሰቀሉበት
የንጹሃን ሲዖል የጨካኞች ገነት
ክርስቶስን ክዶ ለወንበዴው በርባን የሚቃትቱበት ... !!!
ፖለቲካ ግፍ ነው ...
አረመኔ ጨካኝ
" ሚሊዮን ሰው ይርገፍ እኔን እስከደላኝ "
ብለው የማሉበት ... የሞት ቃል ኪዳን ነው
ለዚህ ነው መቶ ዓመት በህመም የኖርነው ... !!!

08/15/2020

እንኳንም ተወለድክ !!
Happy Birthday ABICHUUU....

በቅዥታም ሀገር
ባለ ራእይ ምን ያልማል ?
ነቃይ በሞላበት
ተካይ ምን ያበቅላል ?
በጥላቻ ሰፈር
ፍቅር ምን ያተርፋል ?
በገዳዮች ምድር
ሟች ማንን ያድናል ?
እኛ እንጠይቃለን እርሱም ይመልሳል
" ዛሬም ባይሆን ነገ ፍቅር ያሸንፋል "
ይስብካል፣ ይጮሃል፣ ይሰራል፣ ይደክማል ...
አውቆ የተኛው ግን ቢያርዱት መች ይነቃል ?
ስድቡን ይቀጥላል ... !!!
እኔ ደሞ እላለሁ ...
ዝም ብለህ ለፋህ ዝም ብለህ ደከምክ
በጽንፈኞች መቅረዝ ለብቻህን ነደድክ
በአበው ፍቅር ሰክረህ በታሪክ መረቀንክ
በሌሊት ወፍ ሰማይ ፣ የመስቀል ወፍ ሆነህ
... ለኢትዮጵያ በረርክ !!
መስከረም ሳይጠባ እንደ አደይ ፈነጠክ
ግን... ግን ...
እንኳንም ተወለድክ ... !!

08/09/2020

አድማ ...!!
ዲ.መኩሪያ ጉግሣ
በአማርኛ እንዳናወራ ፣
በአማርኛ አድማ መጥራት
ዳቦ ለመጋገር ብቅል እንደማስጣት
ጌሾ እንደማቡካት ...
ጠላ እጠምቅ ብሎ :
ዶሮን በእንሥራ ጥዶ እንደማቁላላት
ፍየሉ ወደዚህ ወዲያ ቅዝምዝሙ
አማርኛ እንዲሞት አማርኛ ስሙ... !!

08/02/2020
ለግብጾቹና ለፈርዖኖቹ

ኢትዮጵያ በረሃብ ስትረግፍ ፣
በጎርፏ ሰብል ይታጨድ ?
ካይሮ ገላ ሲታጠብ ሀበሻ
በጥም ይሰደድ ?
አይበቃም ??

ለግብጾቹ ፈርዖኖች

08/01/2020

አቶ እከሌ ወ/ሮ እከሊት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ የሚለው የሞት መርዶ የምሥራች እስኪመስል ድረስ ምድሪቱን በደም ያጨቀያችሁ አራጆች እግዚአብሔር ይበቀላችሁ !!

D.Mekuria Gugsa
07/29/2020

D.Mekuria Gugsa

የከሸፉ ወላጆችና ...      የከሸፉ ልጆች !!                         መኩሪያ ጉግሣ         የአንዲት ልጇን ሳትቀጣ በብልግና ያሳደገች ሴት ታሪክ አለ ሴትዮዋ የእናትነ...
07/29/2020

የከሸፉ ወላጆችና ...
የከሸፉ ልጆች !!
መኩሪያ ጉግሣ

የአንዲት ልጇን ሳትቀጣ በብልግና ያሳደገች ሴት ታሪክ አለ ሴትዮዋ የእናትነት ድርሻዋን ያልተወጣች ሆዱን እንጂ ጭንቅላቱንና ልቡን መግባ የማታውቅ የከሸፈች እናት ነበረች። በዚህም ምክንያት ያልተዘራበትን አያበቅልምና ልጇ ምንም ዓይነት ሥነ ምግባር ያልነበረው ዋልጌና ባለጌ ነበር ። ያላደገበትን ከየት ያምጣው ?
ደሞ አታፍርም እንደ ደህና ልጅ አንድ ቀን ከዘመድ ሠርግ ቤት ይዛው ትሄዳለች ልጁ ገና እንደደረሰ ሠርግ ቤቱን በአንድ እግሩ ያቆመዋል አንዴ ጠጁን ሲደፋ ፣ አንዴ የሰው ምግብ ላይ ሲተፋ ፣ አንዴ ቀይ ወጥ ውስጥ ፣ አንዴ ክትፎ ውስጥ ፣ እየገባ ሲያንቦጫርቅ ተው ብትለው፣ ብትለምነው፣ ብትቆጣው፣ ብታባብለው ፈጽሞ ሊሰማት አልቻለም ። ሲብስባትና የሰው ሁሉ ዓይን ልጁን በቁጣ ሲመለከተው ተበሳጭታ መማታት ትጀምራለች ይሄኔ ሁኔታውን ሁሉ ሲታዘቡ የቆዩ አንድ አረጋዊ አባት " ተይው ልጄ ለዛሬ አይደርስልሽም " አሏት ይባላል ። !!
እውነት ነው በሥነ ምግባር ኮትኩተን ካላሳደግነው ልጅ እንዴት ሰብአዊ ሥነ-ምግባር ልንጠብቅ እንችላለን ? እሾህ እየዘራን ወይን ፣ ኩርንችት እየተከልን በለስ እንዴት ልንለቅም እንችላለን ? ሴትዮዋ እቤት ውስጥ በጓዳዋ ያልዘራችውን በሠርግ ቤት በአደባባይ ማጨድ ፈለገች። የለም የምታጭጂው የዘራሽውን ነው ። (አራት ነጥብ !!!)
ዛሬ በሜኒሶታም በሲያትልም በሌሎችም ቦታዎች ያየናቸው ባለጌዎች እመኑኝ የባለጌ ልጆች ናቸው ። ያለምንም ጥርጥር አባታቸው የተከለባቸውን እናታቸው የዘራችባቸውን እሾህና አመኬላ አብቅለው ነው በአደባባይ ካላጨዳችሁኝ ሲሉ ያየነው ... !!
ልጅን በጥላቻ እንደማሳደግ ክፉነት የለም ። በሰለጠነ ዓለም ውስጥ ማሰይጠንን የመሰለ አረመኔነትም የለም። በንጹህ ልባቸው ላይ ቆሻሻ የደፋችሁባቸው ወላጆች እግዚአብሔር ይበቀላችሁ !! በኢትዮጵያ ላይ ያሰባችሁት ጥፋት እንዳይሳካ የእግዚአብሔር መልአክ መንገዳችሁን ይዝጋው !! እናንተ እርግማን ይገባችኋል !! ። የጠጣችሁትን ደም ያክል ጠጥታችኃል አሁን የምታስታውኩትን ያክል እያስታወካችሁ ነው !! ። ይበቃል ... !!! ።
እውነት ጭንቅላት ያለው ሰው ፣ ጤነኛ ሰው እንዴት በሰው ሀገር በስደት መጥቶ እየኖረ አንጥፎ የተቀበለውን ህዝብ ይረግጣል ? እንዴት የበላበትን ወጪት ይሰብራል ? እንዴት እንጀራቸውን እየበላ ተረከዙን ሊያነሳባቸው ይችላል ??? እዴት እንዴት እንዴት ???
እኔ በእውነት ዛሬ የተሰማኝ ድንጋጤና ሀፍረት በዘመኔ በፍጹም ገጥሞኝ አያውቅም እዚህ በአሜሪካ አድገው ተምረው ህግም ፍትህም ባለበትና በብዙ ካሜራዎች ፊት ለፊት እንዲህ አይነት ጭካኔ በገዛ ሀገሩ ላይ( አሜሪካዊ ነጭ ዜጋ ላይ ) ለመፈጸም ከጨከኑ በሻሸመኔ ፣ በሀረርጌ ፣ በአሳሳ ፣በጂማ ወዘተ ... ምን ያህል ጭካኔ ፈጽመው ይሆን !! ??
በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ አንድ ደስ ያለኝ ነገር ግን አለ በእንደዚህ ዓይነት አራጆችና ጨካኞች እጅ የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው አለማየቴ !! እኛ ኢትዮጵያውያን በሥነ ምግባር ያደግን ነን ፣ ጨዋነት ልብሳችን ነው ፣ ይሉኝታ ካባችን ነው ክብር እናውቃለን ሰው እንወዳለን እንግዳ እንቀበላለን እግሩን አጥበን እናሳድራለን ያለንን እናካፍላለን። !! እኛ ይሄ ነን !! ዛሬ ያየነው የከሸፉ ወላጆች ያሳደጓቸው ልጆች ከየት እንደመጡ በፍጹም አናውቅም ። ያደረጉትኮ እግራቸውን አጥቦ እንግድነት የተቀበላቸውን የቤቱን ባለቤት አርዶ ለእራት እንደማቅረብ ነው ። ይሄ በየትኛውም መስፈርት ነውር ነው ፣ ውርደት ነው፣ መዝቀጥ ነው። እነዚህ ከመራራ ምንጭ የተቀዱ መራሮች የከሸፉ ወላጆች ውጤት ናቸውና ለዛሬ ስለማይደርሱልን የካፋ ነገር እንዳያመጡብን በተጠንቀቅ ሆነን ኢትዮጵያን በፍቅርና በአንድነት በጽናት እንጠብቅ !!
ይህው ነው !!
የኢትዮጵያ አምላክ የታመነ ነው

ጭንቅላታቸውን ወደ ሆዳቸው                  ያወረዱ ሰዎች !!                                   መኩሪያ ጉግሣ     ትናንትና  ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ  በፍጹም ረ...
07/29/2020

ጭንቅላታቸውን ወደ ሆዳቸው
ያወረዱ ሰዎች !!
መኩሪያ ጉግሣ

ትናንትና ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ በፍጹም ረስቼው የነበረውን ሰው አስታውሶኝ እንደገና ሰውዬውን መስማትም ማንበብም ካቆምኩበት ቦታ ጀምሬ ሙጥጥ አርጌ ሰማሁት አነበብኩት ... መቼም እግዚኦ ነው ። ሰው ለሥልጣንና ለሆዱ ሲል የሚገለባበጥበት ፍጥነት በፍጹም ለማመን የሚከብድ እጅግ አስገራሚና አሸማቃቂ ነው ።
ሰውዬው ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ ይባላል በኮትና በሱሪ ውስጥ ሆኖ ስትቆጥረው ያው እንደማንኛችንም አንድ ሰው ሆኖ ታገኝዋለህ ። ነገር ግን ለውጡን ተከትሎ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ፣ ቃለ ምልልሱን ፣ ሹመቱን ፣ ሽረቱን የሚጽፋቸውን ጽሁፎች፣ የሚያደርጋቸውን ቅስቀሳዎች አስተውለህ ከተከታተልከው ስንት ሰው እንደሆነ ግራ ይገባሃል !! አንዳንዴ ሊቅ ፣ አንዳንዴ ልቅ ፣ አንዳንዴ ብስል አንዳንዴ ጥሬ እየሆነ ያሰቃይሃል ። እሱን መከተል ይደክምህና በቃ ይሄ ሰውዬ ጭንቅላቱ ሆዱ ላይ ነው ብለህ ትተወዋለህ ። ግን እሱ አይተውህም ያለህበት ድረስ መጥቶ ይፈታተንሃል ። ሳትወድ በግድህ ይሄን ብዙዙዙ ሰውዬ የሆነ ነገር ልበለው ትላለህ። ግን ምንድነው የምትለው ? የትኛውን ማንነቱን ነው የምትሟገተው ?? በዚህ ምክንያት ትቼው ረስቼው ተቀምጬ ነበር ። እንዲህ አይነቱን ከጠቢብነት ወደ ፍልጥነት ተፈጥፍጦ የወደቀን ሰው እንኳን በሃሳብ በስካባተርም አታነሳውም ። መቼም ቢሆን ምክርህም ሃሳብህም አይገዛውም። ። ቢሆንም ግን የሆነ ነገር ለማለት እያሰብኩ ነበር ። በዚህ መካከል የዚህን 'ሰውዬዎች' አቻ መገለጫ ባጭሩ ሊያስቀምጥልኝ የሚችል ምርጥ መልዕክት ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌ ከላከልኝ የፕሮፌሰር ምንዳርአለው ዘውዴ " የእውቀት አክፍሎተኛ " መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ገጽ ላይ ቁጭጭጭ ብሎ አገኘሁት .... !!
እንዲህ ይላሉ ፕሮፌሰሩ
ሌባ በዝምታ ሲታለፍ ያልዘረፈው የሰው ንብረት ይቆጨዋል ። ዘራፊን ንቀህ ስትተወው የፈራኽው ይመስለዋል ። ወንጀለኛንና በዳይን ከተደበቀበት አይተህ እንዳላየ ብታልፈው እራሴ ብበደል ነው ብሎ አብሮ ፈትፋቹን ኡኡ በሉልኝ ይላል ። ሌባን ከተሸሸገበት አይተህ በ "ከእኔ ይቅር " ብትተወው ለህዝቡ ትንሣኤ ሱባኤ ገብቼ ነው ብሎ ያስወራል ። ሰይጣንን ይቅርታ ብታደርግለት መልአክ ስለሆንኩ ነው እያለ ይፈችላል ። ለባዶነቱ ማረጋገጫ ሰዎችን በማጋደልና ወገንን በማቋሰል የድድብናውን ሰርተፍኬት ከአደባባይ ይቀበላል ። ደደብ ጭንቅላት ፍቅርን እንዲሰብክ ብትልከው ጥላቻን ዘርቶ ይመለሳል ። መተሳሰብንና አንተ ትብስ አንቺ ትብሽን እንዲያስተምር ልከህው ቂም ሲቋጥር ዘር ሲቆጥር ታገኝዋለህ... " ይህ ከሙሁሩና ከደራሲው መጽሐፍ ላይ ቃል በቃል ወስጄ ያስቀመጥኩት እውነት ነው።
የፕሮፌሰሩን እያንዳንዱን እውነት ወስጄ ብርሃነ መስቀል ላይ ልሰካው ብትል ሁሉንም ብትንትኑ ለወጣው ስብዕናው ሰጥተህ እሱ ላይ ገና እዳ ይኖርበታል !!
ስልጣን ሲሰጥህ ዶክተር ዓቢይን " ሥርዓት አልበኝነት ከሚሰፍን ከመንግሥቱ ኃ/ማርያምም የከፋ ቢሆን እመርጣለው " ብለህ ተናግረህ በነጋታው ያለዜግነትህ ሰርቀህ የወሰድከውን ሥልጣን ስትነጠቅ " ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንባገነን ናቸው " ካልክ ባጭሩ ጭንቅላትህ ወደ ሆድህ ወርዷል ወይም ሆድህ ጭንቅላትህ ላይ ወጥቷል !!
የምታስበውም የማታስበውም በበላህውና ባልበላህው መጠን ነው ። ከእንዲህ ዓይነት የአደባባይ ውርደት አሥር ጊዜ መመሞት ይሻላል ... !!

ከንጉሡ ፈረሱ !!                   አጫሉን ያለአቅሙ አትፈልጉበት  !!           ሁላችንም እንደምናውቀው ማንኛውም ነገር አቅምና ብቃት ይጠይቃል ። የጭንቅላት የማሰብ አቅም...
06/23/2020

ከንጉሡ ፈረሱ !!

አጫሉን ያለአቅሙ አትፈልጉበት !!

ሁላችንም እንደምናውቀው ማንኛውም ነገር አቅምና ብቃት ይጠይቃል ። የጭንቅላት የማሰብ አቅም ፣ የዓይን የማየት ዓቅም ፣ የጆሮ የመስማት አቅም ፣ የጉሮሮ የማዜምና የመጮህ አቅም፣ ሥራን በአግባቡ የመፈጸም አቅም ወዘተ... ተብሎ ሊተነተን ይችላል ።
ማንም ያለ አቅሙ ምንም ማድረግ አይችልም ። እኔ ነኝ ያለ ዘፋኝ አሥር አልበም ቢያሳትምም እንደ ጥላሁን ሊያዜምና ሊጮህ ግን አይችልም !! ድምጻዊ (አርቲስት) የሚለውን ስም ይጋራው ይሆናል እንጂ እንደጥሌ መራቀቅ፣ እንኳን በጉሮሮሎጂ በቴክኖሎጂም የማይሞከር ነው ... !! ምክንያቱ ምንድነው ? ብለህ ብትጠይቅ መልሱ አቅም ... አቅም ... አቅም ... !!
በህክምናው ዓለም ተደጋግሞ የምንሰማው አንድ ቃል አለ "በሽታን የመከላከል አቅም " የሰዉነት የበሽታ መከላከል አቅም ማለት አንድ ሰዉ በህመም እንዳይያዝ ወይም ህመም አምጪ በሆኑ ነፍሳት እንዳይጠቃ ወይም ከተጠቃ በኋላ እንዳይራቡ የሚዋጋልን የሰዉነታችን ስርዓት ነዉ። አንድ ሰው የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅሙ ሙሉ በሙሉ መሥራት በማይችልበት ጊዜ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ችግር እንዳለበት ይነገረዋል፡፡ የሆነው ሆኖ ነፍሱ እስክትወጣ ድረስ የአቅሙን ያክል ይፍጨረጨራል ። አቅም ከሌለ ግን ያው የለም ነው !!
እኔ በግሌ ጭንቅላቴን ተጠቅሜ ፣ ጥቅሜንና ጉዳቴን አመዛዝኜ እምዬ ምኒልክ የሰጠኝን ክብር አስበዋለው ፣ አከብራዋለው፣ እዘፍናዋለው ፣ እቀኝበታለው ... ። የአፍሪቃ ቀኝ ገዢዎችን ሳገኛቸው በክብር ኢትዮጵያዊነቴን እነግራቸዋለው እነሱ ይሸማቀቃሉ እንጂ እኔ አልሸማቀቅም!! Emperor Minilk king of Ethiopia , The Only Country Never Been Colonized in Africa እያልኩ ኩፍስስስስስ... እላለሁ ደረቴ ላይ በደማቁ ጽፌ አስነብባቸዋለው ። ማን ? እኔ ።
አጭዬ ደሞ ይሄን ሊረዳውም ሊገባውም አይችልም የተማረውን ያክል ተምሮ፣ ያነበበውን ያክል አንብቦ የጠየቀውን ያክል ጠይቆ ፣ የሰማውን ያክል ሰምቶ ከንጉሡ ይልቅ ፈረሡን መርጧል አትጨቅጭቁት በቃ ልኩ ይሄው ነው ።
አጫሉ የፈረሱ ጉዳይ ቢያሳስበው በሱ ልክ : ልክ ነው !! ፣ በሱ እውቀት : እውቀት ነው !! ፣ በሱ ታሪክ :ታሪክ ነው !! በቃ አጫሉ ይህው ነው። ጨምር ብትሉት አይጨምርም ቀንስ ብትሉት አይቀንስም ተንኮለኛ ፣ ሴረኛ ፣ ፓለቲከኛ ፣ ስለሆነ እንዳይመስላችሁ በቃ ልኩ ያ ነው ። ለምን ከልኩ በላይ ትጠይቁታላችሁ ? ኢትዮጵያም ሆነች ኦሮምያ የአጫሉን ጭንቅላት ሳይሆን የምትፈልገው ጉሮሮውን ብቻ ነው !!
ጉሮሮው ደሞ ውብ ነው ። ይችላል፣ ያስደስታል ፣ ያስለቅሳል አንደኛ የሚባል አይነት ነው !!
አጭዬ ትችላለህ ...
ቢሆንም ቢሆንም
ሃሳብህን አንገዛህም
መቼም ሃሳብ ያው ሃሳብ ነውና አያጠላላንም...
እናም ካንተው ጋር Maalan jiraን እያቀነቀን : እኛ ንጉሣችንን እንወስዳለን አንተም ፈረስህን ትወስዳለህ
ይአያጠላላንም

06/10/2020

( በግፍ ለተደፈሩ )
ዲያቆን መኩሪያ ጉግሣ

ልብ ባልነጻበት
---------------------------
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪዋ እንደዘረጋች ነው
ጸሎቷ አልታጎለም በቀንና ሌሊት እየጸለየች ነው
ግና ... ግና...ግና ...
በቋንቃዎች ሁሉ በየ እምነት አይነቱ
ቢደርስ ሥርዓቱ ፣ ቢቀርብም መስዋዕቱ
የመባረካችን የመፈወሳችን የለም ምልክቱ !!
ይልቅ ጾመን ጾመን ጸልየን ስንወጣ
አዲስ ጉድ ወልደን ነው ከፍተን የምንመጣ ።
ይህው ዘመን ከፍቶ ኮረና ቢወረን ፣
ይቅር ተባብለን በንስሃ ወድቀን ፣
መቅሰፍቱን ልንቀስፈው የእምነት ድንበር ንደን ፣
ለወራት ባንድ ላይ አልቅሰን አልቅሰን፣ ጸልየን ጸልየን ፣
ልጁን የሚደፍር አባት ነው የወለድን ።!!

መጾም ያልቀደሰን ...
ጸሎት ያረከስን የምድር ጉዶች ነን ... !!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪዋ እንደዘረጋች ነው
ጸሎቷ አልታጎለም ማዐልትና ሌሊት እየማለደች ነው
ጾም ጸሎት አውጃ ልክ እንደ ነነዌ ፣
ማቅ ለብሳ ለምና ወድቃ በሱባኤ ፣
ተማጽና... ተማጽና ፣ ለምና ... ለምና ፣
ግና ... ግና ... ግና...
እንኳን መቅሰፍት ሊቀር ወረርሽኝ ሊለቀን ፣
ሌላ የግፍ ግፍ ነው ጓዳ ውስጥ የወለድን ። !!
.....
ጆሮ ጭው የሚያረግ አዲስ ክፋት ጨመርን ፣
የኖህ ዘመን ጥፋት ደርሶ እያንኳኳብን እንደገና መረርን ፣
የሰዶምን መርገም ...
ባብራካችን ክፋይ በጭካኔ ፈጸመን !!
አባቱን ለማቀፍ የሚሳቀቅ ጨቅላ ፣
አባቷ የሰበራት ታናሽ ብላቴና ለምድሪቱ ሰጠን ።
ከጾሙ በኃላ ጸሎቱ ሲፈጸም ይህን ነው ያተረፍን ። !!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪዋ እንደዘረጋች ነው
ጸሎቷ አልጎደለም በቀንና ሌሊት እየማለደች ነው
ልቧ ግን በኃጢያት እንደጨቀየ ነው ። !!
ታድያ ... ሺህ መስዋዕት ቢሰዋ
እጅ ቢዘረጋ ልብ ባልነጻበት
ከሰማይ ላይመጣ ጠብታ በረከት
ምን ይሰራል ጩህት ?
ባልተናጻ መዳፍ ፍህሙን ብንደፋበት
ብርጉድ ፋንድያ ነው
መዐዛ ቢስ ቅመም የሜዳ ላይ እበት !!
ከምድር አያልፍም እንኳን ሰማይ ሊሸት !!

...... // ....

ከታላቅ ይቅርታ ጋር   እግዚአብሔር እንደፈቀደው እንጂ ሰው እንዳሰበው አይሆንም ። ዛሬ ሁለት ጊዜ ፕሮግራማችንን ለመቀየር ተገደናል ከአንጋፋዋ ዘማሪ ፋንቱ ወልዴ ጋር ልናደርግ ያሰብነው ቆይ...
04/28/2020

ከታላቅ ይቅርታ ጋር

እግዚአብሔር እንደፈቀደው እንጂ ሰው እንዳሰበው አይሆንም ። ዛሬ ሁለት ጊዜ ፕሮግራማችንን ለመቀየር ተገደናል ከአንጋፋዋ ዘማሪ ፋንቱ ወልዴ ጋር ልናደርግ ያሰብነው ቆይታ ይህው እንዲህ ብንገናኝም የቴክኒክ ችግር አጋጥሞናል በዚህ ምክንያት በድጋሚ ቀኑና ሰዓቱን ቀይረነዋል !!
ይሄ ግን የማይለወጥ ፕሮግራም ነው !!

ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ለብዙዎች ምሳሌ የሆነች በመላው ዓለም ተዘዋውራ ቤተክርስቲያንን ያገለገለች የዝማሬ ምልክት ናት በረጅም የአገልግሎት ዘመኗ ያሳለፈችውን ለመጀመሪያ ጊዜ ይከታተሉ ... !!

የሰማያት ቤተሰብ ይሁኑ !!

https://youtu.be/VCl9LIv7xSQ

Address

5804 Okview Gardens Drive
Falls Church, VA
22041

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when D.Mekuria Gugsa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to D.Mekuria Gugsa:

Videos

Share


Comments

ምናምንቴ ሰው የበደለኛም ልጅ በጠማማ አፍ ይሄዳል፤ በዓይኑ ይጠቅሳል ፣ በእግሩ ይናገራል፥ በጣቱ ያስተምራል፤ ጠማማነት በልቡ አለ፤ ሁልጊዜም ክፋትን ያስባል። መ.ምሳሌ ም፥6 ቁ 11-14።

በእርግጥ በዚህ የህማማት ሰሞን ምልልሱ የማይገባ ቢሆንም በአደባባይ በድፍረት ማንም የማንንም እምነት የመስደብና የማዋረድ መብት ያለው አይመስለኝም።

የኮረናን በሽታ ከአንድ እምነት ጋር አወዳድሮ አማኙን በስድብ መጨፍጨፍ ሌላ ተልኮ ነው።

እኔ ለእግዚአብሔር የምዋጋ ወታደር ሳልሆን ፥ እግዚአብሔር ለእኔ የሚዋጋልኝ ደከማ አማኝ ነኝ።
ስለዚህ በእምነቴ የሚዋጋኝን ፥ ለተዋጊው እግዚአብሔር መስጠት ተገቢ ነው። እምነቴን ጥንቅቄ አውቃለሁ ። ማንም እምነቱን በደመ ነፍስ የሚያመልክ ያለ አይመስለኝም።

ግን ይኸ ትላንት ወንድም የነበረ ፥ ዛሬ እንዲህ በጥላቻ ተነስቶ አንድን እምነት ማዋረድ ምን ይባላል!!!?

መጀመሪያ፤ ቅዱሳን ሰዎችን እና፤: መላዕክትን እንኴን የመለየት ችሎታ ያለው አይመስልም ።

ስግደት እንኳንም አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቀርቶ ፥ ሰዎች ለቅዱሳን ሰግደዋል ። ለምሳሌ፦ አቢግያል ለቅዱስ ዳዊት ሰግዳለች።1ኛ ሳሙ.25 ቁ23

ኦርና በመሬት ላይ ተደፍቶ ለቅዱስ ዳዊት ሰግዷል። 1ኛ ዜና መዋ.ም.21 ቁ.21 ብዙ መጥቀስ ይቻላል።

ስለ ቅዱሳን ፀሎት፥ ሕዝቅያስ በህይወት እያለ ስለ ህዝቡ ፀልዮ እግዚአብሔርም ተለምኖታል። 2ኛ ዜና መዋ.ም30፥ቁ19-21

በአዳስ ኪዳንም ኤልያስና ሙሴ ተገልጠው ሀዋርያት እያዩ ጌታችንን እየሱስ ክርስቶስን እንዳነጋገሩ መስክረውልናል።ማርቆ.9 ቁ 4-5

ቅዱሳን ነቢያት ከሞቱም በኋላ፥ በመቃብራቸው ላይ የወደቀ አስከሪን ሕይወት ዘርቶ እንደተነሳ መ.ቅዱሳችን ይናገራል።2ኛ ነገሥ. 13፥ ቁ 20-21።
በጣም ብዙ ማስረጃ ዙሪያችንን እንደ ደመና ከበውን እያለ ፥
የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሐይማኖትን እና አማኙን በስድብ ማዋረድ ፥ በእውነት ሌላ ከጀርባው ተልዕኮ ከሌለው በጣም አሳፋሪና ሊታረም የሚገባው ነው።

እጅግም ያሳዝናል ። በዚህ ስዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም በሀይማኖቱ/ በእምነቱ / በቤቱ እግዚአብሔር ከመጣው መዓት እንዲሰውረን በፊቱ መውደቅ ሲገባ ፥

" የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ከኮረና የባሰ ገዳይ ነው "። ብሎ ጦርነት ማስነሳት ፥
የከፋ በደል ነው። ሁሉም ሰው
ይኸን ዘማሪ ነኝ ባይ እንዲታረም ሊያስጠነቅቀው ይገባል።

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ክርስቶስ እየሱስን እዳኝና ጌታዋ አምላኳ የእግዚአብሔር ልጅ ፤ እግዚአብሔር ብላ የምታምን የምትሰግድ የምትገዛ። ዳግም ምጽዓቱን የምትጠብቅ።
በመንፈስ ቅዱስ ሙላት የምታምን!!! ግን "ሁሉን በአግባብ አድርጉት"!!
የሚለውን የጌታን ትእዛዝ አክብራ ፥ ያለ ሁከት እራስን በመግዛት የምትመራ ሀይማኖት ናት። ራስን መግዛት ፥ ዘገምተኛ አስመስሏት ካልሆነ።

እግዚአብሔር የሠማይና የምድር ሁሉ ፈጣሪ ፥ ምህረቱን ያበዛልን ዘንድ ፊቱን እንፈልግ።
አበባ ነኝ።
Enkonie lakeduse Michalie adarsachu egzeyabehare amelke bayalchwebatie yetabekachu agarachenie selamie yaregrlnie Amen Amen Amen
በዕምነታችን ላይ ተደጋጋሚ የጥላቻ ጥፋት ሲፈፀም በትዕግስት መታየቱ እንደፍራቻ ተቆጥሮ ቤተክርስቲያን ማቃጠሉ ቀጥሏል አማኞችና የኃይማኖቱ አባቶች ተገድለዋል እነርሱ ለዕምነታቸዉ ሕይወታቸዉን ሳይሳሱ ሰጥተዉ የታላቁን አባታችንን አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ተቀብለዉ የዕምነት ፅናታቸዉን አሳይተዉናል።
ዝምታ ፀረክርስትናዎች በድርጊታቸዉ እንዲቀጥሉበት አድርጓል ከዚህ በኋላ ሌላቤተክርስቲያን ሲቃጠል አባቶችና አማኞች ሲገደሉ ማየት አንፈልግም በቃ ሊባል ይገባል
ቤተክርስቲያን ዝምታዋን ሰብራ ለልጆቿ ጋሻ መከታ መሆንዋን በማሳየት ድርጊቱን አጥብቃ በማዉገዝ የወጣዉን መግለጫ የሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን ቃል ነዉ። አንተም ወንድሜ ይህን የምስራች ስለአሰማኸን እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
በዛወርቅ አስፋው (ብዙዬ)

እኔና ብዙዬን ያገናኝን የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ነው ከጋሽ መሐሙድና ከአዓም ከበደ ጋር ለሦስት ቆንጆ መዝሙር ሰርተው ነበር ። በተለይ የስዋ መዝሙሮች ልዩ ነበሩ ሲዲውን ለመስማት የታደለ ሁሉ " የአዲስ ኪዳን ብሥራትን" እና " ይቅርታን" አይዘነጉትም ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ቡዜን የማገኛት በቤተመቅደስ ብቻ ነው !!

ከእግዚአብሔር ቤት አጥቻት አላውቅም ደስታዬ አምላኬ ብቻ ነው ትለኛለች ሁልጊዜ ያሳለፈችውን ህይወቷን በቃሉ መስታወትነት እያየች እራሷን ትመረምራለች ።

ኢትዮጵያም ስትሄድ አብዛኛውን ጊዜ በየገዳማቱ የአቅሟን ሁሉ በማድረግና በጸሎት ነው የምታሳልፈው

ትናንት ቨርጂንያ ኪዳነምህረት ሳገኛት ስለኢትዮጵያ ያላትን ህመምና ቁጭት በእንባ አወጋችኝ ጸሎቷ ፣ እንባዋ ፣ ግጥሟ ፣ እንጉርጉሮዋ ሁሉ ኢትዮጵያ ብቻ ናት !!

ምን አይነት የጉድ ዘመን ላይ ደረስን ? በምን ፍጥነት እንዲህ ያለ የዘረኝነት እርኩሰት ላይ ወደቅን ? ትላለች በሁለት እጆችዋ ጭንቅላቷን ይዛ ... !!

የምንተክዘውን ያክል ተክዘን የምናለቅሰውን ያህል አልቅሰን በጸሎት ተለያየን !!
#}