
02/06/2025
ዘማሪት የምስራች ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
ልብ የሚሰብር ዜና! ዘማሪት የምስራች ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
ከዘጠኝ ወር ገደማ በፊት በህመም ምክንያት በደጋግ ኢትዮጵያውያን እርዳታ ተደርጎላት ወደ ታይላንድ ሄዳ ህክምና ስትከታተል እንደነበር ይታወቃል። በዚያም እያለች ከሁለት ወር በፊት በታይላንድ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ በድንጋጤ ስትለቅስ የሚያሳይ ቪዲዮም አጋርታ ነበር።
ጤንነቷ ተሻሽሎ ወደ ሀገሯ የተመለሰች ቢሆንም፣ በቅርቡ ባደረባት ከባድ ህመም፣ በተለይም በጀርባዋና በሳንባዋ ላይ በተገኘባት ካንሰር ሳቢያ፣ በፅኑ ህክምና ክፍል ውስጥ ህክምና ሲደረግላት ከቆየ በኋላ፣ ዛሬ ከአንድ ሰዓት በፊት ህይወቷ አልፏል።
ነፍስ ይማር እህታችን። ዘማሪት የምስራች በመዝሙሮቿ ብዙዎችን ያጽናናች እና የመንፈሳዊነት አሻራዋን ያሳረፈች ዘማሪት ነበረች።
ፈጣሪ ነፍሷን በገነት ያኑርልን። ለቤተሰቦቿ፣ ለአድናቂዎቿ እና ብዙ ለለፉት ወዳጆቿ መጽናናትን ይስጥልን።