ጎጆ Tube

ጎጆ Tube Welcome to Our ጎጆ Tube! This page serves as a forum for us as Ethiopians to share experiences related to social, economic, and health matters.
(2)

Let’s support one another and foster a positive environment.

እናቷ እና አባቷ ሲወልዷት አባቷ የ17 አመት እናቷ ደግሞ የ16 አመት ወጣት ነበሩ።የፍቅር ግንኙነት አጋጣሚአቸው የልጂቱ እናት ከልጂቱ አባት ቤተሰብ የቤት ሰራተኛ ነበረች።የልጁ እናት እና ...
17/09/2026

እናቷ እና አባቷ ሲወልዷት አባቷ የ17 አመት እናቷ ደግሞ የ16 አመት ወጣት ነበሩ።የፍቅር ግንኙነት አጋጣሚአቸው የልጂቱ እናት ከልጂቱ አባት ቤተሰብ የቤት ሰራተኛ ነበረች።የልጁ እናት እና አባት በጣም ሃብታሞች ናቸው ነገር ግን ልጅ አንድ እሱ ብቻ ነበር የነበረ ለቤተሰቡ።ከቤት ሰራተኛዋ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀመሩ።በዚህ አጋጣሚ በነበራቸው የፍቅር ግንኘነት እናቷ አረገዘች 6 ወር ሲሆናት እርግዝናው እየታወቀ ሲመጣ የልጁን እናት ስትፈራ ሆዴን አመመኝ ብል ወደ ክፍለ ሀገር ወደ ቤተሰበቿ ሄደች።ከቤተሰቦቿ ወለደቻት ከወለደች ከ11 አመት በኋላ ወደ አረብ ሀገር ልጇን ከአክስቷ ጋር አዲስ አበባ ጥላት ሄደች።እናቷ በሄደች በ4 አመቷ ልጇን ወደ ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም እንድትሰለጥን ደውላ ብር ልካላት እንድትገባ ትልካታለች።እየሰለጠነች/እየተማረች እያለች ከተቋሙ ባለቤት ጋር ፍቅር ትጀምራለች።ፍቅር የጀመረችው ከተቋሙ ባለቤት ከአባቷ ነው።እናቷ ስለ አባቷ ምንም ነገር አልነገረቻትም።የልጂቱ ስም ሚጠራው በአባቷ ሳይሆን በእናቷ አባት ነበር።ልጂቱ ባለሀብት ባል አገኘሁ ብላ ተደስታለች ከዚህ በኋላ እናቴ ወደ ሀገሯ ትመለሳለች እያለች በሀሳብ ብቻዋን በደስታ ትስቃለች ከትንሽ ጊዜ በኋላ አብረው መኖር ጀመሩ ከትንሽ ወራት በኋላ አረገዘች።ለእናቷ ደውላ ከተቋሙ ባለቤት ጋ ትዳር እንዳሰቡ ትነግራታለች እናቷም አልተቃወመችም በልጇ ትዳር ተደሰተች።ነገር ግን ሁለተኛ ሚስት ነበረች ሁለተኛ መሆኗን ግን አታውቅም ለሰራ ወጥቼ አድራለሁ እያለ ከሌላኛዋ ሚስቱ ያድር ነበር።እሷም ወራቷ ደርሶ ከማታቀው አባቷ ወለደች።ከወለደች ከትንሽ ጊዜ በኋላ እናቷ ከአረብ ሀገር ወደ ሀገሯ መጣች።እናቷን ከአየር መንገድ ተቀብላ ከቤቷ ታሳርፋታለች ከትንሽ ሰአት በኋላ አባቷም ባሏም የሆነው ሰውየ ወደ ቤቱ አስቤዛ ይዞ የሚስቱን እናት/የድሮ ሚስቱን/የልጁን እናት ለመገናኘት መጣ ነገር ግን እሷ መሆኗን አያውቅም ነበር ከቤቱ ገብቶ አማቱን ወይም የድሮ ሚስቱን ተገናኝቶ ተቀመጠ በደንብ አልተያዩም ከትንሽ ቆይታ በኋላ ፊት ለፊት ሲተያዩ ሁለቱም ደነገጡ ነገር ግን በደንብ አልተዋወቁም ግን የሁለቱም ሰውነት እንደተያዩ ሰውነታቸው ተንቀጠቀጠ እና ሰላም ነህ ስምህን አልነገርከኝም የልጀ ባል ማን ትባላለህ ስትል ጠየቀችው ስሙን ሲነግራት ደነገጠች እሷም ነገረችው በድንጋጤ ሁለቶችም ከመቀመጫቸው ተነስተው የኔዋ የኔው መባባል ጀመሩ ልጂቷ ደንግጣ ዝም ብላ አይኗ ፈጦ ቀረች ልጁን ያገባት መሆኑን ሲያውቅ እራሱን ሳተ ከቀናት በኋላ ያለውን ንብረት ለልጁ እና ከልጁ ለወለደው ልጁ አውርሷቸው ንስሃ ገብቶ ወደ ገዳም ገባ።የልጂቱ እናትም በድንጋጤ አበደች።ልጂቱም የአባቷን ወይም የልጇን አባት ንብረት ወርሳ ደግማ ባል ላታገባ በፈጣሪዋ ምላ ልጇን ማሳደግ ቀጠለች።ታሪኩ በዚህ ተጠናቀቀ #እባካችሁ ልጆች ወልዳችሁ በአባታቸው ስም ይጠሩ በአያታቸው ስም አታስጠሩ ከቤተሰብ ጋርም አስተዋውቁ ወላጆች በፈጣሪ ስም ይሁንባችሁ።አመሰግናለሁ ሌላ አዲስ ነገር ሲኖር እፅፍላችኋለሁ ለጓደኞቻችሁ ሸር አርጉላቸው። አርጉኝ

  : የታይላንድ መንግስት አዲስ የቪዛ ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።ከዚህም ጋር ተያይዞ ለበርካታ አገራት ሲሰጥ የቆየውን ያለቪዛ መግባት እና የመዳረሻ ቪዛ ተጠቃሚ የሆኑ አገራትን እን...
17/09/2026

: የታይላንድ መንግስት አዲስ የቪዛ ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ለበርካታ አገራት ሲሰጥ የቆየውን ያለቪዛ መግባት እና የመዳረሻ ቪዛ ተጠቃሚ የሆኑ አገራትን እንደገና በመከለስ ለተወሰኑ አገራት ብቻ እንዲሆን አድርጓል።

ቀደም ሲል ወደ ታይላንድ ለሚጓዙ #ኢትዮጵያውያን ሲሰጥ የነበረው የመዳረሻ ቪዛ (visa on arrival) እ.ኤ.አ. ከSep 15 ቀን 2026 ጀምሮ በአዲስ የቪዛ ህግ የተተካ ሲሆን ይኸውም ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ከመነሳታቸው በፊት በOnline የመግቢያ ቪዛ thaievisa.go.th ላይ በማመልከት ሲፈቀድላቸው ብቻ መግባት የሚችሉ መሆኑን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ከአሁን በኃላ ወደ ታይላንድ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ከመነሻው የታይላንድ ቪዛ ማግኘት የሚኖርባቸው ይሆናል።

Via EMBASSY OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPΙΑ NEW DELHI

ጫት ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰድ ተጀመረ‼በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ በብሔረሰብ ምክር ቤቱ የተላለፈውን ክልከላ በመጣስ ጫት ወደ ከተማዋ ያስገቡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የወረ...
17/09/2026

ጫት ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰድ ተጀመረ‼

በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ በብሔረሰብ ምክር ቤቱ የተላለፈውን ክልከላ በመጣስ ጫት ወደ ከተማዋ ያስገቡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ።

የወንጀል መከላከል የሥራ ሂደት የሆኑት ዋና ሳጅን አብዱረሂም አኑር እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል ከህብረተሰቡና ከነጋዴዎች ጋር ስምምነት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ህጉን በተላለፉት ላይ እርምጃ ተወስዷል። በቁጥጥር ሥር የዋለውም ጫት በህዝብ ፊት እንዲወገድ ተደርጓል።

ፖሊስ ሌሎች ነጋዴዎች ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ እያስጠነቀቀ፣ የቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል ሲል የወረዳው ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Via-Wasu Mohammed - Mereja

ኢትዮጵያውያን እባካችሁ! ዛሬ መርካቶ አካባቢ ፓስፖርቴ ጠፋብኝ፤ ዛሬ ማታ በረራ አለኝ ።" አስቸኳይ ትብብር — የጠፋ ፓስፖርት!የሀገራችንን ውበትና እንግዳ ተቀባይነት ለመለማመድ ከሩቅ አሜሪ...
16/09/2026

ኢትዮጵያውያን እባካችሁ! ዛሬ መርካቶ አካባቢ ፓስፖርቴ ጠፋብኝ፤ ዛሬ ማታ በረራ አለኝ ።"

አስቸኳይ ትብብር — የጠፋ ፓስፖርት!

የሀገራችንን ውበትና እንግዳ ተቀባይነት ለመለማመድ ከሩቅ አሜሪካ የመጡት ግራንት (Grant E Fisher) ዛሬ መርካቶን እየጎበኙ ሳለ በድንገት ያልታሰበ አጋጣሚ ገጥሟቸዋል።

ምሳ ሰዓት አካባቢ በነበረው የሰዎች እንቅስቃሴ መካከል የአሜሪካ ፓስፖርታቸውን ጥለውታል።

ጉዳዩን የበለጠ አስቸኳይ የሚያደርገው ደግሞ የግራንት ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት በረራ ዛሬ ከምሽቱ 5:20 ሰዓት ላይ በመሆኑ ነው!

ኢትዮጵያውያን ለችግር ጊዜ እንደምን ደራሽነታችን እና እንግዳ አክባሪነታችን፣ ሁላችንም እጃችንን እንዘርጋ። መርካቶ አካባቢ ያላችሁ፣ ወይም ፓስፖርቱን ያገኛችሁ ሰው ካላችሁ እባካችሁ ወዲያውኑ ወደ አስጎብኛቸው ሚኪ ስልክ በመደወል አግዟቸው።

* የጠፋው ዕቃ: የአሜሪካ ፓስፖርት

* የባለቤቱ ስም: Grant E Fisher

* የጠፋበት ቦታ: መርካቶ

* የመገናኛ ስልክ (ሚኪ): 0924 60 05 04

መልዕክቱ በፍጥነት ለሁሉም እንዲደርስና ግራንት በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እባካችሁ ሁላችንም በማድረግ እንተባበር!

በዘልማድ ወተት መሸጥ ሊቆም ነው👉 የወተት ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው ፡፡ ማህበረሰቡን ከጤና ስጋት ለመጠበቅ እና የወተት ጥራትን በቁጥጥር ስር ለማዋል...
16/09/2026

በዘልማድ ወተት መሸጥ ሊቆም ነው

👉 የወተት ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው ፡፡

ማህበረሰቡን ከጤና ስጋት ለመጠበቅ እና የወተት ጥራትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል አዲስ የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀመሆኑን በአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ማዕቀፉ ተግባራዊ ሲሆን በየቦታው በዘልማድ ወተት መሸጥ የሚቀር ሲሆን፤ አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች ከእርባታ ጀምሮ እስከ ማጓጓዣ ባሉት ጥብቅ ስታንዳርዶች ብቻ እንዲመሩ ይደረጋልም ተብላል፡፡

እንደ ወተት ያሉ ለመበላሸት ቅርብ የሆኑ ምርቶችን ጥራት ለመቆጣጠር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ለሚያፀድቀዉ አካል መላኩን በአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሰርቲፊኬሽን ኢንስፔክሽንና ሬጉላተሪ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ፀጋ ለማ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

እንደ ዶክተር ፀጋ ገለፃ ማዕቀፉ ፀድቆ ተግባራዊ ሲሆን ከወተት ብክለት ጋር ተያይዞ ማህበረሰቡ የሚያነሳቸዉን የጤና ስጋቶች ለመፍታት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ።

ማዕቀፉ በእርባታ ጣቢያዎች የመኖ አቀማመጥ፣ አመጋገብ ፣የህክምና አሰጣጥ እና የእርባታ ሼዶች ዲዛይን ምን መምሰል አለበት የሚለዉን ያጠቃልላል።

በተጨማሪም የወተት ማለቢያ ዘዴዎች እና የማጓጓዣ ዕቃዎችን በተመለከተ ስታንዳርዱ በዝርዝር ማካተቱን ዶክተር ፀጋ ተናግረዋል ።በመሆኑም ማዕቀፉ ሲጸድቅ ከእርባታ ጀምሮ እስከ ማጓጓዝ ድረስ ያሉ ጥብቅ መስፈርቶችን ሳያሟሉ ወተት መሸጥ እንደማይቻል ተመላክቷል።

በየክፍለከተማዉ የወተት ጥራትን ቁጥጥር የሚያደርጉ ባለሙያዎች ተለይተዉ ስልጠና እየወሰዱ መሆናቸዉን የሚገልፁት ዶክተር ፀጋ የወተት መመሪመሪያ መሳሪያዎች ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ተደራሽ እየተደረጉ ናቸው ብለዋል ።

Via በመባ ወርቅነህ
©️ዳጉ_ጆርናል

ልብ የሚነካ ዜና 💔ከቀናት በፊት ከቤት ጠፍቶ የነበረው ወንድማችን ደስታው ባንቲደር ከቀናት ፍለጋ በኋላ ዓባይ ገብቶ ሙቶ ተገኝቷል።ከትናንት በስቲያ ማለትም በቀን በ3/1/2019 ከለሊቱ 9 ...
16/09/2026

ልብ የሚነካ ዜና 💔

ከቀናት በፊት ከቤት ጠፍቶ የነበረው ወንድማችን ደስታው ባንቲደር ከቀናት ፍለጋ በኋላ ዓባይ ገብቶ ሙቶ ተገኝቷል።

ከትናንት በስቲያ ማለትም በቀን በ3/1/2019 ከለሊቱ 9 ሰዓት ገደማ ባህርዳር ቀበሌ 7 ወጣት ደስታው ባንቲደር በሰዓቱ ከላይ ቢጫ ቲሸርት ጥቁር ቱታ ሱሪ እንደለበሰ እስከአሁን ወደ ቤቱ አልተመለሰም ብለናችሁ ነበር።

ልጁ የጤና ችግር ስላለበት ያያችሁ በፈጠሪያችሁ አፋልጉን ብለንም ተማፅኖ አቅርበን ነበር ። በሚያሳዝን ሁኔታ ወንድማችን ደስታው ባንቲደር ከቀናት ፍለጋ በኋላ ዓባይ ገብቶ ሙቶ ተገኝቷል።

ደከመኝ ሳትሉ በፍለጋ ሁሉ ያገዛችሁን መረጃውን በማጋራትና #ሼር በማድረግ ለብዙሃን እንዲደርስ በማድረግ ያገዛችሁን በሙሉ ፈጣሪ የነብስ ዋጋ ያድርግላችሁ !

ለቤተሰቦቹ ለጓደኞቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን ። ነብሱን ይማርልን
#ባህርዳር

ከ50 ዓመታት በፊት የነበሩ ሚንስትሮቻችን አና የትምህርት ዝግጅታቸው:-1. አክሊሉ ሀብተወልድ፦ ከሶርቦን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሩቅ (ማስተርስ)፣2. ማሞ ታደሰ፦ ከፈረንሳይ አገር የ...
15/09/2026

ከ50 ዓመታት በፊት የነበሩ ሚንስትሮቻችን አና የትምህርት ዝግጅታቸው:-

1. አክሊሉ ሀብተወልድ፦ ከሶርቦን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሩቅ (ማስተርስ)፣

2. ማሞ ታደሰ፦ ከፈረንሳይ አገር የሕግ ምሩቅ፣

3. ሥዩም ሀረጎት፦ የሕግ ዶክትሬት (JD): ከታዋቂው የአሜሪካ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (Harvard University) በ1957 እ.ኤ.አ በሕግ ትምህርት ተመርቀዋል።

4. ከተማ ይፍሩ፦ ከዊስኮንሲን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሩቅ፣

5. በላይ አባይ፦ የLondon School of Political Science and Economics ምሩቅ፣

6. ልጅ አንዳልካቸው መኮንን፦ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሩቅ፣

7. ልጅ ሚካኤል አምሩ፦ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሩቅ፣

8. ዶክተር ምናሴ ሀይሌ፦ ከዊስኮንሲን ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ ባችለር ዲግሪ ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በ LLB፣ MA እና PHD ዲግሪ በኢንተርናሽናል ሕግ ተቀብለዋል፣

8. ይልማ ደሬሳ፦ የLondon School of Economics and Political Science ምሩቅ፣

9. ደጃዝማች ዶክተር ዘውዴ ገብረስላሴ፦ ከኦክስፎርድ ዩንቨርስቲ የሕግ፣ ታሪክ አና ፖሊቲካ ሳይንስ ምሩቅ፣

10. ቡልቻ ደመቅሳ፦ የLondon School of Economics and Political Science አንዲሁም Syracuae ዩኒቨርስቲ ምሩቅ…

Jemal Abdulaziz

አንድ ሰሞኑን ሲካሄድ በነበረው የብሪክስ ጉባኤ ለመካፈል ወደ ህንድ ተጉዘው የነበሩት ቭላድሚር ፑቲን ዴልሂ ኤርፖርት ደርሰው ፡  የአውሮፕላኑ በር ተከፍቶ ለመውረድ እየተዘጋጁ እያለ  ባልተለ...
14/09/2026

አንድ
ሰሞኑን ሲካሄድ በነበረው የብሪክስ ጉባኤ ለመካፈል ወደ ህንድ ተጉዘው የነበሩት ቭላድሚር ፑቲን ዴልሂ ኤርፖርት ደርሰው ፡ የአውሮፕላኑ በር ተከፍቶ ለመውረድ እየተዘጋጁ እያለ ባልተለመደ መልኩ ቆም አሉና በር ላይ የቆመችውን ሆስተስ እየጨበጧት አመሰግናለሁ አሏት ። .......
ሁለት

በዚሁ የብሪክስ ጉባኤ ለመካፈል ወደ ህንድ ተጉዘው ከነበሩት የሀገራት መሪዎች መካከል የአቡዳቢው ልኡል ሼክ ካሊድ ቢን መሀመድ ቢን ዛይድ ይገኙበታል ።

ሼክ ካሊድ በዚህ ስብሰባ ሲካፈሉ ቆይተው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ዴልሂ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በቀጥታ ወደሚጠብቃቸው አውሮፕላን ከመግባታቸው በፊት ወደ ኤርፖርት ያመጣቸው ህንዳዊ የሊሙዚን ሾፌር ወደቆመበት ቦታ ተመልሰው ሄደው ፡ አመሰግናለሁ አሉት ።.....
እነዚህ የሁለቱ መሪዎች ቀላል የሚመስል ግን ትህትናን የተላበሰ ሰውኛ ነገር ከብሪክስ ጉባኤ ባልተናነሰ የሚዲያዎችን ትኩረት የሳበና ፡ በብዙዎች ደስ የሚል ነገር ትቶ ያለፈ ነገር ሆኗል

‼️‼️   ለነዛ አይምሯቸው ቀንጭሮ ለቀረ የደብተራ ቅዥትና ተረት በማለት ለተለከፉ   አድርሱልኝ‼️‼️‼️አንተ   የምትለው ነው! Londo, Cambridge university ውስጥ እንዲ  ...
14/09/2026

‼️‼️ ለነዛ አይምሯቸው ቀንጭሮ ለቀረ የደብተራ ቅዥትና ተረት በማለት ለተለከፉ አድርሱልኝ‼️‼️‼️

አንተ የምትለው ነው! Londo, Cambridge university ውስጥ እንዲ #በተመራማሪዎች የሚጠናው‼️
ምስሉን ለሥራ ተጋብዤ በሄድኩበት ያነሳሁት ሲሆን! #በሃገሬ ጥበብ ግን ባይተዋር አርገውኝ የተመለስኩበት ነበር!!! ለመንካት ሁሉ አስፈቅደህ ነው! ከዚህ በተለየ ደግሞ ከፍ ያለ ምርምር የሚደረጉባቸው #የብራና መፃሀፍት ያሉበት ክፍል ውስጥ አይደለም ኢትዮጵያዊያን አፍሪካውያን ጭምር እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም! አንተ ተረት ቅዥት እያልክ የምትሰድበውን ጥበብ አንተ የምታመልካቸው ፈረንጆች በክብር አስቀምጠው ይመራመሩበታል! እንደ እናንተ እራሱን ሚሰድብ ወራዳ ትውልድ ሲገጥም ነው ሃገርም መከራ ሚገጥማት የደብተራ ተረት፣ ቅዠት ለምትሉ አንድ መልዕክት አለኝ እናንተ የሀገር ሸክም ናቹ!!!

Via-Tina_Bekele

አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ የፖለቲካ እስረኞች በምህረት መለቀቃቸው ተገለጸ::በተለያዩ ከባድ የወንጀል ክሶች ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ይገኙ የነበሩ ከ600 በላይ ተጠራጣሪዎ...
10/09/2026

አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ የፖለቲካ እስረኞች በምህረት መለቀቃቸው ተገለጸ::

በተለያዩ ከባድ የወንጀል ክሶች ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ይገኙ የነበሩ ከ600 በላይ ተጠራጣሪዎችና ተፈራጅ እስረኞች በመንግስት ምህረት ተደርጎላቸው መፈታታቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ይፋ አደረገ።

ከእስር ከተለቀቁት መካከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ እንደሚገኙበት የተገለጸ ሲሆን፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በመናድ፣ በሽብርተኝነትና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች ተከሰተው ፍርድ ቤት ሲመላለሱና የእስር ቅጣታቸውን ሲፈጽሙ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ከሆነ፣ ላለፉት አምስት ወራት ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ሲያካሂድ የቆየውን ተከታታይ የምክክርና የድርድር ሂደቶች ተከተሎ በተደረሰበት መግባባት መሰረት እስረኞቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።

በተጨማሪም የኮሚሽኑ ተወካዮች በማረሚያ ቤቶች በአካል በመገኘት ከሚፈቱት ግለሰቦች ጋር ውይይት ማድረጋቸውንና የድርድሩን ውጤት የሚያስጠብቅ አቋም ላይ መደርሱን ገልጸዋል።

©️ኢሰመኮ

Address

Abu Dhabi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጎጆ Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category