10/27/2025
ሮናልዶ እና ሜሲ የተካተቱበት የፊፍፕሮ የዓመቱ ምርጥ 11 ዕጩዎች
የዓለም አቀፉ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር የሚያዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ 11 ተጫዋቾች ዕጩዎች ይፋ ሆነዋል።
26 ተጫዋቾች በዕጩነት በቀረቡበት የ2025 ምርጫ የአል ናስሩ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና የኢንተር ማያሚው አማካይ ሊዮኔል ሜሲ የተካተቱ ሆነዋል።
ፒኤሲጅ በርከታ ተጫዋቾችን በዕጩነት በማስመረጥ ቀዳሚው ሆኗል። የባሎን ዶር አሸናፊው ኡስማን ደምቤሌን ጨምሮ ጃኦ ኔቬስ፣ አችራፍ ሃኪሚ እና ኑኖ ሜንዴዝ ከተመረጡት መካከል ናቸው።
የአርሰናሉ ዊሊያም ሳሊባ፣ የሊቨርፑሉቹ ሙሀመድ ሳላ እና አሊሰን፣ የማድሪዱ ኬይሊያን ምባፔን ጨምሮ ሃለንድ፣ ላሚን ያማል እነወዲሁም ጁድ ቢሊንግሀም እና ኮል ፓልመር በዕጩነት ከቀረቡት መካከል ናቸው።
በ2005 መካሄድ የጀመረው የፊፍፕሮ ምርጥ 11 ሽልማት በዚህ ዓመት ለ21ኛ ጊዜ የሚደረግ ይሆናል።
የ8 ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ 17 ጊዜ ምርጥ 11 ውስጥ በመግባት ቀዳሚው ተጫዋች ነው።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ 15 ጊዜ በመመረጥ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።