25/10/2025
I appreciate & proud of your excellent achievement in every levels 👏👏👏👌👌👌👏👏👏
ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ
በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች የላቀ አገልግሎት
*************
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሜጋ ከተማ ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ድሬ ወረዳ ሜጋ ከተማ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞያሌ፣ ነገሌ ቦረና ተከታትለዋል።
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጤና ሳይንሰ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ በህክምና ዶክትሬት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን ከአዳማ ህክምና ኮሌጅ፣ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዓለም አቀፍ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር (Global Health Supply Chain Management) ከኪንቲ ስቴት እና ኢንፓዎር ስኩል ኦፍ ኸልዝ ከሱዊዘርላንድ እንዲሁም በዓለም አቀፍየህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ከፍተኛ ሰርተፊኬት ከዋሽንግተንዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል።
ሙያዊ ጉዟቸውን የጀመሩት በቦረና አርብቶ አደር አካባቢ ሲሆን በቂ መሠረተ ልማት በሌላቸው አከባቢዎች በበጎ ፍቃደኝነት ለማገልገል ራሳቸውን በፈላጎት አሬሮ ወረዳ መደብ። የአሬሮ ወረዳ በሙያቸው፣ በጤና ጣቢያ ኃላፊ፣ የድሬ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት እና የቦረና ዞን ጤና መምሪያን ጨምሮ በባለሙያነትና በኃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡በአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመምህርነት፣ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በመሆንም ሰርተዋል። በክልሉም የተለያዩ አሰራሮችን በኪልንካል እና በጥራት የሰሩ።
በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት አዳዲስ ሃሳቦች በማመንጨትና በመተግበር አርአያ መሆን የቻሉ ናቸው፡፡ ከ5 የሚበልጡ ጥናታዊ ጽሁፎችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል። ቀጥተኛ የጤና ተቋማትን የመድኃኒት አቅርቦት ከ30 በመቶ ወደ 69 በመቶ በማስፋት፣ ለአመታዊ ቆጠራ እስከ 45 ቀናት መጋዘኖች ተዘግተው ተገልጋዮች ይጉላሉበት የነበረውን አሰራር በመቀየር በአማካኝ ከ5 ቀናት በታች እንዲሆን የሰሩ።
ተቋሙ ከሀገር ውስጥ አልፎ በአካባቢያችን ካሉ አቻ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል በተበጣጠሰ መልኩ ሲተገበር የነበሩ የቴክኖሎጂ ስርዓትን በማዘመን እና የተናበበ እንዲሆን ለማስቻል ዓለም የደረሰበት የመጨረሻውን የቴክኖሎጂ መፍትሄ ERP-SAP የተባለውን አሰራር ዘርፈ ብዙ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር እና በማቀናጀት ሥራ ላይ እንዲውል ሌት ተቀን የተጉ፣ በፖሊሲ ማሻሻያና ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የአቅራቢዎች ኮንፈረንስ የአገር ውስጥ አምራቾችን ሚና እንዲጠናከር አድርገዋል።
ለኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካል አገልግሎት አለም አቀፍ እውቅናን አምጥቷል። የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት ISO የጥራት ሰርተፍኬት እንዲያገኝ አድርገዋል፡፡በደረጃ ቀይ የነበረውን የከሰታም ኮምሸን ደረጃ በማሻሻለእ ለሶስት ተከታታይ አመታት የፕላቲኒየም ታማኝ ታክስ ከፋይነት ደረጃን በማግኘት እና እ.ኤ.አ በ2024 የአለም ጤና አቅርቦት ሰንሰለት ጉባኤ ላይ ከ39 ሀገራት ጋር በመወዳደር የታላቁን (Grand Prize) ሽልማት አሸንፈዋል።
እ.ኤ.አ. ከ2013 ጀምሮ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው እያገለገሉ የሚገኝ ሲሆን በርካታ የአስተዳደር ቦርዶች እና የብሔራዊ ፖሊሲ ቡድኖች አባል በመሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በጤናው ዘርፍ በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዎ ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡
Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB