Zeአራዳ

Zeአራዳ Melake:
Ethiopia's news & entertainment hub. Follow for updates! Bringing you the pulse of Ethiopia!

From breaking news to the hottest trends in entertainment, join our community and celebrate our rich culture.

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል...
09/22/2026

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!

በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም።

ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ገና በቅድስት ሐና ማሕጸን ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ ተአምራት ...
09/22/2026

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ገና በቅድስት ሐና ማሕጸን ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ ተአምራት ታደርግ ነበር፡፡ አንድ አይኗን ያጣች ቤርሳቤህ የተባለች ሴት የሀናን መጽነስ ስትሰማ በደስታ ልትጎበኛት መጣች፡፡ ቅድስት ሐናን እንኳን ደስ አለሽ ብላ ሆዷን ከዳሰሰቻት በኋላ በዚያው እጇ ዓይኗን ብትነካው ዐይኗ በርቶላታል፡፡ ይህን ምሳሌ አደርገው ድውያን እየመጡ ሆዷን ዳሰው ይፈወሱ ነበር፡፡ በመካንነት የነበሩት ወላጆቿ ልጅ ከሰጣቸው ለቤተ እግዚአብሔር ሊሰጡ ስዕለት ገብተው በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ፍሬ ሲያገኙ ዓለም ደግሞ የመድኃኒቱን እናት አጊኝቷል፡፡ እናታችን ቅድስት ሐና ጸንሳ ሳለች የአጓቷ ልጅ አርፎ እጅግ የአልጋውን ሸንኮር እየዞረች ስታለቅስ ከሞተበት ተነስቶ “የሰማይና የምድር ፈጣሪ አያት ሆይ ላንቺ ክብር ይገባሻል” ብሎ መስክሮ ተመልሶ አርፏል፡፡

አይሁድም “ቀድሞ የእነዚህ ዘር የነበሩ ዳዊትና ሰሎሞን አርባ፣ አርባ ዘመን ገዙን አሁን ከዚህች የሚወለድ ምን ሊያደርገን ነው?” ብለው በድንጋይ ሊወግሯት ተነሱ፡፡ የራማው ልዑል ቅዱሰ ገብርኤል ወደ ሊባኖስ ተራራ ወሰዳቸው፤ በእዚያም በጨለማ ውስጥ የነበረው ዓለም ብርሃን የሚያይባት፣ የእውነተኛው ጸሐይ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸው አስታውሰው በሦስት ዓመቷ ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሲሰጧትም ካህኑ ዘካርያስ ስለምግቧ ተጨንቆ፤ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ሊቀበል ሲቀርብ ወደ ላይ ራቀበት፡፡ በዚያ በተሰበሰቡትም ቢሞክሩ አልሆነም፡፡

ዘካርያስም ሐናን “እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ” አላት፤ በዚያም ጊዜ ቅድስት ማርያም እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት፤ በክብር ዐረገ፡፡ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም “የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር” ብለው ታህሣስ 3 ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡ ለ12 ዓመታትም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ይህችን ብርሃን፣ የብርሃን እናት ገዳማውያን አባቶችና እናቶች ዘወትር በጸሎታቸው ያስቧታል፡፡ ገዳማቸውን እናግዝ፣ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ...
09/22/2026

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል፡፡ ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው፡፡ በመዝሙር 33÷7 እደተጻፈው ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፡፡ እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል እንደተናገረው ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው፡፡ ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር መስከረም ዘጠኝ ቀን መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች፡፡ በቀድሞው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች፡፡

ይህች ከተማ በእምነታቸው ጠንካሮች የሆኑ ጥቂት ክርስቲያኖችና በርካታ ኢአማንያን ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት፡፡ በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ፍጹም የእምነት ሰው ነበር፡፡ በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረግ ስለነበር ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ “ዮናናውያን”ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ፡፡ በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ፡፡ በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ፡፡ በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር፡፡ ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ፡፡
ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ፡፡ በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በስተቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ሲወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው፡፡ ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ እንደሚሆን የተረዳው መጋቢ በታላቅ ድንግጤ ውስጥ ወደቀ፡፡ እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ በመላዕክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ምስለ ስዕል ፊት ወድቆ ተማጸነ፡፡ ታላቁ ወንዝ ቤተ ክርስቲያኑን ጠርጎ የሚወወስደው ከሆነም የሚሆነውን ነገር ለመቀበልና ከዚያም ላለመውጣትም ወሰነ፡፡ ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ፡፡ በዚህ ጊዜ የመላዕክት ሁሉ አለቃቸው ለጠራውም ፈጥኖ የሚደርሰው ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ፡፡

መጋቢውንም "ጽና አትፍራ፣ እኔ ካንተ ጋር ነኝና" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት፡፡ በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ፡፡ በአስፈሪ ሁኔታ ሲመጣ የነበረው ወንዝም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ፡፡ የሚገርመው ነገር የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሸለቆው የተፈጠረው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች መሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ግን ጸንቶ ቆመ፡፡ መጋቢውም እግዚአብሔርንና ቅዱስ ሚካኤልን አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ፡፡ በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው፣ መልአኩንም አከበሩት፣ አሕዛብ ግን አፈሩ፡፡

ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ገዳማውያንና ቅዱሳን ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ🙏በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል ...
09/21/2026

ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ🙏

በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም።

ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ ምእራፍ 7÷14 “እግዚአብሔር ምልክት ይሰጠናል ድንግ...
09/21/2026

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ ምእራፍ 7÷14 “እግዚአብሔር ምልክት ይሰጠናል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፡፡ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ እርሱም ድንቅ መካር ኃያል የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።” አለን፡፡ በመሆኑም እመቤታችን የአምላክ እናት የእግዚአብሔር እናት ትባላለች። በ325 ዓ.ም በጉባኤ ኒቂያ በነበረው የሲኖዶስ ውይይት ላይ በአደባባይ ተከራክረው ከሐዲያንን ካሳፈሩ 318 ሊቃውንት አንዱ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ የጌታችንን መለኮታዊ ባህርይ ለሚጠራጠሩ አርዮሳውያንና በተዋሕዶ ሰው ሆኖ መክበሩን ለሚክዱ የተዋሕዶን ምሥጢርና ቅድስት ድንግል ማርያም የመለኮት እናት ስለመሆኗ ሲያስተምር “ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውና አምላክ በተዋሕዶ የከበረ ነው አለ፡፡

በአምላክነቱ መለኮታዊ ባሕርይ ቢኖረውም እንደ ሰውነቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር ተፀንሶ በድንግልና ተወልዷል።ድንግል ማርያም ጌታን ከመፅነሷ በፊት በፀነሰች ጊዜ ከፀነሰችም በኋላ፤ እንዲሁም ከመውለዷ በፊት በወለደችም ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት። ይህንንም እግዚአብሔር ስለገለጸለት ከአበይት ነቢያት መካከል አንዱ ቅዱስ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 44÷1-4 “ወደ ምስራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ ይህ በርም ዝግ ነበር፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ለዘላለም ዝግ ሆኖ ይኖራል።” አለኝ ይላል፡፡

ምስራቅ ያላት ድንግል ማርያምን ነው ፀሐይ ከምስራቅ እንዲወጣ ጨለማውንም ዓለም ብርሃን እንዲያደርግ፤ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስም ከአማናዊት ምስራቅ ከድንግል ማርያም ተልወዶ በኅጢያት ለጨለመው ዓለም የጽድቅ ብርሃን ሆኖ ተገልጧልና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ 4÷4 እንደጻፈው የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ያለ ወንድ ዘር ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአምላክ እናት የተወለደውን አንድያ ልጁን ላከልን፣ እርሱም የእኛን ባህርይም ባህርይ አድርጎ ተወለደ። ልጆችም ስለሆንን እግዚአብሔር አባት ብለን የምንጠራበት የልጅነት መንፈስ ሰጠን፡፡ እመቤታችንም በሕቱም ድንግልና ይህን ጌታ ወለደችልን፡፡ ገዳማውያንም ይህችን እናት ዘወትር አማልጅን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማ...
09/21/2026

የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡

ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡

ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

መድኃኔአለም በሐጢዓት ፈተና ተጠልፎ ከመውደቅ ይጠብቀን🙏እግዚአብሔር እስራኤልን ከደመና መና አውርዶ፣ ከአለት ውሀ አፍልቆ መገባቸው፡፡እነርሱ ግን እዚህ ደጋ ላይ ቢሆንለት የውርጭ ሰደቃ እያበ...
09/20/2026

መድኃኔአለም በሐጢዓት ፈተና ተጠልፎ ከመውደቅ ይጠብቀን🙏

እግዚአብሔር እስራኤልን ከደመና መና አውርዶ፣ ከአለት ውሀ አፍልቆ መገባቸው፡፡

እነርሱ ግን እዚህ ደጋ ላይ ቢሆንለት የውርጭ ሰደቃ እያበጀ፣ ውሀውን እያረጋ፣ መና መገብኳችሁ ይላል እንጅ ቆላ ቢሆነማ ባልተቻለውም ነበር ብለዋል። የርሱን ከሃሊነት፣ የእነርሱንም ሀሰት ሊገልጥ ቢወድ፣ ሙሴን የውሃ ምንጭ የሌለበት በረሐ ይዘሀቸው ሂድ ብሎት በዚያም መናው ወርዶላቸዋል፣ ውሀውም ፈልቆላቸዋል። ነገር ግን ነዘር የሚባል እባብ እየነከሰ ይፈጃቸው ጀመር። በዚህ ጊዜ ከሙሴ ዘንድ ሂደው ከጌታ ምህረት ቸርነት ከእኛ ኃጢአት አይታጣም በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ተናግረን በድለናል እባቦችን እንዲያርቅልን ወደ እግዚአብሔር አመልክትልን አሉት።

ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ ከንጹህ ነሐስ የእባብ ምስል ሠርተህ ከሚገናኙበት አደባባይ ከእንጨት ላይ ስቀልላቸው አለው። እንደተባለው ቢያደርግ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የነሐሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። “ሙሴ እባብን በምድረ በዳ እንደሰቀለው የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ አለው” ተብሎ በዮሐንስ 3÷14 እንደተነገረ፡፡ አባቶቻችንም በትርጓሜ ወንጌል የበረሐው እባብ የዲያብሎስ፤ የብረቱ እባብ የጌታ ምሳሌ ነው። በእባብ መርዝ እንዳለበት በዲያብሎስም ፍዳ ኃጢአት አለበት።

በነሐሱ እባብ መርዝ እንደሌለበት በጌታም ፍዳ ኃጢአት የለበትም። የነሐሱ እባብ በእባብ አምሳል መሰቀሉ ጌታ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ለመሰቀሉ ምሳሌ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል።

ገዳማውያኑም በመስቀል የተደረገልንን ማዳን እያሰቡ ዓለምን ንቀው፣ ስጋቸውን ጎድተው ይከተሉታል፡፡ የጽድቃቸው አክሊል እርሱ መድኃኔ ዓለም የሚወደኝ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ እንዳለ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏 # ጼዴንያ ማርያም 🙏ጼዴንያ በምትባል ሀገር ሥጋ የለበሰች የምትመስልና ከሠሌዳዋ ቅባት ከሚንጠፈጠፍ ሥዕል አምላክን የወለደ...
09/20/2026

የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

# ጼዴንያ ማርያም 🙏

ጼዴንያ በምትባል ሀገር ሥጋ የለበሰች የምትመስልና ከሠሌዳዋ ቅባት ከሚንጠፈጠፍ ሥዕል አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ተአምር ተገለጠ፡፡ ይቺንም ሥዕል የሣላት ወንጌላዊ ሉቃስ ነው፡፡ በጼዴንያ አንዲት ስሟ ማርታ የሚባል መበለት ሴት ነበረችና ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገችና እመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያምንም እጅግ ትወዳት በሚቻላትም ሁሉ ታገለግላት ነበር፡፡ አንድ ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኲሴ በቤቷ በእንግድነት አደረ በመልካም አቀባበልም ተቀበለችው በማግሥቱም ስትሸኘው ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሔድ አወቀች፡፡ ስለዚህም ገንዘብ ሰጠችውና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ አለችው፡፡ እርሱም በራሴ ገንዘብ ገዝቼ አመጣልሻለሁ አላት፡፡ ኢየሩሳሌምም ደርሶ ከቅዱሳት መካናት ተባረከና ሥዕሏን ሳይገዛ ወደ ጐዳናው ተመለሰ፡፡

ያን ጊዜም ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰማ ወደ ገበያም ተመልሶ ላሕይዋና መልኳ ያማረና የተወደደ የሆነ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ገዛት በሐርና በንጹሕ ልብስም ጠቀለላት፡፡ በጐዳናውም እየተጓዘ ሳለ ከማያስፈራ ዱር ውስጥ ወንበዴዎች ተነሡበት ሊሸሽም ወደደ ከዚያቺም ሥዕል መንገድህን ሒድ የሚል ቃል ወጣ የተከተለውም ሳይኖር መንገዱን ተጓዘ፡፡ ሁለተኛም ነጥቆ ሊበላው አንበሳ ተነሣበት ያን ጊዜም ከዚያች ሥዕል የወጣ ድምጽ አንበሳውን አባረረው፡፡ አባ ቴዎድሮስም ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምር ባየ ጊዜ ያቺን ሥዕል ወደ ሀገሩ ሊወስዳት ስለፈለገ ለመበለቲቱ ሊሰጣት አልፈለገም፡፡ ከዚህም በኋላ በመርከብ ተሳፍሮ በሌላ አቅጣጫ ሲጓዝ ታላቅ ነፋስ ተነሥቶ ወደ ጼዴንያ ሀገር ወሰደው ከመርከብም ወርዶ ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ሔደ ማንነቱንም አልገለጣላትም እርሷም አላወቀችውም፡፡

በማግሥቱም ተሰውሮ ወጥቶ ወደ አገሩ ሊሔድ በፈለገ ጊዜ የቅጽሩ መውጫ ጠፍቶበት ሲዞር ዋለ በመሸ ጊዜም ወደ ማደሪያው ተመለሰ፡ ያቺም መበለት ታየው ነበር፡፡ እስከ ሦስት ቀን ይሕ ነገር እየተደጋገመ ቆየ፡፡ ያቺም መበለት ይዛው አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን ስትቅበዘበዝ አይሀለሁና አለችው፡፡ እርሱም በዚያች ሥዕል የሆነውን ተአምር ነገራትና ሥዕሏን ሰጣት፡፡ የተጠቀለለችበትን ልብስ ስትፈታም ከሥዕሊቱ ወዝ ሲንጠፈጠፍ አገኘች፡፡ ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የዚያን መነኲሴ እጆቹንና እግሮቹን ሳመች፡፡ ሥዕሏንም ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር አኖረቻት፡፡ ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮት ሠራችላት፤ በቀንና በሌሊትም የሚበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቅላ ከውጪ የሐር መጋረጃ ጋረደችላት፡፡ ከሥዕሊቱ እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች፡፡

ያም መነኰስ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችንን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ፡፡ የሀገሩም ሊቀ ጳጳሳት የዚያችን ሥዕል ዜና በሰማ ጊዜ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከካህናት ከሕዝቡም ሁሉ ጋር መጣ፡፡ በሠሌዳዋም ውስጥ በአዩዋት ጊዜ ሥጋ የለበሰች ሁና አገኙዋት ከዚህ አምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ ከዚያም ቅባት ቀድተው ለበረከት በተካፈሉ ጊዜ ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ ይመላል፡፡ ሥዕሊቱን ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜ ንውጽውጽታ ሁኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ፡፡ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ በዚያች አገር ትኖራለች፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎትና በረከቷ ከእኛ ጋራ ይኑር፡፡ ይህን ተአምሯን ያመኑ ገዳማውያን በጸሎቷ በረክትና ፍቅር ያገኛሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

09/19/2026

Brighton 3-0 Arsenal

Address

585 Essex Street
Lynn, MA
01901

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zeአራዳ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share