
03/30/2025
ብዓዴን ብልፅግናዬ ተነካብኝ አላቅሱኝ!!
--------//--------
በነገራችን ላይ ደሳለኝ ጣሰውና ደስዬ ደጀን ወንጀለኞች ናቸው። በተለይ ደስዬ ደጀን በመንግሥት የተሰጠውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው በክልሉ በተለይም ጎንደር ከተማ እና ባህርዳር ከተማ ላይ ሰው የሚያሳግቱት እነዚህ በመንግስት መዋቅር ስር የነበሩ ግለሰቦች ናቸው። ደስዬ ደጀን ብዙ ንፁሃንን ረሽኗል። አስረሽኗል። በተለይ ባህር ዳር። የደስዬ ደጀን ጠባቂዎች ዋነኛ አጋቾች ናቸው። ይህ በክልሉ የበላይ አመራሮች ስለተረጋገጠ ግለሰቦቹ በወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው።
የማህበራዊ ሚዲያ ጯሂዎቻቸው በወንጀሉ ሰንሰለት ውስጥ ያለ እና ተጠቃሚዎች ናቸው። ይህ ሰንሰለት በመረጃ፣በገንዘብና በልዪ ልዪ ጥቅማጥቅሞች የተበተቡ ሆነው ከውጪ እስከ ውስጥ የተዘረጉ ናቸው። አሁን የሚጮኸውም የክልሉ መንግስታዊ መረጃም፣ወንጀልም ገንዘብም ምንጫችን ደረቀ ከሚሉ የአማራ ህዝብ ተውሳኮች እንጂ ተቆርቋሪዎች አይደለም። እነዚህ ግለሰቦች (ጯሂዎች) ለአማራ ህዝብ ተቆርቁረው ቢሆን ኖሮ የአማራ ህዝብ የስርዓት ለውጥ ለማምጣት እየታገለ ባለበት ሰዓት ከብአዴን ብልፅግና ውስጥ ተሾመ ተሻረ የሚል ለቅሶ አስፈላጊ አልነበረም።