NEBIL NEBA

NEBIL NEBA ሰላም, ጤና, ፍቅር, ደስታ. ከናንተ ጋር ይሁን እያልን

09/08/2025

Celebrating my 2nd year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

07/25/2025

Tigistu Bekele: የራሻው መሪ ፑቲን ኔቶን አንበረከኩ

07/24/2025

TIGISTU BEKELE : RUSSIA CHINA ENA YE IRAN TEMERET YASEFERAT AMERICA

05/05/2025

Adrash hawala. Ethiopia black market. ሀዋላ። ብላክ ማርኬት።

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጂቡቲ ድንበር አቅራቢያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በደረሰ የድሮን ጥቃት ሰዎች ተገደሉ (መሠረት ሚዲያ)- ሐሙስ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ...
02/04/2025

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጂቡቲ ድንበር አቅራቢያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በደረሰ የድሮን ጥቃት ሰዎች ተገደሉ
(መሠረት ሚዲያ)- ሐሙስ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እና ጂቡቲ ድንበር አቅራቢያ በደረሰ የድሮን ጥቃት ሰዎች መሞታቸውን እና መቁሰላቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
ጥቃቱ መጀመሪያ በሁለት አርብቶ አደሮች ላይ የተፈፀመ ሲሆን አንዱ ሲሞት አንዱ መትረፉ ታውቋል። በተጨማሪም 2 ሴቶች እና 5 ወንዶች በሌላ ጥቃት መገደላቸውን የመረጃ ምንጫችን ገልጸዋል፡፡
በኤሌዳአር ወረዳ ሂሉ እና ቲኪቦ ቀበሌ ሲያሪ ጣቢያ ሟቾችን ወደ ቤተሰብ ይዘው ሲመጡ በድጋሜ ህዝብ በተሰበሰበበት ጥቃት ተፈጽሟል ተብሏል።
"ባለን መረጃ መሰረት ጥቃት የፈጸመው የጅቡቲ መንግስት እንደሆነ እናምናለን" ብለው ለመሠረት ሚድያ የተናገሩት የመረጃ ምንጫችን ከዚህ ቀደም በጣቢያው ያሉ አርብቶ አደሮችን ከቦታው ለማስለቀቅ የጅቡቲ ወታደሮች ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ተኩስ ይከፍቱ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡
ጥቃቱን ተከትሎ በአሜሪካ የሚኖሩ የአፋር ዲያስፖራ ማሕበር አባላት ባወጡት መግለጫ ድርጊቱን "ጨካኝ" በማለት አውግዘውታል።
የዲያስፖራ ማህበሩ ጥቃቱ የተፈጸመው በጂቡቲ መከላከያ ሀይል ድሮን መሆኑን ገልጾ በጥቃቱ ሲያሮ እና ኤሊዳር በተባሉ ቦታዎች 2 ወንድማማቾችን ጨምሮ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና 3 ሰዎች ደግሞ በከፋ ሁኔታ በጽኑ መቁሰላቸውን በመግለጽ ድርጊቱን አውግዞ የሰላማዊ ዜጎች ግድያ እንዲቆም በመጠየቅ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ማህበረሰብ፣ የሰብአዊ መብት ተሟቾችና መገናኛ ብዙሃን ትኩረት እንዲሰጡት ጠይቋል፡፡
በጉዳዩ ላይ በኢትጵያም ሆነ በጂቡቲ መንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡
የሰሜኑ ጦርነት በተቀሰቀሰበት ወቅት የሱዳን ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ መሬት ዘልቀው ገብተው ይገባኛል የሚነሳበትን መሬት መያዛቸው የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ ከደቡብ ሱዳን ዘልቀው የሚገቡ የሙርሌ ታጣዊዎችም ድንበር ጥሰው በመግባት በተደጋጋሚ ዝርፊያ እንደሚፈጽሙ ይታወቃል፡፡
የኤርትራ ጦርም ወደ ትግራይ ገብቶ ከፈጸመው ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ጥሰት በተጨማሪ ትንሽዋ አገር ጂቡቲም በኢትዮጵያ ምድር በሰላማዊ ዜገች ላይ የፈጸመችው ወታደራዊ ጥቃት አነጋጋሪ ሆኗል።
መረጃን ከመሠረት

የተመድ የስደተኞች ኤጂንሲ በ136 ሀገራት የሚያደርገውን ድጋፍ አቋረጠየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለውጭ ሀገራት የሚደረጉ ድጋፎች ለ90 ቀናት እንዲታገዱ መወሰናቸውን ተከትሎ የተባበ...
02/04/2025

የተመድ የስደተኞች ኤጂንሲ በ136 ሀገራት የሚያደርገውን ድጋፍ አቋረጠ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለውጭ ሀገራት የሚደረጉ ድጋፎች ለ90 ቀናት እንዲታገዱ መወሰናቸውን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የእርዳታ ኤጀንሲዎች ስራቸውን እያቋረጡ ነው፡፡
በ136 ሀገራት ከመኖሪያ ቤታቸው በአስገዳጅ ሁኔታዎች ለተፈናቀሉ 122 ሚሊዮን ሰዎች የህይወት አድን እርዳታ የሚያደረግው የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ ሃላፊ ፊሊፖ ግራንዲ የተለያዩ ወጪ ቅነሳዎች እንዲደረጉ በየአካባቢው ለሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ኢሜል ልከዋል።
ኤጀንሲው የአሜሪካ ድጋፍ ማቋረጥን ተከትሎ ከድንገተኛ ሁኔታዎች አቅርቦት በስተቀር ለ90 ቀናት አዲስ ድጋፎች እንዳይደረጉ፣ የቅጥር እና የኮንትራት ማቋረጥ እንዲሁም ሁሉም አለም አቀፍ የአውሮፕላን ጉዞዎች እንዲቆሙ አዟል፡፡
አዲሱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የእርዳታ ማቋረጡ በዋና መድኃኒቶች ላይ፣ የሕክምና አገልግሎት፣ ምግብ እና መሰረታዊ የዕርዳታ አቅርቦቶች ላይ ተጽዕኖ እንደማይኖረው ተናግረው ነበር፡፡

በትግራይ ክልል የፖለቲካ ኅይሎችን  ያወዛገበው አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመየትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት፣ ትላንት እሁድ በይፋ ተቋቁሞ ሥራ ጀመረ።"ምክር ቤቱ የተለያዩ ...
02/04/2025

በትግራይ ክልል የፖለቲካ ኅይሎችን ያወዛገበው አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት፣ ትላንት እሁድ በይፋ ተቋቁሞ ሥራ ጀመረ።
"ምክር ቤቱ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የተሳተፉበት፣ እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሥራዎች የሚከታተል ነው"፣ ሲሉ የክልሉ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ አቶ ሞገስ ታፈረ ዋና ሰብሳቢ፡ የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገበን ደግሞ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል።
በዚሁ ምክር ቤት የተጋበዙት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ የዲያስፖራ አባላት እና የጸጥታ አካላት አልተሳተፉም።

ሄዝቦላ ለሟቹ መሪው ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት የሚያደርግበትን ቀን ይፋ አደረገ።የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ መሪ የሟቹ መሪ ሀሰን ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት በየካቲት 23፣2025 እንደ...
02/04/2025

ሄዝቦላ ለሟቹ መሪው ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት የሚያደርግበትን ቀን ይፋ አደረገ።
የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ መሪ የሟቹ መሪ ሀሰን ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት በየካቲት 23፣2025 እንደሚፈጸም በትናንትናው እለት ይፋ አድርጓል።
የሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ በመሆን ለ30 አመታት ያገለገለው ነስረላህ የተገደለው እስራኤል ባላፈው በመስከረም ወር በፈጸመችው መጠነሰፊ የአየር ጥቃት ነበር የተገደለው። እስራኤል ግድያውን ከፈጸመች በኋላ የሊባኖስን ድንበር በሟቋረጥ በእግረኛ ጦር ዘመቻ መክፈቷ ይታወሳል።
በነስረላህ የተተካው መሪ ናይም ቃሲም በቴሌቪዥን ባስተላለፈው መልእክት ነስረላህ የተገደለው "በአስቸጋሪ ሁኔታ ወቅት" በመሆኑ በሀይማኖታዊ ስነስርአት መሰረት ቡድኑ ጊዜያዊ ቀብር ለማድረግ መገደዱን ተናግሯል።

02/03/2025

ሩሲያ እስራኤልን አስጠነቀቀች! ”ለዩክሬን ሚሳኤል አልሰጠሁም ” እስራኤል

02/03/2025

Tigistu bekele. ትግስቱ በቀለ። የቻይና የጦር መርክብ ወደ ታይዋን ደሴት! የትራምፕ የታሪፍ ዛቻ!

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ "እዚህ ካናዳ ውስጥ የተሰሩ ምርቶችን ለመምረጥ.. ጊዜው አሁን ነው።" በሚል ሕዝባቸው በካናዳ የተመረቱ ምርቶችን እንዲጠቀም ጠየቁ። በትራምፕ አስተዳ...
02/03/2025

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ "እዚህ ካናዳ ውስጥ የተሰሩ ምርቶችን ለመምረጥ.. ጊዜው አሁን ነው።" በሚል ሕዝባቸው በካናዳ የተመረቱ ምርቶችን እንዲጠቀም ጠየቁ። በትራምፕ አስተዳደር ወደ አሜሪካ በሚያስገቧቸው ምርቶች ላይ 25% ታሪፍ የተጫነባት ካናዳ ጠቅላይ ሚ/ር "በቻልንበት ቦታ ሁሉ ካናዳን እንምረጥ። [እቃ ስትገዙ] ሌብሎችን (መለያዎቹን) [በካናዳ የተመረቱ መሆናቸውን] ያረጋግጡ። ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የትሩዶ ጥሪ "የካናዳ ሕዝብ ከአሜሪካ የሚመጡ ምርቶችን ትቶ በሃገራቸው የተመረተው ላይ እንዲያተኩር የሚጠይቅ ነው፡"
ትሩዶ ለትራምፕ፡ "የእርስዎ የታሪፍ ጦርነት የአሜሪካን ፋብሪካዎች ይዘጋል።" ማለታቸው ይታወሳል።

የአንድ ስታዲየም ስፋት ያለው የጠፈር አለት ከሰማይ ወደ መሬት እየተምዘገዘገ ነው ተባለየአሜሪካ ጠፈር ሳይንስ ምርምር ማዕከል ወይም ናሳ እንደገለጸው ከሆነ አሜሪካ በዓለም ጦርነት ወቅት በጃ...
02/02/2025

የአንድ ስታዲየም ስፋት ያለው የጠፈር አለት ከሰማይ ወደ መሬት እየተምዘገዘገ ነው ተባለ

የአሜሪካ ጠፈር ሳይንስ ምርምር ማዕከል ወይም ናሳ እንደገለጸው ከሆነ አሜሪካ በዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ በመቶዎች እጥፍ ሀይል ያለው የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ወደ ምድር እየመጣ ነው ብሏል፡፡

የአንድ ስታዲየም ስፋት መጠን አለው የተባለው ይህ የጠፈር አለት በመጠኑ ባለፉት ስምንት ዓመታት ወደ ምድር ከመጡት ውስጥ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

አፍሪካ፣ ፓስፊክ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ ይህ ጠፈር አለት ያርፍበታል ተብሎ ከሚጠበቁ ቦታዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/42VUKor

Address

America
New York, NY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when NEBIL NEBA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share