አንዲት ኦርቶዶክስ ፩ ሲኖዶስ ፩ ፓትሪያርክ

አንዲት ኦርቶዶክስ ፩ ሲኖዶስ ፩ ፓትሪያርክ

ከዚህ ጽሁፍ ጋር ተያይዞ በቀረበው ምስል ላይ የምትመለከቷቸው 3 ልጆች   ናቸው። የሚኖሩት በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ፣ ሞጣ ከተማ ቀበሌ 05 ውስጥ ነው።  ...
07/28/2024

ከዚህ ጽሁፍ ጋር ተያይዞ በቀረበው ምስል ላይ የምትመለከቷቸው 3 ልጆች ናቸው። የሚኖሩት በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ፣ ሞጣ ከተማ ቀበሌ 05 ውስጥ ነው። በፎቶው ላይ ከልጆቿ ጋር ሆና የምትመለከቷት እናታቸው ናት። ባሏ ጥሏት ስለሄደ ልጆቿን ብቻዋን በማሳደግ ላይ ትገኛለች።

የእናታቸው ሙሉ ስም እትዬ ከቤ መንግስቱ የሚባል ሲሆን የልጆቹ ስም ደግሞ አየነው ተመቸ ቢራራ ፣ ፀጋነሽ ተመቸ ቢራራ እና ልብሞኝ ተመቸ ቢራራ ይባላሉ። አባታቸው 3ቱም ልጆች አይነስውር ሲሆኑበት ጊዜ ትቷቸው ከቤት ወጥቶ በመሄድ ሌላ ሴት አግብቶ ይኖራል። የጭካኔ ጥግ ይሉታል ይኸን ነው፣ ልጆቹ ግን በስሙ ይጠራሉ።

ይህች ምስኪን እናት ግን እነዚህን ልጆች ዘጠኝ ወር የተሸከመችበት አንጀት/ማህጸን አላስጨክን ብሏት በስቃይና በችግር አብራቸው ትኖራለች። የሚገርመው ነገር ብዙውን ጊዜ እናት ልጆቿን የትም ትታ ለመጥፋት ልቧ አይጨክንም። ትቼ ልጥፋ ብላ ብታስብ እንኳ ልጆቿን የሚረዳቸው ሰው ወይም አካል እንዲኖር አመቻችታ ነው።

እናታቸው ሀብት ቢኖረኝ ፣ በቂ ገቢ ባገኝ ኖሮ ልጆቼን የአካል ጉዳተኞች ሚማሩበት ትምህርት ቤት አስገብቼ እንዲማሩልኝ አደርግ ነበር ነገር ግን ድሃ ስለሆንሁ በአሁኑ ወቅት ልጆቼ እየተማሩ አይደለም ትላለች። እናም ይህችን እናት በመርዳት ችግሯን ማቃለልና ልጆቹም የሚማሩበትን ከተቻለም የህክምና እርዳታ አግኝተው ብርሀናቸው የሚመለስበትን ድጋፍ ብናደርግ በፈጣሪ ዘንድ ክብርንና ጽድቅን እናገኛለን።

በሌላ አነጋገር እነዚህን ልጆች የገንዘብ አቅም ያላችሁ ግለሰቦችና ድርጅቶች ብሎም ብሔራዊ የዐይነ ስውራን ማህበር አስፈላጊውን ትምህርትና እርዳታ እንዲያገኙ እንዲያደርጉላቸው እናት አጥብቃ ትማፀናለች። እነዚህ ልጆች እድሉን ካገኙ እንደማንኛውም የአካል ጉዳተኛ ልጅ ተምረው ለቁም ነገር ይበቃሉ። ሀገር የሚጠቅሙ ዜጎችም ይሆናሉ።

ገንዘብ መርዳት ለምትፈልጉ #የባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000593298039 (እትዬ ከቤ መንግሥቱ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
እናታቸውን አግኝቶ ለማነጋገርም ሆነ በማንኛውም መንገድ መደገፍ የሚፈልግ ሰው ወይም አካል በስልክ ቁጥር፦ 0960810503 መደወል ይችላል።

Address

New York, NY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አንዲት ኦርቶዶክስ ፩ ሲኖዶስ ፩ ፓትሪያርክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category