04/18/2026
የመምህራን ግለ-ማህደር (Teacher's personal Portfolio) ጥቅሞች!
1️⃣ የሙያ እድገትን ማሳየት
የመምህሩ የስራ እድገትና ብቃት እንዴት እንደተሻሻለ ያሳያል
CPD, ስልጠናዎችና የInduction ተሳትፎ ማስረጃ ይሆናል
2️⃣ የአፈጻጸም ግምገማን ማጠናከር
ለአመታዊ ግምገማ (Performance Appraisal) ጠንካራ ማስረጃ ይሰጣል
የትምህርት ቤት አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች መምህሩን ለግምገማ በቂ መረጃ ከማህደር ስለምያገኙ ግምገማውን ቀላል እና ቀልጣፋ ያደርጋል
3️⃣ የትምህርት ጥራትን ማሻሻል
የትምህርት እቅዶች (Lesson Plans) እና የተግባር ሪፖርቶች በመመዝገብ ሙሉ መረጃ በማሰባጠር ይይዛል
የተማሪዎች ውጤትን ለመከታተል ያግዛል
4️⃣ ሙያዊ ተጠያቂነትን ማጠናከር
መምህሩ ሥራውን በሥርዓት እንዲያከናውን ያበረታታል
የተሰጠ ሥራና ውጤት ግልጽ ይሆናል
5️⃣ ለሽልማትና ለሹመት መሠረት መሆን
ለደረጃ ዕድገት
ለምርጥ መምህር ሽልማት መመርጫ መሠረት ይሆናል
6️⃣ ለክትትልና ሱፐርቪዥን መሳሪያ
የትምህርት ቤት ክትትልን ውጤታማ ያደርጋል
የተጠየቁ ሰነዶች በአንድ ቦታ ይገኛሉ
7️⃣ ራስን ግምገማና ማሻሻያ
መምህሩ ድክመቱንና ጥንካሬውን እንዲለይ ያግዛል
የቀጣይ እቅድ ለማዘጋጀት መሠረት ይሆናል።
የመምህራን ማህደር (Teacher's Portfolio) በተለምዶ የመምህሩን ሙያዊ መረጃ፣ የሥራ አፈጻጸምና የእድገት ማስረጃዎችን ይይዛል።
የመምህራን ማህደር በውስጡ ምን ምን ያካትታል ?
ከዚህ በታች በክፍል ተከፍሎ የሚካተቱ ነገሮች ተዘርዝረዋል፦
1️⃣ የግል መረጃና የሙያ መግለጫ
ሙሉ ስም
የትምህርት ደረጃና ሙያ
የተመደበበት ትምህርት ቤት
የስራ ልምድ
የሙያ እሴቶችና ዓላማ (Professional Statement)
2️⃣ የትምህርት ሰነዶች
የዓመት ዕቅድ (Annual Plan)
የክፍል ዕቅድ (Scheme of Work)
የትምህርት እቅድ (Lesson Plans)
የትምህርት መርሀግብሮች
የተጠቃሚ የመማሪያ መሳሪያዎች
3️⃣ የግምገማና የተማሪ ውጤት
የተማሪዎች ውጤት መዝገብ
ፈተናዎችና የጥያቄ ወረቀቶች
የግምገማ መሳሪያዎች (Rubrics, Checklists)
የውጤት ትንታኔ (Analysis)
4️⃣ የCPD እና Induction ሰነዶች
የInduction ፕሮግራም ሪፖርት
የCPD እቅድና ሪፖርት
የስልጠና ማስረጃ (Certificates)
የWorkshop / Seminar ተሳትፎ ማስረጃ
5️⃣ የክትትልና ሱፐርቪዥን
የክፍል ክትትል (Classroom Observation) ሪፖርቶች
የሱፐርቫይዘር ግብረመልስ
የማሻሻያ እቅዶች (Action Plans)
6️⃣ የአፈጻጸም ግምገማ
የዓመታዊ የሥራ ግምገማ ፎርም
የራስ ግምገማ (Self-Assessment)
የተመዝገቡ ስኬቶች
7️⃣ ተጨማሪ ሙያዊ ተሳትፎ
የክለብ እና የተጨማሪ ኃላፊነቶች
የማህበረሰብ ተሳትፎ
የተለያዩ ሽልማቶችና ማስረጃዎች
8️⃣ ሪፍሌክሽን (Reflection)
የዕለት/ወር/ዓመት ሪፍሌክሽን
ተማሪ አፈጻጸም ላይ ያለ ግምገማ
የሚቀጥለው የማሻሻያ እቅድ