Eyasu Demeke

Eyasu Demeke እንኳን ደህና መጡ!
ማንኛውንም ሀሳብ በFacebook Boost አናደርጋለን!

"ቦዮ ሐይቅ" የሀዲያ ዞን ተፈጥሯዊ ገጸ በረከት...የሀዲያ ዞን ተፈጥሯዊ ገጸ በረከት የሆነውን "ቦዮ ሐይቅ" የማልማት ሥራ ትኩረት እንደሚያስፈልገው ተመላክቷል።20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች...
11/17/2025

"ቦዮ ሐይቅ" የሀዲያ ዞን ተፈጥሯዊ ገጸ በረከት...

የሀዲያ ዞን ተፈጥሯዊ ገጸ በረከት የሆነውን "ቦዮ ሐይቅ" የማልማት ሥራ ትኩረት እንደሚያስፈልገው ተመላክቷል።

20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ለማስተናገድ የተዘጋጀው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለበዓሉ ያደረገውን ዝግጅት የሚዲያ ባለሙያዎች ምልከታ እያደረጉ ነው።

ጉብኝቱ በክልሉ የሚገኙ የቱሩዝም መደረሻ ሥፍራዎችን ያካተተ ሲሆን ÷ በሀዲያ ዞን የሚገኘው ቦዮ ሐይቅም ምልከታ ከተካሄደባቸው የተፈጥሮ መስህቦች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

ከአዲስ አበባ በ230 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ቦዮ ሐይቅ ከሆሳዕና ከተማ በስተምስራቅ አቅጣጫ 54 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከቦኖሻ ከተማ ደግሞ በ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

የቦዮ ሐይቅ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ በቆላማውና ለጥ ባለ ሜዳማው ሻሾጎ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን÷ በዞኑ ከሚገኙ ሐይቆች በስፋት ትልቁ ነው፤ በክረምት ወራት እስከ 6 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ይሸፍናል።

በጥልቀቱ እስከ 8 ሜትር እንደሚደርስ የሚገመተው ሐይቁ÷ ከስልጤ፣ ከምባታና ዙሪያው ከሚገኙ ወረዳዎች የሚነሱ ትልልቅ ገባር ወንዞች አሉት፡፡

ሐይቁ በውስጡ ባለው ደለል ምክንያት ጭቃማ ቢሆንም ከፍተኛ የሆነ የዓሣ ምርት ከመያዙ በተጨማሪ ለቱሪዝም ተመራጭ የሚያደርጉትን የዱር እንስሳትና አዕዋፋት በዙሪያው ይዟል። በተለይም የተለያዩ ሀገር በቀልና ስደተኛ አዕዋፋት ለሐይቁ ድምቀትና ውበት አጎናጽፈውታል፡፡

የሻሾጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ግርማ ሎቤ÷ ይህ የተፈጥሮ መስህብ ተገቢ ትኩረት አግኝቶ የጥበቃና የልማት ሥራ ከተሰራለት አካባቢው በቀላሉ ሊለማ የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል።

ከልጅነት እስከ ዕውቀት "ከቦዮ ሐይቅ" የተዛመዱ የአካባቢው ነዋሪዎች ሐይቁ ለምቶና ጎብኚ ሲጎርፍበት ማየት የሁል ጊዜ ሕልማቸው መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

አካባቢው ቢለማ እንደ ሌሎች የኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት ማየት እንደሚቻል አስረድተዋል።

የመሰረተ ልማት እና ተደራሽነት፣ የሐይቁ ጥብቅና የአካባቢ አስተዳደር፣ የቱሪዝም ምርቶች ልማት እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተጨምሮ አካባቢውን የተሻለ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራ የመሆን ዕድልን እንደሚሰጠው አመልክተዋል።

በሰለሞን በየነ

11/15/2025
05/16/2025
ሆሳዕና፡ የካቲት 29/2017 ዓ.ም የሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራምእሁድ የካቲት 30/2017 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በሀዲያ ባህል አዳራሽ ይካሄዳል።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ...
03/08/2025

ሆሳዕና፡ የካቲት 29/2017 ዓ.ም
የሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም
እሁድ የካቲት 30/2017 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በሀዲያ ባህል አዳራሽ ይካሄዳል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ/ርዕሰ መዲና የሆነችውን ሆሳዕና ከተማ ኑ..!! በጋራ እናልማ !!

👉በዕለቱ ካልደረሱም ድጋፍ ማድረጊያ የባንክ ቁጥሮች የሚከተሉት ናቸው ፦

የንግድ ባንክ አካውንት - 1000671934389

የብርሃን ባንክ አካውንት - 1130100337647

ዳሽን ባንክ አካውንት - 5051537473011

ህብረት ባንክ አካውንት - 5131914994890081

ንብ ባንክ አካውንት - 7000100344357

አቢሲንያ ባንክ አካውንት - 219537287

ኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከፍተኛ እምነት አ...
03/08/2025

ኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች

1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤

2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር

3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከፍተኛ እምነት አለመጣል፤

4. የጓደኝነት ጥያቄን በአካል ከምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንቀበል፤

5. ሁልጊዜ ስለምንለጥፈው ነገር በጥንቃቄ ደጋግሞ ማንበብ

6. በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ላይ የግላዊነት(privacy 🔏) መጠበቂያዎችን መጠቀም፤

7. ሁሉም ሰው በኦንላይን እሱ እንደሆነ የሚነግረን ሁሉ እውነት አድርጎ አለመቀበል፤

8. ተገቢ ያልሆነ ይዘትን ሲያጋጥመን ወዲያውኑ ሪፖርት እናድርግ፤

9. ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰባችን ጋር ስንመለከታቸው ምቾት የሚሰጡንን ምስሎች ብቻ ማጋራት፤

10. የይለፍ ቃላችንን በፍጹም ከማጋራት መቆጠብ፤

ዩኒቨርሲቲዎች ነፃ ምሁራዊ ውይይት የሚካሄድባቸው የሀገር የሀሳብና የእውቀት መሪ ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ አሳሰቡ።                ------------------------...
03/07/2025

ዩኒቨርሲቲዎች ነፃ ምሁራዊ ውይይት የሚካሄድባቸው የሀገር የሀሳብና የእውቀት መሪ ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ አሳሰቡ።
-----------------------------------------
(የካቲት 28/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ አመራሮችና ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች ተልዕኳቸውን በሚገባ እንዲወጡ ከመንደር አስተሳሰብና ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በነፃነት እውነተኛ ምሁራዊ ውይይት የሚደረግባቸው የዚች ሀገር እውቀት መሪ ሊሆኑ ይገባል፤ ወደዛ እንዲሄዱም እንፈልጋለን ያሉ ሲሆን፤

ዩኒቨርሲቲዎች ትክክልና ስህተትን የሚለዩ ጥሩ ሥነ-ምግባር የተላበሱ ምሩቃንን የሚያፈሩ እንዲሁም ሙስናን የሚቃወሙና የሚከላከሉ ሊሆኑም እንደሚገባም አሳስበዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ሪሶርስ በአግባቡ ለመጠቀም የቅድሚያ ትኩረት ጉዳዮችን ለይተው በመስራት ችግሮችን ደረጃ በደረጃ መፍታት ይጠበቅባቸዋል ፤

በዚህም አዲሱ አመራር የትምህርት ጥራት የሚያረጋግጡ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይኖርበታልም ብለዋል።

በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ(ዶ/ር) በተቋሙ የታዩ ጠንካራና መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች ለውይይት መነሻ ያቀረቡ ሲሆን የዩኒቨርስቲው አዲስ አመራሮች ተቋሙን ካለበት ችግር ለማውጣት ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው አብራርተዋል።

የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ታደሰ ረጋሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው ተቋሙን ለመለወጥ ከሁሉም አመራርና በለድርሻ ጋር በመግባባት ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልፀዋል።

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላትም የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የአመራር ለውጥ ከተደረገላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

02/25/2025

ምርጡ በቀል ራስህን ቀይረህ ማሳየትህ ነው!

ብዙዎች አሁን ያለህበትን ሁኔታ እያዩ ይሳለቁብሀል።ብዙዎች የራሳቸውን ደካማ መንፈስ አንተ ላይ ለመዝራት ይጣጣራሉ።ብዙዎች ያንተን መለወጥ ሞትን እንደመጋፈጥ እንደሆነ ይነግሩሀል።ነገር ግን አንድ ማስታወስ ያለብህ ነገር ይህ ሌላኛው የለውጥ መሠሰናክል ነው።የነሱ ደካማ አስተሳሰብና የአልችልም መንፈሳቸው አንተ ላይ እንደማይሰራ አሳያቸው። ማመን እስከሚያቅታቸው እራስህን ቀይረህ መቀየርን አስተምራቸው።

02/20/2025

Address

Paris, VA

Opening Hours

Monday 9am - 5pm
Tuesday 9am - 5pm
Wednesday 9am - 5pm
Thursday 9am - 5pm
Friday 9am - 5pm
Saturday 9am - 5pm

Telephone

+251939697902

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eyasu Demeke posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share