Journalist Abdlwehab Bilall

Journalist Abdlwehab Bilall Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Journalist Abdlwehab Bilall, Media/News Company, Philadelphia, PA.
(2)

በዚህ አመት በሚዲያዎች የተወሰዱ እርምጃዎች 1 ሁለት የሮይተርስ ጋዜጠኞች ፈቃድ ታገደ2 ሁለት የDW ጋዜጠኞች ፈቃድታገደ3 የዋዜማ ሬዲዮ ፈቃድ ተሰረዘ4 የአዲስ ስታንዳርድ ፈቃድ ተሰረዘ5 ጄ...
08/07/2026

በዚህ አመት በሚዲያዎች የተወሰዱ እርምጃዎች
1 ሁለት የሮይተርስ ጋዜጠኞች ፈቃድ ታገደ
2 ሁለት የDW ጋዜጠኞች ፈቃድታገደ
3 የዋዜማ ሬዲዮ ፈቃድ ተሰረዘ
4 የአዲስ ስታንዳርድ ፈቃድ ተሰረዘ
5 ጄ Fm ለ6 ወራት ከአየር እንዲወርድ ታገደ
6 ለአርትስ tv የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ
7 ለአሀዱ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

ሁለት ወንዶች የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መስረተው  በመገኘታቸው በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባምባሲ ከተማ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ !    ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለ...
08/07/2026

ሁለት ወንዶች የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መስረተው በመገኘታቸው በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባምባሲ ከተማ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ !

ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ።

ባምባሲ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም| ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባንቢስ ከተማበፎቶ የተመላከቱት እኒሁ ታደለ እናውጋውና በፀሎት እንየው የተባሉ ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በመመስረታቸው...

በማህበረሰቡ ጥቆማና ተጠርጣሪዎቹም የእምነት ቃላቸውን በሰጡት መሰረት ፖሊስ ተገቢውን የምርመራ ስራ መጀመሩንና በቀጣይ ውጤቱን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን' ሲል የባንቢስ ከተማ አስተዳደር ገልጿል።

አደገኛ የጦርነት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ህወሃት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሜካናይዝድ ጦሩን ወደ ራያ ግንባር እያጓጓዘ እንደሆነ እንዲሁም በአማራ ክልል እና አፋር ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች  ም...
08/07/2026

አደገኛ የጦርነት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል
ህወሃት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሜካናይዝድ ጦሩን ወደ ራያ ግንባር እያጓጓዘ እንደሆነ እንዲሁም በአማራ ክልል እና አፋር ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች ምሽጎችን እየቆፈረ እንደሚገኝ DW ዘግቧል ። በድንበር አከባቢዎች ላይ ያለው ውጥረት ከምንግዜውም በላይ ማየሉን ዘገባው ያመላክታል ።

ይህ መቃሚያ ቤት አይምሰላችሁ መስሪያ ቤት ነው😎
08/06/2026

ይህ መቃሚያ ቤት አይምሰላችሁ መስሪያ ቤት ነው😎

አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ከEBS ተባረረ ፤ የእሁዱን በEBS አቅራቢ የነበረው ዳንኤል ተገኝ ፤ በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ስም በተፈፀመ መጠነ ሰፊ ማጭበርበር ተጠርጥሮ ታስሮ የነበረው ዳንኤል ተ...
08/06/2026

አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ከEBS ተባረረ ፤ የእሁዱን በEBS አቅራቢ የነበረው ዳንኤል ተገኝ ፤ በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ስም በተፈፀመ መጠነ ሰፊ ማጭበርበር ተጠርጥሮ ታስሮ የነበረው ዳንኤል ተገኝ ፤ በዚህ ምክንያት ከEBS ቴሌቪዥን ጣቢያ የተባረረ ሲሆን ጣቢያ በዳንኤል ቦታ ሌላ ሰው ለመቅጠር እያፈላለገ ይገኛል ።

በአዲስ አበባ ባለቤትነት ላይ ተወሰነ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ 250 ስልታዊ ቡድን አዲስ አበባ የፌዴራል ከተማ ሆና እንድትቀጥል መስማማቱን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል ።
08/06/2026

በአዲስ አበባ ባለቤትነት ላይ ተወሰነ
በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ 250 ስልታዊ ቡድን አዲስ አበባ የፌዴራል ከተማ ሆና እንድትቀጥል መስማማቱን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል ።

ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ አሜሪካ ውስጥ መጥፋቱ ተገለፀ ። ዮናስ ከበደ ለስራ ወደ አሜሪካ በሄደበት አጋጣሚ ነው የጠፋው ።
08/06/2026

ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ አሜሪካ ውስጥ መጥፋቱ ተገለፀ ። ዮናስ ከበደ ለስራ ወደ አሜሪካ በሄደበት አጋጣሚ ነው የጠፋው ።

ይህ ፎቶ ሌሎች ሰዎች ሰርተው የለቀቁት መስሎኝ ነበር ሳረጋግጥ ጀዌ በራሱ በተረጋገጠ ገፁ ያጋራው ነው የትነው በሰላም መኖር የምችለው? ይላል ከፎቶው አብሮ የፃፈው ፁሁፍ ። ምን ትላላችሁ እ...
08/06/2026

ይህ ፎቶ ሌሎች ሰዎች ሰርተው የለቀቁት መስሎኝ ነበር ሳረጋግጥ ጀዌ በራሱ በተረጋገጠ ገፁ ያጋራው ነው የትነው በሰላም መኖር የምችለው? ይላል ከፎቶው አብሮ የፃፈው ፁሁፍ ። ምን ትላላችሁ እናነተ የት በሰላም ይኑር ?

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያለው ውጥረት ማደግ አሳሳቢ መሆኑን የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን አስታወቀ፤ ዘላቂ ሰላም እንዲወርድ ጥሪ አቀርቧል  የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን  በኢት...
08/05/2026

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያለው ውጥረት ማደግ አሳሳቢ መሆኑን የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን አስታወቀ፤ ዘላቂ ሰላም እንዲወርድ ጥሪ አቀርቧል

የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ህወሓት) መካከል በቅርቡ እያደገ የመጣው ፖለቲካዊ እና የደህንነት ውጥረት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገለጿል ።

ተቋሙ ማክሰኞ ነሐሴ 4 ቀን 2026 ዓ.ም በወጣው ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫው፣ ሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ ትዕግሥት በማድረግ ወደ አዲስ የጦርነት ግጭት ከማምራት እንዲቆጠቡና የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገብሩ ጥሪ አቅርቧል።

ተቋሙ ከአካባቢው እና ከዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን የተገኙ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ እንደገለጸው፣ በአዲስ አበባ እና በመቀሌ መካከል ያለው ግንኙነት ባለፉት ሳምንታት ውስጥ እየተበላሸ መጥቷል።

ይህንንም ተከተሎ በሁለቱም በኩል የሚታየው የወታደራዊ ኃይል እንቅስቃሴ እና ቅስቀሳ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን አቅራቢያ የሚገኙ የድንበር አካባቢዎችን ጨምሮ እንደገና የታጠቀ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም የተቀሰቀሰው እና ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በተፈረመው የፕሪቶሪያ የዘላቂ ሰላም እና የተኩስ ማቆም ስምምነት አማካኝነት በይፋ የተጠናቀቀው አስከፊ ጦርነት፣ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ ይታወሳል።

የዚያ የትግራይ ክልል አውዳሚ ጦርነት በርካታ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈ፣ ሚሊዮኖችን ከመኖሪያ ቀያቸው ያፈናቀለ፣ መሰረተ ልማቶችን ያደቀቀ እና በአፍሪካ ቀንድ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አስከፊ ሰብዓዊ ውድመት ያስከተለ እንደነበር መግለጫው አስታውቋል ።

የፕሪቶሪያው ስምምነት ኢትዮጵያ ጠብን አቁማ፣ የእርስ በእርስ እምነትን መልሳ በመገንባት ወደ ሀገራዊ እርቅ እና ዘላቂ ሰላም የምታደርገውን ጉዞ እንድትጀምር ታሪካዊ እድል ፈጥሮ የነበረ መሆኑን ያመላከተው የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን፤ ሆኖም በስምምነቱ አፈጻጸም ላይ የተፈጠሩ አለመግባባቶች አሁን ላለው ስጋት ምክንያት መሆናቸውን ጠቁሟል።

በተለይም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና በህወሓት መካከል ያለው ውጥረት እንዲሁም በመቀሌ እና በአዲስ አበባ መካከል እያደገ የመጣው አለመተማመን ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡትን ጉልህ የሰላም ውጤቶች አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑ ተገልጻል።

ለፖለቲካዊ አለመግባባቶች በጭራሽ ወታደራዊ መፍትሔ ሊኖር እንደማይችል ጽኑ እምነታችን ነው ያለው የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን መግለጫ፤ ወደ የታጠቀ ግጭት መመለስ በከፍተኛ ጥረት የተገኘውን ሰላም ወደኋላ የሚመልስ፣ የሕዝቡን ሰብዓዊ እንግልት የሚያበዛ፣ የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን የሚያጋጭ እንዲሁም የኢትዮጵያን ሀገራዊ የማገገም፣ የኢኮኖሚ እድገት እና የዲሞክራሲያዊ ሽግግር ጥረቶች የሚያደናቅፍ መሆኑን አስገንዝቧል።

መግለጫው አክሎ እንደገለጸው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት፣ ፍትህ እና ዘላቂ ልማት ይገባዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና ህወሓት ከፍተኛ የሆደ ሰፊነት እና የትዕግሥት እርምጃዎችን እንዲወስዱ፣ ሁኔታዎችን ሊያባብሱ የሚችሉ ማናቸውንም ድርጊቶች እንዲያቆሙ እና ለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ ትግበራ ዳግም ቁርጠኝነታቸውን እንዲያረጋግጡ አሳስቧል።

በተጨማሪም ተቋሙ "ዓለም አቀፍ ሰላም 2030 የተሰኘውን የሰላም ጥረት መነሻ በማድረግ፣ ሁለቱም ወገኖች ልዩነቶቻቸውን ሰላማዊ፣ አሳታፊ እና ግንቢ በሆነ ውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል።

በማንኛውም ሁኔታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም፣ ደህንነት እና ደህንነቱ የተጠበቀ ህይወት ከማንኛውም ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ስሌቶች በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን አጥብቆ አሳስቧል።

አሜሪካ ሄደው ይጠፋሉ ‼️አትሌቶቹ የቀሩበት ትክክለኛ ምክኒያት ታወቀ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶቹ እንዳይሄዱ ያደረገው አሜሪካ ሄደው ሊጠፉ ይችላሉ በሚል ስጋት  ለአሜሪካ ኤምባሲ...
08/05/2026

አሜሪካ ሄደው ይጠፋሉ ‼️
አትሌቶቹ የቀሩበት ትክክለኛ ምክኒያት ታወቀ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶቹ እንዳይሄዱ ያደረገው አሜሪካ ሄደው ሊጠፉ ይችላሉ በሚል ስጋት ለአሜሪካ ኤምባሲ ማስያዝ የነበረበትን 10 ሺህ $ ዶላር ባለየማስያዙ እንደሆኑ ከውስጥ ምንጮች አረጋግጠናል ።

በአፍሪካ ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 400 ሜትር ሴቶች ወርቅ ያመጣችው አጃይባ አሊዬን ጨምሮ ሌሎች ለውድድሩ ብቁ የሆኑ አትሌቶች በዚህ ምክንያት ሳይሄዱ ቀርተዋል ።
በጣም አስገራሚ ደግሞ የቡድኑ ሀኪምም ከቡዱኑ ጋር አልሄዱም ፤ በአትሌቶቹ ጉዳት ቢደርስ የሚያክማቸው የለም ።

የፌዴሬሽኑ የኮሚኒኬሽን ባለሞያዎች ሳይቀር ሳይሄዱ ቀርተዋል ። የፌዴሬሽኑ ሃላፊዎች ተሰባስበው ጥቂት አትሌቶችን ይዘው አሜሪካ ገብተዋል ።

ከሀገር ክብር ይልቅ ለገንዘብ ቅድሚያ በተሰጠበት በዚህ ህደት ፤ ቡድኑ ለውድድሩ ብቁ የሆኑ 7 አትሌቶችን ቀንሶ በጥቂት ቦታዎች ይወዳደራል ።

ፌዴሬሽኑ ለመንግሥት ሚዲያዎች ሳይቀር በይፋ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፍቃዳኛ ሳይሆን ቀርቷል ።

Address

Philadelphia, PA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Journalist Abdlwehab Bilall posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share