MSS Entertainment

MSS Entertainment Motivational and Entertaining Video Creator

የነፃነት ወርቅነህ ባለቤት ለምን ተሸፋፈነች? ዳዊት ልጁ በታመመ ጊዜ በእጅጉ አዝኖ ነበር፡፡እጅግም ታምሞ ነበር፡፡ ዳዊትም ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ዳዊትም ጾመ፣ ገብቶም በመሬት ላይ...
01/24/2026

የነፃነት ወርቅነህ ባለቤት ለምን ተሸፋፈነች?

ዳዊት ልጁ በታመመ ጊዜ በእጅጉ አዝኖ ነበር፡፡እጅግም ታምሞ ነበር፡፡ ዳዊትም ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ዳዊትም ጾመ፣ ገብቶም በመሬት ላይ ተኛ፡፡ ለሰባት ቀናትም እንጀራ አልበላም በሰባተኛውም ቀን ሕፃኑ ሞተ የዳዊትም ባሪያዎች ሕፃኑ በሕይወት ሳለ ብንነግረው አልሰማንም፤ ይልቁንስ ሕፃኑ እንደሞተ ብንነግረው እንዴት ይሆን ?» በነፍሱ ክፉ ያደርጋል ብለው ሕፃኑ እንደሞተ ይነግሩት ዘንድ ፈሩ፡፡ በመጨረሻም ነገሩት ዳዊትም ከምድር ተነሥቶ ታጠበ፣ ተቀባም፣ ልብሱንም ለወጠ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ፡፡ ወደ ቤቱም መጣ፣ እንጀራ አምጡልኝ አለ፤ በፊቱም አቀረቡለት፣ በላም፡፡

የምንወደው ሰው በሞት ከእኛ ሲለይ በእጅጉ እናዝናለን፤ እናለቅሳለንም፡፡
ትክክል ነው፣ በሐዘን ውስጥ ዝምታ አለ ከተባለ የቃላት ቅንብር ከማውጣት ይልቅ የብስለት ምልክት የሚሆንበት ጊዜ አለ!!! እውነት ነው፣ ዝምታ ብዙ ሃሳብን ከመግለጽ ይልቅ የስሜት ጠንካራነትን የሚያሳይበት ጊዜ አለ!!!

ኢዮብ በአንድ ቀን ዐሥር ልጆቹ ሞተውበታል፤ በዚያው ቀንም ሊቆጠር የማይችል ሀብትና ንብረቱን አጥቷል፤ እርሱ ግን «እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሣ» አለ እንጂ አላማረረም፤ ሐዘኑንም በቅጡና በሥርዓቱ ተወጥቶታል፡፡

በጣም ትክክል! ዝምታ ሁልጊዜ የሃሳብ ማጣት ሳይሆን፣ ይልቁንም የጥልቀት እና የትዕግስት መግለጫ የሚሆንባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ። ዝምታ የብስለት ምልክት የሚሆንባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች፦

1. ራስን መግዛትን ያሳያል፦ በንዴት ወይም በስሜታዊነት ጊዜ ከመናገር ተቆጥቦ ዝምታን መምረጥ ትልቅ የስሜት ጥንካሬን (Emotional Intelligence) ይጠይቃል።
2. ለማስተዋል እድል ይሰጣል፦ ብዙ ከመናገር ይልቅ ዝም ብሎ ማዳመጥ ሁኔታዎችን በሰከነ መንፈስ ለመረዳት ይረዳል።
3. ከማያስፈልግ ንትርክ ያድናል፦ አንዳንድ ጊዜ ለሁሉም ነገር ምላሽ አለመስጠት አላስፈላጊ ግጭቶችን በሰላም ለማለፍ ምርጡ መንገድ ነው።
4. የቃላት ክብርን ይጠብቃል፦ ብዙ የማይናገር ሰው የሚናገራቸው ጥቂት ቃላት በሰዎች ዘንድ የበለጠ ክብደትና ትኩረት ያገኛሉ።

ዝምታ አንዳንድ ጊዜ ከሺህ ቃላት በላይ መልዕክት ያስተላልፋል!

«ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈረስ፣ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘለዓለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንፃ እንዳለን እናውቃለንና፡፡

ነፍስ ይማር

ሮማሪዮ ሪከርድስ

ትልቅ ይቅርታ ለወንድሜ ማስተር አብነትውዱ ወንድሜ ማስተር አብነት የሽኝት ቦታው ላይ ባልገኝም ለተሻለ ህክምና ወደ ውጭ መሄድ እንደነበረብህ ተነጋግረን ነበር ጊዜው ደርሶ በመሄድህ ደስተኛ ነ...
01/20/2026

ትልቅ ይቅርታ ለወንድሜ ማስተር አብነት
ውዱ ወንድሜ ማስተር አብነት የሽኝት ቦታው ላይ ባልገኝም ለተሻለ ህክምና ወደ ውጭ መሄድ እንደነበረብህ ተነጋግረን ነበር ጊዜው ደርሶ በመሄድህ ደስተኛ ነኝ። ህክምናህን በስኬት ጨርሰህ በሀይል የምትገለጥበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። በድጋሚ እኔም የህክምና ባለሙያ ሁኜ በስራ መብዛት ምክንያት የሽኝት ቦታው ላይ ባለመገኘቴ ይቅርታን እየጠየኩ ህክምናህ አልቆ ስትመለስ ኤርፓርት ድረስ በመምጣት በደስታ እንደምቀበልህ ቃል እገባለሁ። እግዚአብሄር ከአንተ ጋር ይሁን

ዶክተር አብይ ታደሰ

https://www.youtube.com/live/Iy4EwhzKU-g?si=OBZRqyyJ7a_gT3-5
04/16/2025

https://www.youtube.com/live/Iy4EwhzKU-g?si=OBZRqyyJ7a_gT3-5

ውድ የአርጂና ስፖርት የዩቲዩብ ቤተሰቦቻችን፣ የአርጂና ስፖርት ዩቲዩብ ቻናልን Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! #አርጂናስፖርት #ሪያልማድሪድ #...

      መቅድም...ይህ የኔ እይታ ነው። እኔ ሶሻል ክሪትክ ነኝ። ማንንም አልምርም! ይህ ደግሞ አደባባይ ላይ የተሰጣ ጉዳይ ስለሆነ ከስድስት ዓመታት በኃላ ሰይፉን የማየት አጋጣሚ በዚያው ...
08/02/2024





መቅድም...

ይህ የኔ እይታ ነው። እኔ ሶሻል ክሪትክ ነኝ። ማንንም አልምርም! ይህ ደግሞ አደባባይ ላይ የተሰጣ ጉዳይ ስለሆነ ከስድስት ዓመታት በኃላ ሰይፉን የማየት አጋጣሚ በዚያው አገኘው። እንኳን ደስ ያለህ ሰይፍሻ! አርጅና አይቶሃል...እናም ንስሐ ገብቷል ምናምን እያልክ አጉል ካባ አትደርብለት...እንዲህ ዓይነት ነገር እኔ ጋር አይሰራም!
ያየሁትን፣የተሰማኝን እተቻለው፣ ሳድንቅም ልክ የለኝም!

እስክ ትንሽ ዘርዘር ላርግልህ...

~የቃለ መጠይቁ ዓላማ:

ዓላማው ግልፅ ነበር። በነሱ ቤት ማስተባበያ መስራታቸው ነው! ዳሩ ግን የበለጠ ክፍተት፣ ስህተት፣ ትምክህት ፣ግብዝነት፣ማን አለብኝነት፣ ሴቶችን መናቅ፣ አሁን ታውቅያለውና እኔ ነኝ ልክ " የሚል አላዋቂነቱን ያሳየበት ቃለመጠይቅ ሆኖ ነው ያገኘሁት! ጀምሮ እስኪ ጨርስ ድረስ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚል ነገር ግን ምንም ሃይማኖቱ የሚጠይቀውን ትህትናና መሰበረን ያላሳየ አስመሳይ-ቲሸርት ብቻ የሆነ ሰው ነው😭

~ሰይፉ ፋንታሁንና እከ:

ሰይፉ የ40 ዓመት ጓደኛው ነው። ካለመታወቅ እስከ መታወቅ አብረው ተጉዘዋል። ድሮ ከብስራተ ድምፅ ራዲዮ ጊዜ ጀምሮ! ታዲያ የጥንት ታሪክ የሚጋሩ ጓደኛሞች ናቸው! ሰይፉ፣ከአርባዎቹ ሽማግሌዎች አንዱ መሆኑ አይገርምም!ለዚህያም ይህን ቃለ መጠይቅ ያዘጋጀለት...እኔ አንተ ይባሉልሃል ደግሞ...እንኳን ይኼን ቀጣዩዋን የሄኖክ ድንቁን እጩኛ እናውቃለን እኛ😂

~ሰይፉ ብቻውን :

ለሁሉም "አርቲስት" ነፍስ አባት ነኝ ይላል ሰይፉ። እናም ይህን ነፍስ አባትነቱን ተጠቅሞ ንብረትን ጉዱን ሊሸፋፍንለት ጥሯል። አበላሽቶበታል ሳያውቀው!
አንድ ሁለቱን ላንሳ...

~ጥያቄዎቹ

ሰይፍሻ...ሲጀምር እንዲ ይላል...
" ሃና ጋር ደውዬ ነበር። ሳራ ጋር!"
አከ ይቀበለውና...ሃና የምትባል አለች ደግሞ ይላል ልክ ድንገቴ አድርጐ! አባዬ ይህኮ ላይቭ አይደለም፣40X የተቆረጠ ቪዲዮ ነው፣ክሽፈት 2

ሰይፉ ይቀጥላል:-" እንዴት ነው ያለ ትዳር 3 ልጆች አይከብድም?"
ንብረት ገላው:- "እንደ እኛ የህይወት Experience፣ ከተለያዩ ሴቶች ጋር እንደ መሄዴ መጠን ልጅ ቀርቶ በሽታ ቢሆንስ😢 የለሁም ነበር🙈 እሞት ነበር!🙄የእግዚአብሄር ቸርነቱ ነው ልጅ ያደረገው!"

ይህ ነውር ነው😭 ነውር 102!

እንዲሁም
~ የሁሉም የሙያ አጋሮቹ ልምድ:

ኸረ ጐበዝ ይህ ምን ማለት ነው? ሁሉም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንደኔ ሂያጅ ናቸው? ይባላል? የተዋንያን ህይወት experience ከተለያዩ ሰዎች ጋር መውጣት ነው እንዴ? ይህ ጭልጥ ያለ ስም ማጥፋት ነው...

ሰይፉ ጋር ሳልመለስ ከዚህ ጋር የተያየዘ አንድ ነጥብ ላንሳ...

~ዜማዊ ነኝ።

ትርጉሙን ለማታውቁ...ያገኘሁትን እከካለው ማለት ነው። የፈለጋቹት መዝገበ ቃላት ላይ እዩ! አሁን ይኼን የሚነገርን እኛ ንስሐ አባቱ ነን? ይህ ነገርስ በኩራት የሚነገር ነው? ድንገት ተሳስቶ ዘማሪ ያለ መስሎት ነው?/ ብቻ እከ ዜማዊ ነው። ከዚህ በሽታውም ንስሐ ገብቶ እንደ ነፃ ነግሮናል...ይህ አሪፍ ነገር ነው! መሐሪው ፈጣሪ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም የebs ሰይፉ፣ዩትዩብ ተመልካች ገመናህን ያይልሃል እንጂ አሸፍንልህም !

የሰይፉ ሌላኛው ጥያቄ ጋር እንለፍ
~ ዲፋመሽን :

"በዚህ በተፈጠረው ግርግር ስሜ ፣ዝናዬ ጠፍቷል ብለህ ታስባለህ?

አከ ይመልሳል በኩራት...

"በፍጹም! እንዲሁም በዚህ ጊዜ የሚሸሸኝ ደጋፊ ሲጀመር ፌክ ነው''

እኔ ግን እላለው....እጅግ በጣም ነው ህዝብን የናቀው! በድርጊቱ ሳይሆን በግብዝ ንግግሩ ! ዜማዊ ወዳጅ እንደሚያፈራ ግን ጥርጥር የለኝም!

~የሴት ልጅ ክብር:

ሰውዬው፣ ንብረት ገላው...ከላይ እንደነገርኳቹ ብሔራዊ ቴሌቪዥን የመጣው ስሙን ለማደስ ነው! ይሁን እንጂ የልጆቼ እናት ለሚላት ሴት ምንም ክብር እንደሌለው ነው በተደጋጋሚ ያረጋገጠው!
" አንድም ቀን ምሳ በልተን አናውቅም"
'' ለስሜት ብቻ ነው የምተኛት"
" አንድም ፎቶ ካሳየኸኝ እቀጣለው"
" አሁን መለወጤን አይታ ነው"
"ገንዘብ ነው እንደዚህ የሚያደርጋት"
" የመሳላትን መርጣ እንደኔ በቁርባን ታግባ"
" በኔ ድጐሞ ነው የምትኖረው"

ይህ የተግተለተለ ስድብና ንቀት እንጂ ሌላ አይደለም! ንስሐ የገባ ሰው፣ ከሃጢያት የነፃ ፣ስጋ ወደሙ የተቀበለ እንዲህ ነው የሚለው?

~የልጆቹ ነገር:

ብዙ ክብር የሚነኩ ነገሮችን ብሏል። እጅግ ያሰደነገጠኝ ግን " ሚስቴ አለችላቹ፣አይዟቹ" ያለው ነገር😭ኸረ እፈር! ሴትዮዋ ጥሩ ሰው ልትሆን ትችላለች ሙሽሪት...ግና መቼም ደሃ እናታቸውን አታክልም! ገና ለገና ጨላ ያላት ጋር ተጠጋና...የገዛ ልጆቹን በአደባባይ በዚህ ልክ ማሳጣት የጤና ነው? አልመሰለኝም😢

ካፌ ምናምን ወስጄ ፣ፎቶ ተነስተን ያለው ደግሞ ዝቅታ ነው! ከ10 ዓመት በላይ አባት ከሆነ ሰው አይጠበቅም! ዝም ማለትኮ ይቻላል!

ልጆች ያደጉ ጊዜ ምን ይሉኛልኮ ይባላል...

~የሶሻል ሚዲያ:

እከደከ ከማንም በላይ አበጀ በሶሻል ሚዲያ ሚስቱ ( የልጆቹ እናት) ምስጢሩም ስላወጣችበት ተንገብግቧል። መጥፎ ፕላትፎርም ነው ሁላ ብሏል።
ታጋይ ሃና ዮሐንስ ጐጂዬ የሽምግልና ቪዲዮውን ስለለቀቀችበት ግን አመስግኗል ፣አድንቋታል😢

~አለባበሱ:

ዊዝ ኦል ዱ ሪስፔክት ምንድነው የለበሰው? የጫጉላ ሽርሽሩን ጥምቀተ ባህር ነው እንዴ ያደረገው? የባህል ልብስ አድናቂ ነኝ! ይህን ግን ምህርተአብ ማንቅያው ደወል ጋር ወይም ዮኒ መልካም ወጣት ጋር ሲሄድ ቢለብሰው ቅር አይለኝም ነበር😢

ኢት ድድንት ጄስት ፊት ዚ ስቴጅ! ( በርግጥ ሞቲቩን እረዳለው) ነገር ግን ከመተቸት ወደኃላ አልልም!

~41ኦቹ ሽማግሌዎች:

ሰይፉም ነበረበት!

በነገራቹ ላይ ሀገር ፍቅር ቴአትር ጠይቁልኝ መልዕክት ለዚያ ሁሉ ሽማግሌ ሲያስተላልፍ የተቀዳው ቪዲዮ ከሰርጉ ቀድሞ ወጥቷል! አሁን ላይ ደርሶ ሰርጌ ስለጮኸ ነው ምናምን ማለት...ዋቴ ነው ይላሉ የኛ ሰፈር፣የለሚ ኩራ ልጆች!
ባለሃብት፣ ጋዜጠኛ ፣ አርቲስት ሆነው ግብዳ ስም የያዙ ሰዎች ናቸውና ለክብራቸው ሲሉ የልጆችን ጉዳይ አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው! ከ3 ሽማግሌ 40 ግን የደረሰው መች ነው?/ አይ "የኢትዮጵያዊነት ባህል" በየሳምንቱ ይቀየራል መቼስ....

~በመጨረሻም....

አንጋፋው ተዋናይ ንብረት ገላው.....ዝም ቢል ይሻለው ነበር ከሚሉ ወገኖች አይደለሁም! እውነቱን ህዝብ ማወቅ አለበት....አንዴ አደባባይ ተሰጥቷልና!
ሌላው አንዲት ልጅ አሜሪካ እንድትወስደው ጠይቋት እምቢ ያለችበትን ምክንያት ባውቅ ደስ ይለኝ ነበር😂😢

"በኩረ ሰባኪያን መምህር ምህረተአብ አሰፋ ተቆጥቶት ፣የሚደረገውን አድርገህ፣ የሚከፈል ገንዘብ ከፍለህ...." ይህችን ሴት አፏን አስዘጋው ብሎኛል ሲል...ትን አለኝ 🙄

አበስኩ ገበርኩ🙏

ሳራ ግን ምህረተአብ ጋር ስደውል እንደማያውቅ ነው የሆነብኝ ብላለች....

የሷን ሳይድ ስቶሪ ይዤላቹ እመለሳለው አይሻልም?

የትም እንዳትሄዱ...

ሳልሄድ በፊት...

ንብረት ገላው " የአብርሃም እና የሳራ" ጋብቻ ይሁንልህ እንዳልልህ....ሳራን አትወዳትም 😂 ለስሜትህ ብቻ ነበር የምትፈልጋት....አስራምናምን ዓመት🙈😭

ግን ደግሞ ምንታን እንደ አንድ የምትቆጠረው ግን አንተ የሙሴ ዘመን ሰው ነህ?

⚡የዛሬ ሁለት ዓመት የተፃፈ

04/26/2024

አረቄና ኮሚክ

     ክፍል 3"ሂጅ ከዚህ!" እነዚህ ሁለት ቃላት ብቻ እማማ ሎላሼን የጨው ሃውልት ለማድረግ በቂ ነበሩ። ልክ ቀልባቸው ሲመለስ፣መጮህ ጀመሩ! "እርዱን! እርዱን! ልጄን እየገደለው ነው!" ...
11/22/2023



ክፍል 3

"ሂጅ ከዚህ!"
እነዚህ ሁለት ቃላት ብቻ እማማ ሎላሼን የጨው ሃውልት ለማድረግ በቂ ነበሩ።
ልክ ቀልባቸው ሲመለስ፣መጮህ ጀመሩ! "እርዱን! እርዱን! ልጄን እየገደለው ነው!"
ወዲያው፣የአስናቀች ኩባንያ ዋርድያዎች መጥተው ከበቧቸው።
"ምን ተፈጠረ፣እማማ ሎላሼ?" አለ የዋርድያዎች አለቃ ወይዘሮዋን በማስታወሱ ሄዶ እየከለላቸው።

"ቶማስዬ! እስኪ ይኼን ደቃቃ ሰው አንዴ እየው!" አሉ እማማ ሎላሼ ታምሩ ላይ እየጮኹ። ልክ የኾነ ነገር ለማድረግ ሲዘጋጁ፣ አንድ ድምፅ ከኋላቸው ተሰማ!

"ምን የምታደርጉ ይመስላችኋል?"
እጅግ አስደማሚ ውበት ያላት ፣የለበሰችው ረጅሙ ወርቃማ ቀሚስ የቅዱስ ሚካኤል እህት አስመስሏታል። በባዲ ጋርዶቿ መታጀቧ ደሞ ለፀብ ሳይሆን ልንግስ የወጣች አማላክትን እንድትወክል አድርጓታል። ከንፈሯውን የተቀባችው ቀይ ሊፕስትክ ከንፈሯን ጉረሱኝ ጉረሱኝ ያስብላል። የሰውነት ቅርጿ ከአሊባባ በሚገዙ ቁሳቁሶች ያልተሰራ መኾኑን ያሳብቃል። እያንዳንዷን እንቅስቃሴዎቿን እየተከተሉ ከሰማይ ወፎች ይዘምሩላታል፣የሚያዩዋት ወንዶች ልብ ተሰቅሎ አልወርድ ይላል። ሳር ቅጠሉ ካልሰግንልሽ ይላል። ከብልፅግና ገበታ ለሀገር ሪዞርቶችና ፓርኮች የበለጠ ውብ አማላይ ናት። ባዲ ጋርዶች ዓይናቸውን ተክለው መንቀል ተስኗቸዋል ።
"አቶ ታምሩ ደህና ኖት?

ሴትዮዋ ያን ሁሉ ያፈጠጠባትን ወፈ ሰማይ ዓይኖችን ንቃቸው ቀጥታ ወደ ታምሩ አመራች።
"ማን ልበል ?" አለ ታምሩ ግራ ገብቶት። ማን እንደሆነች ለማጣራት አተኩሮ እያያት። ንዴቱን አቀዝቅዞታል።
"ስላገኘሁክ ደስ ብሎኛል፣ ጫልቱ ጴጥሮስ እባላለው። አቶ ቶንቦሌ ነው የላከኝ። አለች ያን እንደ ታላቁ ሩጫ ሯጮች ግጥም ያለውን በረዶ ጥርስ እየበረገደችለት።
" ጫልቱ ጴጥሮስ? " የዱንጉዛ ቤተሰብ ወራሽ?

"የፈጣሪ ያለ?!" ምን ልታደርግ መጣች?"

ጫልቱ ጴጥሮስ እጅግ ዝነኛ ሰው ናት።ከተማው በሙሉ የሚያውቃት። ቆንጆ ፣ተፅእና ፈጣሪና ብልጣብልጥ ነገር ናት።ገና በ22 ዓመቷ የዱንጉዛ ኮባንያን በእጇ አስገብታለች።የራሷን ግዙፍ ድርጅት ለማቋቋም አምስት ዓመት ብቻ ነው የፈጀባት።

"አሃ ፣አንቺ ነሻ።" ታምሩ...ራሱን ነቀነቀ።
ስለ ጫልቱ ከዚህ በፊት ሰምቷል። ከአቶ ቶንቦሌ ጋር ግኑኝነት እንዳላቸው ግን አያውቅም ነበር።

"አቶ ታምሩ ፣እባክዎን መኪና ውስጥ ይጠብቁኝ።ይኼን ጉዳይ እኔ አበርደዋለው"
ብላ ጣቶቿን አንቋቋቻቸው። እሷን ተከትለው ባዲ ጋርዶቿው ወደፊት ተጠጉ። የድርጅቱ ዋርድያዎች ወደኃላ አፈገፈጉ።

"ከርስዎ በኃላ፣አቶ ታምሩ" ብላ ማንም ሱሪ የታጠቀ እጁን ሊያነሳ እንዳልሞከረ ስታይ ጫልቱ ፈገግ እያለች ታምሩን ወደ መኪናው መራችው። ምንም ሳይተነፍስ ፣ታምሩ የተሰባበሩ ከአዞ ጥርስ የተሰሩ ፣የተሰባበሩ ሃብሎችን ከመሬት ሰብስቦ ጫልቱን ተከትላት። የሚያቆመው እኔ ነኝ ያለ ሰው ጠፋ።
"ምንድነው ችግሩ? እንዴ? እንዲሁ በነፃ በቃ ለቀቃቹት ማለት ነው?" አያሉ ጮኹ፣እማማ ሎላሼ እየሆነ ያለውን ነገር በጥሞና ካስተዋሉ በኃላ።
አሁንም አንድም ሰው ጫልቱ ላይ ጣት ጠቋሚ እንኳን ጠፋ!

የባሰ እርስ በርስ ተያይተው ላለማውራት ሁላ አፋቸውን ያዙ-ዋርድያዎቹ።
"ምን ተፈጠረ?"
አሉ ሳራና ስናፍቅሽ ግርግሩን አይተው።
"ሳርዬ፣መጣሽልን! እሴይ! እይው እስኪ ወንድምሽ እንዴት እንደተቀጠቀጠ" አሉ እማማ ሎላሼ ልጃቸውን ሲያዩ ማልቀስ ጀምረው። ልክ እርሳቸው እንደተደበደቡ ለማስመስል እየቃጣቸው።

"ምን ተፈጠረ? ማነው ይኼን ያደረገው?" አለች ሳራ አስፓልት ላይ የተገለበጠ የተረኞች ሪቮ የመሰለውን የወንድሟን ቁስል እያየች። ስሜቷም ተረበሸ።

"ያ ታምሩ ነዋ!" አሉ እማማ ሎላሼ ፣እንባቸው እየፈሰሰ።
"አሁን እዚሁ አገኘነው። ጳውሎስዬ ለእምነቱ ያደረው ልጄ ፣እሱ መሬት ላይ የጣለውን አንገት ሃብል አንስቶ ሊሰጠው ሲል ወንድምሽን ሌባ፣ከኔ ሰርቀህ ነው ብሎት እንደ አሰላው የአህያ ጭንቅላት ቅጥቅጥ አደረገው ። በጐ ለሰራ ይኼ ነው ምላሹ?"
አሉ የበለጠ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እያለቀሱ።

"ታምሩ" አለች ሳራ በንቀት።
ለሦስት ዓመታት ያህል በዘለቀው ትዳራቸው ማንነቱን ጠንቅቃ ታውቃለች። እንዲሁ ያለ ምክንያት ቱግ የማይል፣እንደብልፅግናው መንግሥት ህገ ለማስከበር የማይቸኩል፣ ነገሮችን በሰከነ አእምሮ የሚመለከት የተረጋጋ ሰው ነው። ያለ ምክንያት ከሜዳ ተነስቶ የሰው ልጅ ላይ እጁን አያነሳም።
"እስኪ ወንድምሽን ተመልከችው።የሚታየው እውነት አይበቃሽም? ካላመንሽን፣ እነዚህን ዘበኞች ጠይቅያቸው።ሁሉንም የኾነውን አይተዋል።" አሉ እማማ ሎላሼ ዋርድያዎችን በዓይናቸው እየቃኙ።
"እትዬ ሳራ፣እናትዎ ልክ ናቸው" አለ የዋርድያዎቹ ሃለቃ ሃላፊነቱን በሚገባ እያስተዋለ።
"ያለውን ሰማሽ? እኔኮ በባዶ ሰው አልወነጅልም። እንዲሁም እሱ አሁን ሌላ ሴት ሁሉ ይዟል"

ይኼን ስትሰማ ሳራ የበለጠ አዘነች።የእውነት ታምሩ እንዲህ አይነት ነገር አደረገ?ምን አልባት ስለ ፍቺው ተቆጥቶ በወንድሜ በኩል እየተበቀለኝ ይኾናል። ይህ እውነት ከኾነ፣አልተረዳሁትም ማለት ነው። አለች ለራሷ።

በሁነታዎች መሃል...."እየመጡ ነው፣ እየመጡ ነው..."የሚለው የአረጋኻኝ ወራሽ አዲሱ ዜማ ስፍራውን ያዘ።

ይቀጥላል

©ኢንጆይ ሪድንግ
© Tarekegn S Hadero

🖊 ኾላ

>                                              /አርጅና ሲንየር /⚽ክልልነት "የፈጠረው" ክልል:                     ከጄኖሳይዱ በፊት:          ...
11/21/2023



>



/አርጅና ሲንየር /

⚽ክልልነት "የፈጠረው" ክልል:

ከጄኖሳይዱ በፊት:

እኛ ብሔርብሄረሰቦች እና ህዝቦች በአንድ ክንድ ሆነን፣ ድህነት ላይ የዘመትን መኾናችን ይታወቃል። ለምዕራባዊያን አንጃ ግራንጃ ፕሮፖጋንዳ የማይሸበር፣ የተገመደ ህዝብ ነው እየፈጠርን ያለነው! በእንጨትና በድንጋይ ለሚያምነው ህዝብ ሃይማኖትን፣ መዝናኛ ለሌለው -ኳስን ፣ለኋላ ቀሩ ህዝብ-እምነት ጥበብና ስልጣኔን፣ ዳንኪራ ለሚወደው ዜማን-ዘፈንን፣ የማርያም ፅላትን፣ ዘጠኙን ቅዱሳን ፣ ግዕዝን፣ አማርኛን፣ የአክሱም ሃውልትን፣ አል ነጃሺን፣ ያበረከትን ኩሩ ህዝቦች ነን! ቅዱስ ያሬድንና ሚሚ ስብሐቱንም ለዓለም አበርክተናል! ይኽ ዓለም ዋንጫ በዚህ የተነሳ በጣም ታሪካዊ እና ለወደቁ ሰምዓታት ማስታወሻ ነው!

ይህ የመላው የብሔር ብሔረሰባችን ድል ነው❗ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ከጄኖሳይዱ በኃላ :

ፋሽስቱ የአብይ ሰራዊትና አውሬው የኤርትራ ሰራዊትን ከአማራ ተስፋፊ ሃይሎች በጋራ የጋረጡብንን ዘር የማጥፋት አደጋ ድባቅ በመታንበት ማግስት የሚደረግ ታሪካዊ ዓለም ዋንጫ ነው!

ድል ለTDF!
ትግራይ የወራሪዎች መቀበርያ ትሆናለች!
ሞት ለመሸረፍት!
ትግራይ ትስዕር!
💛❤

ከስምምነቱ በኃላ:

የፌዴራል መንግሥቱ ከቅዥት ወጥቶ ፣እንደ ሰው ማሰብ የጀመረበት ወቅትና ህዝባችን ማለት የኳሱ ተመልካች ቢራ መጠጥ ምናምን እንደ ካታር ሳንከለክል በስፋት የሚያገኝበት ታሪካዊ ያለም ዋንጫ ነው!

ምሽግ ቆፋሪው የኤርትራ ሰራዊት፣ ይህ ዓለም ዋንጫ ሳያልቅ ብን ብሎ መጥፋት ይጠበቅበታል!

ህገመንግስቱ ይከበር!

⚽ተረኛው ክልል :

በጦር ሜዳና በየስንዴው ማሳ ያደረግነውን ድል ይህን ዓለም ዋንጫ በማዘጋጀት ለዓለም አሳይተናል። ብዙ እኛን አንገት ለማስደፋት የሚጥሩ ምዕራባውያን እኛ ኩሩ ህዝብ አንድነት ያለን መሆናችንን አይተዋል።

ፓርክ ፣መዝናናኛ መናፈሻ ምናምን መገንባት በለመድነው ልምድ መሰረት ይኽን ዓለም ዋንጫ በሚደንቅ ፍጥነት እና ጥራት አዘጋጅተናል። ይኽም በቆራጡ መሪያችን አቅጣጫ መሰረት የሆነ ነው!

ሀገራችን በብልፅግና ጐዳና ላይ መሆኗም በዚህ ተመልክቷል !
ብርቅዬዎቹን ቀነኒሳን፣ ደራርቱን ፣ኮሜዲያን አብይ አህመድን ለዓለም አበርክተናል!
ኃይሌ ገብረስላሴ ፣አይ እሱ እንኳን አሁን ብሔር ቀይሯል!
ብቻ

🇺🇸
የሰሜኑን ድል በምስራቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ እንደግማለን!
የተገኘውን ዜጋ በድሮን በሞርታር እንቆላለን!
ከዚያ በፓርላማ መግባት አልቻልንም እንላለን!

ሺህ ዓመት ንገስ አባቢያ!

⚽የተከዳው ክልል:

እኛ ኢትዮጵያዊያን ዓለም ኳስን ሳታውቅ ያወቅን ፣ ዓለምን ታኬታ (የኳስ ጫማ) ያለበስን፣ ብራዚል እና እንግሊዝ ኳስ ወልደን አሳድግናል እያሉ የሚደሰኩርት ፣እኛ እዚህ ጢስ አባይ ፕሪሚየር ሊግ አዘጋጅተን መጫወት ከጀምርን ከ2000 ዓመት በኃላ ነው! ያው መፅሐፈ ሄኖክን ፣ ብዙ የብራና ቅርሶችን በሰረቁት መንገድ ነው የኳስ ጥበባችንን የሰረቁት !

ይኸው አሁን አስመልሰናል። ዓለም በታሪኳ አይታ የማታውቀውን ዓለም ዋንጫ አዘጋጅተናል። ይኼ ብሔር ፣ክልል ቅብርጥሴ ብለን ሳንከፋፈል " አንድ ህዝብ ፣አንድ ኢትዮጵያ " እንደግመዋለን፣ " አንድ ህዝብ ፣አንድ ኢትዮጵያ! "ብለን ከፍታችንን ከሰማይ ላይ በቀዳነው ቀለም ደምቀን አስውበናል (💚💛❤)

ለዓለም ይኽን ባንዲራ ከማርያም መቀነት ላይ ወስድን አስተዋውቀናል!
የመጀመሪያው ዓለም ዋንጫ የተዘጋጀው እዚህ በጌምድር ነው!
ይኽም አዳም ጐዣሜ መሆኑን ለዓለም ያሳየ ሃቅ ነው!

ቅዱስ ላሊበላንም፣ ቅዱስ ዳንኤል ክብረት የኛው ናቸው!

ትልቅ ነበርን፣ ትልቅም እንሆናለን!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

⚽ደቡብ:

የፊፋው ፕሬዚዳንት ጃን ኢንፋንትኖ ደቡብ ክልል የሚለውን ለመስማት ጆሮውን አቆመ።

ያለም ዋንጫው አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀመንበር ጉራጌው ርስቱ ይርዳው ወደ ፖዲየሙ ሲጠጋ፣ አንድ የዲቻ አባል የተቃውሞ ድምፅ አሰማ:
" እኛ ወላይታዎች ደቡብ ክልል አይደለንም" ...የመክፈቻ ስነ ስርዓቱን LIVE የሚከታተለው ያለም ህዝብ ደነገጠ።
አብዛኞቹ የደቡብ ክልል ዞኖች የየራሳቸውን መክፈቻ እንዳዘጋጁ ተናገሩ።
እንደሚከተለው አቀረቡ!

⚽የዲቻ ክልል:

እኛ የካዎ ጦና ልጆች ነን! ከኢትዮጵያ በታሪክ እንበልጣለን እንጂ አናንስም! ለሰሜኑ ኢትዮጵያ የኳስን ጥበብ ያሳየን እኛ ነን። የጦና ንቦቹ፣ የቦዲቲ ከነማ፣ በዳሞት ስልጣኔ ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮኑ ዳሞት ጋሌ ፉትቦል ክለብ ነበር! ሰሜኑ ታሪክ የመቀየር ፣የመቀማት፣ ማንነት የመለወጥ አባዜው ዛሬም አልለቀቀውም!

ሃኮ!
እኛ ማለት ሳንቾ ገብሬን ለታላቁ ማንችስተር ዩናይትድ!
ታሪክ አዋቂውን ታዲዮስ ታንቱን ለአማራ ያበረከትን !

ዲቻ ህዝቦች ነን❗

-ኢየሱስ ጌታ ነው🙌

⚽ ጉራጌ ክልል:

ዘበርጋ ተነሳ። ሱቅ ክፍት አድርጐ ለመክፈቻው ስለመጣ በጣም ተናዷል። ምንድነው ነገር የምታራዝሙት? ክልሉን ትሰጡናላቹ አትሰጡንም? እኔ ከእንግዲህ በማይረባ ተቃውሞ ሱቄን መዝጋት አልፈልግም!

ይህ ዓለም ዋንጫ እንዲሁም ለጉራጌ ምኑ ነው? ዋናው ክልል ነው!

ደቡብ አቅጣጫ ነው!
ጉራጌ ክልል ነው!
ካታር አረብ ነው!

ብሎ ማይኩን ጥሎ ሄደ።

⚽አርባምንጭ ክልል:

ጋሞና ተረኛ ተናጋሪ ሆነ። አቦ እኛ በኢትዮጵያ አንድነት አንደራደርም!(💚💛❤)
ማንም ይኼን ዋንጫ ያዘጋጅ፣ እኛ ከኢትዮጵያ ጋር ወደፊት!

እውቁን ተጫዋች አዝጌ ዴንዳሾን ለኢትዮጵያ አፍርተናል ብሎ ንግግሩን ቋጨ። አቦ ክልል ክላስተር እያላቹ አታዛጉን ሲልም አከለ። እነ ክርስትያን ታደለ፣ ሃብታሙ አያሌው ማጨብጨባቸውን ሲያረጋግጥ ..... ሙዝ እየላጠ ፣ወደ አዞ እርባታ ሄደ።

ኑ ዴሬይ ጋሞ ጐፋ፣ ኦይቻ አርባምንጬ ❗

የሚለው ዘፈን በskysport, BeIN sports እና BBC እንዲሁም DSTV ላይ ከፍ ብሎ ተደመጠ።

ሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች ይኽ ጥንቅር እስከተዘጋጀበት ድረስ ሀገሪቱ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ አልሰሙም 😂

⚡⚽ሳሮ



የናንተው አርጅና ኢሳያስ ጂራ ነኝ ከዶሃ፣ ቃጣር

Tarekegn S Hadero

***

~ግረባ😎😂[ይህ ጡፍ አንድ ዓመት ሆነው]
~ኾላ🙈😂😂😂

//The Walking Dead in Addis Ababa//በቅርቡ የአንድ ወዳጄ የቅርብ ዘመድ አረፉ። ቀብራቸውም ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ነበር። ሟች ኑዛዜ ነበራቸው። ቀብራቸው በሰሌን እንዲፈጸም።...
11/21/2023


//The Walking Dead in Addis Ababa//

በቅርቡ የአንድ ወዳጄ የቅርብ ዘመድ አረፉ። ቀብራቸውም ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ነበር። ሟች ኑዛዜ ነበራቸው። ቀብራቸው በሰሌን እንዲፈጸም።
ቃላቸው መጠበቅ አለበትና በሰሌን ተጠቅልለው ለአያያዝ እንዲመች እስከቀብር ስፍራው በሬሳ ሳጥን እንዲሄዱ ከቀብር መኪና አስፈጻሚው ድርጅት ጋ ቤተሰብ ስምምነት አደረገ። የሸጡትን ሳጥንም መልሰው ቀብር አስፈጻሚዎቹ እንደሚወስዱት ጭምር። ይህ ለእነሱ ተጨማሪ ገቢ ነው።
በተባለው መሰረት ቀብር ስፍራ ተደረሰ። በኑዛዜው መሰረት ሟችን ከሬሳ ሳጥን አውጥተው በሰሌን ቀበሯቸው።
ከእዚህ በኋላ ነው ሌላ ታሪክ የተፈጠረው። ሳጥኑ አብሮ አልተቀበረምና ከመኪና አከራዬቹ ጋ በተደረገው ስምምነት መሰረት ሳጥኑን እንዲወስዱት ተጠየቁ። አንወስድም፣እንብየው ብለው ድርቅ አሉ። ለምን ሲባሉ "ምን ይሰራልናል፣ ምን እናደርገዋለን፣ ለሌላ አንገለገልበት"
መቼም ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነው። ቢባሉ ቢለመኑ አሻፈረኝ አሉ። በኋላ እንደማንገራገር ብለው "እሺ በቃ ገንዘብ ጨምሩልን!" አሉ።
መቃብር ስፍራ ያንን ሳጥን ትቶ መሄድ ቤተሰቡ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ አለ። የሬሳ ሳጥኑንም ሀዘንተኞቹ ወደቤት ይዘውት አይሄዱ ነገር ጭንቅ ነው።
የሟች ቤተሰብ የሰዎቹ ጭካኔ እያስገረማቸው ላለመወዛገብ በመፈለግ የተባለውን ጭማሪ ከፈሉ። አስፈጻሚዎቹም ሳጥኑን ይዘውት ከቀብር ስፍራ እብስ አሉ። ያው ጠረግረግ አድርገው ለሌላኛው ተረኛ መሸጣቸው አይቀር። በእነሱ ቤት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መሆኑ ነው!
የሙታን መንደር ላይ ቆሞ ስለጥቅም ከማሰብ በላይ ሞት አለ!?

~ይህ አሳዛኝ ገጠመኝ የተወዳጁ ፀሐፈ ቴውኔት የ ውድነህ ክፍሌ ነው

~ኾላ😭💔

      ክፍል 2..ታምሩ በደረጃው እየወረደ ከአዞ ጥርስ በተሰራው ሃብል ላይ ዓይኑን ተከለ።ከፋው። ከዚህ ከረጅሙ የቀን ቅዤት መንቅያው ሰዓት ደርሶ ነበር።የስልኩ ጩኸት ከሰመመን መለሰው።የ...
11/19/2023



ክፍል 2
..ታምሩ በደረጃው እየወረደ ከአዞ ጥርስ በተሰራው ሃብል ላይ ዓይኑን ተከለ።ከፋው። ከዚህ ከረጅሙ የቀን ቅዤት መንቅያው ሰዓት ደርሶ ነበር።የስልኩ ጩኸት ከሰመመን መለሰው።

የለመደው ድምፅ ነበር። "አቶ ታምሩ፣ ቶምቦሌ ነኝ ከአስናቀች ኩባንያ። ዛሬ የአንተና የወይዘሮ ሳራ ጋብቻ እዩበልዩ እንደሆነ ሰማሁ።ስለዚህ ቆንጅዬ ስጦታ አዘጋጅቼላችኋለው። ወደበኃላ ጊዜ ካለህ ላቀብልህ እያሰብኩ ነበር፣ይመችሃል? አለው ቶንቦሌ አክብሮት ባለው ድምፀት።

"ለደግነትህ አመሰግናለው።ከዚህ በኃላ ጊፍት አንቀበልም አዝናለው" አለ ታምሩ።
"ለምን?" አለ ቶንቦሌ አንዳች ነገር እየጠረጠረ።
" ሌላ እንድናወራበት የምትፈልገው ጉዳይ ይኖር ይኾን፣አቶ ቶንቦሌ?"
"በርግጥ ፣አዎ አለኝ።አለ ቶንቦሌ ባልተለመደ ሁኔታ ጉሮሮውን ለማውራት እያፀዳ። " አንድ ጓደኛ አለኝ እና ሰሞኑን አንድ የባዕድ በሽታ ይዞት እያንዘፈዘፈው ነው። ደጅ ያልጠናው ዶክተር ክሊክ ወይም ሆስፒታል፣እሱን ያልመረመረው ዶክተር የለም። የትኞቹም አልረዱትም እንጂ። አንተ ልትረዳው እንደምትችል ተስፋ እያደረግኩ ነበር" አለ ቶንቦሌ በረጅሙ እየተነፈሰ።

"አቶ ቶንቦሌ፣ህጐቼን ታውቅ የለ?''
" በሚገባ! ለዚህ ነውኮ በትህትና መጠየቄ። በዚያ ላይ ጓደኛዬ የአፕል ችግኝ አለው፣አንተ ደሞ ምርጥ ዘር እንደምትፈልግ አውቃለው።
ከረዳኸው እንዲመረዳህ እርግጠኛ ነኝ" አለ ቶንቦሌ ።
"የእውነትህን ነው?" ሲል ጠየቀ ታምሩ፣ፊቱን ቅጭም አድርጐ።
"አዎ የእውነት ነው"
"እንደዛ ከኾነ እሺ፣ መጥቼ አየዋለው" አለ ታምሩ በፍጥነት በመስማማት።
ታምሩ ገንዘብ ቀልቡን አልሳበውም።ይልቁንም ልዩ ልዩ ምርጥ የችግኝ ዘሮችን መሰብሰብ ይወዳል።ለህይወት አድን ይፈልጋቸዋል።

"አመሰግናለው አቶ ታምሩ። ወዲያው ፣የሆነ ሰው መጥቶ እንዲወስድህ አደርጋለው" አለ ቶንቦሌ እፎይታ እየተሰማው።

ቶንቦሌ፣ እንደ አስናቀች ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚነቱ እና ከኩባንያው ቱባ ባለሥልጣናት ሦስት ሰዎች አንዱ ሆኖ እያለ ፣በታምሩ ፊት ተምቦይቀራል።
"መልካም!።ንድ ተጨማሪ ስራ ሞቷል። አምስት ይቀራል።ያለኝ ጊዜ በደንብ ይበቃኛል" አለ ታምሩ ከራሱ ጋር እየተነጋገረ።
በሰማው ዜና ስሜቱ ትንሽ ተሻሽሏል።

ልክ ደረጃውን እንደጨረሰና ከህንፃው እንደወጣ ሁለት የሚያውቃቸው ሰዎች ወደሱ ሲመጡ አየ። የሳራ እናት እማማ ሎላሼ ተስፋዬ እና ወንድሟ ጳውሎስ ነበሩ።"እማማ..." ብሎ ታምሩ ሰላምታ ሰጣቸው።
"አንተና ሳራ ተፋታቹ እንዴ?" እናትየው ጊዜ አላቃጠሉም።
"አዎን፣ተፋተናል" አለ ታምሩ በግድ እየፈገገ።"እንዳይወቅሷት፣ጥፋቱ የሷ አይደለም "ሲል አከለ።

ይህን ሲሰሙ እማማ ሎላሼ ቀዝቀዝ ያለ የሀዘን ድምፀት አሰሙ። "እኮ...ሲጀመር መች አጣሁት! ልጄን ጠንቅቄ አውቃታለው።ችግሩ ያንተ ነው። የኾነ ግብዳ ችግር ሳታመጣ፣እንዴት ትፈታሃለች?"...አሉ ድምፃቸውን ጐርነን አድርገው ልጃቸው ላይ በመተማመን።

ታምሩ ክው አለ። ምን ጉድ ነው ይኼ? የወደቀ ዛፍ ላይ ምሳር ማብዛት? ተጐጂን መውቀስ?

" እማ፣ ኽረ ጊዜሽን አታጥፊ እባክሽን" አለ ጳውሎስ ወደፊት ተጠግቶ። " ይኸውልህ ብሮ፣ ማነህ አቶ ታምሩ፣ እህቴን ብትፈታት ባትፈታት ጉዳዬ አይደለም፣ነገር ግን ከሷ ያገኘኸውን ገንዘብ በጠቅላላ ትሰጠኛለህ፣ገባህ?" አለ በኩራት ።
"ገንዘብ?፣የምን ገንዘብ? አለ ታምሩ ፣ደንግጦ፣ሀዘንም ልቡን ወረረው።

"ጭራሽ ! እንደተጐጂ ታስመስላለህ? እህቴ ለፍቺው ካሳ ስለ ሰጠችህ 20ሚሊዮን ብር ነው የማወራው!" አለ ጳውሎስ ድርቅ ብሎ።
"አዎ ያ የልጄ ብር ነው! መልስልኝ!" አሉ እማማ ሎላሼ እጃቸውን እየዘረጉ።
" ድንቡሉ፣ዱዲ ከሷ እኔ አልተቀበልኩም"
ሲል ታምሩ ተሟገተ።

"በቃ ደደቦች ነው የምንመስልህ?" አለ ጳውሎስ ምንም አላመነውም።
"አቶ ታምሩ ክፉ ባትመልስልኝ ጥሩ ነው። አታበሳጨኝ!" አሉ እማማ ሎላሼ በማስጠንቀቂያ ቃና።
" ኸረ ፣ካላመናችሁኝ፣ሳራን መጠየቅ ትችላላችሁ" አለ ታምሩ ከዚህ በላይ ለእነሱ ማብራራት እንደሌለበት ባለመፈለግ።
ጳውሎስ ታምሩ ኪስ ውስጥ ዘሎ ገባ። እማማ ሎላሼም ተከተሉት።
"እማማ፣ ይኼን ማድርገዎ ተገቢ ነው?" አለ ታምሩ እያዘነ። እናትየው በንቀት በአፍንጫቸው አፏጩ።
" ሃሃ፣ኡኡቴ! ማንን ነው እናቴ ፣እማማ የምትለው? ማን ነኝ አልክ ባክህ? አሉ እማማ ሎላሼ የልጃውን የቀድሞ ባል ኪስ እየፈተሹ። ጥቂት ከፈተሹ በኃላ ምንም የፈልጉትን አላገኙም።

"የምር አልወሰደም እንዴ?" አለ ጳውሎስ እያዘነ።
ድንገት፣ የታምሩን አንገት ሃብል አየ። በፍጥነት ከአንገቱ ላይ ነጠቀው።
"ይህ የእህቴ ሃብል አይደል?ምን ይሰራል እዚህ?ሰርቀኸው ነው?" አለ ጳውሎስ መልስ ፈልጐ።
"አይ ፣አይ ይህ የቤተሰቤ ውርስ ነው። መልስልኝ" አለ ታምሩ በሀዘን ተቆራምቶ።
"የቤተሰብ ውርስ?" ይህ ማለት ይህ ሃብል ፈራንካ ያወጣል ማለት?" ...አለ ጳውሎስ በደስታ ሃብሉ ላይ አፍጥጦ።
"እንደዛ ከኾነ፣ ከኛ ጋር ሦስት ዓመት የኖርክበት በሱ ይጣጣም! ማሚ እንሂድ!"
እማማ ሎላሼ ልጇን እየት አድርገው ለመሄድ ተዘጋጁ።

"ቁም!" አለ ታምሩ የጳውሎስን እጆች ይዞ። "ሃብሉን መልስልኝ"
ራሱን ከታምሩ እጆች ማላቀቅ እንደማይችል ሲገባው ጳውሎስ ሃብሉን መሬት ላይ ወረወረው። በቅፅበት ሃብሉ መዓት ቦታ ተሰነጣጠቀ። ታምሩ በድንጋጤ ፊቱ ከሰል መሰለ። እናቱን የሚያስታውስበት ብቸኛ ማስታወሻ ይህ ሃብል ነበር ።
"እንዴት ብትኮራ ነው እጅህን እኔ ላይ ያነሳኸው! ላንተ ከምሰጥህ መስበሩን መርጫለው!" አለ ጳውሎስ እጆቹ እያመሙት።
ታምሩ የያዘውን እጅ የበለጠ አጠበቀው። ደምስሩ ተገታተረ። በንዴት ዓይኑ የማረቆ በርበሬ መሰለ።
ሲብስበት፣ ታምሩ ጳውሎስን ፊቱ ላይ በሃይለኛ ቦክስ ነረተው።

ከአቅሙ በላይ ስለተመታ ጳውሎስ ራሱን መቆጣጠር ተሳነው። አዞረው። አጥወለወለው። ተዘለፍልፎ ምድር ላይ ተደፋ። እንዴት ይነሳ?
" ና እስኪ ስነ ስርዓት ላስተምርህ!" አለ ታምሩ ጳውሎስን በፀጉሩ ይዞት ከመሬት ቀና እያደረገው። ፋታ ሳይሰጠው ፊቱ ላይ መዓት ቦክስ አሳረፈበት። ወዲያው የጳውሎስ ፊት ኢህአዴግ ጀምሮት ብልፅግና በታንክ የሄደበት ኮብል ስቶን መሰለ።
"እንዴት ብትቀብጥ ነው ልጄን የምትደበድበው?" አሉ እማማ ሎላሼ ልጃቸውን ለመርዳት እየጮኹ።
"ሂጅ ከዚህ!" አለ ታምሩ ድምፁን ከፍ አድርጐ በሚያስገመግም ሁኔታ። ከቁጣው ጉልበት የተነሳ እማማ ሎላሼ ባሉበት ደርቀው ቀሩ።

©ኢንጆይ ሪድንግ
© Tarekegn S Hadero

ይቀጥላል

🖍ኾላ

ተዋናይ አስቻለው ቢርቦ( አስቼ )(የፊሽካዎቹ ኮማንዶ)በወዳጆቹ እና በፈጣሪ ድጋፍ የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎለታል። እግዚአብሔር ይመስገን።🙏አንዳንዴ በመስመር መሃልም ሸጋ ዜና መስማት ደስ ...
02/04/2023

ተዋናይ አስቻለው ቢርቦ( አስቼ )(የፊሽካዎቹ ኮማንዶ)
በወዳጆቹ እና በፈጣሪ ድጋፍ የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎለታል። እግዚአብሔር ይመስገን።

🙏
አንዳንዴ በመስመር መሃልም ሸጋ ዜና መስማት ደስ ይላል!

Address

San Fransisco, CA

Telephone

+14153361597

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MSS Entertainment posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to MSS Entertainment:

Shortcuts

Share

Category