08/22/2026
በ28 ዓመት ታሪክ ከፍተኛውን ውጤት ላስመዘገበችው ተማሪ ቤተ መጻሕፍት በስሟ ተሰየመ‼️
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እንጅባራ ከተማ የሚገኘው አገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በ28 ዓመት ታሪኩ ከፍተኛውን የትምህርት ውጤት ላስመዘገበችው ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ ልዩ እውቅና ሰጥቷል።
ተማሪ ህዳሴ በ11ኛ ክፍል 99.67% በማምጣት በትምህርት ቤቱ ታሪክ ከፍተኛውን ውጤት መመዝገብ ችላለች። ይህንን የላቀ ስኬቷን ለማክበርም ትምህርት ቤቱ ቤተ መጻሕፍቱን “ህዳሴ ቤተ መጻሕፍት” በማለት በስሟ ሰይሞላታል።
ህዳሴ የተሰጣት እውቅና ለቀጣይ ጥረቷ ትልቅ መነሳሳት እንደሆነ ገልጻ፣ በወደፊት በሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተሰማርታ ሀገሯን ለማገልገል ትልቅ ራዕይ እንዳላት ገልጻለች።
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተናም ከትምህርት ቤቱ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤቶች ተመዝግበዋል፤ በሴቶች 583/600 እና በወንዶች 591.6/600 በማምጣት ትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተቋማት መካከል ሆኗል።
ምንጭ- ጌጡ ተመስገን