
08/15/2025
የአውሮፓ እግር ኳስ ሊግ ውድድሮች ዛሬ ምሽት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሻምፒዮኑ ሊቨርፑልና በርማንውዝ ጨዋታ ይጀመራሉ።
ውብ እግር ኳስ ውድድሮችን በማስተላለፍ የሚታወቀው ሱፐርስፖርት ደግሞ ከብዙ አማራጮች ጋር ለተመልካቾች ሊያቀርብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።
የተወዳጅ ሊጎች እግር ኳስ ውድድሮች መገኛ የሆነው ዲኤስቲቪ /ሱፐርስፖርት የ2025/26 ውድድሮች ከዛሬ ጀምሮ በላቀ ጥራት ማስተላለፍ ይጀምራል።
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ እና የጣልያን ሴሪ አ ውድድሮች በተለያዩ አማራጮች ቤታችሁ ሆናችሁ እንድትከታተሉ በሱፐርስፖርት ይዤ መጥቻለሁ ብሏል።