ሰሉ ዘ ተዋህዶ Selu Z’ Tewahedo

  • Home
  • ሰሉ ዘ ተዋህዶ Selu Z’ Tewahedo

ሰሉ ዘ ተዋህዶ Selu Z’ Tewahedo ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ❤️🥺❤️🙏🙏 Orental Orthodox ❤️🙏

ሙስሊሞች ክርስቶስን አመኑ ..!!             ❤️☝🏽
08/06/2025

ሙስሊሞች ክርስቶስን አመኑ ..!! ❤️☝🏽

11/05/2025

♥️🙏🏽♥️

በዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 11 ንዑሰ ክርስቲያን ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ  ! ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን !አሜን !ምንጭ:- ምንጭ...
03/05/2025

በዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 11 ንዑሰ ክርስቲያን ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ !

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን !

አሜን !

ምንጭ:- ምንጭ፦ SPOT Church (የቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን፣ ሜሪላንድ)

“ነዓ ነዓ፥ ነዓ ጊዮርጊስ፤እንዘ ትጼአን በፈረስ፤ወነዓ ፍቁርየ ዘልዳ ንጉሥ!” (ስብሐተ ፍቁር)🌹     🙏🏽 ሰሉ ዘ ተዋህዶ Selu Z’ Tewahedo
01/05/2025

“ነዓ ነዓ፥ ነዓ ጊዮርጊስ፤
እንዘ ትጼአን በፈረስ፤
ወነዓ ፍቁርየ ዘልዳ ንጉሥ!” (ስብሐተ ፍቁር)🌹
🙏🏽 ሰሉ ዘ ተዋህዶ Selu Z’ Tewahedo

-የወይን ጠጅ የላቸውም -ይህ ጥያቄ እመቤታችን ለምትጠይቃቸው ጥያቄዎች መጀመሪያ ነው። የጽድቅ ሥራ መሥራት ስለአቃታቸው ሰዎች ንጽሕናቸውን፣ ቅድስናቸውን፣ ስላጡ ሰዎች ሥነምግባር  ስለሌላቸው...
29/04/2025

-የወይን ጠጅ የላቸውም -

ይህ ጥያቄ እመቤታችን ለምትጠይቃቸው ጥያቄዎች መጀመሪያ ነው። የጽድቅ ሥራ መሥራት ስለአቃታቸው ሰዎች ንጽሕናቸውን፣ ቅድስናቸውን፣ ስላጡ ሰዎች ሥነምግባር ስለሌላቸው ሰዎች አስራት ጸሎት መጾም መስጠት ስላቃታቸውውና ራሳቸውን መግዛት ስለተሳናቸው ሰዎች :- ጽድቅ እኮ የላቸውም' ንጽሕና ቅድስና እኮ የላቸውም' ሥነምግባር እኮ የላቸው' ኃጢአትን የማሸነፍ ችሎታ እኮ የላቸው / ሥርየተ ኃጢአት ይደርግላቸው / ብላ ስለምታቀርበው ምልጃ መጀመሪያ ነው።

♥️🙏🏽  እናቴ ንኢ ንኢ ቤዛዊት ዓለም 🙏🏾❤️
24/04/2025

♥️🙏🏽 እናቴ ንኢ ንኢ ቤዛዊት ዓለም 🙏🏾❤️

‹‹ቤዛ›› ማለት ምን ማለት ነው? እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም የአለም ቤዛ ናትን ?ብዙ ጊዜ ድንግል ማርያም እንዴት የአለም ቤዛ ትሆናለች? ይላሉ፤ በእርግጥ ግን እናታችን ቅድሥት ድንግ...
21/04/2025

‹‹ቤዛ›› ማለት ምን ማለት ነው? እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም የአለም ቤዛ ናትን ?

ብዙ ጊዜ ድንግል ማርያም እንዴት የአለም ቤዛ ትሆናለች? ይላሉ፤ በእርግጥ ግን እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም የአለም ቤዛ ናት ።‹‹ ቤዛ ›› በቁሙ ሲተረጐም ዋጋ አለው ወይም ጥቅም አለው ማለት ነው ። እንዲሁም ቤዛ የሚለው ቃል "ቤዘወ"፦ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ቤዛ በቁሙ ሲተነተን እንዲህ ማለት ነው ። ዋጋ ፣ ካሳ ፣ ለውጥ ፣ ምእትክ ፣ ሀላፊ ፣ ዋቢ ፣ ዋሥ ፣ መድኅን ፣ ተያዥ ፣ ጥላ ፣ ጋሻ ... ማለትነው ።ቤዛ በደቂቅ አገባብ ሲፈታ ደግሞ ሥለ፣ ፋንታ፣ ምክንያት የሚሆንተብሎም ይተረጐማል ። አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ መፅሐፍ ሠዋሠው ውግሥ በመዝገበ ቃላት ሐዲሥ 1948 ዓ ም ገፅ 266፡፡ ወይምደግሞ በሌላ መንገድ ከሣቴ ብርሐን ተሠማ መፅሐፋቸው ቤዛ ሲተረጉሙ እንዲህ ብለው አሥቀምጠውልናል ለውጥ፣ካሣ፣ወይም ደግሞ በአንድ ሠው ላይ መከራና ሞት ተላልፎ መሞትማለት ነው ወይም ታደገኝ ወይም ምትክ ሆነኝ ማለት ነው ወይም ደግሞ ለመከራ ለሞት ለወጠኝ ማለት ነው ወይም ቤዛ ሆነኝ ማለትነው ። የበለጠ ለመረዳት አልያም ቤዛ ሥለሚለው ቃል በደንብ ለማወቅ እነዚህን መፅሐፍቶች መመልከት ይቻላል ። እንደዚሁምቤዛ የሚለው ቃል ፦ ካሣ ፣ የደም ቤዛ ፣ አንዱ ሠው የሠውንደም ሥለሚያፈሠው ለውጥ ወይም ዋጋን ፣ ገንዘብን ፣ ካሣን መሥጠት ወይም መዋጀት ማለት ነው ።ከሣቴ ብርሐን 1951 ዓ.ምገፅ 532ድንግል ማርያምን ስለምን የአለም ቤዛ እንላታለን?የእመቤታችን ቤዛነትም ከላይ በተረዳነው መሠረት ቤዛ ከሚሉት የትርጓሜ ቃላት መካከል ምትክ፣ ዋሥ፣ምክንያት ... ከሚሉት መካከል ምትክ የሚለውን ስንወስድ ድንግል ማርያም የህይዋን(ሔዋን) ምትክ በመሆኗ ነው፤ ‹ምክንያት› የሚለውን ስንወስድ ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም ለኛ መዳን ምክንያት ስለሆነች ነው። እግዚአብሔር ለአለም መዳን በድንግል ማርያም ታላቅ ስራን አድርጉአልና ቤዛዊት ዓለም እንላታለን። የድንግል ማርያም በእምነት መታዘዝ ለዓለም መዳን ምክንያት ሆናለች። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ስለተቤዤ ቤዛዊት ዓለም እንላታለን። ቤዛ የሚለው ቃል ለሙሴም ተሰጦት እናነባለን። ( የሐዋ ሥራ 7:35) በመልአክ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።እንግዲህ ይህ የፍጡር ቤዛነት የእግዚአብሔርን ቤዛነትይሽራልን? አይደለም፡፡ እንዲያውም ቸር እግዚአብሔርለወዳጆቹ የሚሰጠውን የባለሟልነት ስጦታ ብዛት ይገልፃልእንጂ፡፡ ሙሴ ወገኖቹን ከመጥፋት እንደምን አዳናቸው(ተቤዣቸው)(ታደጋቸው)? እንደክርስቶስ ደሙን በማፍሰስ ነውን? አይደለም በእግዚአብሔር ዘንድ ‹ይህን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍኽ እባክኽ ደምሰሰኝ› በማለትየተወደደፀሎቱንበማቅረብእንጂ (ዘጸ.32፤32) ፡፡ዳዊትም ‹ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም ኖሮ›› ሲል የገለፀው ይሄንኑ ነው፡፡ስለዚህም መጽሐፍ የፃድቅሰውፀሎትበስራዋእጅግሃይልንታደርጋለችይላል፡፡የእመቤታችንና የድንግል ማርያም ቤዛነት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርሥቶስ ቤዛነት ጋር ያለው ልዩነትእጅግ የሚራራቅ ነው።ጌታችን በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው ። እንዲሁም በደሙ ዋጅቶ በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው። ቤዛ ማለትእራሥን ሥለሌሎች አሣልፎ መስጠት ማለት ሥለሆነ ጌታችንም ሥለበጐቹ እራሱን አሣልፎ ሠጥቷል ሆኖም የአለም ቤዛ ነው ። ታዲያ የአለምቤዛ ክርስቶስ ከሆነ ድንግል ማርያምስ ቤዛዊት አለም መባሏ ስለምን ነው ቢሉ፦ ክርስቶስ አለምን ሁሉ ከሞት ወደህይወት ያሻገረበት፣ ሃጢአታችንን ሁሉ የደመሰሰበት፣ የሚደመስስበትም ክቡር ደሙ፣ ቅዱስ ስጋው ከእመቤታችን ስለነሳው ነው፤ በዚህም ክርስቶስ ከመወለዱ አንስቶ በቤተልሄም የከብት ግርግም ተጀምሮ፡ በግብፅ ስደቱ በቀራኒዮ ስቃዩና ሞቱ ሁሉ አብራው አለችና በክርስቶስ የድህነት ስራ ውስጥ የእመቤታችን ስራ ጉልህ ሆኖ ይታያልና ነው፡፡ለማጠቃል ያክል፡- ሙሴ ምክንያት ሆኖ ነጻ ያወጣቸው ለጥቂት ነገዶች ወይም ‹ለእስራኤላውያን› ብቻ በመሆኑ‹‹ቤዛ›› ብቻ ተብሏል፡፡ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ግን ምክንያተ ድኅነት ሆና ነጻ ያወጣችው ‹ዓለም ሙሉ›ስለሆነ (ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ተሰቅሏልና) ‹‹ቤዛዊተ ዓለም›› ትባላለች፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን ለቅዱሳንም በጸጋ ተሰጥቷል፤ በመጸሐፍየጸጋ አምላክነት ለቅዱሳን ተሰጥቶ እናያለን ‹እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦እይ፥እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌኻለኹ›፤ ክርስቶስየዓለም ብርሃን እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ቅዱሳንንም ‹እናንተየዓለም ብርሃን ናችኹ› በማለት በጸጋ የዓለም ብርሃን እንደሚባሉ መጽሐፍ ምስክርነው ( ዘጸ7፤1 ማቴ 5፤14)የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲህ ነዉ፤ አምልኮ ምስጋና ክብር ለጌታችን በደሙ ለተቤዠን ለምድኃኒአለም ይሁን ለዘላለም ♥️🙏🏽ክብርና ምሥጋና ለቤዛዊት አለም ለእመቤታችን ለቅድሥት ድንግልማርያም ይሁን አሜን።ምንጭ(ከተለያዩ ድህረ ገጾች ተሰብስቦ የተዘጋጀ)ሐመረ ወርቅ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን

ሚያዝያ 10 በሊቢያ በአክራሪዎች ሰማዕት የሆኑ ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ "የክርስቶስን አምላክነት የእናቱን አማላጅነት አትክድም?""የለም አልክደውም""አልክደውም ካልክ በሰይፍ ታርደህ ህይወትህ...
19/04/2025

ሚያዝያ 10 በሊቢያ በአክራሪዎች ሰማዕት የሆኑ ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ

"የክርስቶስን አምላክነት የእናቱን አማላጅነት አትክድም?"

"የለም አልክደውም"

"አልክደውም ካልክ በሰይፍ ታርደህ ህይወትህን እንደምታጣ ታውቃለህ?"

"ህይወቴ ክርስቶስ ነው እናቱ ደግሞ እናቴና አማላጄ ናት የአለም ህይወቴን ባጣ ዘላለማዊ ህይወትን እርሱ ያድለኛል "

እያንዳንዱን ሰማዕታት አረመኔዎቹ አራጆች እንዲህ ያሏቸው ይመስለኛል እነርሱ ግን "እንሞታለን እንጂ አንክድም" አሉ ለተመረጡት ንዑዳን ክቡራን የአምላክ ወዳጆች ብቻ በተገባው የሰማዕትነት ህልፈት ሊያልፉ ተመርጠው ነበርና

ሰማዕትነት እድል ነው መመረጥ ነው ደግሞም ለቅድስና መታጨት ነው ይህን እድል ብዙኃን አበው የሚመኙት ነገር ግን የተመረጡ ቅዱሳን ብቻ የሚያገኙት ልዩ ሽልማት ነው

ቅዱሳን ሰማእታት ሆይ ደጉ አምላካችን የእናንተን የክብር ሞት ያድለን ዘንድ ቸሪቱ አማላጅቱ እናታችንም በእቅፏ ትቀበለን ዘንድ ለምኑልን በረከታችሁ በላያችን ይደር

አሜን

Address

WA

Telephone

+12068861016

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰሉ ዘ ተዋህዶ Selu Z’ Tewahedo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሰሉ ዘ ተዋህዶ Selu Z’ Tewahedo:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share