
07/11/2025
"የክለቦች ዓለም ዋንጫ ያስፈልጋል" - ቬንገር
የቀድሞው የፈረንሳይ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር የክለቦች ዓለም ዋንጫ ውድድር አስፈላጊነት እንደሚያምኑ ገለጹ።
በቅርቡ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ለውድድሩ መጀመር ባቀረቡት ትችት ላይ ምላሽ የሰጡት ቬንገር፣ "የውድድሩ ደጋፊ ነኝ" ብለዋል። የቀድሞው የአርሰናል ታሪካዊ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር በአሁኑ ወቅት የፊፋ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዕድገት ኃላፊ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።
"የክለቦች ዓለም ዋንጫ ውድድር ያስፈልጋል" ያሉት ቬንገር፣ እዚህ የነበሩትን ሁሉንም ክለቦች ብትጠይቁ በድጋሚ መወዳደር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ውድድሩ በደጋፊዎች ስለመወደዱ አንስተውም፣ "የተመልካች ቁጥር ዝቅተኛ ነው ተብሎ ቢገመትም ከፍ ብሎ ታይቷል፤ ምላሹ ይሄ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።
ይህን እና ሌሎችንም አዳዲስ የስፖርት ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk