09/08/2026
የቀይ ባህር እሳት፡ የአልቡርሃን እና የኢሳያስ ምስጢራዊ የኬሚካል ሴራ‼️
በሱዳን ደም አፍሳሽ ጦርነት በስተጀርባ የተሸሸገው አስፈሪ እውነት ይፋ ሆኗል፤ ጄኔራል ቡርሃን የተከለከሉ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ጥቅም ላይ ማዋላቸውን የሚጠቁሙ የምርመራ መረጃዎች ወጥተዋል።
ይህ አደገኛ እርምጃ የቀጣናውን የደህንነት ስጋት ወደ አዲስ የጥፋት ምዕራፍ ያሸጋገረው ሲሆን፣ የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂም የዚህ ሴራ ቀጥተኛ ተባባሪ እና ከበስተጀርባው እጁ ያለበት መሆኑ ተጋልጧል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታውን ሰብሮ አጣዳፊ እርምጃ ካልወሰደ የቀይ ባህር ቀጣና በፍፁም አጥፊ እሳት ውስጥ መውደቁ አይቀሬ ነው። የሴራው ጥልቀት እና የስልጣን ጥመኞች ጥረት የምስራቅ አፍሪካን ህዝቦች ደህንነት አደጋ ላይ ጥሎታል።