ኢትዮጲክ - Ethiopique

ኢትዮጲክ - Ethiopique በዲሲ-ሜትሮ አካባቢ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችንና መረጃዎችን በአንድ ቦታ። ጥያቄ እንቀበላለን። መልሱን እኛ ባናቀው ተከታታዮቻችን ያውቁታል።
(2)

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች የሰራተኞች የኋላ ታሪክ የማጣራት ሂደት ላይ ከባድ ክፍተቶች መኖራቸውን የዋና ኢንስፔክተር ጽ/ቤት ሪፖርት አጋለጠ። ከተማሪዎችጋ በቀጥታ የሚገናኙ ...
08/08/2025

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች የሰራተኞች የኋላ ታሪክ የማጣራት ሂደት ላይ ከባድ ክፍተቶች መኖራቸውን የዋና ኢንስፔክተር ጽ/ቤት ሪፖርት አጋለጠ። ከተማሪዎችጋ በቀጥታ የሚገናኙ በርካታ ሰራተኞች ባክግራውንድ ቼክ አልተደረጉም ተባለ።
ዝርዝሩ
https://ethiopique.com/?p=6507

ማስታወቂያ...የኢትዮጵያ ኮሚውኒቲ ማህበር በሜሪላንድ አመታዊውን የኢትዮጵያ ቀን በሲልቨር ስፕሪንግ ሲቪክ ሴንተር በቬተራን ፕላዛ ኦገስት 31 ያከብራል:: ሁላችሁም ተጋብዛችሁዋል::
08/08/2025

ማስታወቂያ...
የኢትዮጵያ ኮሚውኒቲ ማህበር በሜሪላንድ አመታዊውን የኢትዮጵያ ቀን በሲልቨር ስፕሪንግ ሲቪክ ሴንተር በቬተራን ፕላዛ ኦገስት 31 ያከብራል::
ሁላችሁም ተጋብዛችሁዋል::

08/07/2025
አንዱ መረጃ ሌላ ጥያቄ ይዞ እየመጣ ነው:: በጥያቄያችሁ መሰረት ኦሽን ሲቲ ሄጄ ከቢችና ውሀ ሌላ ምን ላድርግ ብላችሁ ለጠየቃችሁ እነሆ:: ከ3 አመት በፊት የከተብነው መረጃhttps://eth...
08/07/2025

አንዱ መረጃ ሌላ ጥያቄ ይዞ እየመጣ ነው:: በጥያቄያችሁ መሰረት ኦሽን ሲቲ ሄጄ ከቢችና ውሀ ሌላ ምን ላድርግ ብላችሁ ለጠየቃችሁ እነሆ:: ከ3 አመት በፊት የከተብነው መረጃ

https://ethiopique.com/?p=906

የዲሲ ዩናይትድ ስቴድየም ኦውዲ ፊልድ ከዛሬ ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ሳምንታት የውጪ ሲኒማ(Outdoor Cinema) አዘጋጅቷል:: መግቢያ በነፃዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾https://ethiopique.co...
08/07/2025

የዲሲ ዩናይትድ ስቴድየም ኦውዲ ፊልድ ከዛሬ ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ሳምንታት የውጪ ሲኒማ(Outdoor Cinema) አዘጋጅቷል:: መግቢያ በነፃ
ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾

https://ethiopique.com/?p=6506

ትላንት ያወጣነውን የተመላሽ ሞገድ ማስጠንቀቂያ ዜናን ተከትሎ በርካቶች ሰሞኑን ወደ ቢች እንደምትሄዱ ነግራችሁናል:: ስለሆነም ይህን ትንሽ ቆየት ያለ ስለ ዋና ልብስመጣ የሚያትት ዜና እንድታ...
08/07/2025

ትላንት ያወጣነውን የተመላሽ ሞገድ ማስጠንቀቂያ ዜናን ተከትሎ በርካቶች ሰሞኑን ወደ ቢች እንደምትሄዱ ነግራችሁናል:: ስለሆነም ይህን ትንሽ ቆየት ያለ ስለ ዋና ልብስመጣ የሚያትት ዜና እንድታነቡት እንመክራለን.. የምንለብሰው የዋና ልብስ ቀለም የመስጠምና የመሞት አደጋን በተወሰነ መልኩ ይቀንሳል

https://ethiopique.com/?p=6006

ማስታወቂያ..ማንኛውንም እቃ ወደ ኢትዮጵያ ይልካሉ + ያስመጣሉ ! ቁጥር 1 :- 3819C S George Mason Dr, Falls Church, VA 22041ቁጥር 2 :- 1206 Underwoo...
08/07/2025

ማስታወቂያ..
ማንኛውንም እቃ ወደ ኢትዮጵያ ይልካሉ + ያስመጣሉ !

ቁጥር 1 :- 3819C S George Mason Dr, Falls Church, VA 22041

ቁጥር 2 :- 1206 Underwood St NW, Washington, DC 20012

ቁጥር 3 :- 14827 Build America Dr, Woodbridge, VA

ስልክ
571-579-1286 ወይም 571-579-0939

ዋሳ ኤክስፕረስ - የልብ አድርስ

ኦሽን ሲቲ፣ ሜሪላንድ – እርስዎ ወይም ሌላ የሚያውቁት ሰው በዚህ ሳምንት ወደ ኦሽን ሲቲ ለመዝናናትና ለመዋነት የሚያመሩ ከሆነ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ። ብሔራዊ የሜሮሎጂ አገልግሎት ሰዎች ...
08/07/2025

ኦሽን ሲቲ፣ ሜሪላንድ – እርስዎ ወይም ሌላ የሚያውቁት ሰው በዚህ ሳምንት ወደ ኦሽን ሲቲ ለመዝናናትና ለመዋነት የሚያመሩ ከሆነ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ። ብሔራዊ የሜሮሎጂ አገልግሎት ሰዎች ስለ አደጋዎቹ ሳያውቁ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ እንዳይዋኙ አስጠንቅቋል።
ዝርዝሩ 👇🏾
https://ethiopique.com/?p=6501

ቢግ ቦልስ በሚል ቅፅል ስም የሚጠራው የዶጅ ተቀጣሪ ወጣት በዋሽንግተን ዲሲ የመኪና ስርቆት ሙከራና ድብደባ ከደረሰበት በሁዋላ ፕሬዘደንት ትራምፕ  ዲሲን በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር እንደ...
08/06/2025

ቢግ ቦልስ በሚል ቅፅል ስም የሚጠራው የዶጅ ተቀጣሪ ወጣት በዋሽንግተን ዲሲ የመኪና ስርቆት ሙከራና ድብደባ ከደረሰበት በሁዋላ ፕሬዘደንት ትራምፕ ዲሲን በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚያስገቡ ዝተዋል:: በአስራዎቹ እድሜ የሚገኙ የዲሲ ታዳጊዎች ማንኛውንም የህግ አካል አይፈሩም ሲሉ የወቀሷቸው ሲሆን:: ጥፋተኛ ታዳጊዎች እንደ አዋቂ መቀጣትና ለረጅም ጊዜ መታሰር አለባቸው ሲሉም አክለዋል::

ዛሬ በስራ ምክንያት አመታዊውን ከቤት ውጭ የማምሸት በአል (የናሽናል ናይት አውትን) ለማክበር ከዲሲ በስተ ደቡብ 55 ማይል ላይ ወደምትገኘው ወደ ፍሬድሪክስበርግ ቨርጂንያ ወርደን ነበር:: ...
08/06/2025

ዛሬ በስራ ምክንያት አመታዊውን ከቤት ውጭ የማምሸት በአል (የናሽናል ናይት አውትን) ለማክበር ከዲሲ በስተ ደቡብ 55 ማይል ላይ ወደምትገኘው ወደ ፍሬድሪክስበርግ ቨርጂንያ ወርደን ነበር:: በቆይታችን አይናችንን ከሳቡት ጥቂት ጉዳዮች አንዱ ታዲያ ይህ የምግብ ማደያ ነው:: ይህ ፍሪጅ ውስጡ የበሰሉ ምግቦች የሰፈሩ ሰው እያመጣ ያስቀምጥበታል... የፈለገ ሰው መቶ የፈለገውን ይወስዳል::

ቅዳሜ አሳ እያጠመድን ይሄ የውሀ ላይ ታክሲ ሲያልፍ ያየች የ3/4 አመት ዕድሜ ታዳጊ...Mommy, is that a school bus?… 😂😂one of the many little things th...
08/05/2025

ቅዳሜ አሳ እያጠመድን ይሄ የውሀ ላይ ታክሲ ሲያልፍ ያየች የ3/4 አመት ዕድሜ ታዳጊ...Mommy, is that a school bus?… 😂😂
one of the many little things that put a smile on our face.

የቴክሳስ አገረ ገዢ በቴክሳስ ያሉ የምርጫ ዞኖችን በአዲስ ለማካለል ያሰቡትን እቅድ ለማሸፍ የስቴቱ የዴሞክራት ተወካዮች ለምርጫ የሚያስፈልገውን ኮረም ለማጉደል በማሰብ ቴክሳስን ጥለው ወተው ...
08/04/2025

የቴክሳስ አገረ ገዢ በቴክሳስ ያሉ የምርጫ ዞኖችን በአዲስ ለማካለል ያሰቡትን እቅድ ለማሸፍ የስቴቱ የዴሞክራት ተወካዮች ለምርጫ የሚያስፈልገውን ኮረም ለማጉደል በማሰብ ቴክሳስን ጥለው ወተው በኢሊኖይስና በመሳሰሉ ስቴቶች ይገኛሉ::
ይህ የዴሞክራቶች ስሌት ያልተዋጠላቸው ሪፐብሊካኖች ታዲያ እኚህ ተወካዮች ታስረው እንዲመጡ በገዢው በግሬግ አበት በኩል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል::
የቴክሳስ ገዢ በትዊተር ገፃቸው ይህን ማስፈራሪያ ለጥፈዋል::
የቴክሳስ ሪፐብሊካኖች የምርጫ ዞኖችን እንደ አዲስ በማካለል ዴሞክራቶች በቴክሳስ መቀመጫ እንዳይኖራቸው ለማድረግ ያለመ አካሄድ ነው:: ዝርዝሩን በኮመንቱ ስር ይመልከቱ::

Address

Washington D.C., DC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮጲክ - Ethiopique posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share