20/08/2026
''ድምፃዊ ይሁኔ በላይ "ዞማዬ" የተሰኘ 10ኛ አልበሙን በአዲስ ዓመት ሊለቅ ነው!
ተወዳጁ ድምፃዊ ይሁኔ በላይ 12 ዓመታትን ተጨንቆና ተጠቦ ያዘጋጀውን ድንቅ የጥበብ ፍሬ፣ 10ኛ አልበሙን "ዞማዬ" በሚል መጠሪያ ከአድናቂዎቹና ከአድማጩ ጋር ሊያገናኝ ዋዜማ ላይ ይገኛል!
• ከጎጃሙ የኪነት እንቁ "ግሽ አባይ" ተነስቶ እስከ ግዙፎቹ የሙዚቃ መድረኮች የተጓዘው ይሁኔ በላይ፤ ጥበብን በዕውቀት ከተፈጥሮ ድምፁ እና ባህሪውን በሕዝብ ፍቅር አምቆ፣ አቋሙን ደግሞ በሃገር ወዳድነት አፅንቶ የኖረ ብርቅዬ የጥበብ ሰው ነው።
• ይህ "ዞማዬ" የተሰኘው አስረኛ አልበሙ ተራ የሙዚቃ ስብስብ አይደለም፤ ሙሉ 12 ዓመታትን በስሜት፣ በሙያዊ ብስለት እና በጥበብ ፍለጋ የተጠመቀ የጥበብ ማዕድ ነው!
• የሃገራችንን ህብረ-ቀለማት ያንጸባረቁ የይሁኔ በላይ' ዞማዬ' አልበም ውስጥ………..
1: መላ አለው
2: እኔስ ባገሬ
3: እንጃልኝ
4: ዞማዬ
5: እኔ ሆይ
6: አገኜሽኝ እና
7: ተይ ዘው ዘው
8: እቴ አዶ ወሸባ.. የተሰኙ ስምንት ልዩ ልዩ የዜማ ስልቶች ተካተውበታል።
• ስለ ሃገር፣ ፍቅር እና ባህል: ልብን የሚነኩ፣ መንፈስን የሚያድሱና የቆየ ትዝታን የሚቀሰቅሱ መሳጭ ግጥሞችና ዜማዎች አሰባስቧል።
• የዝነኛውና አንጋፋው የግጥምና ዜማ ደራሲ አበበ ብርሃኔ እና የሌሎች ታላላቅ ባለሙያዎች አስደናቂ አሻራ አርፎበታል።
• ሙዚቃዎቹን አስቀድመው ያደመጡ ታዋቂ ግለሰቦችና የጥበብ ሰዎች በስራው ጥራትና ውበት በመደመም አልበሙ ለህዝብ ክፍት እስኪሆን ድረስ በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ!"
• የባህል አምባሳደር እና የሃገር ፍቅር ህያው ምስክር የሆነው የይሁኔ በላይ ድምፅ ዳግም ቤታችንንና ልባችንን ሊሞላው ጥቂት ቀናት ቀርተውታል።
• የድምፃዊ ይሁኔ በላይ ፕሮሞተር ደመወዝ ገነቱ እንደገለጹት፤ ይህ ድንቅ ስራ በከፍተኛ ጥራትና በቃት ተሰርቶ በአዲሱ ዓመት ለህዝብ ይደርሳል። ካሉ በኋላ
"ጆሮአችሁን አዘጋጁ... "ዞማዬ" መንገድ ላይ ነው! "ብለዋል።
• ከዳሞት ምድር እስከ ዓለም አቀፍ መድረክ የዘለቀው የኢትዮጵያ ባህል አምባሳደር እና
የኢትዮጵያ ባህላዊ ዜማ ውበት የሆነው ተወዳጁ ድምፃዊ ይሁኔ በላይ፣ ተወልዶ ያደገው በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሀገር በቆላ ደጋ ዳሞት አውራጃ በምትገኘው በውቧ ፍኖተ ሰላም ከተማ ነው።
ምንጭ:- ፕሮሞተር ደሞዝ ገነቱ