Hunda Eda Tube

Hunda Eda Tube እውነትን አልክድም ከውሸት ጋር መቼም አላብርም!!

11/12/2022

ግልጽ ደብዳቤ

ለኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፤
ለደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ትምህርት ቢሮ
ሀዋሳ፤
ለሀዲያ ዞን አስ/ር ጽ/ቤት
ለሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያቅ2
ሆሳዕና፤
ለወለይታ ዞን አስ/ር ጽ/ቤት
ለወለይታ ዞን ትምህርት መምሪያ
ወለይታ ሶዶ፤

ጉዳዩ፡ በ 7ተኛ ክፍል Performing and Visual Arts የተማሪዎች መጽሃፍ ውስጥ የተፈጠረው ስህተት ማስተካከያ እንዲደረግና ተገቢው ማብራሪያ እንዲሰጥ ስለማሳሰብ፤

መት ሀዲዮማ የምሁራን ማህበር በአለም ሁሉ በሚገኙ የሀዲያ ተወላጅ እና ወዳጆች በሆኑ ምሁራን የተቋቋመና በኢትዮጵያ የተመዘገበ የሲቪክ ማህበርሰብ ድርጅት ሲሆን በልማት፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡ ማህበሩ ከሚሰራቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ የሀዲያን ብሔር ቱባ ባህል ማስጠበቅ፣ መንከባከብና ማሳደግ ቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡ ከዋና ዋና የሀዲያ ባህላዊ ጨዎታዎች ውስጥ የሴሌሜ ሴሌሜ ባህላዊ ዳንስ/ጭፈራ የሀዲያ ብሔር ከሚታውቅባቸው ባህላዊ ክዋኔዎች ውስጥ ግንባር ቀደም ስፍራ ይይዛል፡፡

የሴሌሜ ሴሌሜ ባህላዊ ዳንስ ከጥንት ጀምሮ የሀዲያ ብሔር ባህላዊ ዳንስ/ጭፈራ እንደሆነ በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ ቢሆንም በ7ተኛ ክፍል Performing and Visual Arts በሚል ርዕስ በተዘጋጀዉ የተማሪዎች መጽሃፍ ውስጥ በገጽ 83 ላይ ሴሌሜ ሴሌሜ የወለይታ ብሔር ባህላዊ ዳንስ ተደርጎ የተጻፈው እንዲሁም የተቀመጠው ስዕል በግድ የለሽነት ወይም ሆን ተብሎ ችግር ለመፍጠር የተቀመጠ ከፍተኛ ስህተት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ የተማሪዎች መጽሃፍት ሲዘጋጁ በአግባቡ ተገምግመውና ተፈትሸው ጥቅም ላይ መዋል ሲገባቸው ከእነ ስህተታቸው ለተማሪዎች መቅረባቸው ተገቢነት የለውም፡፡

በመሆኑም ሆን ተብሎ ወይንም በእንዝላልነት በመጽሃፉ ላይ የተፈጸመው ስህተት በአስቸይ ማስተካካያ እንዲደረግ እያሳሰብን መጽሃፉም እስኪስተካከል ታግዶ እንዲቆይ እንጠይቃለን፡፡
እንደዚህ አይነት በግድየለሽነት የሚፈጸሙ ስህተቶችና የትርክት መዛባቶች በሀገራችን ከፍተኛ የሆኑ ቁሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካ ችግሮችን እያስከተለ አላስፈላጊ ዋጋ እያስከፈለ እንደሚገኝ በጥብቅ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡

መት ሀዲዮማ የምሁራን ማህበር
ትምህርት ሚኒስቴር SNNPR Education Bureau Hadiya.TV Hadiya Zone Education Department የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት Hadiya Zone Prosperity Party Office Hadiya zone Government Communication Affaris Department የሀድያ ዞን የመ/ኮ/ጉ መምሪያ Ethiopian Broadcasting Corporation FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

11/11/2022
09/17/2022

Address

Washington D.C., DC

Telephone

+12027162489

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hunda Eda Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hunda Eda Tube:

Share