09/15/2026
#የምርመራዘገባ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የሰራተኞች ቅጥር በባለስልጣናት በሚፃፍ የድጋፍ ደብዳቤ እና ከ50 ሺህ ብር ጀምሮ በሚሰጥ ጉቦ መሆኑ ስጋት ፈጠረ
"ከሁሉም በላይ አስገራሚው እና አሳዛኙ ድርጊት የተፈጸመው በ NICU/PICU (የጨቅላ ህጻናት እና የህጻናት ጽኑ ህክምና ክፍል) የቅጥር ሂደት ላይ ነው... የጽሁፍ ፈተና እንኳን ሳይወስዱ ለቃል ፈተና ተመርጠዋል ተብሎ በጤና ቢሮው የተወጣው የስም ዝርዝር በአብዛኛው በእውነተኛው አለም የሌሉ፣ በሀሰት የተፈጠሩ የሰዎች ስሞች ናቸው"
ተጨማሪ ያንብቡ:
(መሠረት ሚድያ)- የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የሰራተኞች ቅጥር ላይ ከፍተኛ የሙስና፣ የአድልዎ እና ሌሎች ውንጀላዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጭምር በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።