26/08/2026
✍️መረዳት ያለብን የህይወት እውነታዎች
1📌ሰውን ለመቀየም አንቸኩል:
አይደለም በሌላ ሰው መጎዳት ራሳችንም ራሳችንን ስንቴ ክደን ጎድተነዋል ?? ስንቴ ከራሳችን ጋር ተጣልተናል? ጥርሳችን ምላሳችንን ስንቴ ነክሶ አድምቶታል??
ኑሮ ይህ ነው! ብዙ ህመም ብዙ ፈውስ ፣ብዙ ለቅሶ ብዙ ሳቅ ....ብዙ መጎዳት ብዙ መጠገን።
መራር አለመሆን ነው:: ህይወት መልኳ ብዙ ነው ስለሆነም Enjoy the ride😊
2📌አንዳንድ ችግር የሚፈታው በጊዜ እንጅ ብዙ በማስላት እና በመጨነቅ አይደለም። ጊዜ ይፍታው!
3📌"ንፅፅር ደስታ ነጣቂ ነው " ያሉት ልክ ናቸው። ኑሯችንን በጎረቤት ወይም በሚዲያ ለመቃኘት መሞከር በተቀደደ ኪስ ውስጥ ገንዘብ እንደማስቀመጥ ነው።
4📌መውደቅ ሰውኛ ነው እንደገና መነሳትም እንደዛው። እወድቃለሁ በሚል ፍራቻ ሳንሞክር ለምን እናድራለን?
5📌 ፀፀት ለመታረም ጥሩ ቢሆንም በፀፀት ውስጥ ለአመታት መኖር ግን ደጋግሞ መውደቅ ነው። አንዳንድ ፀፀት ከጥፋታችን የበለጠ በቁም ይገድለናል
5📌ተመስገን ለማለት ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ አንጠብቅ። ተተረማምሶም ተመስገን ማለት ክፉ ቀናት እንድናልፍ አቅም ይሰጠናል። በምስጋና ውስጥ ድል አለ" እንደሚል ቅዱስ ቃሉ። የሚያሳዝነን እያለ እናመስግን እና እናሸንፍ