Yom Media ዮም ሚድያ

Yom Media ዮም ሚድያ your Best media. we deliver real info with evidence . follow us and share our content.

29/06/2025
የሶሪያ ከፍተኛ የክርስቲያን መሪዎች በቤተክርስቲያን የቦምብ ጥቃት ላይ መንግስትን ወቀሱ። የሶሪያ ከፍተኛ የክርስቲያን መሪ በእሁድ ቀን በርካታ ሰዎችን ለገደለው የቤተክርስቲያን ፍንዳታ የሶሪ...
29/06/2025

የሶሪያ ከፍተኛ የክርስቲያን መሪዎች በቤተክርስቲያን የቦምብ ጥቃት ላይ መንግስትን ወቀሱ።

የሶሪያ ከፍተኛ የክርስቲያን መሪ በእሁድ ቀን በርካታ ሰዎችን ለገደለው የቤተክርስቲያን ፍንዳታ የሶሪያውን ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራአን መንግስትን ወቅሰዋል ፣በስደት ላይ ያሉ ክርስቲያኖችም ሀዘናቸውን ገለጸዋል።

ባሳለፍነው እሁድ በደማስቆ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰው ፍንዳታ ከሞቱ 25 ሰዎች በተጨማሪ 59 ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል።
መሪዎቹ በመንግስት ጥበቃ በሚሰጠው ዋስትና ላይ መመካት አለመቻላቸውን እና ያላቸውን ጥርጣቄ አጠናክሯል ተብሏል።

በአንጾኪያ የግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ጆን (ኤክስ) ያዚጊ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ “በፍቅር እና በአክብሮት ክቡር ፕሬዝደንት ሀዘናችሁን ለመግለፅ በስልክ መነጋገራቸውን ገልጸው ለስልክ ጥሪው አመስጋኞች ነን ግን የተፈጠረው ወንጀል ከዚህ ትንሽ ይበልጣል ሲሉ ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ "ጨካኝ እና ፈሪነት የተሞላበት ጥቃት" ሲል የገለፀውን ድርጊት አውግዞ የሶሪያ መንግስት ሁከት ፈጣሪዎችን ሁሉ በህግ እንዲጠየቅ እና የሃይማኖት እና የጎሳ አባላትን ጨምሮ የመላው ሶሪያውያን ደህንነት እንዲያረጋግጥ ጠይቋል።

ዋሽንግተን የሶሪያን መንግስት “በሀገራቸው እና በሰፊው ቀጠና ላይ አለመረጋጋት እና ስጋት ለመፍጠር ከሚፈልጉ ሃይሎች ጋር በሚዋጋበት ጊዜ” መደገፏን ቀጥላለች።

ክርስቲያኖች ከጦርነት በፊት ከነበሩት 22 ሚሊዮን የሶሪያ ህዝብ 10 በመቶ ያህሉ ናቸው ነገር ግን በ 14 ግጭት ዓመታት ቁጥራቸው በስደት ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ሲሆን አሁን በሶሪያ እንደሚኖሩ የሚገመተው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ናቸው።

በሟቾች የቀብር ስነ-ስረዓት ላይ በሶሪያ አዲስ መንግስት ውስጥ ብቸኛዋ ክርስቲያን እና ብቸኛ ሴት የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሂንድ ካባዋት መገኘታቸውን የዎርዚ ኒውስ በዘገባው አክሎ ገልጿል።

እንደ ኦፕን ዶርስ መረጃ መረሰረት ሶሪያ ለክርስትና አስቸጋሪ ከሆኑ 50 ሀገራት መካከል 18ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በዮሐንስ ግርማ
Yom Media ዮም ሚድያ

እንኳን ለሊቀ መላእክቱ ለቅዱስ ገብርኤል በዓል አደረሳችሁ መላእኩ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ
26/06/2025

እንኳን ለሊቀ መላእክቱ ለቅዱስ ገብርኤል በዓል አደረሳችሁ
መላእኩ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ

ፈረንሳይ   ❤🙏Yom Media ዮም ሚድያ
22/06/2025

ፈረንሳይ ❤🙏
Yom Media ዮም ሚድያ

ምስክርነት 🙏❤️ከህመሙ እያገገመ ያለው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን 100 ሺህ ብር ለቤክርስቲያን ለገሰ::"ከተሰበሰበልኝ ብር ላይ 100 ሺህ ብር ለዳንኩባት ቤተክርስቲያን አስገባለሁ። ከዚህ በ...
22/06/2025

ምስክርነት 🙏❤️

ከህመሙ እያገገመ ያለው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን 100 ሺህ ብር ለቤክርስቲያን ለገሰ::

"ከተሰበሰበልኝ ብር ላይ 100 ሺህ ብር ለዳንኩባት ቤተክርስቲያን አስገባለሁ። ከዚህ በኋላም ሰርቼ ከማገኘው አንድ አስረኛውን አቅፋ ለተቀበለችኝ ቤተክርስቲያን እሰጣለሁ።"

ቤተክርስቲያን ከጎኑ እንደነበረች፣ በመንፈሳዊም ሆነ በሞራል ድጋፍ እንዳበረታታችው ያሳያል።

አሁን ሲያገግም ደግሞ ውለታዋን ባለመዘንጋት፣ ትንሽም ቢሆን ለረዳችው ቤተክርስቲያን ለመስጠት መወሰኑ እውነተኛ ምስጋናና የመንፈሳዊነት ጥግ እምነቱንና ቁርጠኝነቱን ያሳያል።።

ውለታዋ አለብኝ ያለው ጋዜጠኛው ከዚህ በኋላም ሰርቼ ከማገኘው አንድ አስረኛውን አቅፋ ለተቀበለችኝ ቤተክርስቲያን እሰጣለሁ ብሏል::

Via ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን

Yom Media ዮም ሚድያ

"ሁሉን ያደረገችልኝ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ነች።"ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴበዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን መርሐ ግብር ላይ ልምዱን እያካፈለ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የሃያ ሰባት ሪከርዶች ባ...
22/06/2025

"ሁሉን ያደረገችልኝ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ነች።"
ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

በዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን መርሐ ግብር ላይ ልምዱን እያካፈለ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የሃያ ሰባት ሪከርዶች ባለቤት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሩጫዬ ሁሉ ኪዳነ ምሕረት ረዳቴና አማላጄ ናት ሲል ተናግሯል።

የሕይወት ውጣ ውረድ እና ፈተናን በከፍተኛ ትዕግስትና ብርታት ያለፍኩት በእናቴ በቅድስት ድንግል ማርያም ብርታት ነው ብሏል።

በሽርፍራፌ ሴኮንዶች ብዙ አጥቼ ብዙ አግኝቼአለሁ ያለው ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የጊዜን ዋጋ ትርጉም በመስጠት ራዕይን ማሳካት ይገባል ሲል መልእክት አስተላልፏል።

በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ ሦስተኛ ወለል ላይ እየተካሄደ የሚገኘው መርሐ ግብር እንደቀጠለ ነው።
Yom Media ዮም ሚድያ
ምንጭ: ማኅብረ ቅዱሳን

በሶርያ ምሥራቅ ደማስቆ በቅዱስ ኤልያስ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የሽብር ጥቃት ደረሰሰኔ 15 ቀን 2025 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)ከደማስቆ በስተምሥራቅ በድዋይሌህ አካባቢ ...
22/06/2025

በሶርያ ምሥራቅ ደማስቆ በቅዱስ ኤልያስ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የሽብር ጥቃት ደረሰ

ሰኔ 15 ቀን 2025 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
ከደማስቆ በስተምሥራቅ በድዋይሌህ አካባቢ የሚገኘው የቅዱስ ኤልያስ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በቅዳሴ ላይ በነበሩበት ወቅት ኢላማ የተደረገ ሲሆን በጥቃቱ ከ15 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በትንሹ 20 ሰዎች መቁሰላቸውን የሶሪያ አረብ የዜና አገልግሎት (SANA) እና በርካታ አለም አቀፍ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል።

በሩሲያ የዜና አገልግሎት ኖቮስቲ የዘገበው የመጀመርያ ዘገባዎች እንዳመለከቱት አንድ አጥፍቶ ጠፊ በጸሎት ወቅት ወደ ቤተክርስቲያኑ በመግባት በነበሩት ምእመናን ላይ ተኩስ በመክፈት ድንጋጤ ፈጥሯል። ከዚያም የሚፈነዳ ቀበቶ በማፈንዳት ከፍተኛ ፍንዳታ በማድረግ የቤተክርስቲያኑ ክፍሎች ወድሞ የበርካታ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።

አል-ኢኽባሪያ ቲቪ እንደዘገበው የሀገር ውስጥ የጸጥታ ሃይሎች የጥቃቱን መንስኤ ለማወቅ የወንጀል ምርመራ መጀመሩን ዘግቧል። ይህ በንዲህ እንዳለ የአምቡላንስ እና የሲቪል መከላከያ ቡድን ቁስለኛዎቹን በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታሎች በማጓጓዝ ከፍተኛ የህክምና ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ነው የተገለጸው።

የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን በደማስቆ እና በአካባቢዋ ከሚገኙት ታዋቂ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ነው። ከነቢዩ ኤልያስ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በጥንታዊ እና ታሪካዊነቱ ይታወቃል።
Yom Media ዮም ሚድያ

19/06/2025

አእላፋት የተዋሕዶ ልጆች በሰሜን አሜሪካ ቅዳሜ እና እሁድ ሰኔ 28 እና 29 (July 5 and 6) ተአምር ሊሠሩ ነው:: እልፍ አእላፋት ኦርቶዶክሳውያን በነጫጭ ልብሶቻቸው አሸብርቀው በቅዱስ ያሬድ ዜማ ብፀዕት እያሉ ሊያወድሷት በሰኔ ወር መጨረሻ ተቀጣጥረዋል:: ዳግመኛ በባዕድ አገር ታሪክ ሊደገም ነው::
"ዝማሬ ሶልያና"
አዘጋጅ በሰሜን አሜሪካ ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
አድራሻ: 6935 Columbia Pike Annandale ,VA 22003
ሰዓት ሁለቱንም ቀን ከ 3 PM -8 PM
ለበለጠ መረጃ: 5714943101

አእላፋት የተዋሕዶ ልጆች በሰሜን አሜሪካ ቅዳሜ እና እሁድ ሰኔ 28 እና 29 (July 5 and 6) ተአምር ሊሠሩ ነው::  እልፍ አእላፋት ኦርቶዶክሳውያን በነጫጭ ልብሶቻቸው አሸብርቀው በቅ...
19/06/2025

አእላፋት የተዋሕዶ ልጆች በሰሜን አሜሪካ ቅዳሜ እና እሁድ ሰኔ 28 እና 29 (July 5 and 6) ተአምር ሊሠሩ ነው:: እልፍ አእላፋት ኦርቶዶክሳውያን በነጫጭ ልብሶቻቸው አሸብርቀው በቅዱስ ያሬድ ዜማ ብፀዕት እያሉ ሊያወድሷት በሰኔ ወር መጨረሻ ተቀጣጥረዋል:: ዳግመኛ በባዕድ አገር ታሪክ ሊደገም ነው::
"ዝማሬ ሶልያና"
አዘጋጅ በሰሜን አሜሪካ ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
አድራሻ: 6935 Columbia Pike Annandale ,VA 22003
ሰዓት ሁለቱንም ቀን ከ 3 PM -8 PM
ለበለጠ መረጃ: 5714943101
Yom Media ዮም ሚድያ

15/06/2025

Address

Hoàng Xá

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yom Media ዮም ሚድያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yom Media ዮም ሚድያ:

Share