Endalk Fm

Endalk Fm የሀሳብ ድሀ ላላመሆን መረጃ ሀብት ማድረግ።

  እዚህ ቦታ ተፈጥሮ አፍ አውጥቶ ይናገራል።  ለዓይን ማረፊያ፣ ለነፍስ እረፍትና ለአእምሮ ሰላምን የሚሰጥ የፈጥሮ  ስጦታ የተፈጥሮ ቦታ ነው። ይህ ውበት በተለያዩ መልኮች ይገለጣል።እኔ ምደ...
12/12/2025



እዚህ ቦታ ተፈጥሮ አፍ አውጥቶ ይናገራል። ለዓይን ማረፊያ፣ ለነፍስ እረፍትና ለአእምሮ ሰላምን የሚሰጥ የፈጥሮ ስጦታ የተፈጥሮ ቦታ ነው።

ይህ ውበት በተለያዩ መልኮች ይገለጣል።
እኔ ምደሰተው እኔ ምረካው ከሰማይ ጠቀስ ተራሮች ግርማ ሞገስ እስከ ለምለም ሜዳዎች ስፋት አይደለም ።

የኔዋ የልጅነት እድሜ መጋዣዬ። በዚች ቦታ እርፍ ስል ነው።
ባህር ማዶ አያስመኝ ። ከአድማስ የረዘመ የባህር ዳርቻ እስከ ጥልቅና ንጹህ ወንዞች ፍሰት ድረስ አያስጎመጅ ።

ይህ ከጀርባዬ ያለው ተፈጥሮ በውብ ብሩሽ ሰአሊ የሳለው የሚመስል ተፈጥሯዊ ገፅታ ነው። ግን ተፈጥሯዊ ነው።

በፀሐይ መውጫ ወይም መጥለቂያ ጊዜ ተራሮችና ደመናዎች የሚላበሱት ቀለማት፣ የዛፎችና የቁጥቋጦዎች አረንጓዴነት፣ እንዲሁም የዱር አራዊትና የአእዋፍ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚያሳየው ህያውነት እጅግ ማራኪ ምድር ነው።

ንጹህ አየር፣ በቅጠሎች መካከል የሚነፍሰው ልስልስ ያለ ነፋስና የአእዋፍ ዝማሬ ለአእምሮ መረጋጋትና ለመንፈስ እርካታ ያጎናጽፋል ።

የከተማ ጩኸትና ግርግር ርቀን እውነተኛ ሰላምን የምናገኝበት ነው። በተፈጥሮ ውስጥ መመላለስ፣ አንዱ ጫፍ ላይ ሆኖ አድማስን መቃኘት ወይም በወንዝ ዳርቻ ተቀምጦ ማሰላሰል የሰውን ልጅ ከተፈጥሮው ዓለም ጋር የሚያገናኝና የስነ ልቦና ጤንነትን የሚያጎለብት ነው።

እዚህ ቦታ የፍጭም ፉርጥ ላይ ሆነህ አይንህ ያማትራል። ዋዠራ ዳባ ኗገጀ ጅማ ወለኔ ወሸርቤ ወልቂጤ ያስቃኛል

09/12/2025
ሃገር   ማፅናት ማንነት  #ማሻገር እንደ ሰይፈ‎አቶ ሰይፈ ወልዴ  ሃገር መውደድ ፣ባህል ፣ወግ  መጠበቅ  ፣ባህል መጎልበት  በርቱዕ ቃላት በጣፈጠ አንደበት በአማርኛ እና ጉራጊኛ ቋንቋ  ገ...
08/12/2025

ሃገር ማፅናት ማንነት #ማሻገር እንደ ሰይፈ

‎አቶ ሰይፈ ወልዴ ሃገር መውደድ ፣ባህል ፣ወግ መጠበቅ ፣ባህል መጎልበት በርቱዕ ቃላት በጣፈጠ አንደበት በአማርኛ እና ጉራጊኛ ቋንቋ ገጥም ከምክር ጋር ይመርቁ ነበር።

‎ ለጉራጌ ባህልና ቋንቋ ማደግ ጉዳይ እንቅልፍ ይነሳቸው ነበር።
ሞት የማይቀርብበት ጉዞ ነውና። በጣም ያሳዝናል ውጥናቸው ብዙ አለና ።

ነፍስ ይማር ወዳጅ ዘመድ መፅናናትን ያድል።



06/12/2025
ጀንቦሮ _ጉመር  _ ጉራጌ  _ኢትዮጵያ _ዓለም ፎቶውን ሳላውቅ አንስቶ የላከልኝ ሙባሪክ ጌረሞ ሲሆን ለምን እንዳነሳኝ ስጠይቀው ከተመራማሪ እና ዳይሬክተሩ ቤተል ነክር ስራ አጠያየቅህ ምርቱ ...
04/12/2025

ጀንቦሮ _ጉመር _ ጉራጌ _ኢትዮጵያ _ዓለም

ፎቶውን ሳላውቅ አንስቶ የላከልኝ ሙባሪክ ጌረሞ ሲሆን ለምን እንዳነሳኝ ስጠይቀው ከተመራማሪ እና ዳይሬክተሩ ቤተል ነክር ስራ አጠያየቅህ ምርቱ እፍስ አድርገህ እያመላከትከው በመደነቅ ይመስላል አለኝ።
እውነት ነው ። ውስጤን ተረድቶ ከፊቴ አንብቦ ነው።

የወልቂጤ ሚሰራቸው ተግባራት እጅ ከመዳፍ የሚያስጭኑ ናቸው።
ይህ ምታዩት ሰብል ስንዴ አይደለም ። የአጃ ገብስ ከስንዴ ጋር በማዳቀል የተፈጠረ አዲስ ዝርያ ነው።

የንግድ በዛሩና አውደ ርዕዩ ምርቶችን ለማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ምቹ እድል ፈጥሯል  ወልቂጤ፤ ሕዳር 25/2018 (ኢዜአ)፦የንግድ በዛሩና አውደ ርዕዩ ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና...
04/12/2025

የንግድ በዛሩና አውደ ርዕዩ ምርቶችን ለማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ምቹ እድል ፈጥሯል


ወልቂጤ፤ ሕዳር 25/2018 (ኢዜአ)፦የንግድ በዛሩና አውደ ርዕዩ ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ምቹ እድል መፍጠሩን ኢንተርፕራዞችና ማህበራት ገለጹ፡፡

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት በወልቂጤ ከተማ የንግድ ባዛርና አውደ ርዕይ እየተካሄደ ነው።
በባዛሩ ላይ የተሳተፉ ኢንተርፕይዞችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እንደገለጹት፤ ባዛሩ ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ፣ የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጠናከርና የገበያ ትስስር ለመፍጠር አግዟቸዋል።
በንግድና ባዛሩ ከተሳተፉ የኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች መካከል ከስልጤ ዞን የመጣችው ወይዘሪት አክራም አዝማች፤ የባህል አልባሳት ይዛ መቅረቧን ገልጻለች፡፡
በዚህም የክልሉን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህል ከማስተዋወቅ ባለፈ ምርቶቿን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንደሆነችና አዳዲስ የገበያ ትስስር መፍጠሯን ነው ያስረዳቸው፡፡በዓሉ ለብዙዎች የሥራ እድልም እየፈጠረ መሆኑን ተናግራለች፡፡

ከሆሳዕና ከተማ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ይዘው በባዛሩ ላይ እየተሳተፉ ያሉት አቶ ተሻለ ተስፋዬ በበኩላቸው፤ በባዛሩ ባገኙት የገበያ እድል በኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
ከገበያ እድል ባለፈ የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጠናከርና የባህል ልውውጥ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከወልቂጤና ሃላባ ቁሊቶ ከተማ የባልትና ውጤቶችን ይዘው የተሳተፉት ኢንተርፕራይዞች በበኩላቸው፤ የንግድ ባዘሩና አውደ ርዕዩ አምራቹን ከሸማቹ በማገናኘት ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢንርፕራይዞቹ ሰብሳቢዎች ወጣት ፀጋዬ ብዛ እና አብራክ ወልደጊዮርጊስ፤ በዓሉ ኢትዮጵያዊያን ካሉበት በመሰባሰብ ደምቀው የሚታዩበት ብቻ ሳይሆን የሚገበያዩበትንም እድል ይዞ መምጣቱንም ገልጸዋል።
ለበዓሉ በወልቂጤ ከተማ የተከፈተው የንግድ ባዛርና አውደርዕይ ምርቶቻቸውን በስፋት ለማቅረብና የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡

በባዛሩ ላይ ግብይት ሲፈጽሙ የነበሩት አቶ ፈቀደ ደድገባ እና ወይዘሮ ጸጋነሽ ኮርማ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ባዛሩ ከበዓሉ ጋር ተያይዞ መከፈቱ የተለያዩ ባህላዊ አልባሳትና ቁሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በቅርበት ለመሸመት አስችሏቸዋል።
እርስ በርስ የባህል ልውውጥ ለማድረግ እያገዘ መሆኑንም ነው ጠቅሰዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፤ የንግድ ባዛርና አውደ ርዕዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እሴቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

በባዛሩ ከ200 በላይ አምራቾችና ነጋዴዎች መሳተፋቸውን ጠቁመው የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የእደ ጥበብ ውጤቶችም መቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡

እስከ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየው ባዛርና አውደርዕይ የገበያ ትስስር ለመፍጠር፣ ልምድ ለመለዋወጥና የእርስ በእርስ ግንኙነትን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለውም ተመላክቷል።

02/12/2025

አስደንጋጭ ነው። መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል

01/12/2025

Address

Wolkite
KEY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Endalk Fm posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share