Yonas Tade

Yonas Tade ይህ ቻናል መንፈሳዊ መልእክቶች እና ዝማሬዎች ይተላለፉበታል:

03/09/2025

ወዳጀ ሆይ👈
አስተውል
ቆሞ መሄድህ መብላት መጠጣትህ ጥሩ መልበስ ጥሩ መናገር ወይንም ሀብት ክብርና ዝናህ ያንተን ሰውነት በፍጹም ሊያረጋግጡልህ አይችሉምና፡፡

ይልቅ አትዘግይ! አሁኑኑ ራስህን ፈልግ. ዙሪያህንም አስስ ያንተ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድረስላቸው ፡፡

ጊዜህን ባግባቡ ተጠቀም ከሚያጸጽቱህ ነገሮች ቀድመህ ለመቆጠብ ሞክር ለህሊናህ እንጅ ለስሜትህም አትገዛ ላለፈ ነገር እየተጸጸትክ ቀሪ ጊዜህን አታባክን፤ ከራስህ ከፍታ ይልቅ ለሰዎችና ለሃገርህ ከበሬታ ይኑርህ ፡፡

የወደቁትን አንሳ ያዘኑትን አጽናና የተራቡትንም ሽራፊ ቁራሽ አትንፈግ፡ ባይኖርህም ፍቅር ስጣቸው እርሱ ከሁሉም ይበልጣልና! ለወሬ እጅ አትስጥ በጉዞህ ሂደት ውስጥ ለሚጮሁ ዉሾች ሁሉ አትደንግጥ አላማህን ለማሳካት በጽናት ጉዞህን ቀጥል ፡፡

ችግር መከራ ስቃይና ደስታንም አምኖ ለመቀበል ራስህን ዝግጁ አድርግ፤ ክፉን በክፉ ለመጋፈጥ ከመሞከር ይልቅ ውስጥህን በይቅርታና በመጸጸት ከተንኮል አጽዳ ፡፡

ከሰወች ጉዳትና ሞት ደስታን ወይም ሃብትን አትሻ! አትጠራጠር ያኔ! የንጹህ ልብ ህሊናና የዘላለም ደስታ ባለቤት የሃብታሞች ሁሉ ሃብታም …. የሰውም ሰው ነህ !

ስለዚህ ሰው ሁን!!!!

03/09/2025

" ሞገሳችን ክብራችን የመድኃኒታችን ቀንድ !
እሱን የምናምንበት የፍቅር አንድነታችን ምልክት፤ የምንጠጋበት የደህንነታችን ግድግዳ የማእዘን ማቆሚያ የህይወት ድንጋይ፤ የተሰበሰበ ወርቅ የተሸሸገ እንቁ የበዛ ወቄት አስር እልፍ ነጥር ወርቅ ፤ ያልተሰራ ልብስ ያልተፈተለ መጎናጸፊያ ፤ዱቄቱን ወደ መጣጣ የሳበ እርሾ ያለውን ያጣፈጠ ጨው፤ ቀላል ሸክም የለዘበ ቀምበር ፤ ወደ አባቱ ለመሄድ መንገድ ወደ አባቱ የሚያስገባ በር ይህ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

01/09/2025

አይሰማም አትበለው አንተም ትሰማለህ
አያይም ትላለህ ቸርነቱ በዝቶ ዛሬም ትኖራለህ
የት አለ? እያልከው ሁሌ ስታማርር ነገር እያበዛህ
በአባትነት ፍቅሩ ላይጥልህ ላይተውህ በደሙ የገዛህ
ሁሌም ከአንተ ጋር ነው በጣም የሚወድህ

29/08/2025

ጌታ ሆይ፤ ካንተ በላይ ዳኛ፣ ከእጅህም የላቀ ኃያል እጅ የለም። አቤቱታችን ለአንተ እንጂ ለማን ይሆናል? በአንተ የተመራ በማንም ሊሳሳት አይችልም። የኔ ሰላም ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ፤ አንተ የተውከው ግን እንደ አንተ ሌላ መሪ የለውም። ስምህ ይቀደስ!

29/08/2025

እግዚአብሔር ሆይ ከመበደላችን ይቅር ማለትህ
ከመዛላችን መበርታትህ ከመታከታችን ፍቅርህ
ይደንቃልና ተመስገን

29/08/2025

ጌታ ሆይ ለመናገር ጥበብ
ለመስማትም ማስተዋል
ለመኖርም ብርታት አንተ ሁነን::

"ተነሡ፥ እንሂድ"(የማርቆስ ወንጌል 14፥42)ተነሱ! ዛሬ አዲስ ቀን ነው፤ በብርሃን ለተሞላው ነገአችን ደግሞ አዲስ ጅማሬ!ተነሱ! ዛሬ ሁሉም ነገራችሁ የሚቀየርበት ቀን ነው፤ ተነሱ! ዛሬ እ...
26/08/2025

"ተነሡ፥ እንሂድ"
(የማርቆስ ወንጌል 14፥42)

ተነሱ! ዛሬ አዲስ ቀን ነው፤ በብርሃን ለተሞላው ነገአችን ደግሞ አዲስ ጅማሬ!
ተነሱ! ዛሬ ሁሉም ነገራችሁ የሚቀየርበት ቀን ነው፤ ተነሱ! ዛሬ እግዚአብሔር ሊያገኛችሁ ይወዳል፥ ሊባርካችሁ፥ ሊፈውሳችሁ፥ ሊቀድሳችሁ፥ ሊጠግናችሁ፥ ሊያድናችሁ፥ እንደ አዲስ ሊፈጥራችሁ፥ ከወደረኞቻችሁ እጅ ሊያድናችሁ፥ ወደ እረፍታችሁ ወደብ ሊያደርሳችሁ ወዷልና።
በጨለማ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ተኝታቹሃል እና ዛሬ ክርስቶስ ኢየሱስ ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ፥ ከምርኮ ወደ ፍፁም ነፃነት፥ ከምድራዊ ጉዳይ ወደ ሰማያዊ ጉዳይ ሊያሻግራችሁ መርከብ ሆኖ ይጠብቃቹሃል!

ጌታ እንዲህ ይላቹሃል፦ "ልጆቼ ሆይ ተነሱ እንሂድ! ከእናንተ ጋር ዘላለማዊ የሆነውን ዝምድና ፈለግሁ። ዛሬ ትግላችሁን ያየሁበት፥ ህመማችሁ ያመመኝ፥ ፀሎታችሁን የሰማሁበት ቀን ነውና ፈፅሜ ላድናችሁ መጣሁ። ዕድል ትሰጡኛላችሁ? ስለተራ ነገር ቃል አልገባላችሁም ነገር ግን ከእናንተ ጋር፥ ለእናንተ፥ በእናንተ ውስጥ እኖር ዘንድ፤ ልቤ ልባችሁ ውስጥ ፍቅሬ ፍቅራችሁ ውስጥ እንዲነግስ። ልጆቼ ሆይ እመኑኝ ድጋሚ ፈፅሞ ብቻችሁን አትጓዙም!"

አሜን! እናምንሃለን! እንታመናለን! እናመሰግንሃለን!

>>>>> ሰላም ለእናንተ ይሁን!

ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦቼ እንኳን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏
22/08/2025

ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦቼ እንኳን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏

21/08/2025
ሰላም ለሁላችሁ፤-ፈንዲሻ ለምንድን ነው እንዲህ አበባ የመሰልሽው ቢሏት እሳቱን ስለታገስኩት ነው  አንዳንድ ጓደኞቼ ግን እሳት ነካን ብለው ዘለው ከድስቱ ቢወጡ በእግር ተረጋግጠው ቀሩ በክብር...
20/08/2025

ሰላም ለሁላችሁ፤-ፈንዲሻ ለምንድን ነው እንዲህ አበባ የመሰልሽው ቢሏት እሳቱን ስለታገስኩት ነው አንዳንድ ጓደኞቼ ግን እሳት ነካን ብለው ዘለው ከድስቱ ቢወጡ በእግር ተረጋግጠው ቀሩ በክብር ወደ መሶቡ አልተገለበጡም አለች፡፡ፈተና ሰውን እንደአበባ የሚያፈካ ለስላሳ እሳት ነው፡፡ ያበስላል፣ አእምሮን ያሳድጋል ለእግዚአብሄር ምርጥ ዕቃ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በኑሮ ውጣ ውረድ ውስጥ የምታልፉ ሁሉ ከትግል በኃላ የሚሰጠውን በጎውን በረከት ለመቀበል መታገስ እንደሚገባ ከማሽላ ፍሬ እንማራለን፡፡ ቸኩለው ተባረው ከቤተክርስቲያን የሚወጡ፣ ወይም የኑሯቸውን ትግል አቋርጠው ተስፋ የሚቆርጡ፣ አገልግሎታቸውን የሚተው፣ ያላቸውን መልካም ምግባር ለሰው የሚከፍሉትን ዋጋ ርግፍ አድርገው የሚተው፣ ፈተና ወደቅን ብለው አለም ጨለማ ሆኖ የታያቸው ወጣቶች ሁሉ ተፈናጥረው ከወጡትና ተረግጠው ከቀሩት ትናንሽ ፍሬዎች ሊማሩ ይገባል፡፡ በለሱን የጠበቀ ፍሬውን ይበላል ተብሏል በመጽሐፍ፡፡ እባካችሁ ለሌሎች ሼር አድርጉት ተባረኩ፡፡
ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም

Address


Telephone

+14047865011

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yonas Tade posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yonas Tade:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share