ዮሐንስ ዋሌ ጓዴ - Yohannes Walie Guadie

  • Home
  • ዮሐንስ ዋሌ ጓዴ - Yohannes Walie Guadie

ዮሐንስ ዋሌ ጓዴ - Yohannes Walie Guadie Follow this page to get important information.

በምስራቅ አርሲ ዞን በ 3 ወረዳዎች በጥቅምት ወር ብቻ  25  የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች  ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች  በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህ...
31/10/2025

በምስራቅ አርሲ ዞን በ 3 ወረዳዎች በጥቅምት ወር ብቻ 25 የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቋሚ ሲኖዶስ መግለጫ አውጥቷል::

"በነጻነት የማምለክ ህገመንግስታዊ መብትን የሚጋፋ" ሲል የገለጸው ሲኖዶሱ: መንግስት ህግ እንዲያስከብር በመጠየቅ ግድያውን በጽኑ አውግዟል::

በሌላ በኩል: በምስራቅ አርሲ ዞን ተፈጸመ የተባለውን ግድያ በተመለከተ፣ የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ከድር "ፍጹም ውሸት ነው" ሲል አስተባብሏል::

♦️   አሰብ እና ኢትዮጵያ    ~ ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት የባህር መዳረሻ  አጥብቆ መፈለጉን ተከትሎ የኢትዮ-ኤርትራ ውጥረት  እያየለ መጥቷል::  ~ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ አመራ...
31/10/2025

♦️ አሰብ እና ኢትዮጵያ

~ ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት የባህር መዳረሻ አጥብቆ መፈለጉን ተከትሎ የኢትዮ-ኤርትራ ውጥረት እያየለ መጥቷል::

~ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ከአሰብ በቅርብ ርቀት የሚገኙ ቀጠናዎችን ከመጎብኘት ጀምሮ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም የቃላት ጦርነት ውስጥ ከገቡ ውለው አድረዋል::

~ የኤርትራ ከፍተኛ አመራሮች በበኩላቸው "ልንወረር ነው" በሚል ስጋት ከቃላት የመልስ ምት እስከ ግብጽ እና ጁቡቲ የደረሰ የአጋር ፍለጋ መኳትን ላይ ናቸው::

~ በዚህ የኢትዮጵያ መንግስት አሰብን የመቆጣጠር ዝንባሌ በተመለከተ ሁለት (2) ተቃራኒ ሀሳቦች ይንጸባረቃሉ!

1) አሰብ የኢትዮጵያ ቀደምት ግዛት ነበረች:: አሰብ የኤርትራ አካል ሳትሆን በወሎ ክፍለ-ሀገር ስር የነበረች ግዛት እንጂ የኤርትራ ታሪካዊ አካል አልነበረችም:: ኤርትራ ስትገነጠል በማናለብኝነት እና "በ ጠያቂ ማጣት" አሰብንም ጠቅልላ ተገነጠለች እንጂ አሰብን ጨምራ እንድትገነጠል የፈቀደም የወሰነም ኢትዮጵያዊ አካል አልነበረም:: ስለሆነም አሰብ ወደ ታሪካዊ ባለቤቷ ኢትዮጵያ መመለስ አለባት:: ይህን ደግሞ ማሳካት የሚቻለው አምባገነኑን የኤርትራ መንግስት በመለማመጥ ሳይሆን ታሪካዊ ግዛታችንን በወሰደበት የሀይል አማራጭ በመጠቀም ነው: የሚል ጠንካራ ሀሳብ ይንጸባረቃል::

2) አሰብ በየትኛውም መንገድ፣ በየትኛውም ሁኔታ ( በስህተትም ይሁን በትክክለኛ መንገድ) አንዴ የኤርትራ አካል ሆናለች:: በዚህም ኤርትራ ለ 40 አመታት ገደማ ሉዓላዊት ሀገር ሆና ስትኖር አሰብ የግዛቷ አካል ሆናለች:: ስለሆነም በሀይል አማራጭ አሰብን የማስመለስ ሂደት ፍጹም የተሳሳተ እና አለም-አቀፋዊ ውግዘትን የሚያስከትል ስህተት መስራት ብቻም ሳይሆን ዘላቂነት ያለው የወደብ ባለቤትነትን አያረጋግጥም:: የኢትዮጵያ መንግስት አሰብን በሀይል አማራጭ የግዛቱ አካል ቢያደርጋት እንኳን፣ የሻቢያ መንግስት በቀጠናው ትርምስ በመፍጠር ኢትዮጵያ በአሰብ ላይ ሰላማዊ እና የተረጋጋ የንግድ እንቅስቃሴ ማድረግ አትችልም:: ስለሆነም የሀይል አማራጭን ሳይሆን "ሰጥቶ በመቀበል መርህ" : ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጨረስ ያስፈልጋል የሚል አቋም ይደመጣል::

እርስዎስ ምን ይላሉ ❓❓

ኢትዮጵያ አሰብን በየትኛውም መንገድ የግዛቷ አካል ማድረጓ ግን የማያወላውል ውሳኔ መሆን አለበት የሚል የግል አቋም አለኝ (Out of poletical perspective):: መቼ፣ በማን እና በምን ሁኔታ የሚለው ሊያወያየን ይችላል!

< ሀሳብዎን ሲያካፍሉን በጨዋነት ይሁን >

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በጭብጨባ ያደመቁት አስተያየት ምንድነው ❓የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ መሀመድ ቆቤ የተናገሩት ንግግር ፤ ቀሪው የምክር ቤቱ አባል በጭብጨባ...
28/10/2025

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በጭብጨባ ያደመቁት አስተያየት ምንድነው ❓

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ መሀመድ ቆቤ የተናገሩት ንግግር ፤ ቀሪው የምክር ቤቱ አባል በጭብጨባ አድምቆታል፡፡

ሀሳቡ እንደሚከተለው ቀርቧል!

~ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተባበርን ፤ ከተደመርን ፤ ከተደማመጥን ከሰራን ምንም የሚሳነን እንደሌለ የሚያሳይ ታሪካዊ ድል ነው፡፡

~ በክቡሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ጥረት እና በዜጎች ትብብር በሀገራችን እየታየ ያለውን ለውጥ በግልጽ ማየት ያልቻሉ፤ በጥላቻ እና በቅናት የታወሩ፤ ባህር ውስጥ እየኖሩ የማይረጥቡ አሳዎች መኖራቸው እሙን ነው፡፡

~ አለም ያደነቀውን የለውጥ ፍሬ ማየት አለመቻል ማለት፤ በሁለት እጅ የጸሀይ ብርሀንን በመከለል መሬት ላይ እንዳያርፍ ለመቆጣጠር እንደማሰብ ነው፡፡ ልፋ ያለው በህልሙ ግንድ ተሸክሞ ይዞራል እንዲሉ፤ የሀሰት ወሬ ነጋሪ እና የአሉባልታ ወሬ አራጋቢዎች የኢትዮጵያ የእድገት ጉዞ እና የብልጽግና ግስጋሴያችንን ሊገቱ ይሞክራሉ፡፡ ሊያደናቅፉን አይችሉም፡፡

~ የአብይን ስም ለማጥፋት የሚደክሙ ሁሉ ቅዠታቸው አይሰምርላቸውም፡፡ ዝሆን እሾህ ወጋኝ ብሎ እንደማያነክስ ሁሉ፤ ዝሆን እንኳን ስለመወጋቱ ፡እሾህ መኖሩንም እንደማያስበው ሁሉ፤ ጉዟችን ይገሰግሳል፡፡ የእድገት ፍላጎታችንም እስከ ሰገነቱ ድረስ በትወልድ ቅብብሎሽ ይቀጥላል፡፡

( የተከበሩ መሀመድ ቆቤ)

በዚህ ሀሳብ ላይ ምን አስተያየት አልዎት ❓❓❓

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ  እንደተጠበቀው ጠንከር ያለ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የህዳሴ ግድቡ ቢዘገይም መጠናቀቁን  በማመስገን የጀመረው ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አንስቷል፡፡1) መሬት ላ...
28/10/2025

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እንደተጠበቀው ጠንከር ያለ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
የህዳሴ ግድቡ ቢዘገይም መጠናቀቁን በማመስገን የጀመረው ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አንስቷል፡፡

1) መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ የህዝቡን ጥያቄ ማቅረብ ተስፈኛነት እንጂ ጨለምተኛነት አይደለም ያለው ዶክተሩ፡ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተቀሰቀሱ ግጭቶች ተባብሰው ቀጥለዋል፡፡ በእነዚህ ግጭቶች የተጎዱ ንጹሀን ነዋሪዎች እና የንጹሀን መሰረተ_ልማት ጉዳቶች ቁጥር በግልጽ ሊነግሩን ይችላሉ ወይ ?
2) መንግስት ችግሮችን ለመፍታት ጽንፈኛ እና አሸባሪ የሚሏቸውን ቡድኖች ከመውጋት ባለፈ ለሁለቱ ክልሎች ከወታደራዊ አማራጮች ውጪ ያሉ ፖለቲካዊ መፍትሄዎችን ለመስጠት ለምን አይሰራም?

3) የኢትዮጵያ ህዝብ ተንቀሳቅሶ በሰላም ሰርቶ መኖር አቅቶታል፡፡ የሰላም እጦት ሰልችቶታል፡፡ሀገራችን እንደ ኮሎምብያ ከውስጥ ታጣቂዎች ጋር ለ 50 አመታት ስትዋጋ አትኖርም፡፡ በህግ ማስከበር ስም የሚወሰድ የዘፈቀደ እስር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የፖለቲካ እና የህሌና እስረኞች ጉዳይ እልበት እንዲሰጠው ብንጠይቅም ምላሽ እየተሰጠ አይደለም፡፡ በዚህ ሁኔታ ቀጣዩ ምርጫ ነጻ እና ፍትሀዊ እንደሚሆን ምን አይነት ዋስትና ይኖራል?

4) መንግስት ዋና ትኩረቱን በአፋጣኝ እልባት ከሚፈልጉ በሀገር ውስጥ ያሉ የጸጥታ ችግሮች ላይ ከማዋል ይልቅ ወደ ሀገር ውጪ እና ወደ ቀይ ባህር አዙሯል፡፡ መንግስት ዋና ትኩረቱን ለምን ከራሱ ህዝብ እና ከራሱ ሀገር ችግር ጋር አያደርግም ?

5) መንግስት አስር (10) ድስት ጥዶ አንዱንም ሳያማስል እንደ ማሳረር ነው፡፡ መንግስት አንዴ ከኤርትራ ጋር፤ አንዴ ከሶማሊያ ጋር፤ ሌላ ግዜ ከጁቡቲ ጋር የሚደረግ ሙከራ ነገር ግን ፍሬ የማያፈራ መፍጨርጨሮች ይታያሉ፡፡ መንግስት ከትግራይ ሀይሎች ጋር ከፍተኛ መካረር ውስጥ ገብቷል፡፡ እንደ ሀገር ስንት ትውልድ እየበላን እንቀጥላለን? ካለፈው ስህተታችን የምንማረው መቼ ነው? መንግስት ከእነዚህ ታጣቂ ሀይሎች ጋር በሰላማዊ እና በድርድር ችግሮችን እንዲፈታ፡ ከቀይ ባህር ጋር የገባበትን ውጥረትም በህጋዊ እና ሰጥቶ መቀበል መርህ እንዲያስተካክል እጠይቃለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

( ድ/ር ደሳለኝ ጫኔ )

ይህ ምስል  ፌስቡክ ላይ ሲዘዋወር  ተመለከትኩ::  አርቲስትም አክቲቪስትም ነኝ  የምትለዋ  ቤተልሄም ዳኛቸውን ጨምሮ አንዳንድ ግለሰቦች  ይህን ፎጣ መልበሳቸውን  ተቃውመው፣ አውግዘው ጽፈዋ...
27/10/2025

ይህ ምስል ፌስቡክ ላይ ሲዘዋወር ተመለከትኩ:: አርቲስትም አክቲቪስትም ነኝ የምትለዋ ቤተልሄም ዳኛቸውን ጨምሮ አንዳንድ ግለሰቦች ይህን ፎጣ መልበሳቸውን ተቃውመው፣ አውግዘው ጽፈዋል::

" × " ምልክት አድርጎ በአደባባይ ይህን ፎጣ አትልበሱ፣ የጎጃምን ባህል አታቆሽሹ፣ ይህ ፎጣ የጎጃም ባህላዊ አልባሳት አይደለም የሚሉ መልክቶችም ተላልፈውበታል::

የፎጣውን ክብር የሚቀንስ ወይም ከመነሻው የዚህን ፎጣ ባለቤቱን (የጎጃምን) ክብር የሚያጎድፍ ምን የሚታይ ነገር አለ? የጎጃም ባህላዊ ልብስ ቢሆንስ ጉዳቱ ምንድነው? ፎጣ ለባሽ እየተባለ ሲሰደብ የነበረው ማህበረሰብ፣ በድፍረት በክብር ለብሶት በአደባባይ እንዲታይ እየተደረገ ባለው ሂደት ውስጥ "አትልበሱት" የሚል ትችት ከአንድ "አክቲቪስት ነኝ ባይ" የሚጠበቅ ነው ወይ?

ምናልባት የልብሱን ስያሜ በተመለከተ ውይይት ሊያስፈልገው ይችላል:: "ጎጃም አዘነ" የሚል ስያሜ ያለው ይህ ፎጣ ፣ ስያሜው መቀየር አለበት በሚል ወደ "ጎጃም አበበ" የሚል ስም የተቀየረ መሆኑን የሚያመላክቱ ጭምጭምታዎች አሉ:: በማን እና መቼ እንደተቀየረ ተጨባጭ ማስረጃ ባይኖረኝም:: የሆነው ሆኖ የፎጣውን በአደባባይ መለበስ በተለይም በአርቱ ዘርፍ በስራቸው ላይ ማካተታቸው ተቃውሞ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም::

ነገ በሚካሄደው የህዝብ ተወካዮች መደበኛ ስብሰባ ላይ      ከ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠንከር ያለ ጥያቄ  እጠብቃለሁ!
27/10/2025

ነገ በሚካሄደው የህዝብ ተወካዮች መደበኛ ስብሰባ ላይ ከ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠንከር ያለ ጥያቄ እጠብቃለሁ!

አቶ ልደቱ አያሌው በተደጋጋሚ   " የከሰርኩ ፖለቲከኛ ነኝ ፣ ለ 30  አመታት ያህል  በፖለቲካው አለም ውስጥ ታግያለሁ ነገር ግን ፍሬ አላፈራሁም፣ ተጨባጭ ለውጥም አላመጣሁም፣ በዚህም የከ...
26/10/2025

አቶ ልደቱ አያሌው በተደጋጋሚ " የከሰርኩ ፖለቲከኛ ነኝ ፣ ለ 30 አመታት ያህል በፖለቲካው አለም ውስጥ ታግያለሁ ነገር ግን ፍሬ አላፈራሁም፣ ተጨባጭ ለውጥም አላመጣሁም፣ በዚህም የከሰርኩ ከንቱ ፖለቲከኛ ነኝ":: ሲል ይደመጣል::

የጨበጠው ሁሉ የሚበተንበት፣ የገባበት ሁሉ የሚፈርስበት ፖለቲከኛው ልደቱ አያሌው፣ ላለፉት 30 አመታት የከሰረበትን በመድገም፣ ለቀጣይ ተጨማሪ 30 አመታት ለመክሰር የወሰነ ይመስላል::

ስለ ሀብታሙ አያሌው እና Ethio 360  አሁን ላይ ምን ይሰማችሗል?ከተወሰኑ ግዜያት በፊት "ጋዜጠኝነት እና  የህዝብ ድምጽ መሆን  ማን  እንደ እኛ"   ሲሉ የነበሩት  እነ ሀብታሙ አያሌ...
25/10/2025

ስለ ሀብታሙ አያሌው እና Ethio 360 አሁን ላይ ምን ይሰማችሗል?

ከተወሰኑ ግዜያት በፊት "ጋዜጠኝነት እና የህዝብ ድምጽ መሆን ማን እንደ እኛ" ሲሉ የነበሩት እነ ሀብታሙ አያሌው አሁን ላይ ቋንቋቸው ሁሉ የተደበላለቀ ይመስላል::

ተከፋፍለው እና ተሰነጣጥቀው የእርስ በርስ ቡጢ ጀምረዋል:: ሀብታሙ "እናንተን አዝየ አልቀጥልም" ያለ ሲሆን: እነ እየሩስ ደግሞ "አተን አዝለን አንቀጥልም" የሚል የመተዛዘል ፉክክር ላይ ናቸው::

"እኔ ያልኩትን የማይቀበል ሁሉ ይፈርሳል" በሚል የሚታወቀው ሀብታሙ: አሁን ላይ የራሱን ግለሰብ-መር ተቋምም እያፈረሰው ቀጥሏል::

ኢቲዮ ፎረም (Ethio Forum)  በሚል የዩቲዩብ ሚዲያ የሚታወቁት  ጋዜጠኞች: ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና ጋዜጠኛ አበበ ባዩ "ለሰርግ ጥሪ ወደ ኬንያ እየሄድን ነው" በሚል ሰበብ ወይም ...
23/10/2025

ኢቲዮ ፎረም (Ethio Forum) በሚል የዩቲዩብ ሚዲያ የሚታወቁት ጋዜጠኞች: ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና ጋዜጠኛ አበበ ባዩ "ለሰርግ ጥሪ ወደ ኬንያ እየሄድን ነው" በሚል ሰበብ ወይም ማታለያ ከሀገር በመውጣት መቀመጫቸውን ውጪ ሀገር ካደረጉ ሰነባብተዋል::

ኢትዮ ፎረም እጅግ ፈጣን የተከታይ ቁጥር እያገኘ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከ 1 ሚሊዮን 290 ሺህ በላይ ተከታይ (subscribers) ያለው ሚዲያ ነው:: በትንታኔው ያየሰው ሽመልስ : በዜና አቅራቢነት ደግሞ አበበ ባዩ ይታወቃሉ:: ነገ ግን በዚህ ሚዲያ በዋናነትም በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦች ይንጸባረቃሉ::

ለአብነትም:-

1) የተወሰኑ ግለሰቦች ያየሰው "በህወሀት ፓርቲ የተጠመቀ፣ ከ ትህነግ/ ህወሀት ውጪ ሌላ ፓርቲ ያለ እስከማይመስለው ድረስ ለህወሀት ፍጹም ድጋፍ ያደርጋል:: ኢትዮጵያ በህወሀት እስካልተመራች ድረስ ሀገር ሆና መቀጠል አትችልም የሚል ደፋር አቋም እስከመያዝ የደረሰ ነው" በማለት ያየሰውን (Ethioforum) አጥብቀው ይቃወሙታል:: ያወግዙታልም::

2) የተወሰኑ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ደግሞ ያየሰው ሽመልስ "የአማራን ሙሁራን እና ሊሂቃን አጥብቆ የሚጠላ፣ የሚጸየፍ፣ የሚንቅ፣ በዚህም የአማራን ሙሁራን እና ሊሂቃንን (ፖለቲከኞችን ፣ መምህራንን፣ አክቲቪስቶችን እና ሌሎችንም) ስማቸውን ሲያጠለሽ እና ጭቃ ሲቀባ የሚደመጥ ጋዜጠኛ ነው ይሉታል:: እንደ ሙጀሌ: አማራ ሙሁራን እና ሊሂቃን ላይ ተጣብቆ ሰላማቸውን ሲያሳጣቸው፣ የዘወትር የአፍ መክፈቻው እነዚህን አካላት በመሳደብ ነው፣ ከትግራይ ሊሂቃን እና ሙሁራን ውጪ ሌላው አሰስ ገሰስ፣ ተራ አድር ባይ ተላላኪ እና ሆዳም ነው ብሎ የሚያምን በዚህም ተደጋጋሚ የትችት ወይም የስድብ ትንታኔ የሚሰራ ሰው ነው" ይላሉ:: በዚህ ምክንያት ያየሰው በግልጽ የአማራ ጠላት ነው ብለው ያወግዙታል:: ይጠሉታልም::

3) የተወሰኑ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ደግሞ ያየሰው ሽመልስ የታጠቁ ሀይሎችን በመደገፍ ሀገር ለማፍረስ የሚተጋ ጸረ-ልማት እና ጸረ-ብልጽግና ነው ይሉታል::

4) የተወሰኑ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ደግሞ ያየሰው ሽመልስ ወይም ኢትዮ ፎረም "ፍጹም ገለልተኛ፣ ለሙያው የታመነ እና ሚዛናዊ የሆነ፣ በሀቅ እና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ፣ ለተወሰኑ ቡድኖች ሳይሆን ለሰፊው የተገፋ ህዝብ ድምጽ የሚሆን፣ ግፍን እና ኢፍትሀዊነትን የሚያወግዝ ጋዜጠኛ እና ሚዲያ ነው በማለት አድናቆት ያጎርፉለታል::

እርስዎስ ምን ይላሉ ❓❓

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና አበበ ባዩ (Ethio forum) በየትኛው ምድብ ውስጥ ሊመደቡ ይችላሉ ❓❓

ትክክለኛ እንባ ይህ ነው!
20/10/2025

ትክክለኛ እንባ ይህ ነው!

ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ "Ethiopian Academy of Sciences EAS" በተሰኘ ሚድያ ላይ በድጋሜ  በግዕዝ ቋንቋ ዙሪያ የሚከተለውን ሀሳብ አጋርቷል፡፡~ ዶክተር በድሉ ከወራት በፊት ...
20/10/2025

ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ "Ethiopian Academy of Sciences EAS" በተሰኘ ሚድያ ላይ በድጋሜ በግዕዝ ቋንቋ ዙሪያ የሚከተለውን ሀሳብ አጋርቷል፡፡

~ ዶክተር በድሉ ከወራት በፊት ባስተላለፈው መልዕክቱ "የግዕዝ ቋንቋ ከ 25 ሺህ በታች ተናጋሪ ካለው የጠፋ ቋንቋ ነው" ብሎ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ አንድ ቋንቋ ከ 25 ሺህ በታች ተናጋሪ ካለው ሞተ ሳይሆን "አደጋ ውስጥ የገባ ቋንቋ ይባላል" ብሏል፡፡ በተለያየ ቀን የተናገረው ንግግር እርስ በራሱ የተጋጨ ነው፡፡

~ ግለሰቡ በሌላኛው ሀሳቡ "የጠፉ ቋንቋዎችን እንደገና ህይዎት እንዲዘሩ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለአብነትም 'ሂብሩ' የተባለ ቋንቋ ከጠፋ በኋላ እንደገና ህይዎት ዘርቶ የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንዲሆን ተደርጓል" የሚል ሀሳብ ከሰጠ በኋላ "ነገር ግን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግዕዝ ቋንቋን ማሳደግ እና ለአፍ መፍቻነት የሚጠቀምበት ማህበረሰብ መፍጠር አይቻልም" የሚል ሀሳብ አስተላልፏል፡፡ የጠፋውን ሂብሩ የተባለን ቋንቋ በማሳደግ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ማድረግ ከተቻለ ፡ ግዕዝን በማሳደግ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ማድረግ የማይቻልበትን ሁኔታ ግን አልተናገረም፡፡

ደግነት፣ ቅንነት፣ አዛኝነት፣ መልካምነትን  አሟልተው የያዙ❗አንደበታቸው ለአድማጭ የሚጣፍጥ❗ፍጹም ሰውነት የሚታይባቸው አባት❗ረጅም እድሜ ያድልዎት❗
15/10/2025

ደግነት፣ ቅንነት፣ አዛኝነት፣ መልካምነትን አሟልተው የያዙ❗

አንደበታቸው ለአድማጭ የሚጣፍጥ❗

ፍጹም ሰውነት የሚታይባቸው አባት❗

ረጅም እድሜ ያድልዎት❗

Address

United States Of America

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዮሐንስ ዋሌ ጓዴ - Yohannes Walie Guadie posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዮሐንስ ዋሌ ጓዴ - Yohannes Walie Guadie:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share