PP Fans

PP Fans Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from PP Fans, Digital creator, .

15/02/2024
27/07/2023

ብልጽግና በአዲስ እይታ ለአዲስ ለዉጥ የሚሠራ ፓርቲ ነዉ።ብልጽግና ኢትዮጵያን በሚመስል የሀሳብ ማዕቀፍ የተዋቀረ የለዉጥ ጎዳና ነዉ።

በሀሳብ የበላይነት የሚዳኝ፣ ብዝሃ አመለካከትን የሚያስተናግድ አካታች እሳቤ ነዉ ብልጽግና።

ብልጽግና ደማቅ የለዉጥ ራዕይን የሰነቀ፣ የተስፋ፣ የብርሃንና የስኬት መንገድ ነዉ።

የብልጽግናዉ ጉዞ በህዝባችን የነቃ ተሳትፎ ፣ በመሪዎቻችን ትጋት ታግዞ ስኬቶቹን እያፀና ፣ ፈተናዎችን ወደ እድል እያሸጋገረ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ከሚለያዩን ጉዳዮች ይልቅ የሚያቀራርቡን ምክንያቶች ኃያል ናቸዉ። ከጎዳሉን ይልቅ ፀጋዎቻችንና በረከቶቻችን ዘርፈ ብዙ ናቸዉ።ከመነጣጠል ይልቅ በመደማመጥ ፣ በአንድነት በመቆም እናተርፋለን።

መለያየት፣መከፋፈል ብርታታችንን ይቀማል። መተባበር ፣መሰባሰብ፣ መደመር ጥንካሬን ያጎናጽፋል ።ሰንረዳዳ ፣ ስንተሳሰብ ሥነ ልቦናዊ እርካታን፣በረከትን እናተርፋለን።

አንድነታችንን ለማዳከም ታቅደዉ የሚዘረጉ አደናጋሪ ትርክቶችን እየመከትን የጋራ ዕጣፈንታችን የተሻለ እንዲሆን በጋራ እንቁም።

27/07/2023

ብልፅግና ፓርቲ በትውልድ ቅብብሎሽ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እዉን የማድረግ ራዕይ ሰንቆ የተነሳ ፓርቲ ነው።

ብልፅግናን በማረጋገጥ ሂደት ሠላም መሠረታዊ አስፈላጊ እሴት ነው።
የብልፅግናው ጉዞ አልጋ በአልጋ እንደማይሆን የሚጠበቅ ቢሆንም የጉዞውን ሂደት የሚያደናቅፉ፣ የጉዞዉን ፍጥነት የሚገቱ የሠላምና የደህንነት ስጋቶችን ምንጫቸዉን በተቻለ መጠን ማድረቅ አስፈላጊ ነው።

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጡ ራዕይ እዉን እንዲሆን ራዕይው የአብዛኛው ህብረተሰብ የጋራ ራዕይ እንዲሆን፣ አንፃራዊ የሆነ የዓላማና የተግባር መሰናሰልንና አረዳድ መፍጠር ይጠይቃል።

በዓላማና በተግባር የተጣመረ የቁጭት መንፈስ በመፍጠር ፀጋዎቻችንን በማልማት ዘላቂና ተከታታይ እድገት ብቻ ሳይሆን ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ጥረት ዘላቂ ለማድረግ ሠላም መሠረታዊ ነዉ። የፖለቲካ ስብራቶቻችንን በማረም የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት እሴቶችን እና ትርክቶችን ማጎልበትም ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው።

በተለይም አካታች ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ የልዩነት ሀሳቦችን በአንፃራዊነት አቀራርቦ የይቅርታና የፍቅር ድልድይ በመዘርጋት፣ ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ የሚያስችል አይነተኛ መሣሪያ መሆኑን የተለያዩ ሀገራት ልምድ ያሳያል።

የአካታች ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ እና ዉጤቱ የተሳካ እንዲሆን ማድረግ ማለት ጠንካራ ዲሞክራሲን እና ዘላቂ ሠላምን ኢትዮጵያ ውስጥ ማረጋገጥ ማለት ነዉ።

ሠላም በጋራ ጥረት የሚሳካ መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ የጉዳያችንን ማዕከል የኢትዮጵያ ሠላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲሆን በማድረግ፣ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሰላም መሠረታዊ በመሆኑ ለዘላቂ ሠላም የየበኩላችንን ማበርከት አለብን።

27/07/2023
27/07/2023

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when PP Fans posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share