Z Fun Go Eran Da + $ Da-

  • Home
  • Z Fun Go Eran Da + $ Da-

Z Fun Go Eran Da + $ Da- To Tranisact Timley And Valuable Information For Public.

ለአንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት በሁለተኛውም አምሳ። የሚከፍሉትም ቢያጡ ለሁለቱም ተወላቸው። እንግዲህ ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው ማንኛው ነው?I'...
08/06/2025

ለአንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት በሁለተኛውም አምሳ።
የሚከፍሉትም ቢያጡ ለሁለቱም ተወላቸው። እንግዲህ ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው ማንኛው ነው?

I'm not telling you about money.

911

Sabbath

ምክንያቴ ብዙ ነው
via Gildo Kassa

ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፈደራል የተወሰነዉን የድምቱ ከተማ አስተዳዳር ወሰን ርክብክብ እንድደረግ እንጠይቃለን!!!የድምቱ ከተማ አስተዳደር  በወላይታ ዞን ዉስጥ ሻንቶ ከተማ አስተዳደር ጋር፣በዴሳ...
01/06/2025

ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፈደራል የተወሰነዉን የድምቱ ከተማ አስተዳዳር ወሰን ርክብክብ እንድደረግ እንጠይቃለን!!!
የድምቱ ከተማ አስተዳደር በወላይታ ዞን ዉስጥ ሻንቶ ከተማ አስተዳደር ጋር፣በዴሳ ከተማ አስተዳደር ጋር እና ቦምቤ ከተማ አስተዳደር ጋር አዉቅና ያገኘች መሆኗ ይታወቃል እና ብላቴ ጨርቾ -ብላቴ ማሰልጠኛ-አባላ አባያ መገነኛ መሆኗ ልዩ ያደርጋታል፡፡

ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱ ከተማ አስተዳደሮች የሕዝብ ጥያቄ መነሻ በማድረግ ርክብክብና የወሰን መካለል ሁሉንም ጨርሶ ባሉበት ወቅት የዲምቱ ከተማ አስተዳደር ከፈደራል ጀምሮ እሰከ ወረዳ ማዘጋጃ ድረስ የተወሰነዉን ወሰን በፕላን እንድመራ የሕዝብ ጥያቄ መሰረት ርክብክብ አለመጀመሩና አለመደረጉ የከተማይቷን ዕድገት ወደኋላ የሚጎትት ስለሆነ በዲምቱ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መድረክ ተፈጥሮ በፍጥነት መጀመር ያስፈልጋል፡፡

የቆየበት ምክንያት መጀመሪያ የተጠናው ጥናት ውድቅ እንድደርግ ከአንዳንድ አካላቶች ከፍተኛ ጫና እየተደረገ መሆኑ እንደሆነ መረጃ ሰጭዎች ይናገራሉ። የህዝብ ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልኩና የብልፅግና መንግስት የህዝብ ጥያቄን ቃል በገባው መሰረት መመለስ እንዳለበት የዚህ አከባቢ ህዝብ ያምናል፤ የድምቱ ከተማና አከባቢው ህዝብ ከተማ አስተዳደርነት ደረጃ መደራጀቱን ጥሩ መሆኑን አምነው ተቀብሏል።
ይህ ለአከባቢው ህዝብ ቀላል የማይባል የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝና አንዳንድ ጉዳዮችን በቅርበት ለመፍታት የሚያስችል ነው ብሎም ያምናል።

ሆኖም ግን መጀመሪያ የተጠናው ጥናት ወደ መሬት እንዳይወርድና እንዳይፈፀም የሚያደርጉ አካላቶች እንዳሉ ህዝቡ መረጃውን ማግኘት ችሏል፤ የድምቱ አከባቢ ህዝብ ፍላጎት ስምንቱን ፋንጎ ይዘው የመደራጀት ነበር፤ ያ ማለት በተቀመጠው የከተማ አስተዳደር መመሪያ ጋር የሚቃረን ሳይሆን የሚዛመድ ነው። መንግስት ህዝቡን ማስቀደምና ማዳመጥ እንዳለበት እናምናለን።

ይኸው በድምቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ መካለል አለባቸው ተብሎ በመጡ ባለሞያዎች ተጠንተው የተቀመጡ ቀበሌዎች (ድምቱ፤ ፋንጎ ኮይሻ፤ ፈንጎ ቦሎሶ፤ ፋንጎ ኦፋ፤ ፋንጎ ዳሞታ፤ ፋንጎ ሶሬ፤ ፋንጎ ቢጆ እና ብላቴ ኤታ) ናቸው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የዲምቱ ከተማ አስተዳደር ወደ አራት አቅጣጫ ማደግ እንዳማይችል የሚታይ ሀቅ ነው፤ በሁለት አቅጣጫ ብቻ ነው ማደግ የሚችለው።
ለዚህ ነው ብላቴ ጫርቾ ወደ ድምቱ መካለል አለበት ብለን እየጠቅን የቆየነው።

የከተማ አስተዳደር መመሪያ በሚፈቅደው መልክ በጥናቱ መሰረት ብቻ መፈፀም አለበት፤ ነገር ግን ይህ ሁሉ ተጥሰው ግን አሁን ከእኛ ጋር ወደ ፈርጅ ሶስት ያደጉ ከተማ አስተዳደሮች ስራ ሲገቡ የእኛ እስካሁን ከተጠናው ጥናት ቀበሌዎችን መቀነስ አለበት በሚል ከአንዳንድ አካላቶች በሚነሳው ሰበብ አሰባብ ሳይፈፀም እስካሁን ቆይቷል።

እነዚህ ሰዎች ሊከራከሩ ይችላሉ፤ በተጠናው ጥናት መሰረት መፈፀም የለበትም ልሉም ይችላሉ፤ ቀበሌዎች መቀነስ አለባቸው ማለትም ይችላሉ፤ ግን አይነካቸውም።

ስለዚህ በጥቂት ሰዎች ክርክር የህዝቡን ፍላጎት መገደብ እንደሌለበት የዞኑ መንግስት አውቀው በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ መስተካከል ያለበትን አስተካክሎ የተሰጠውን የድምቱ ከተማ አስተዳደር ህዝቡ በሚፈለገው ልክ ማስፈፀም እንዳለበት ጥሪ እናደርጋለን።
አሁን እየተወራ ያለው አሉባልታ ወሬ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል፤ የህዝብ ፍላጎት ብላቴ ጫርቾን ይዘው መደራጀት ነው። ከዚህ ውጪ የሚደረግ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለም።

የዎላይታ ንጉሠ ነገሥት የመንግሥት መዋቅርካዎ ----------------------------------- ንጉሥቡሻሻ ------------------------ --------- አልጋ ወራሽ ዱቢያ -...
31/05/2025

የዎላይታ ንጉሠ ነገሥት የመንግሥት መዋቅር

ካዎ ----------------------------------- ንጉሥ
ቡሻሻ ------------------------ --------- አልጋ ወራሽ
ዱቢያ ------------ አማማይ/ቃለ መሀላ አስፈጻሚ
ዛካራ ጉዳ ----------------------------- ትዕዛዛ አስተላላፊ
ዛባ ዳና ------------------------ ንብረት ክፍል ኃላፊ
ባሊሞላ ----------------------- የህዝብ ምክር ቤት
እራሻ ---------------- ጥገናና ዕድሳት ክፍል ኃላፊ
ዴንቻ ----------------------- የደሃ ዕንባ ጠባቂ
ወዳላ ጋንጂያ ----------------- ሪፖርተር/ጋዜጠኛ
ጋና --------------------------------- አምባሳደር
ሚጣ ሞጮና ------------------------------- ተዋጊ
ካሮ ሞጮና ---------------------- ፕሮቶኮል ክፍል
ወሼ ሞጮና ------------------- ዳር ድንበር ጠባቂ
አላና ዳና ---------------------- የወረዳ አስተዳደር
መንዲዳ ዳና ------------------------- ጭቃ ሹም
ኦቾሏ ----------------------- ደንና ዱር ልማት ኃላፊ
አሩዋ ---------------- የእንስሳ ሀብት ልማት ኃላፊ
ቅርናጃ ------ የንጉሥ ግቢ አስተዳዳሪ/ሚኒስቴር
ጣጬ ሞጮና -------------- ፖሊስ/ሕግ አስከባሪ
ማያ ------------------ ለቤተ መንግሥት ንብ አርቢ
ሁዱጋ --------------------------- የቀበሌ ተጠሪ
ቶንዲያ ------------------------ የንዑስ ቀበሌ ኃላፊ
አዱማ -------------------------------- የሰፈር ሹም

ለዚህ ፌስቡክ ገጽ አዲስ ከሆኑ በዚህ ዎንታ ሚዲያ ውስጥ በመግባት follow የሚለውን አንድ ጊዜ በመንካት አዳዲስ መረጃዎችን ያግኙ።

በጌታቸው ረዳ እና ጓዶቻቸው ይመራል የተባለው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የተሰኘ ፓርቲ ዛሬ በይፋ ተመዝግቧል።
26/05/2025

በጌታቸው ረዳ እና ጓዶቻቸው ይመራል የተባለው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የተሰኘ ፓርቲ ዛሬ በይፋ ተመዝግቧል።

MPoxን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫአዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት MPox አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።ተቋማቱ...
25/05/2025

MPoxን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት MPox አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ተቋማቱ በጋራ የሰጡት መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

25/05/2025
25/05/2025

ለመጀመሪያ ጊዜ ዎላይታ ውስጥ ዘመናዊ ት/ቤት ይክፈቱ ክቡር አቶ ቦጋለ ዋለሉ ማን ናቸው ?

ክቡር አቶ ቦጋለ ዋለሉ ከአባታቸው አቶ ላንጋና ባላና ከእናታቸው ወ/ሮ ሾጌ አዴቶ በ1902 ዓ.ም በዎላይታ አውራጃ ዳሞታ ጋሌ ወረዳ ሻንቶ ቀበሌ ተወለዱ፡፡ በልጅነታቸው ወደ አዲስ አበባ ተሰደው አጎታቸው ባሻ ዋለሉ አዴቶ (የእናት ወንድም) ዘንድ ፊደል ቆጥረው በአጎታቸው ስም እየተጠሩ ወደ ደብረ ሊባኖስ በመሄድ የቤተክህነት ትምህርት ተከታተሉ፡፡

ቀጥለውም ዘመናዊ ወደ ሆነው ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ገብተው መጽሐፍ እያዞሩ በመሸጥ በወቅቱ በነበረው የትምህርት ፖሊሲ መሠረት የመጨረሻ የሆነውን 8ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አጠናቀቁ፡፡

የዐ/ፄ ኃ/ሥላሴ ልጅ ልዕልት ተናኘወርቅ የጎፋ ገዥ የነበረውን ደጃዝማች በየነ መርዕድን አግብታ ስትኖር ምጥ ይዟት በዐፄ ኃ/ሥላሴ ትዕዛዝ ዶ/ር ሁፐር የተባለ ካናዳዊ ሐኪም ወደ ጎፋ ሲሄድ አስተርጓሚ በማስፈለጉ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ት/ቤት ተማሪ የነበሩ አቶ ቦጋለ ዋለሉ አብሯቸው በዎላይታ በኩል ጎፋ ይዘዋቸው ሄደው ተመልሰዋል፡፡

አቶ ቦጋለ ዋለሉ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ከዶ/ር ሁፐር ጋር መግባባት በመፍጠራቸው ልዕልት ዘነበወርቅ ሆስፒታል በቱርጁማንነት ተቀጥረው በመሥራት ላይ እያሉ ዐፄ ኃ/ሥላሴ ለጉብኝት ሲመጡ እዛው ተገናኝተው የሆስፒታሉን ኃላፊነት ሰጧቸው፡፡

በዚህም የፋሺስት ጠላት ሀገራችንን እስኪወር ድረስ በኃላፊነት ሲሰሩ ቆይተው ወደ ትውልድ መንደራቸው ተመለሱ፡፡ ዎላይታ ውስጥ ዘመናዊ ት/ቤት ከፍተው በመስራት ላይ እንዳሉ የከፈቱትን ተማሪ ቤት በራሳቸው እጅ እንዲያቃጥሉት ጠላት አዘዛቸው፡፡

ከፋሺስት ጦር ጋር በዚህ መልክ መተናነቁ ፋይዳቢስ መሆኑን የተረዱት መምህር ትዕዛዙን ፈፀሙለት፡፡ ይሁንና ትግላቸውን በሌላ መልክ በመቀጠላቸው ብዙውን የጠላት ዘመን በእስር ቤት ማሳለፋቸው አልቀረም፡፡

ያ ሁሉ አልፎ ሀገራችን የፋሺስት ጠላትን ድል እንዳደረገች ክቡር አቶ ቦጋለ ዋለሉ በ 31 ዓመታቸው የዎላይታ አውራጃ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ፡፡ የትምህርትን ጠቀሜታ እጅግ የተገነዘቡ በመሆናቸው ት/ቤቶችን አስፋፍተው ከፈቱ፡፡ በለቅሶ፣ገበያና ሠርግ ላይም ስለ ትምህርት ጠቀሜታ ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር፡፡

የሲዳሞ ክ/ሀገር ት/ቤቶች ኃላፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ዎላይታ ላይ የጀመሩትን የትምህርት አርበኝነት በማጠናከር ሲዳማ ውስጥ በቀን መብራት እያበሩ “ልጆቻችሁን አስተምሩ ከጨለማ ኑሮ ይላቀቁ'' በማለት በርካታ ተማሪዎችን አፍርተዋል፡፡

ብዙ ጫናዎችን አልፈው የተለያዩ መጻሕፍትን በመጻፍ ለብዙዎች አርአያ ከመሆናቸውም በላይ የዎላይታ ታሪክ ለትውልድ እንዲተላለፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል የዎላይታ ሕዝብ ታሪክና ባርነት እንዴት እንደተወገደ 1956 ዓ.ም አዲስ አበባ ፣ ሰብአዊ አእምሮና የጨዋ ልጅ (የካቲት 1948 ዓ.ም በተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት የታተመ) ፣ብርሃን በመንገዱ የመሠረተ ትምህርት ጮራ 1949 ዓ.ም(በመርሐ ጥበብ ማተሚያ ቤተ 3ኛ የታተመ) ይጠቀሳሉ፡፡

የብርሃንናሰላም ማተሚያ ድርጅት አስተዳደሪ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በጊዜው የነበረውን የዐፄ ሥርዓት የሚጻረሩ ጽሑፎች እንዲታተሙ እየፈቀዱ ስላስቸገሩ ከሥራቸው እንዲነሱ ተደርገዋል፡፡

በመጨረሻም ከ1954 - 1958 ዓ.ም የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል በመሆን ሥልጣን ሳይደልላቸው ለፍትህና እኩልነት ሲታገሉ ቆይተው በ 56 ዓመታቸው ጥር 18 ቀን 1958 ዓ.ም አርፈው አራት ኪሎ በሚገኘው ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተቀበሉ።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዲሽታ ጊና በሚል ተወዳጅ ዘፈኑ የሚታወቀው ድምጻዊ ታሪኩ ጋንኪሲ  ሽልማት ለመቀበል ወደ አሜሪካን ሀገር ለመምጣት የቪዛ ጥያቄ አቅርቦ መከልከሉን መዝናኛ መጽሔት ዘግቧል።በአ...
24/05/2025

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዲሽታ ጊና በሚል ተወዳጅ ዘፈኑ የሚታወቀው ድምጻዊ ታሪኩ ጋንኪሲ ሽልማት ለመቀበል ወደ አሜሪካን ሀገር ለመምጣት የቪዛ ጥያቄ አቅርቦ መከልከሉን መዝናኛ መጽሔት ዘግቧል።

በአሜሪካን ሐገር የሚገኘው ኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ዲቪሎፕመንት ካውንስል የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተመሰረተበትን 42ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አስመልክቶ፡ ለሰላም እና ለፍትህ የቆሙ ሦስት ግለሰቦችን በደመቀ ስነ ስርዓት የዕውቅና ሽልማት ባለፈው ሀሙስ መስጠቱ ተገልጿል።

"ታሪኩ ጋንጋሲ ለሰላም እና ለፍትህ መስፈን ላበረከተው ላቅ ያለ አስተዋፅዖ እንዲሸለም" ወደ አሜሪካ እንዲመጣ ተቋሙ ለኢምባሲው ደብዳቤ ጽፎ የነበረ ቢሆንም፤ ድምጻዊው ታሪኩ ጋንጋሲም ቪዛ ለመውሰድ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ፣ አማርኛ ተናጋሪ የሆነው ፈረንጁ የቪዛ ኦፊሰር “ለምንድን ነው ወደ አሜሪካን ሀገር የምትሔደው?” ብሎ በአማርኛ ይጠይቀዋል።

ታሪኩም “በአሜሪካ፡ በቋሚነት ለመኖር” በሚል፡እንደመለሰና በዚህ የተነሳ የቪዛ ኦፊሰሩም ወደ ሃገርህ የመመለስ ዕቅድ የለህም በሚል ቪዛውን እንደከለከለው መጽሔቱ ዘግቦ አንብበናል። በዚህም ምክንያት ታሪኩ በሌለበት ሽልማቱ ተበርክቶለታል።

የዲሽታ ጊና ሙዚቃ አቀንቃኙ ታሪኩ፤ ከሽልማቱ በኋላ በቪዲዮ ተቀድቶ ከጂንካ ባስተላለፈው መልዕክት “ይህንን ሽልማት ስለሸለማችሁኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፣ ወደ አሜሪካን ሀገር ለመምጣት አስቤ አልተሳካም፣ አሁን ጂንካ ተመልሼ በግብርና ሥራዬ ላይ ተሰማርቻለሁ" ብሏል።

24/05/2025

Our culture, welaita!!!!

በድጉና ፋንጎ ወረዳ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ሳይመለስ ዓመታትን አስቆጥርዋል ሆኖም ግን የታችኛው ፋንጎ ይብሳል፡፡ በየጊዜው በአቴት:በኮለራና የመሳሰሉ በንፁ ወሃ እጥረት የምከሰቱ በሽታዎች የብ...
24/05/2025

በድጉና ፋንጎ ወረዳ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ሳይመለስ ዓመታትን አስቆጥርዋል ሆኖም ግን የታችኛው ፋንጎ ይብሳል፡፡ በየጊዜው በአቴት:በኮለራና የመሳሰሉ በንፁ ወሃ እጥረት የምከሰቱ በሽታዎች የብዙ ሰዎችን ሕይውት ቀጥፉውል፡፡
‎በወረደው የመረት አቀማመጥና የlandforms or Agro -Ecological type መሠረት ዴጋ በኩል ያሉት ቀበልያት ምንም ዓይነት የወሃ ሽፋን ባለመኖራቸው ምክንያት ከሰው እስከ እንስሳ በዘመናት እንደተጎዱ ማንም የምያምነው እውነት ነው::
‎ Additionaly በገጠር መሠረት ልማት ዋናኛውና አንጋፋ የሆነው የገጠር መንገድ ጥገና ጋር ተያይዘው ድሮ በኢሕአዴግ ግዜ የተሰሩ መንገዶች ተቆራርጦ እናቶቻችን በምወልዱ ሰዓት ወደ ጠና ተቋማት ለማድረስ እንደተቸገረን የሁል ግዜ ጬሄታችን ብሆንም ሴም አካል አጥተናል፡፡
‎ ነገር ግን ጉዳዩ ስመለከታቸው ለግል ምቾታቸው ብሎ ዝም በማለት ዕድምያቸውን የጨረሱ ሰዎቹን አይተናል:: የሆነው ሆኖ አሁንም ስላልረፈደ ጉዳዩ የምማለከታቸው አካላቶች አስፈላግዉን እርብርብ በማድረግ ህዝባችን ከሞትና ከመሰል አደጎች እንድታደጉ ከሀደራ ጭምር አሳስባለሁ፡፡
‎ .......ይህን መልዕክት share ባማድረግ ለተጎዱ ለታችኛው ፋንጎ ሕዚብ አፈ በመሆን ድርሻቸውን እንድወጡ በማለት አሳስበዋለሁ

Address


Telephone

0926407305

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Z Fun Go Eran Da + $ Da- posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share