በጂንካ ከተማ መንግሥት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Jinka Town Government Communication Office

  • Home
  • በጂንካ ከተማ መንግሥት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Jinka Town Government Communication Office

በጂንካ ከተማ መንግሥት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Jinka Town Government Communication Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በጂንካ ከተማ መንግሥት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Jinka Town Government Communication Office, Digital creator, .

‎በጂንካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የተመራ ስትሪንግ ኮሚቴ የኮደርስ ስልጠና የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ኢኒሼቲቭ አፈፃፀም ገመገመ።‎       ‎    ...
08/11/2025

‎በጂንካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የተመራ ስትሪንግ ኮሚቴ የኮደርስ ስልጠና የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ኢኒሼቲቭ አፈፃፀም ገመገመ።

‎ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም
‎ ጂንካ
‎የፋይዳ መታወቂያን አስመልክቶ የአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ እንዲሁም የንግድ ስራዎችን ለማፋጠን የፋይዳ መታወቂያ አስፈላጊነቱ እጅግ የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

‎ኮደረስ ዕቅድ አፈፃፀም እንደ ጂንካ ከተማ የተሻለ አፈፃፀም ላይ መሆኑን የገመገመ ስሆን ‎ኢኒሼቲቭ አፈፃፀም የትኩረት አቅጣጫ እንደ መሆኑ ‎በከተማ የተጀመረ ስሆን በቀጣይ በቀበሌ ደረጃ ተግባራዊ እንድሆን በጋራ መስራት ይጠበቃል ስሉ የጂንካ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ውባለም ገዛህኝ ።

የገቢዎች ጽህፈት ቤት ቅዳሜ መደበኛ የሥራ ሰዓት  ከጠዋቱ  2:30 ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማንጎ ከበደ አሳወቁ።‎‎   ...
08/11/2025

የገቢዎች ጽህፈት ቤት ቅዳሜ መደበኛ የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማንጎ ከበደ አሳወቁ።

‎ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም
‎ ጂንካ
‎ማንኛውም ባለጉዳይ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ መደበኛ የሥራ ሰዓት እንደመሆኑ ወደ ተቋሙ በመገኜት የቀን መሉ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ኃላፊው አሳወቁ።

በጂንካ ማረሚያ ተቋም የታራሚዎች የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏልጥቅምት 29/2018 ዓ.ምበጂንካ ማረሚያ ተቋም የታራሚዎች የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል።በዛሬዉ ዕለትም...
08/11/2025

በጂንካ ማረሚያ ተቋም የታራሚዎች የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም
በጂንካ ማረሚያ ተቋም የታራሚዎች የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዛሬዉ ዕለትም የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተካህዷል።

የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሉቃስ ቡሪ በማስ ስፖርቱ ላይ ተገኝተዉ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ተቋሙ ታራሚዎችን ከማረም ባሻገር የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ታራሚዎች በስነ ምግባር የታነፁና የተስተካከለ የሰዉነት አቋም እንድኖራቸዉ የተለያዩ ስፖርቶችን መስራት እንድችሉ ለማድረግ ከተቋሙ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የተጀመሩ የማስ ስፖርትና ሌሎች ሶፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዉ እንድቀጥሉ የስፖርት ቁሳቁስና የማበረታቻ ድጋፎችን መምሪያዉ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የመምሪያዉ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግዛቸዉ ሐሚ በበኩላቸዉ ማስ ስፖርት ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ራሳችንን ለመከላከል ትልቅ ጥቅም እንዳለዉ ገልፀዋል።

ታራሚዎች ከበሽታ ራሳቸዉን ለመከላከልና የተስተካከለ የሰዉነት አቋም እንድኖራቸዉ ዘዉትር ቅዳሜ ጠዋት የማስ ስፖርት ለመስራት ቀድመዉ እንድነሱ መልዕክት በማስተላለፍ የማስ ስፖርቱን በማሰራት እየተባበሩ ያሉ ወጣቶችን አመስግነዋል።

የጂንካ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ታራሚዎች በአካልና በስነ ልቦና ብቂ እንድሆኑ ስፖርት መስራትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸዉ ተናግረዋል።

የጂንካ ማረሚያ ተቋም የስፖርትና መዝናኛ ቡድን መሪ ረዳት ኢኒስፔክተር አለማየሁ ንጉሴ በተቋሙ ከማስ ስፖርቱ በተጨማሪ ሌሎች የስፖርት እንቅስቃሴዎች መኖራቸዉን ገልፀዉ ዞኑና ከተማዉ ለተግባሩ መጠናከር እያደረጉ ላለዉ ድጋፍ አመስግነዋል።

በማስ ስፖርቱ ሴቶች፣ህፃናትና ጠቅላላ የተቋሙ ታራሚዎች ተሳትፈዋል።

ምንጭ ኣ/መ/ኮ

‎በኣሪ ዞን በጂንካ ከተማ አስተዳደር ነገ በቀን 29/2/ 2018 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30  ቤንዚን በሐበሻ / በገነት ማደያ የመንግስት ሠራተኛ ብቻ የሚስተናገዱ መሆኑን የጂንካ ከ...
07/11/2025

‎በኣሪ ዞን በጂንካ ከተማ አስተዳደር ነገ በቀን 29/2/ 2018 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 ቤንዚን በሐበሻ / በገነት ማደያ የመንግስት ሠራተኛ ብቻ የሚስተናገዱ መሆኑን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ባይስማይ አሳወቁ ።

‎ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም
‎ ጂንካ
‎የጂንካ ከተማ አስተዳደር የንግድና ገቢያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ባይስማይ እንደገለፁት በነገው ዕለተ ቅዳሜ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት የመንግስት ሠራተኛ ብቻ የምስተናገዱ መሆኑን ኃላፊው አመላክተዋል ።

በዚህም መሠረት ‎ከተፈቀደላቸው ተገልጋዮች ውጪ በማደያ መገኘት የተከለከለ መሆኑን የገለፁ ስሆን የ2018 በጀት ዓመት የታደሰ ኮፔን እና የሥራ መታወቂያ በመያዝ የምስተናገዱ መሆኑን አክለው ኃላፊው አሳስበዋል ።

‎ማሳሰብያ ፦ የነገ ተረኛ ተገልጋዮች በሙሉ ከላይ በተቀመጠው ፕሮግራም እና የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት አስገዳጅ መሆኑ አውቀው ወደ ማደያ እንድገኙ አሳስበዋል ።

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ትምህርት  ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ውባለም ገዛኸኝ በጤናዳም ርሆቦት አፀደ ህፃናት ትምህርት ቤት ተገኝተው የመምህራን ስልጠና አስጀምረዋል ።‎  ...
07/11/2025

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ውባለም ገዛኸኝ በጤናዳም ርሆቦት አፀደ ህፃናት ትምህርት ቤት ተገኝተው የመምህራን ስልጠና አስጀምረዋል ።

‎ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
‎ ጂንካ
‎የክላስተር ሱፐር ባይዘር አካላት የስልጠና ቦርድ መምህራን የተገኙ ስሆን በጋራ ተቀናጅቶ መስራት ውጤታማ እንምመያደረግ እና ተከታታይ ማሻሻያ ስልጠናዎች እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

‎መምህራን ተወዳዳሪ እንድሆኑ አጫጭር ስልጠናዎች አስፈላጊ መሆኑን እና በተጨማሪም የማጠናከሪያ ትምህርት ለተማሪዎች መስጠት እንደሚያስፈልግ በንግግራቸው ወቅት አመላክተዋል ።

‎የስልጠና ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አድማሱ ዱባለ ፣ የጤናዳም ሮሆቦት አፀደ ህፃናት ር/መ እሱባለው ዳንካ ‎ለሎች የባለድርሻ አካላት በቦታው የተገኙ ስሆን ስልጠናውን የጂንካ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ በይፋ አስጀምረዋል ።

‎የጂንካ ከተማ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባገኘችው የመልማት ዕድል ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ትገኛለች‎      ‎          ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም‎የጂንካ ከተማ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ...
07/11/2025

‎የጂንካ ከተማ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባገኘችው የመልማት ዕድል ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ትገኛለች

‎ ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም
‎የጂንካ ከተማ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባገኘችው የመልማት ዕድል ፈጣን እድገት እያስመዘገበች እንደምትገኝ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ውብአለም ገዛኸኝ አመለከቱ።

‎ከአዲስ አበባ 755 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የጂንካ ከተማ በ1940ዎቹ መጨረሻ እንደተቆረቆረች ይነገራል።

‎ከተማዋ ባሳለፈቻቸው ዓመታት የመልማት እድል ባለማግኘቷ ከሌሎች አቻ ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ መሆን ተስኗት ብትቆይም በቅርቡ የተጀመረው የኮሪደርና የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ስራዎች እድገቷን እያፋጠኑ ይገኛሉ።

‎ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ውብአለም ገዛኸኝ፥ የጂንካ ከተማ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባገኘችው የመልማት ዕድል ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ትገኛለች።

‎በከተማው ''ጂንካን በጋራ እናልማ'' በሚል መርህ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የኮሪደርና የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

‎በዚህም ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመዝናኛ ፓርኮች፣ የአደባባይ ልማት፣ የመንገድ አካፋዮችና ዳርቻዎች የአረንጓዴ ልማት እና የከተማዋን የምሽት ገፅታ የሚያጎሉ የምሽት መብራቶችን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

‎እያደገ የመጣውን የከተማዋን ነዋሪ ፍላጎት ያማከለ መሰረተ ልማት የመዘርጋቱ ስራ በፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን የጂንካ ንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክትም በከተማዋ ከሚከናወኑ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ይጠቀሳል ብለዋል፡፡

‎የፕሮጀክቱ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ወደ 87 በመቶ መድረሱን ጠቁመው፥ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የከተማዋን፣የተቋማትን እና የሆቴሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ያስችላል ብለዋል።

‎የኮሪደር ልማት፣የመንገድ መሰረተ ልማት፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ እንዳሉ ጠቅሰው እነዚህን የልማት ስራዎችን በማፋጠን ጂንካን ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

‎በከተማ አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የመሰረተ-ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ቡድን መሪ አቶ ፈለቀ ወርቁ በበኩላቸው፥ የመዝናኛ ፓርኮችን ጨምሮ ህዝባዊ ክብረ በዓላት የሚከናወኑባቸው ውብ፣ ፅዱና ማራኪ ቦታዎችን ያካተተ ስራ በመጀመሪያው ምእራፍ የኮሪደር ልማት መከናወኑን ገልጸዋል።

‎በሁለተኛው ምዕራፍ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች ከስድስት ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን የተቀናጀ የኮሪደር ልማት ሥራ እንደሚተገበርም ተናግረዋል።

‎የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ለማዘመን፣ ዕድገቷን ለማፋጠንና ተወዳዳሪነቷን ለመጨመር ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቁመው ለቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ተመራጭነቷን እያሳደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

‎የጂንካ ከተማ በአሪ ዞን እና በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሮአዊ የቱሪስት መስህቦችን ለመጎብኘት የሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ አገራት ቱሪስቶች መዳረሻ ስፍራ በመሆን እያገለገለች ያለች የጠረፍ ከተማ ናት።

‎የጂንካ ሙዚየምን ጨምሮ የከተማዋን ጎዳናዎች፣ የገበያ ስፍራዎችን እና የመዝናኛ ፓርኮችን በመጎብኘት አስደሳች ጊዜ እያሳለፉ እንዳሉ የተናገሩት የቼክ ሪፐብሊክ ዜግነት ያላቸው ጥንዶች ቬሮኒካ ቱች ኮቫ እና ባትስላቭ ሚልራደር ናቸው።

‎ወደ ጂንካ ሲመጡ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቁመው፥ ከ6 ዓመታት በፊት ከጎበኟት ጂንካ ከተማ በእጅጉ የተለየ ፈጣን ለውጥ ማየታቸውን ተናግረዋል።
ምንጭ ፦‎ኢዜአ

የከተሞች ፎረምን ማስተናገድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል-የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ሰመራ፣ጥቅምት 28/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ የሚካሄደውን የከ...
07/11/2025

የከተሞች ፎረምን ማስተናገድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል-የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር

ሰመራ፣ጥቅምት 28/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ የሚካሄደውን የከተሞች ፎረም ማስተናገድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቃቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም መካሄድ ከተሞችን እርስበርስ ለማስተዋወቅ፣ በከተሞች መካከል የውድድርና የፉክክር መንፈስ እንዲጎለብት በማድረግ የከተሞችን የልማት ጉዞ ለማፋጠን መነሳሳት እንደሚፈጥር ተመልክቷል።

በተጨማሪም በከተሞች ለቱሪዝም የሚውሉ ታሪካዊ፣ባህላዊና ማህበራዊ እሴቶች ለማስተዋወቅም ፎረሙ ጉልህ ድርሻ አለው ተብሏል።

ሰመራ ሎጊያ ከተማ “የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት" በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው 10ኛውን የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ታስተናግዳለች።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዱ ሙሳ እንደገለፁት፥ ፎረሙ ሰመራን እና አጠቃላይ በአፋር ክልል ያለውን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብቶችን ለማያስተዋውቅ የሚያግዝ ነው።

ሰመራ ለዝግጅቱ ድምቀት ዘርፈ ብዙ የዝግጅት ስራዎችን መከናወናቸውን ገልጸው፥ በተለይም 6 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ ለዐውደ ርዕይ እና ለሌሎች አገልግሎት የሚውል ስፍራ የዝግጅቱ አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

ስፍራው ለዐውደ ርዕይ የሚሆን ሼድ፣ ውሃ፣ መብራት፣ ስልክና የገመድ አልባ ኢንተርኔት እንዲያገኝ ተደርጓል ነው ያሉት።

በዘንድሮው የከተሞች ፎረም ላይ የሚሳተፉ 148 ከተሞች ምርቶቻቸውን የሚያሳዩበት ስፍራም መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ከህዳር 6 እሰከ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄድ አመልክተው፥ የፎረሙ መክፈቻ እና መዝጊያ ሁነቶች የሚካሄዱበት የሰመራ ስታዲዮም እና ሌሎች ሁነቶች የሚስተናገዱበት የተለያዩ የስብሰባ አዳራሾች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ከከተሞች ፎረም ጎን ለጎን በከተማው የተሰሩ የኮሪደር ልማት፣የልማት ስራዎችና የተፈጥሮ መስህብ መዳረሻ ቦታዎች ጉብኝት እንደሚደረግም ታውቋል።

በፎረሙ ላይ ከዐውደ ርዕይና ሌሎች ሁነቶች በተጨማሪ በተለያዩ መስኮች ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡና በከተማ ልማት ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

ምንጭ ፦ ኢዜአ

የጂንካ ከተማ ም/ቤት የ2018 ዓ,ም 4ተኛ ዙር 13ኛ ዓመት 54ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ መሆኑ ተገለፀ ።     ጥቅምት 28/02/2018 ዓ,ም                ጂንካ ።1, የዕ...
07/11/2025

የጂንካ ከተማ ም/ቤት የ2018 ዓ,ም 4ተኛ ዙር 13ኛ ዓመት 54ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ መሆኑ ተገለፀ ።
ጥቅምት 28/02/2018 ዓ,ም
ጂንካ ።

1, የዕለቱ አጀንዳዎች የም/ቤት የ2018 ዓ,ም 4ተኛ ዙር 13ኛ ዓመት 54ኛ መደበኛ ቃለ ጉባኤ ማስፀደቅ ፦
2, የከተማውን ምክር ቤት የ2018 ዓ,ም የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብና ማስፀደቅ ፦
3, የጂ/ከ/አስ/የአስፈጻሚውን የ2018 የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብና ማስፀደቅ ፦
4, የጂ/ከ/መ/ደ/ፍ/ቤት የ2018 የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብና ማስፀደቅ ፦
5, የህንጻ ውል እድሳትን በተመለከተ ፦
6, ሹመት ማቅረብና ማስጸደቅ ባጠቃላይ ከላይ በተዘረዘሩት አጀንዳዎች መሠረት የዕለቱ ጉባኤ እንደሚካሄድ እያሳወቅን ቀሪ መረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል ፦

በኣሪ ዞን በጂንካ ከተማ አስተዳደር በጤናዳም 01 ከተማ ቀበሌ በሰላም 02 ቀጠና የአከባቢው ማህበረሰብ በነቅስ የአከባቢ ጽዳት እና ውበት አካሄደ።‎‎           ጥቅምት 28/2018 ዓ...
07/11/2025

በኣሪ ዞን በጂንካ ከተማ አስተዳደር በጤናዳም 01 ከተማ ቀበሌ በሰላም 02 ቀጠና የአከባቢው ማህበረሰብ በነቅስ የአከባቢ ጽዳት እና ውበት አካሄደ።

‎ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
‎ ጂንካ
‎የጽዳት ዘመቻው በሁሉም የልማት ህብረት ተጠናክሮ ልቀጥል እንደምገባ እና ከፊታችን የሚከበረው የዲሽታ ግና በዓል እሴት የሆነው አንዱ ጽዳትና ውቤት ነው ስሉ የቀጠናው አስተዳደር አቶ ደጀኔ አልቅማይ አስገንዝበዋል ።

የጂንካ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከጥቅምት 29/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰበታ በሚካሄደው የኢትዮጵያ ሊግ አንድ ጨዋታ ላይ ለመሳተፍ በቂ ዝግጅት ያደረገ ስሆን በዛሬው ዕለት ልዩ የሽኝት መርሃ-ግ...
06/11/2025

የጂንካ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከጥቅምት 29/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰበታ በሚካሄደው የኢትዮጵያ ሊግ አንድ ጨዋታ ላይ ለመሳተፍ በቂ ዝግጅት ያደረገ ስሆን በዛሬው ዕለት ልዩ የሽኝት መርሃ-ግብር በጂንካ ከተማ አስተባባሪ ኮምቴ አመራር አካላት በተገኙበት ተካሄደ ።

‎ ጥቅመት 27/2018 ዓ.ም
‎ ጂንካ

የውሃ ፈሳሽ መተላለፊያ ቱቦ ፣ የመንገድ መብራት በየቦታው የምገኙ አፑል ፣ ወጥ የሆነ ቀለም መጀመር እና ያረጁ ታፈላዎችን የማጽዳት የመንገድ እንቅፋቶች ፣ የወል ቦታዎችን ፣ የአንድነት ፓር...
06/11/2025

የውሃ ፈሳሽ መተላለፊያ ቱቦ ፣ የመንገድ መብራት በየቦታው የምገኙ አፑል ፣ ወጥ የሆነ ቀለም መጀመር እና ያረጁ ታፈላዎችን የማጽዳት የመንገድ እንቅፋቶች ፣ የወል ቦታዎችን ፣ የአንድነት ፓርክ ፣ የገበያ ቦታዎች ጨምሮ ልስተካከሉ የምገቡትን ቅድሚያ ተሰቶ በትኩረት ልሰራ ይገባል።

‎ወቅታዊ ተግባራት እና የድሽታ ግና አከባበር በተመለከተ በሰፊው ውይይት የተካሄደ ስሆን ልዩ ትኩረት ልሰጡ በሚገቡ የመንገድ ከፈታ እንዲሁም የህብረተሰብ ተሳትፎ ጨምሮ በጋራ የተጀመሩ ተግባራት ተቀናጅቶ የምሰራ መሆኑን አሳስበዋል።

‎የወባ ወረሽኝ ጉዳይ ፦ የአከባቢ ቁጥጥር በተቋማት በግለሰብ እንዲሁም በማህበረሰቡ አከባቢውን በማያፀዳ ላይ እርምጃ መወሰድ እንደምገባ አሳስበዋል ።

‎የገቢ ሥራን አስመልክቶ የገቢ ደረሰኝ መሰጠቱን በአግባቡ መከታተል እንዳለበት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ልመራ እንደምገባ መክረዋል ።

‎ስራዎችን ለማሳካት ቁራጥ መሆን እንደምገባ ሀላፊው የገለፁ ስሆን ተግባሮቻችን በተቀመጠለት ጊዜ ተፈፃሚ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል ።

‎በኣሪ ዞን የጂንካ  ከተማ  አስተዳደር  የአርክሻ 02 ከተማ ቀበሌ 05 ቀጠና ጋር በመቀናጀት በማቆያ ለሚቆዩ ለወላድ  እናቶች በሚሊኒዬም ጤና ጣቢያ ተገኝተው ድጋፍ አደረጉ  ።‎‎     ...
06/11/2025

‎በኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር የአርክሻ 02 ከተማ ቀበሌ 05 ቀጠና ጋር በመቀናጀት በማቆያ ለሚቆዩ ለወላድ እናቶች በሚሊኒዬም ጤና ጣቢያ ተገኝተው ድጋፍ አደረጉ ።

‎ ጥቅምት 27/02/2018
‎ ጂንካ
‎በጂንካ ከተማ በጤናዳም 01 ከተማ ቀበሌ በሚሊኒዬም ጤና ጣቢያ በወላድ ማቆያ ላሉት እናቶች 12250 ብር የገንዘብ በጥረ እና የዘይት እና ስኳር የመሳሰሉትን ድጋፍ አድርገዋል ።

‎የጂንካ ከተማ አስተዳደር የአርክሻ 02 ከተማ ቀበሌ በሥፍራው ተገኝተው እንዳሉት ፦ ይህ በቂ አይደለም እናቶች የሞቀው ቤታቸውን ጥለዉ ሲመጡ ቡዙ ነገር ያስፈልጋቸዋል ፤ ስለዝህ ከጎናቸው በመሆን የአቅማችንን በመደገፍ ግዴታችንን እንወጣ በማለት ሃሳብ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጂንካ ከተማ መንግሥት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Jinka Town Government Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share