Ewnet Check

Ewnet Check Ewnet Check is a project to combat misinformation, hate speech and fraud in Ethiopia'a internet landscape and beyond.

በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ ባለፉት አመታት ከብሄራዊ ባንክ ተመን ጋር ሲነጻጸር ምን ይመስል ነበር? ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውስ? ሙሉ ትንተናው ይመልከቱ።
07/01/2022

በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ ባለፉት አመታት ከብሄራዊ ባንክ ተመን ጋር ሲነጻጸር ምን ይመስል ነበር? ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውስ? ሙሉ ትንተናው ይመልከቱ።

በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ በዚህ አመት ምን ይመስል ነበር? ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውስ ትንተናው ይመልከቱ..Continue readingዳታ ሪፖርት : በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ ኢኮኖ....

Wanna know what Ethiopians are interested in and are searching on Google & Youtube. Check out our Twitter Bot twitter.co...
21/12/2021

Wanna know what Ethiopians are interested in and are searching on Google & Youtube. Check out our Twitter Bot
twitter.com/EthGoogling
that tweets daily what's trending in 🇪🇹

Check your business names for hateful or unwanted meanings in multiple Ethiopian languages with our tool here.https://ew...
30/11/2021

Check your business names for hateful or unwanted meanings in multiple Ethiopian languages with our tool here.
https://ewnetcheck.org/hate-check

Trying to decide a name for your business or child? have you considered what your potential name might mean in another language? What if it's something hateful? checks your word against swear words and unwanted associations in 9 Ethiopian languages/dialects. Including Amharic, Afaan Oromo, Af Somali...

Telegram, the social messaging app, was widely used as a fraud tool in Ethiopia’s national exams, our investigation reve...
14/11/2021

Telegram, the social messaging app, was widely used as a fraud tool in Ethiopia’s national exams, our investigation revealed.
The government blocked the app last time nationwide exams took place in March and also now in November.

Telegram widely used as a fraud tool in Ethiopia’s national examination Posted on November 10, 2021November 12, 2021 The national examination for Grade 12 students, also known as Ethiopian University Entrance Exam(EUEE), conducted earlier in march and ended on March 11, 2021. It was marred with co...

https://youtu.be/H-Wjp7CM5jg
14/11/2021

https://youtu.be/H-Wjp7CM5jg

Volume . Addis Habtamu on her work at Wolaita S**o University COVID19 treatment center.Dr. Addis is MD graduate from Hawassa Universit...

      Top Performing posts on Social Media Election Day.1. EBC: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበሻሻ ድምፅ መስጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል ...
21/06/2021



Top Performing posts on Social Media Election Day.

1. EBC: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበሻሻ ድምፅ መስጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል (2.5M likes,207.3ሺ views in 4 hours)
2. EBC: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 6ኛው አገራዊ ምርጫን አስመልክተው ለኢቲቪ የሰጡት አስተያየት (2.5M likes,59.2ሺ views in 1 hour)
3. Fana: ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በበሻሻ ድምጽ ሰጥተዋል (2.5M likes,108.2ሺ views in 4 hours)

using CrowdTangle

   ኢንጅነር የታከለ ኡማ በቁጥጥር ስር ዉለዋል ተብሎ የሚናፈሰዉ መረጃ የሀሰት ነዉ ተባለ። አሁን ላይ የቴክኖሎጂ አብዮት መምጣቱ ተከትሎ በርካታ የሀሰተኛ መረጃዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮ...
21/06/2021


ኢንጅነር የታከለ ኡማ በቁጥጥር ስር ዉለዋል ተብሎ የሚናፈሰዉ መረጃ የሀሰት ነዉ ተባለ።

አሁን ላይ የቴክኖሎጂ አብዮት መምጣቱ ተከትሎ በርካታ የሀሰተኛ መረጃዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ሲሰራጩ ይስተዋላል።

ከቀናት በፊት በይትዮብ ቻናሎች በአዲስ አበባ ቦምብ እንዲፈነዳ እና ይህንም እንዲሆን ያደረገዉ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ነዉ በማለት ከአንድ ቪዲዮ ላይ የሚናገር ግለሰብን በመጥቀስ ያሰራጩት መረጃ የሀሰት እንደሆነ እዉነት ቼክ ባደረገዉ ማጣራት አረጋግጧል።

የቀድሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ የአሁኑ ደግሞ የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስተር የሆኑት ታከለ የኡማ ለእስር እንደተዳረጉ ተደርጎ የተናፈሰዉ የፈጣራ መረጃ እንደሆነ እና ከአራት ቀናት ማለትም ሰኔ 10/2013 ዓ.ም ላይ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን በአሶሳ ከተማ ሁለተኛውን የከሰል ድንጋይ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመራቸዉን የሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል

እንዲሁም ዛሬ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ደግሞ የሀገር አቀፍ ምርጫዉን ተከትሎ
ድምፅ መስጠታቸዉን በራሳቸዉ ማህበራዊ ድረገፅ ላይ አስፍረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም እዉነት ቼክ ያደረገዉ ማጣራት በአዲስ አበባ ዉስጥ ኢንጅነሩ ታስረዋል ተብሎ በይትዮብ የተናፈሰዉ ወሬ የሀሰት እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

https://www.ewnetcheck.org/minister-takele-uma-not-arrested/
ምንጭ :

 ምርጫዉን በማስመልከት ዛሬ ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎች ተሰርዘዋል ስለተባለዉ መረጃ እዉነታዉ ምንድነዉ...? ዛሬ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫዉን በማስታከክ  የሀገር ውስጥ በረራዎች እን...
21/06/2021


ምርጫዉን በማስመልከት ዛሬ ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎች ተሰርዘዋል ስለተባለዉ መረጃ እዉነታዉ ምንድነዉ...?

ዛሬ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫዉን በማስታከክ የሀገር ውስጥ በረራዎች እንደተሰረዙ የሚገልፁ ፅሁፎች በማህበራዊ ሚድያ ላይ፣ ሲሰራጩ ነበር።

ይህን ተመልክቶ እዉነት ቼክ ባደረገዉ ማጣራት በዛሬዉ ዕለት ምንም አይነት በረራ እንዳልተቋረጠ ተመልክቷል። ፍላይት ራደር (FlightRadar24) ን በመጠቀም ዳሰሳ ያደረገዉ በሀሰተኛ መረጃ ላይ የሚሰራ ተቋሙ በዛሬዉ ዕለት ሀዋሳን ጨምሮ ወደ ሦስት ቦታዎች በረራ እንዳለ ተመልክቷል።

ከዚሁ ጋር በተለያያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳስታወቀዉ የሰዓት መሸዋወዳ ካልሆነ በስተቀር ሁሉም የሀገር ዉስጥ በረራዎች እንዳልተቋረጡ ተናግረዋል።

"በረራዎች እንደበፊቱ እንደቀጠሉ ናቸው። ከሌላው ቀን ምንም የተለየ ነገር የለም" በማለት ደግሞ ምላሽን የሰጡት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው ናቸዉ ሲል Ethiopia Check በድረገፁ አስነብቧል።

በአጠቃላይ ወደ ባህርዳር፣ ደሴ እና ሌሎች ከተሞች በረራዎች እንዳሉ ባደረግነዉ ማጣራት አረጋግጠናል።

"በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 100 በላይ የሀሰተኛ ገፆችን እና አካዉንቶችን መዝጋት ችያለሁ" ሲል ፌስቡክ አስታዉቋልከኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ጋር ግንኙነት አላቸዉ ያላቸዉ...
17/06/2021

"በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 100 በላይ የሀሰተኛ ገፆችን እና አካዉንቶችን መዝጋት ችያለሁ" ሲል ፌስቡክ አስታዉቋል

ከኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ጋር ግንኙነት አላቸዉ ያላቸዉን እና የሃሰተኛ እና አሳሳች ይዘቶችን የሚያወጡ በርካታ አካዉንቶችን ማገዱን አስታዉቋል።

ምርጫ ሊካሄድ ቀናት ሲቀረዉ ትላንት ፌስብክ ባወጣዉ ወራዊ በሪፖርቱ ላይ መቀመጫቸዉን በሀገር ዉስጥ እና በባህር ማዶ በማድረግ እንዲሁም ብዙ ተከታዮችን በማፍራት ያልሆነ/ያልተፈጠረ ክስተቶችን በመዘገብ እና ማህበረሰቡን ለማሳሳት ትኩረት አድርገዉ ይሰራሉ ያላቸዉን 176 የፌስቡክ እና የኢንስታግራም አካዉንቶችን ማገዱን አስታዉቋል።

ፌስብክ ባወጣው ሪፖርት ላይ የሰኔን ወርን ጨምሮ ያለፈዉን ማለትም የግንቦትን ወር ላይ የተከሰቱ ክዋኔዎች ዳሰሳ አድርጓል።

ላለፉት አራት ዓመታት በዚህ ስራዉ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራዉ ተቋሙ በዚህ ወር ደግሞ ትክክለኛ እና የተቀናጀ ያልሆነ ባህሪን እንዲሁም ግንኙነቶችን በማሻከር ያልተገባ ስም በመስጠት እና በማሳሳት ዉዥንብርን የፈጠሩ ገፆችን ነዉ አግጃለሁ ያለዉ።

እነዚህም 65 የፌስቡክ አካዉንቶች ፣ 52 የፌስቡክ ገፆች ፣ 27 ግሩፖች ፣ እንዲሁም 32 መለያዎችን ከኢንስታግራም በአጠቃላይ 176 የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እና አካዉንቶችን አስወግጃለሁ ብሏል ፌስብክ ባወጣዉ ሪፖርት።

“በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 100 በላይ የሀሰተኛ ገፆችን እና አካዉንቶችን መዝጋት ችያለሁ” ሲል ፌስቡክ አስታዉቋል Posted on June 17, 2021June 17, 2021 “በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 100 በላይ የሀሰተኛ ገፆችን .....

Code for Africa (CFA) and DW Akademie ባዘጋጁት ከፊት ለፊታችን ያለዉን ምርጫ በተመለከተ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭቶችን መቆጣጠር  ዙሪያ በተጨማሪም ደግሞ CIB (Coordi...
17/06/2021

Code for Africa (CFA) and DW Akademie ባዘጋጁት ከፊት ለፊታችን ያለዉን ምርጫ በተመለከተ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭቶችን መቆጣጠር ዙሪያ በተጨማሪም ደግሞ CIB (Coordinated inauthentic behavior) በሀገራችን ምን እንደሚመስል በስፋት ስልጠና ተሰጥቶናል።

በዚህ ስልጠና ላይ EwnetCheck ተሳትፎ አድርጓል። ጥሩ ጊዜም አሳልፈናል።

አዘጋጆቹ እና ባለሞያዎች ያላቸዉን ልምድ ስላካፈሉ እናመሰግናለን።

Code for Africa (CfA) and Deutsche Welle Akademie provided us with extensive training on how to control the spread of false information during the upcoming elections, as well as how to discern CIB (Coordinated Inauthentic Behavior) online.

EwnetCheck colleagues participated in this training. We had a good time.

Thank you to the organizers and experts for sharing their knowhow.

15/06/2021

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በመራጮች ምዝገባ ወቅት የተመዘገቡ ዜጎች በቦርዱ በተወሰነው የድምፅ መስጫ ቀን የተመዘገቡበት የምርጫ ጣቢያ በመሄድ ድምፅ ይሰጣሉ፡፡ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ የሚከተለውን ይመስላል:

• የድምፅ መስጠት ሂደት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በተመሳሳይ ሰዓት ይጀመራል፡፡

• በዕለቱም መራጮች በምርጫ ጣቢያው ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ እከስ ምሽት 12፡00 ሰዓት ድረስ በመገኘት ድምፃቸውን መስጠት ይችላሉ፡፡ በነዚህ ሰዓታት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ያልተቋረጠ የድምፅ መስጠት ተግባር ይከናወናል፡፡

• ማንኛውም መራጭ ዜጋ በምርጫ ጣቢያው በአካል በመገኘት በሙሉ ነፃነት ድምፅ ይሰጣል፡፡

• ማንኛውም ዜጋ ድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ ከሚመርጠው እጩ አጠገብ ባለው ቦታ ማንኛውንም (ኤክስ፣ ራይት ወይም የጣት አሻራ) ምልክት በማድረግ ድምፁን ይሰጣል፡፡

• ማንኛውም ድምፅ የሚሰጠው በሚስጥር ነው፡፡ ድምፅ ለመስጠት እገዛ የሚያስፈልጋቸው ድምፅ ሰጪ ዜጎች ድጋፍ የሚሰጣቸውን ሰው ይዘው የሚስጥር ድምፅ መስጫ ውስጥ መገኘት ይችላሉ፡፡ ድጋፍ ሰጪው መብቱ በህግ ያልተገደበ መሆን አለበት፡፡

ማንኛውም መራጭ ድምፅ መስጠት የሚችለው:

• በመራጭነት በተመዘገበበት የምርጫ ጣቢያ ላይ፣

• የመራጮች መታወቂያ ካርድ ሲኖረው፣

• በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ሲገኝ፣

• እንዲሁም ድምፅ ያልሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡

• ማንኛውም መራጭ ድምፅ ለመስጠት በተገኘበት ምርጫ ጣቢያ ላይ ይዞ የተገኘውን የማንነት መግለጫ ሰነዶች በጣቢያው ላይ በሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች ድምፅ እንዲሰጥ መፍቀዳቸውን ማጣራት ይችላሉ፡፡

• አካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያን፣ ህጻናትን የያዙ ወላጆች እና ነፍሰ ጡሮች በምዝገባም ሆነ በድምፅ አሰጣጥ ሂደት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

ድምፅ የተሰጠባቸው ወረቀቶች ከሚከተሉት በአንዱ ምክንያት ዋጋ አልባ ሊሆኑ ይችላሉ:

• የመራጩ ማንነት በስም የተገለፀ ከሆነ፣

• ለምክር ቤቱ መምረጥ ከሚቻለው እጩዎች ቁጥር በላይ ምልክት የተደረገበት ከሆነ፣

• መራጩ ማንን እንደመረጠ መለየት የሚያስቸግር ከሆነ፣

• ሕጋዊ የድምፅ መስጫ ወረቀት ያልሆነ ወይም በምርጫ ጣቢያው ያልተሰራጨ የድምፅ መስጫ ወረቀት ሆኖ ከተገኘ፡፡

ምንጭ: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ewnet Check posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share