አቢሲኒያ ሚዲያኢትዬ

  • Home
  • አቢሲኒያ ሚዲያኢትዬ

አቢሲኒያ ሚዲያኢትዬ ኢትዮዽያ Ethiopian

"የጠባብ ቡድን ጠባቂ አንሆንም" የህወሓት ታጣቂዎች!የታጠቁት የህወሓት አባላት በትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት የጠባብ ቡድን ጠባቂ አንሆንም በማለት ተቃውሞ እያሰሙ ነው። ታጣቂ...
18/09/2025

"የጠባብ ቡድን ጠባቂ አንሆንም" የህወሓት ታጣቂዎች!

የታጠቁት የህወሓት አባላት በትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት የጠባብ ቡድን ጠባቂ አንሆንም በማለት ተቃውሞ እያሰሙ ነው። ታጣቂ ሃይሎች የቀድሞ የህወሓት መሪ የነበረው ፅንፈኛ ቡድን ለጦርነት ዝግጅቱን እንዲያቆም የተቃውሞ ድምፁን አሰምቷል።

ከዚህም ጋርተያይዞ ታጣቂዎቹ በህወሓት አመራሮች በት በመግባት ዘረፋ እያካሄዱ መሆናቸውም ተገልጿል።አመራሮቹም ለህይወታቸው ሰግተው ተደብቀው እንዳሉም እየተየገረ ነው።

አጋልጥየነውረኞች ስብስብ ኢትዮ 360 ሚዲያ በም/አ/ር ዘሪሁን ምትኩ ዙሪያ ይፋ ያደረገው መረጃ በሙሉ ከእዉነት የራቀ ነው!ኢትዮ 360 የሚባል የዩትዩብ ጡረተኞች የሚዘውሩት ሚዲያ ሰሞኑን አ...
18/09/2025

አጋልጥ
የነውረኞች ስብስብ ኢትዮ 360 ሚዲያ በም/አ/ር ዘሪሁን ምትኩ ዙሪያ ይፋ ያደረገው መረጃ በሙሉ ከእዉነት የራቀ ነው!

ኢትዮ 360 የሚባል የዩትዩብ ጡረተኞች የሚዘውሩት ሚዲያ ሰሞኑን አንድ በፌዴራል ፖሊስ ውስጥ አባል በነበረ፣ ም/አ/ር ዘሪሁን ምትኩ በሚባል ግለሰብ ዙሪያ የሰራው ዘገባ ከእውነት ጋር የሚቃረን መሆኑን ከደረሱን ማስረጃዎች እና መረጃዎች ለማወቅ ችለናል። ግለሰቡ በፌዴራል ፖሊስ ውስጥ የኬሚካል ባይሎጂካል ራድዬሽን ኒውይክለር ዲፓርትመንት መስራች፣ በኢትዮጵያ የባይሎጂካል ሽብር መከላከል ኢንተርፖል ተጠሪ እና የመጀመሪያው ፖሎግራፊ የምርመራ ቴክኒክ መስራች ነው በሚል የተነዛው ወሬም የሚዲያውን እውነተኛ ማንነት ለህዝብ ግልፅ ከማድረግ ውጭ ምንም ከእዉነት ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ለማወቅ ተችሏል። በዚህም መሰረት ከፌዴራል ፖሊስ ተቋም የተገኘ መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ ይህ ግለሰብ በተቋሙ ውስጥ ተራ የአይሲቲ ባለሙያ ሆኖ የቆየ ሲሆን ከላይ ግለሰቡ የመሰረታቸው ወይም የሰራባቸው በሚል ሚዲያው የዘረዘራቸው የስራ መደቦች በሙሉ ከእዉነት የራቁ ናቸው።

አጠቃላይ ግለሰቡ በተቋሙ የቆየበትን ሁኔታ ስንመለከት በደብዳቤ ቁጥር ወምቢ/አ5/1143/14 በተፃፈ ደብዳቤ ግለሰቡ በፖሊስ ሳይንስ የድህረ ምረቃ ትምህርቱን አጠናቅቆ በፎረንሲክ ምርመራ ምክ/ዋና መምሪያ ስር ፈፃሚ አባል ሆኖ ተመድቧል። ከዚህም በኋላ በደብዳቤ ቁጥር ወምቢ/ሠ271/3852/17 በተፃፈ ደብዳቤ ደግሞ በአይሲቲ ዋና ክፍል የአይሲቲ ባለሙያ ሆኖ እንደተመደበ ለማወቅ ተችሏል። ግለሰቡ በተመሳሳይ ዓመት በደብዳቤ ቁጥር ወምቢ/ሠ271/4247/17 ዓ.ም ጀምሮ በተቋሙ በፎረ/ም/ም/ዋና መምሪያ በፎረ/ምር/ላብራቶሪ ስር አባል ሆኖ እንደቆየም ተጨባጭ መረጃዎች እና ማስረጃዎች ጠቁመዋል።

ነገር ግን እዉነታው ይህ ሆኖ ሳለ የነውረኞች ጥርቅም ኢትዮ 360 ሚዲያ መረጃዉን ከየት አምጥቶ ነው ያን ሁሉ ስልጣን እና እውቀት ለም/አ/ር ዘሪሁን ምትኩ የሰጠው? ግለሰቡ በቅጡ ሰምቶት ስለማያውቀው ጉዳይ እምጥተው የመጀመሪያው ፖሎግራፊ የምርመራ ቴክኒክ መስራች ምንትሴ ሲሉስ ትንሽ ነውር አይሰማቸውም እንዴሁ?ለነገሩ ነውር ጌጣቸው አይደል!

በ2014 ዓ.ም በፖሊስ ሳይንስ የድህረምረቃ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ሰው እንዴት ሆኖ ነው የኬሚካል ባይሎጂካል ራድዬሽን ኒውይክለር ዲፓርትመንት መስራች፣ በኢትዮጵያ የባይሎጂካል ሽብር መከላከል ኢንተርፖል ተጠሪ እና የመጀመሪያው ፖሎግራፊ የምርመራ ቴክኒክ መስራች ሊሆን የቻለው? የሆነው ሆኖ የሚዲያውን ቅጥፈት ከዚህ በታች የተቀመጠውን የምስል መረጃ በማየት ሁሉም ሰው ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡

በቃ!🤔
18/09/2025

በቃ!🤔

በጎጃሙ ፋኖ ሞት የታወጀበት በላይነህ አላምነው !እራሱን የጎጃሙ ፋኖ ብሎ የሚጠራው ቡድን ውስጥ የተለኮሰው እሳት ተጋግሎ እንደቀጠለ ነው። በዚህ ግጭት እስከ ዛሬ ከተፈጠሩ የእርስ በርስ ግጭ...
18/09/2025

በጎጃሙ ፋኖ ሞት የታወጀበት በላይነህ አላምነው !

እራሱን የጎጃሙ ፋኖ ብሎ የሚጠራው ቡድን ውስጥ የተለኮሰው እሳት ተጋግሎ እንደቀጠለ ነው። በዚህ ግጭት እስከ ዛሬ ከተፈጠሩ የእርስ በርስ ግጭት ለየት ያለእና በቁጥር የሚያዳግቱ ወጣቶች እንደቅጠል መርገፋቸውን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያሳያሉ።

ነገሩን ያባባሰው የእርስ በርስ አለመተማመን ሲሆን አንዱ አንዱላይ እንዲነሳም ምክንያት ሆኗል።በዚህም በላይነህ አላምነው የሚባል የጎጃሙ ፋኖ አመራር የነበረ ግለሰብ ላይ ከቡድኑ አባላት በከፊሉ ጣት እየቀሰሩበት ይገኛል።ከዚህም በተጨማሪ እርስ በርስ የመጋጨታችን ምክንያት በላይነህ የለኮሰው እሳት ነው በሚል ለመረሸን እየፈለጉት ይገኛሉ።
እንግዲህ ከወዲሁ ነፍስ ይማር ብለናል።

የጽንፈኝነት መጨረሻው እራስን መብላት ነው!

18/09/2025

#ጌች🤔
ጫካ ፕሮጀክትን ስጎበኝ አዲስ ከተማ እንጂ ቤተ መንግሥት አላየሁም
አቶ ጌታቸው ረዳ

የአውግቸው ተረፈን “ወይ አዲስ አበባ” ሳነብ አንድ የሚያስቀኝ ክፍል አለ፡፡ ከጎጃም ገጠር የመጣው አውግቸው አንድ ቀን አራዳ ሲዘዋወር “አንድ ረዥም ሕንጻ” ያያል፡፡ እዚያ ሕንጻ ሥር ቆሞ ...
18/09/2025

የአውግቸው ተረፈን “ወይ አዲስ አበባ” ሳነብ አንድ የሚያስቀኝ ክፍል አለ፡፡ ከጎጃም ገጠር የመጣው አውግቸው አንድ ቀን አራዳ ሲዘዋወር “አንድ ረዥም ሕንጻ” ያያል፡፡ እዚያ ሕንጻ ሥር ቆሞ ሽቅብ ሲያየው፣ ሕንጻው “ዘመም እያለ ወጥቶ” ሊወድቅ የደረሰ ይመስለዋል፡፡ ከዚያ “ወግድ ሊወድቅ ነው” እያለ ሩጫውን ተያያዘው፡፡ ሩጦ ሩጦ ከደከመው በኋላ ነበር ሕንጻው እንዳልዘመመና እንደማይወድቅ የገባው፡፡ ለካስ ሊወድቅ የደረሰው በረሃብ የተሰቃየው ራሱ አውግቸው ነበረ፡፡

አንዳንዴ ዋሽንግተን ፓርኪንግ ሎት ውስጥ ተቀምጠው “መንግሥት ሊወድቅ ነው” የሚሉትን ሰዎች ስሰማ አውግቸው ተረፈ ትዝ ይለኛል፡፡

ከሥር ሆኖ፣ ቀና ብሎ ማየት፣ እንዴት ከባድ ነገር ነው፡፡ ራስ ያዞራል።
ዳንኤል ክብረት

ኢትዮጵያ ልጇን አሰብን አግኝታ ናፍቆቷን ትወጣለች!የኢትዮጵያ ህዝብ አሰብን እንደ የዘላለም ልጁ አድርጎ ይቆጥራታል። የባህር በር እና የኢኮኖሚ ህይወት መተንፈሻ ከመሆኗ በተጨማሪ አሰብ እና ...
18/09/2025

ኢትዮጵያ ልጇን አሰብን አግኝታ ናፍቆቷን ትወጣለች!

የኢትዮጵያ ህዝብ አሰብን እንደ የዘላለም ልጁ አድርጎ ይቆጥራታል። የባህር በር እና የኢኮኖሚ ህይወት መተንፈሻ ከመሆኗ በተጨማሪ አሰብ እና ኢትዮጵያ የነበረችው ታሪካዊ እና ባህላዊ ትስስር ጥልቅ ነው። በአሁን የተነሱ የባህር በር ጥያቄ ኢትዮጵያ ለልጇ አሰብ ያላትን ጥልቅ ናፍቆት ያሳያል። አሰብ ከኢትዮጵያ ጋር ብትቀላቀል የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከማደጉም በተጨማሪ፣ የሺህ አመታት ታሪካዊና ህዝባዊ ትስስርም ወደ ቦታው ይመለሳል የሚል እምነት በብዙዎች ዘንድ አለ።

በዚህ ምክንያትም ኢትዮጵያ ልጇን አሰብን አግኝታ ናፍቆቷን የምትወጣበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን ግልፅ ነው።

18/09/2025

ከተሜነት ለሽፍታ አይመችም

17/09/2025

ታሪካዊ ክደት🤔🤔😮😮
#መረጃ

17/09/2025

ጃውሳ የአማራ ህዝብ ጠላት እንደሆነ ከራሳቸው ሰው

ሀገር መውደድን፣ አርቆ አስተዋይነት፣ ፅናት እና ቁርጠኝነትን በተግባር ሆነህ አሳይተሃል።  #የመደመርመንግስት
17/09/2025

ሀገር መውደድን፣ አርቆ አስተዋይነት፣ ፅናት እና ቁርጠኝነትን በተግባር ሆነህ አሳይተሃል።
#የመደመርመንግስት

17/09/2025

ኢትዮጵያ ሰላም ታስቀድማለች፣ ደህነትን ትፋለማለች፣ መውጫ መግቢያ በሯን ታበጃለች!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አቢሲኒያ ሚዲያኢትዬ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share