ፅናት ሚዲያ -Tsinat media

  • Home
  • ፅናት ሚዲያ -Tsinat media

ፅናት ሚዲያ -Tsinat media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ፅናት ሚዲያ -Tsinat media, Media/News Company, .

ምክርና ጥቆማ ለፌደራል ፖሊስ፤ የጅምላ ፍተሻ ሕዝብን ማሸበር ነው፤+++በትላንትናው የመንግስት ዜና እወጃ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ማህበራዊ ድህረ-...
26/07/2025

ምክርና ጥቆማ ለፌደራል ፖሊስ፤ የጅምላ ፍተሻ ሕዝብን ማሸበር ነው፤
+++

በትላንትናው የመንግስት ዜና እወጃ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ማህበራዊ ድህረ-ገጾችን በመጠቀም ለአመጽ ቅስቀሳ የሚያደርኩ አካላትን አድኖ ለመያዝ የተጠናከረ የጅምላ ፍተሻና የእጅ ስልክ ብርበራ እንደሚያደርግ ዛቻና ማስፈራሪያዎች የተቀላቀለበት መግለጫ ሰጥቷል።

በመጀመሪያ ይህ ዜጎችን በየመንገዱ ድንገት አስገድዶ በማቆም ስልካቸውንም ሆነ እራሳቸውን የመበርበር እርምጃ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው፣ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች የሚጥስና ሽብርን የሚነዛ ሕገ ወጥ እርምጃ ነው። የከፋ ችግር ሲኖርና ለአጭር ጊዜ ብቻ ተመጣጣኝ የሆነ ብርበራ ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ሊካሄድ ይችላል። ነገር ግን ፖሊስ በአዋጅ ከነገ ጀምሮ የሁሉንም ሰው ስልክ በየመንገዱ እበረብራለሁ ብሎ እንዲያውጅና በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ የዜጎችን መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች እንዲጥስ የሚፈቅድ አሠራር ግን በምንም መልኩ ተቀባይነት የለውም። መንግስት አመጽ ለመቀስቀስ አስበዋል ብሎ የጠረጠራቸው አካላት ወይም ግለሰቦች እንኳ ካሉ የመበርበሪያ የፍርድ ቤት ማዘዣ አውጥቶ ሥራውን በጥንቃቄ ይሰራል እንጂ በጅምላ የዜጎችን ነጻነት በዚህ መልክ በማጥበብና በመግፈፍ ሕገ መንግስታዊ ጥሰት ሊፈጽም አይገባም።

ነገርየው ከመንግስታዊ ፍርሃት የመነጨ ሕዝብን የማሸበሪያና የማስጨነቂያ፤ እንዲሁም በህብረተሰቡ ውስጥ ፍርሃትን የማስረጽ ስልት እንደሆነ ማሳያው ከአገር ውጪ ሆነው መረጃ የሚያሰራጩትንም አንምርም የምትለው ሐረግ ነች።

ለማንኛውም የኔ ምክር ፌደራል ፖሊስ የዜጎችን መረጃ የመለዋወጥ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና ያለ በቂ ምክንያት ያለመጠርጠርና ያለመፈተሽ መብትን በመጣስ ሊፈጽም ያሰበውን ሕገ ወጥ ተግባር ከወዲሁ እንዲገታና በእርግጥም አመጽ ለመቀስቀስ የተዘጋጁ አካላት መኖራቸውን የደረሰባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ካሉ ሕጋዊ ሥርአትን በተከተለ መልኩ እና በበቂ መረጃ ላይ ተመስርቶ በተጠረጠሩት ላይ ብቻ በማተኮር አደጋውን እንዲከላከል ነው። ለዛ ደግሞ የፖሊስ የዕለት ተዕለት ሥራ ስለሆነ እወጃ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ አያስፈልገውም።

ይልቅስ ለፖሊስ የምሰጠው ጥቆማ ደግሞ አዎ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አመጽ እና ከፍ ያለ ሕዝባዊ ቁጣ ሊቀሰቀስ የሚችልበት ሰፊ እድል አለ። ይህ እንዲሆን የሚከተሉትን ሕዝብን ለአመጽና ለቁጣ የሚቀሰቅሱ ተከታታይ እርምጃዎችን የታቀደ በሚመስል መልኩ በየቀኑ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ፤ ምንም እንኳ ሕዝቡ አልሰማና አላምጽ ቢለውም፤ አመጽ እንዲጠነሰስ፣ አመጽ እንዲቀሰቀስና አገሪቱ ወደለየለት ቀውስና ብጥብጥ እንድታመራ ሌት ተቀን በጀትና የሰው ሃይል መድቦ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል እየሰራ ያለ አካል አለ። እሱም ያው አገሪቱን የሚያስተዳድረው ራሱ የብልጽግና መንግስት ነው። ለጥቆማ ያህል፤

- መቶ ሺዎችን በከተማ ግንባታና በኮሪዶር ልማት ስም ቤታቸውን አፍርሶ፣ ንብረታቸውን ሜዳ ላይ በትኖ፣ ከቀያቸውም አፈናቅሎ መንደራቸውን ለከበርቴና ለውጪ ዜጎች በመቸብቸብ ሕዝብን ለአመጽ የቀሰቀሰ፣

- በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ካሉ ታጣቂዎች ጋር ጦርነት ውስጥ ገብቶ ሚሊዬኖች እንዲፈናቀሉ፣ በመቶ ሺዎች እንዲሞቱ፣ በአስር ሺ የሚቆጠሩ ሴቶችና ሕጻናት እንዲደፈሩ፣ የሕዝብና የአገር ሀብት እንዲወድም ዋነኛ ምክንያት በመሆን ሰላም ፈላጊውን ሕዝብ ለአመጽ የቀሰቀሰ፣

- ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳይመለሱ በማድረግና በተበላሸ የትምርት ሥርዓት ሚሊዮን ወጣቶች ሥራ አጥ እንዲሆኑ በማድረግ፣ የሥራ ዋስትና በማሳጣት ወጣቱን ለአመጽ የገፋፋና ያነሳሳ፣

- በየቀኑ በሚንረው የኑሮ ውድነት ሳቢያ ልጆቹን በቀን አንዴ ማብላት የተሳነው የመንግስት ሰራተኛ እርሃቡን ለማስታገስና ቤተሰቡን ለመቀለብ ፌስታል ይዞ በየሆቴሉ ትርፍራፊ እንዲለምን በማድረግ፤ ያም አልበቃ ብሎት ተመጣጣኝ ያልሆነ የገቢ ግብር ከሠራተኛው ደሞዝ ላይ እንዲጎመድ የሚያደርግ አዋጅ ያጸደቀና በፖርላማ ጭምር ቢለመን አሻፈረኝ በማለት ሠራተኛውን ለአመጽና ለአድማ የገፋፋና ያነሳሳ፣

- ወጣቱን በየምክንያቱ በጅምላ እያፈሰ በየማጎሪያ ውስጥ ያለምንም የፍትህ ሂደት አሥሮ በማሰቃየት በአገሩ ላይ እንዲያቄም፣ አገሩን እንዲጠላ፣ ጫካ ገብቶ ነፍጥ እንዲይዝና ገሚሱም በባህርም እንዲሰደድም ምክንያተት በመሆን መጣቱን ለወንጀልና ለአመጽ የገፋፋና ያበረታታ፣

- ነጋዴውን በየምክንያቱ ለመንግስት ድግስና የልማት ማስኬጃ ገንዘብ አምጣ እያለ ከማማረር አልፎ ተመጣጣኝ ያልሆኑና አንዳንዴም ምንም አይነት ሕጋዊ መሠረት የሌላቸው የግብር አይነቶችን በመጫን ያማረረና ብዙዎች የንግድ ሥራቸውን እንዲያቆሙ ጭምር ምክንያት በመሆን ነጋዴውን ለአመጽና ለአድማ ያነሳሳና የገፋፋ፣

- የፖለቲካ ፖርቲዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና የመብት አቀንቃኞችን እያዋከበ፣ እያሰረ፣ እያሳደደ፣ ከአገር እንዲሸሹ እየያደረገና ሲከፋም እንደ አቶ በቴ በጥይት ደብድቦ እየደፋ ለአመጽ እንዲነሳሱ፣ ከሰላማዊ ትግል ይልቅ ነፍጥን እንዲመርጡ ያላሰለሰ ጥረትና እርምጃ እየወሰደ ያለ፣

- ዜጎች በነጻነት ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱና በሰላም ወጥቶ መግባት ከባድ እስኪሆን ድረስ የደህንነት ስጋት እንዲገጥማቸውና የሕግ የበላይነትን የማስፈን ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አቅቶት በአገሪቱ የደቦ ፍርድና ጭካኔ የተሞላው የግፍ እርምጃ እንዲስፋፋ በማድረግ ሕዝብ የመንግስት ያለህ ብለሰ እንዲያምጽና አደባባይ ወጥቶ ፍትህ እንዲጠይቅ ተግቶ እያነሳሳ ያለ፣

ሌሎችም ሕዝብን ለአመጽ የሚዳርጉ እጅግ በርካታ የግፍና ሕገ ወጥ እርምጃዎችን በተከታታይ እየወሰደ አገሪቱ ምድራዊ ሲኦል እንድትመስልና ወደ ከፋ ግጭትና ነውጥ እንድትገባ ያደረገው የብልጽግና አስተዳደር ሆኖ ሳለ የፌደራል ፖሊስ ይሄ ሁሉ ውርጅብኝ ለአመታት ሲወርድበት በዝምታ እያስተናገደ አላምጽም፣ አላድምም፣ ደግ ቀን እስኪመጣ እጸልያለሁ እያለ ወደፈጣሪው የሚያለቅስን ሕዝብ በአመጽ በመጠርጠር የእጅ ስልክህ ውስጥ የተደበቁ አመጽ ቀስቃሾችን ለመፈለግ ብርበራ አደርጋለሁ የሚል የማስፈራሪያ ዜና እወጃ ይዞ አደባባይ ብቅ ማለቱ ምነዋ? ይህ የፖሊስ ዛቻና ሽብር መንግስት አሁንም አገሪቱ ከገባችበት አደገኛ ሁኔታ እና አዘቅት ለመታደግ ዝግጁ አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን ብቃቱም እንደሌለው፣ ብልሃቱም እንደጠፋው ማሳያ ይመስለኛል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አመጸኛ ቢሆን ኖሮ ብልጽግና ታሪክ ሆኖ የሚያልፍበት ዘመን ቢያንስ ወደኋላ በሦስትና አራት አመት ይመለስ ነበር።

'ሕዝብ እና እምቢተኝነት' በሚለው ቀጣይ ጽሁፌ 'ሕዝባዊ እምቢተኝነት' ወይም civil disobedience ከሰብአዊ መብቶች አንዱ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ምን መልክ እንዳለው በሰፊው እመለስበታለሁ።

እስከዛው ፌደራል ፖሊስ ሕዝብን ለቀቅ አድርጎ አለቆቹን ጠበቅ እንዲያደርግ እመክራለሁ።

ቸር እንሰንብተት
Yared Hailemariam

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አቶ ያሬድ ኃ/ማሪያም

ሰበር መረጃ!ለፅናት ሚዲያ የደረሰ በዛሬው እለት  በቀን 18/11/2017ዓ.ም የኦሕዴድ ብልፅግና ልሳናት በጀሞ ሶስት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ማርያም ሰፈር ፖሊስ ጣቢያ የተፈፀመውን ክስተት ከሆለ...
25/07/2025

ሰበር መረጃ!

ለፅናት ሚዲያ የደረሰ

በዛሬው እለት በቀን 18/11/2017ዓ.ም የኦሕዴድ ብልፅግና ልሳናት በጀሞ ሶስት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ማርያም ሰፈር ፖሊስ ጣቢያ የተፈፀመውን ክስተት ከሆለታ እና ከጋርመንት ሰዎችን ሰብስበው በማምጣት የአይ ኤስ እና ኦነጎ ጥቃት ነው እንዲሉ ሐሰተኛ ቃለመጠይቅ አድርገዋል።

በዚህ ጉዳይ ዶክመንታሪ እያዘጋጀ ሲሆን ክስተቱንም በአይ ኤስና ኦነግ የተፈጸመ ነው በማለት በቀጣይ በአዲስ አበባ የታቀደ አደገኛ አደጋ በአይ ኤስና ኦነግ ለማሳበብ እንደሆነ የፅናት ምንጮች አረጋግጠዋል። የዚህ የሐሰት መረጃ ሰለባ የሚሆነው ከጦርነት ጋር በተያያዘ የአማራና ትግራይ የአዲስ አበባ ወጣት የብልፅግና ተቃዋሚ የማጥቂያ መሳሪያ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስንገልጽ ቆይተናል። ይህ የአፈሳ ዘመቻ ለማከናወን በዝግጅት ላይ ናቸው ሲሉ የመረጃ ምንጮች እየገለጹ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንፍረስ እንዳይበላሽብን አዲስ አበባ በውጥረት ተከባለች የፀጥታ መዋቅሩ በፅንፈኞች እጅ ተጠልፏል። አዲስ አበባ በፀጉረ-ልውጥ እየተፈተነች ነው ከአቅማችን በላይ ሆ...
25/07/2025

የአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንፍረስ እንዳይበላሽብን አዲስ አበባ በውጥረት ተከባለች የፀጥታ መዋቅሩ በፅንፈኞች እጅ ተጠልፏል። አዲስ አበባ በፀጉረ-ልውጥ እየተፈተነች ነው ከአቅማችን በላይ ሆኗል።

ይኽን ቡድን የሚቀሰቅስና የሚያደራጅ በውስጥና በውጪ ይገኛሉ። ከጌዲዮን ውጪ ጉዳይ ሚ/ር ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር እናውላቸዋለን። ውስጣችን አልጸዳም የፀጥታ መዋቅሩ የእጅ ስልክ ይፈተሽ ወደከተማው የሚገቡና የሚወጡ በአራቱም አቅጣጫ ቁጥጥር ይደረግ ሰላማችን ተናግቷል።
የጨነቀው የፌ/ፖ ደንበላሽ ገ/ሚካኤል

25/07/2025

የቦሌ አዝማሪ

የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባል ሙሉነሽ ጌታዬ መታወቂያ ለመጠየቅ በሄደችበት በፌደራል ፖሊስ ዳግማዊ አፈና ተፈፀመባት።አውሎግሶን አንድነት-Awulogson Andinet ፣ ሀምሌ 17/2017...
24/07/2025

የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባል ሙሉነሽ ጌታዬ መታወቂያ ለመጠየቅ በሄደችበት በፌደራል ፖሊስ ዳግማዊ አፈና ተፈፀመባት።

አውሎግሶን አንድነት-Awulogson Andinet ፣
ሀምሌ 17/2017 ፣ አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባል ሙሉነሽ ጌታዬ አዳነ ትባላለች።

ነዋሪነቷ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ቻይና ካንብ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

በአዲስ አበባ ፖሊስ አማካኝነት ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሚያዝያ 8/2017 ነበር የመጀመሪያው አፈና የተፈፀመባት።

በወቅቱ የተያዘችውም ከትዳር አጋሯ ከአበባው ነገሰ አለኽኝ ጋር ነበር ፤ በሽብር ወንጀል የተከሰሰው አበባው ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት ወርዶ አሁንም ድረስ በእስር ላይ መሆኑ ይታወቃል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማዕከላዊ (ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ) ያለፍትህ ከሚያዝያ 8/2017 እስከ ሰኔ 20/2017 በእስር ላይ ቆይታለች።

ከሰኔ 20/2017 ጀምሮ ግን ክስ ተመስርቶባታል መባሉን ተከትሎ ወደ ቃሊቲ ማ/ቤት ተወስዳለች።

የቀረበባት ክስም መጀመሪያ ላይ ሽብር በሚል በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ ፍ/ቤት ትቀርብ ነበር።

በመቀጠልም ሀሰተኛ ሰነድ በሚል መደበኛ ክስ ስለተመሰረተባት በዛው ልደታ ሁለተኛ ወ/ችሎት ፍ/ቤት ስትመላለስ ቆይታለች።

በመጨረሻም ሰኔ 10/2017 በ3 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትፈታ ፍ/ቤቱ በመወሰኑ ሀምሌ 10/2017 ግዴታዋን ከፍላ ሀምሌ 11/2017 ከቃሊቲ እስር ቤት ተፈታለች።

ይህን ተከትሎ ሀምሌ 15/2017 ወደ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሜክስኮ በተያዘችበት ወቅት የተወሰደባትን ፋይዳ (ዲጂታል) መታወቂያ ለመቀበል ትሄዳለች።

ዳሩ ግን ሙሉነሽ በሄደችበት አልተመለሰችም ፤ በዛው ቀረች ፤ መላ ቤተሰቡም ለከፋ ጭንቀትና አለመረጋጋት ተዳረገ።

ሙሉነሽን የበላ ጅብም አልጮህም አለ።
በመጨረሻ ግን ከመቼ ጀምረው ከፌደራል ፖሊስ ተረክበው እንደወሰዷት ባይታወቅም ቤተሰብ ሲያፈላልግ ሀምሌ 17/2017 በደብረ ብርሃን ከተማ ተገኝታለች።

የተገኘችውም በከተማው ውስጥ ባለ እቴጌ ጣይቱ ክ/ከተማ 8ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለዳግም እስር ተዳርጋ ነው።

የሙሉነሽ እጣፈንታ ፍ/ቤቱ እንዳዘዘው እና የዋስትና ገንዘብ እንደከፈለችው መፈታት ሳይሆን ከእስር ወደ ሌላ እስር ፣ ከአንደኛው አፈና ወደ ሌላኛው አፈና መንገላታት ሆኗል።

ጀግናዋ ሙሉነሽ ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ዳግም መንግስታዊ አፈና ሲፈፀምባት መቀየሪያ ልብስ እንኳ አልያዘችም ነበር።

ሙሉነሽ ከጥቅምት 2013 ጀምሮ የአማራ ልዩ ኃይል በይፋ ፈርሷል እስከተባለበት እስከ 2015 ድረስ በልዩ ኃይሉ ውስጥ አባል በመሆን ለክልሉ ብሎም ለሀገር ሰላምና ፀጥታ መስፈን የድርሻዋን ስታበረክት የቆየች ብርቱ ታጋይ ስለመሆኗ ለማወቅ ተችሏል።

በአማራ ማንነታቸው ምክንያት በፈጠራ የሽብር ወንጀል በተለያዩ አካባቢዎች ከሕግ ውጭ የታሰሩ እና እየታሰሩ ያሉ የብዙዎች የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች እጣፈንታ ተመሳሳይ ከሆነ ከራርሟል።

የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ መንግስታዊ እገታ ሲፈፀምባቸው በፌደራል ፖሊስ የሚወሰድባቸው ንብረት በአግባቡ ሕግና ስርዓቱን ጠብቆ አይመለስላቸውም ፤ ይልቁንስ ተዘርፈው ይቀራሉ እንጅ!- ይህ ተቋማዊ ዝርፊያ ሕገ ወጥ ሕግ አስከባሪነት ከማለት ውጭ ሌላ ምን ሊባል ይችላል!

እንደአብነትም ከበርካታ ዓመታት ተደጋጋሚ እና አሰልች የግፍ እስር በኋላ አሁን ላይ በስደት የሚገኘው ስንታየሁ ቸኮል ከወራት በፊት በዋስትና ከእስር ሲፈታ በፖሊስ የተወሰደብኝ ንብረት ይመለስልኛል በሚል አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሄደበት ወቅት በማይጠየቁ የአገዛዙ ኃይሎች በተመሳሳይ ለ4 ቀናት ያህል ዳግማዊ መንግስታዊ እገታ ነበር የገጠመው።

ፍትህ ለሙሉነሽ ጌታዬ!
ፍትህ በማንነታቸው የተነሳ በስደት ለሚኖሩ እና ያለምንም ፍትህ በግፍ እስር ላይ ለሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ይሁን!

24/07/2025

የፅናት ሚዲያ ቤተሰብ

"ኦህዴድ ማነው ስራችንን ጨርሰናል!?
ቀጣዩ የነሽመልስ እቅዶች በሚል ርዕስ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በፅናት ሚዲያ ፖለቲካውን እንዳስሰዋለን።
መረጃ እንለዋወጣለን ይጠብቁን።

የተለያዩ ፈጣን መረጃ እንዲደርሳችሁ ቴሌግራም ቻናላችን ተቀላቀሉ
የፅናት የዩቱብ ቻናል ሰብስክራይብ አድርጉ
የፅናት ፌስቡክ ገጽ ይወዳጁ።

https://t.me/SintayehuChekol

https://youtube.com/?si=Y-09FC_Y93WmTdyK

https://www.facebook.com/share/1QhfJYQNVp

24/07/2025

ፋኖ ወሳኝና ግዙፍ ሃይል እየሆነ መጥቷል።

የቀጠናው አሰላለፍ ወታደራዊ ነገሩ ተቀይሯል የአገዛዙ ሰራዊት በፋኖ እየፈረሰ ይገኛል ሰራዊቱ ተሰላችቷል። እጅ እየሰጠ ነፍሱን የሚታደግ የብርሃኑ ሰራዊት ወደመፈራረስ እየሄደ መሆኑ በማስረጃ እየተረጋገጠ ይገኛል። መሬት ላይ ካደረሱን መረጃ ይኽን ያሳያል።

ጀግናው የአማራ ፋኖ የብልፅግና አገዛዝ በመደምሰስ የቀጠናዉ ወሳኝና ግዙፍ ሃይል እየሆነ መጥቷል።

በእሳት ተፈትኖ በድል እየገሰገሰ ያለው የአማራ ፋኖ የአገዛዙ ሰራዊት በማንኮታኮት በትጥቅም በወጊያ የድል ፋሲካ ላይ ቆሟል። የሰራዊቱ የታችኛው አመራር ጎመን በጤና ራሳችን እናድን ጨዋታ ጀምረዋል። ማመን አለማመን ያንተ ፋንታ ነው ዐብይ አህመድ አብቅቶለታል። በፋኖና በነገው ዕጣፈንታ በሚወስኑ ሃይሎች ሀገሪቷ ወድቃለች። ተሰባሰብ!

Sintayehu Chekol - Balderas

የአገዛዙ ሰራዊት በፋኖ ተፈረካከሰ እጅ ሰጠፋኖ ጦርነቱን እያጠናቀቀው  ይገኛል
24/07/2025

የአገዛዙ ሰራዊት በፋኖ ተፈረካከሰ እጅ ሰጠ
ፋኖ ጦርነቱን እያጠናቀቀው ይገኛል

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፅናት ሚዲያ -Tsinat media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share