10/11/2025
ብላይ ተራራ
ብላይ ተራራ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን ጨታ ወረዳ ዲያ ቀበሌ ይገኛል፡፡
ከዞኑ ዋና ከተማ ከቦንጋ ከ65 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ እና ከወረዳ ዋና ከተማ ከሻማ በግምት 10 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝ ብላይ ተራራ ትልቅ የቱሪስት መዳረሻ ነው።
የተራራው ከፍታ 2600 ሜትር ሲሆን ይህም በከፍታው በካፋ ዞን ውስጥ ካሉ ተራራዎች መካካል የመጀመሪያ ያደርጋዋል።
ሌላው ይህን ተራራ ልዩ የሚያደረገው ለመጀመሪያ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በወረዳው መጥቶ ያረፈበትና የሰፈረበት መሆኑ ነው፡፡
በተራራው መጨረሻ ክፍል ላይ አራት ሄክታር ለጥ ያለ የእርሻ ማሳ የሚገኝ ስሆን ከአራት በላይ የምንጭ ውሃዎችም ይገኙበታል ።
ከቦንጋ ከተማና ከሌሎች አጎራባች ወረዳዎች እንድሁም ከሌሎች አጎራባች ዞኖች ማለትም ከኮንታ ፣ ከዳውሮ ፣ ከካንባታ ፣ ከቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ ዞን ወረዳዎች ሆኖ በቀላሉ የሚታይ ታሪካዊ የቱሪስት መስብ ስፍራ ነው።
ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክና ቴሌግራም ገፆቻችን ይከታተላሉ ፣ይወዳጁ👇👇👇👇👇????
በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100091368031356
በቴሌግራም፦https://t.me/C12g6/1057?single
በቲክቶክ፦https://vm.tiktok.com/ZMHtnCGMKnVKa-Th2vR/