10/07/2025
አርሰናል ቀነ ገደብ ተሰጠው
ስፖርቲንግ ሊዝበን አርሰናል የቪክቶር ዮኬርሽን ዝውውር እንዲያጠናቅቅ ቀነ ገደብ ሰጠ
አርሰናል የስፖርቲንግ ሊዝበን አጥቂውን ቪክቶር ዮኬሬሽን ለማስፈረም ድጋሚ አዲስ መነቃቃትን የጀመረ ሲሆን የፖርቹጋሉ ክለብ በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት ውስጥ ከባድ ድርድር ለመቀጠል መዘጋጀቱን ዘ ሚረር ጆን ክሮስ ዘግቧል።
ለ27 አመቱ ስዊድናዊ ኢንተርናሽናል የዝውውር ክፍያ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት በስፖርቲንግ የመሸጥ ፍላጎት መቀዛቀዝ የታየ ሲሆን ከአውሮፓ ድንቅ አጥቂዎች አንዱን ለማስፈረም ድርድር ለማካሄድ በድጋሚ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
አርሴናል ከ 2025/26 የውድድር ዘመን በፊት የ9 ቁጥር ተጫዋች ለመጨመር በዚህ ክረምት ዮኬሬሽ የአንድሬ በርታ እና የ አርቴታ ምኞት ዝርዝር አናት ላይ ይገኛል።
በ2023 ከኮቨንተሪ ሲቲ ስፖርቲንግን ከተቀላቀለ በኋላ አጥቂው በ102 ጨዋታዎች 97 ጎሎችን አስቆጥሯል፤ ባለፈው የውድድር አመት 54 ጎሎችን በ52 ጨዋታዎች ያስቆጠረ ሲሆን በቻምፒየንስ ሊግ ማንቸስተር ሲቲ ላይ ሃትሪክ መስራቱ ይታወቃል።
Via [ Mirror Football ]