Orodollo press Agency

  • Home
  • Orodollo press Agency

Orodollo press Agency Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Orodollo press Agency, Media/News Company, .

የዶክተር ስነ ምግባር የሌለው ታካሚዎች ለዛውም ሴት የሚማታ ጥልዝ!!!
11/03/2026

የዶክተር ስነ ምግባር የሌለው ታካሚዎች ለዛውም ሴት የሚማታ ጥልዝ!!!

14/12/2025

ዜና፡ የፌዴራል መንገድ መዘጋት በሺንሺቾ ከተማ – የአሽከርካሪዎች እንግልትና የመንግስት አካላት ምላሽ ማጣት

ሺንሺቾ፣ ከምባታ ዞን – በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በከምባታ ዞን ስር በምትገኘው ሺንሺቾ ከተማ የሰርግ ፕሮግራምን ምክንያት በማድረግ ሁለቱም የፌዴራል መንገዶች መዘጋታቸውን ተከትሎ በአሽከርካሪዎችና ተጓዦች ላይ ከፍተኛ እንግልት መድረሱን ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

ለነገ እሁድ ለሚደረግ የሰርግ ሥነ-ሥርዓት ዝግጅት ተብሎ፣ ዛሬ ቅዳሜ ከሌሊት ጀምሮ የመንገዱ መዘጋት ተፈጽሟል። ይህ መዘጋት በከተማው ውስጥ የሚያልፉትን ሁለቱን ዋና ዋና የፌዴራል የመንገድ መስመሮች ያካተተ ነው።

መንገዱ በአግባቡና በጊዜያዊነት መዘጋቱ ባስከተለው መስተጓጎል፣ መንገዱን ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚጠቀሙ የሕዝብና የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች፣ እንዲሁም ሞተረኞች ለእንግልት ተዳርገዋል።

“የከተማውን ትራፊክ ፖሊስ እና የመንገድ ትራንስፖርት ባለሙያዎችን ለማነጋገር ሞክረን ነበር፤ ሆኖም ግን ችግራችንን የሚፈታ ምንም ዓይነት ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም” ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ለዜና ክፍላችን ገልጸዋል።

የፌዴራል መንገዶች የሀገሪቱ የትራንስፖርት መረብ የጀርባ አጥንት በመሆናቸው፣ መዘጋታቸው የሚፈቀደው በከፍተኛ የመንግሥት አካላት ውሳኔና በግልጽ በታወቁ ልዩ ሁኔታዎች ስር ብቻ ነው።

ለግል ዝግጅት ሲባል ሁለቱንም የፌዴራል መንገዶች በአንድ ጊዜ መዝጋት በሕግ አግባብ የተፈቀደ ስለመሆኑ ጥያቄ ተነስቷል።

የመንገድ ትራንስፖርት ጉዳዮችን በበላይነት የሚከታተለው የፌዴራል ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወይም የአካባቢው የትራንስፖርት ቢሮዎች ብቻ ለጊዜያዊ የሥራ ወይም የድንገተኛ አደጋ ምክንያቶች አማራጭ መንገድ በማዘጋጀትና ለሕዝብ በማሳወቅ የመዝጋት ሥልጣን ሊኖራቸው ይችላል።

የአሽከርካሪዎቹን ቅሬታ ተከትሎ፣ የዜና ክፍላችን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ለማግኘት ወደሚመለከታቸው ከፍተኛ ተቋማት ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎችን አድርጓል።

* ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትራንስፖርት ቢሮ

* የፌዴራል ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
ሆኖም ግን፣ የሚመለከታቸውን ኃላፊዎች ማግኘት አልተቻለም።

በመሆኑም፣ የዜና ክፍላችን መንገዱ ተዘግቶ በሕዝብ ላይ ስለደረሰው እንግልት እና ስለጉዳዩ ሕጋዊነት የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች መግለጫ ካላቸው ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

ዘጋቢ፡ ሔኖክ ወ/ገብርኤል

🌴🌴🌴

13/12/2025
ይሄን ዘመን ያመጣሽ ኦሮሞ ነኝ ባይ እዩልኝ !
26/05/2025

ይሄን ዘመን ያመጣሽ ኦሮሞ ነኝ ባይ እዩልኝ !

26/02/2025

የሺንሽቾ ህዝብ ሆይ መጠየቅ ልመድ!

ፋይናንስ በየቀኑ በአበል እያለቀ ያለው ግብር ብለው ላንቃህ ላይ ቆመው የሰበሰቡት ብር ነው። ስለዚህ ለምን ብለህ አስቁም! በየስጋ ቤቱ እና ከአገር እስከአገር እየዞሩ እየጠጡ እየጨፈሩ የምዝናኑት በብርህ ነው ስለዚህ የት አስገባችሁት ምን ሰራችሁበት በል።

ማህበረሰብ መድሃንት ቤት በፍጥነት ኦድት ይደረግ ከፍተኛ ዝርፍያ እየተካሄደበት ነው። መድሃኒት ለውጭ መድሃንት ቤት ሳይቀር በውሸት ማዘዣ እያወጡ እያዘረፉ ነው ስለዚህ ጠይቅ ብርህ ነው እየተዘረፈ ያለው።
ሆስፒታሉ በነዚህ ሶስት አመታት አንዴም ኦድት ተደርጎ አያቅም አሁንም በተስፋውን ቀጭን ትዕዛዝ የተጀመረው ኦድት እንድቆም ተደርጓል ስለዚህ በፍጥነት ጠይቅ ኦድት ርፓርት እንድወጣ!

ማጤማ አድስ ብለው ስመጡ አድስ እሺ በል ግን ደግሞ መድሃኒት አስገቡ በል ባዶ ሆስፒታል ለምትሄደው ፋራስታሞል እንኳን ለማታገኝበት ብታድስ ምን ያደርግልሃል። የህክምና ማሽኖች እንድገዙ ጠይቅ። ያሉትንም አስተካክሉ በላቸው መብትህ ነው በብርህ ነው ነው አበል እያሉ ምወራጩት። በትንንሽ ምክንያቶች ዱራሜ ሶዶ ሆሳዕና መሄድ አልሰለቸህም? ሁሉንም ነገር ከውጭ ግዛ ውጭ አሰራ መባል አልደከመህም?

በነፃ በመንግስት ድጎማ የምመጣውን የወባ መድሃኒት ከሆስፒታል አውጥተው አገባቢው ላይ ባሉ ፓርማስዎች በ1000ሺ እና ከዛ በላይ ስያስገዙክ ለምን አትጠይቅም ምን እስክትሆን ነው የምትጠብቀው? በ3 ወር ውስጥ የማህበረሰብ ፋርማስውን ግንባታ እንጀምራለን ብለው የሰበሰቡት ብር የት እንደገባ ጠይቅ! ሁሌ እየተዘረፍክ እና እየተጨበረበርክ ለምን ትኖራለህ

16/01/2025

ለሚመለከተው ሁሉ

በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ሥር ለአነስተኛ ቤት መሥሪያ ቦታ እንዲሰጠን ብዙ ግዜ በአካል ተመላልሰን ብንጠይቅም ምንም አግባብ ያለውን መልስ ለማግኘት ስላልቻልንእና በጣም እየተጉላላን ስለሆነ መብታችንን ለማስከበር ስንል ሁሉም የመከላከያ ሠራዊት ፤መምህራን፤የጤና ባለሙያዎች/ሆስፒታል ሠራተኛ/፤ እና ከተየያዪ ሴክተር መሥሪያ ቤት በማህበር ተደራጅተን የነበርን ጥያቄያችን ለሚመለከተው አካል ለማሰማት ስንል በቅርቡ ሠላማዊ ሠልፍ የምንወጣ መሆኑን በአክብሮት ለማሳሰብ እንወዳለን !

"ቅድሚያ ለከተማው ወጣት "!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Orodollo press Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed media company?

Share