Tena Adam Medeia and Communication

  • Home
  • Tena Adam Medeia and Communication

Tena Adam Medeia and Communication Reliable source of information!

24/09/2024

የማንጨርሰውን አንጀምርም።
Red sea!

11/09/2024

2017 እንኳን አደረሰን መልካም በዓል ይሁንልን

Disgusting image!
05/09/2024

Disgusting image!

05/09/2024

አራት ኪሎ ግን እንደዚህ የሚያስጎመጃቸው በጤና ነው???

ኢትዮጵያና ሞሮኮ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ ግብፅ ድንጋጤ ውስጥ ገባችራባት -የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም እና ጄኔራል ኢታማዦር ሹም ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገላቻን ከነሐሴ 25 እስከ ...
30/08/2024

ኢትዮጵያና ሞሮኮ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ ግብፅ ድንጋጤ ውስጥ ገባች
ራባት -የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም እና ጄኔራል ኢታማዦር ሹም ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገላቻን ከነሐሴ 25 እስከ 29 በሞሮኮ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገላቻን ተቀብለዋል።

በራባት በሚገኘው የብሔራዊ መከላከያ አስተዳደር ዋና መሥሪያ ቤት ባደረጉት ውይይት ሁለቱ ባለሥልጣናት በሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብር ሁኔታ ላይ ተወያይተው የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክሩባቸውን መንገዶች ገምግመዋል።

ሁለቱም ባለስልጣናት በሞሮኮ እና በኢትዮጵያ መካከል ባለው ወዳጅነት እና ትብብር መደሰታቸውን ገልፀው በቀጣይ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት እና ቁርጠኝነት አፅንዖት ሰጥተው ነበር ሲል የፋርስ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም መግለጫ አመልክቷል።

ውይይቱ በተለያዩ የወታደራዊ ትብብር ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ባለስልጣናቱ በሁለቱ ጦር ኃይሎች መካከል ያለውን እድገት አድንቀው ይህንን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ወደ ሌሎች የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳዮችም መክረዋል።

ሞሮኮ እና ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ትብብር፣ በፖለቲካ ድጋፍ እና በባህል ልውውጥ የሚታወቁ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ጠብቀዋል። ሁለቱም ሀገራት በአፍሪካ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ ታሪክ ያላቸው እና በክልላዊ ጉዳዮች አንዳቸው የሌላውን አቋም ይደግፋሉ።

የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል።

እ.ኤ.አ ህዳር 2016 ንጉስ መሀመድ 6ኛ ኢትዮጵያን ጎብኝተው የሁለትዮሽ ግንኙነትን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ርምጃ አሳይተዋል። በዚህ ጉብኝት የሞሮኮ ኦሲፒ ቡድን በድሬዳዋ ሰፊ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። 3.7 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማሳደግ ያለመ ነው።

24/08/2024
22/08/2024

በእንተ ፍቁር ወልድከ መሐረነ አብ።
አብ ሆይ፤ በተወደደው ልጅህ ማረን።

02/08/2024

መሠረተ ድንጋይ 🤣🤣🤣🤣🤣
23/07/2024

መሠረተ ድንጋይ 🤣🤣🤣🤣🤣

16/07/2024

የክርስትና እውነተኛ ልኬቱ ክርስቶስ ኢየሱሰ ባይኾን፣ ምን ይውጠን ነበር? አብ ሆይ የቤተክርስቲያንን ራስና መሥራች ክርስቶስን ብቻ ስላደረግህ አመሠግንሃለኹ!

05/07/2024

ወርቅ ሲደብስ!


ጳጳሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን አላነበቡምን?

ጳጳሱ ለማርያም ያላቸው አስተምኅሮ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒ የቆመ ነው፤ እንዲህ ያለ ነገር በርግጥ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ “የታወቁ መምህራን” የሚናገሩት ነው፤ ከዚህ ቀደም ዲያቆን ኃይሌ፣ “እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን መሥራት ትችላለች” ብሎ መናገሩንና ለዚህም ምላሽ መስጠታችን ይታወሳል፡፡ ለምን ኾን ብለው ማርያምን በማግነንና በማስመለክ፣ እግዚአብሔርንና ስሙን መሳደብ እንደሚፈልጉ አላውቅም፤ እግዚአብሔርንና እግዚአብሔር በልጁና በመንፈሱ የሠራውን ሥራ ባለማወቃቸውም እጅግ እደነቃለሁ!

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኤጲስ ቆጶስ መኾን ስላለበት አገልጋይ ሲናገር፣ “እንደ እግዚአብሔር መጋቢ … ለማስተማር የሚበቃ፥” (ቲቶ 1፥7፤ 1ጢሞ. 3፥2) ይላል፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ጳጳሳት ለዚህ ታላቅ የጌታ ቃል አለመታደላቸውን ሳስብ ከልብ አዝናለሁ፡፡ ከዚህ የተነሣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የተናገሩትን ሥራ ላይ ልናውል ይገባናል፤ እንዲህ ብለዋል፦

“ጌታችን እንደ ተናገረ መምሕራን የሚያስተምሩን ትምሕርት ከወንጌል ቃል ጋራ መስማማቱን እየመረመርን እንቀበላቸዋለን፡፡ ስለ ሥራቸው ግን በግድ ፍለጋቸውን ለመከተል አልታዘዝንምና የእነርሱን ፍለጋ ትተን የጌታችንን ፍለጋ እከተላለን፡፡ (ማቴ. ፳፫፥፫)”[1]

በርግጥም ጳጳሱ የተናገሩት ቃል የወንጌል ቃል ተቃራኒ ነውና አንቀበላቸውም፤ ድንግል ማርያም ባትኖር እግዚአብሔርም ክርስቶስም የሉም ብለን ጽርፈትን አንናገርም! እግዚአብሔር እንደ ወደደ የሚሠራ፣ ልዑልና ኃያል ጌታ ነውና እንዲህ እናምነዋለን!

ሊቀ ሥልጣናት ሀ/ማርያም ወርቅነህ፣ ስለ ክርስቲያናዊ ስብከት በተናገሩት መጽሐፋቸው፣

“ለስብከት ሳይዘጋጁ መቅረብ በአንድ በኩል ምእመኑን መናቅ ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ እርሱ ኃላፊነቱን ዘንግቶታል፤ ሥራውን አቅልሎታል ማለት ነው፡፡”[2]

ይላሉ፡፡ በርግጥ ጳጳሱ ጳጳስ ስለ ኾኑ ብቻ ተናገሩ፣ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጥንቅቅ ብለው ተዘጋጅተው ጠቅሰው አላስተማሩም፤ ይህ ደግሞ ምእመኑን ከመናቅ በዘለለ ከባድ ነውርም ነው!

ሊቀ ሥልጣናት በመቀጠልም እንዲህ ይላሉ፣

“የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን የምናድሰውና የምናንጸው በእጃችን ሳይኾን በልሳናችን ነው፤ ማለት በስብከታችን ነው፤ እንግዲያውስ ስብከት የማነጽ ጠባይ ያለው ስለሆነ አለመስበክ ደግሞ በተቃራኒው ማፍረስ መሆኑ ነው፡፡ … ከዚህም ጋር በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመራ የእግዚአብሔርም ጸጋ የተሰጠው ሰው እንዲሆን ያስፈልጋል፤ እንዲሁም በንቃት፤ በትጋት የሚያስተምር በነገሩም አምኖበት በግለት የሚያስተምር ካህን መሆን አለበት፡፡”[3]

እንኪያስ እንዲህ ከባድ የስህተት ትምህርት ያለበትን ትምህርት ያስተማሩበትን ጳጳስ፣ ንስሐ እንዲገቡ አልያም ደግሞ ለዚህ የስህተት ትምህርት ማስተካከያ እንዲሰጡና እንዲቆጠቡ በቅዱሱ በእግዚአብሔር ቃል እንማጸናለን! ወርቁ ግን ለምን ደበሰ?!

“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24)`

[1] ኅሩይ ወልደ ሥላሴ(ብላቴን ጌታ)፤ ጎህ ጽባሕ፤ 1919 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ አሳታሚ ጎሐ ጽባህ፤ ገጽ 146

[2] ሊቀ ሥልጣናት ሀ/ማርያም ወርቅነህ፤ የስብከት ዘዴ፤ 1980 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ትንሣኤ ማተሚያ ድርጅት፤ ገጽ 9

[3] ዝኒ ከማኹ ገጽ 16

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tena Adam Medeia and Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share