Awaday Post

Awaday Post Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Awaday Post, Media/News Company, .

የኢትዮጵያን ትክክለኛ የመሻገር መንገድ የመረጠ መሪ!አንድን ሀገር ካለበት ችግር ወደተሻለ ለመለወጥ ሁለት መንገዶችን መከተል ይቻላል። አንደኛው ለአገሪቷ ችግር መንስኤ የሆነውን ነባሩን ስርዓ...
07/09/2024

የኢትዮጵያን ትክክለኛ የመሻገር መንገድ የመረጠ መሪ!

አንድን ሀገር ካለበት ችግር ወደተሻለ ለመለወጥ ሁለት መንገዶችን መከተል ይቻላል። አንደኛው ለአገሪቷ ችግር መንስኤ የሆነውን ነባሩን ስርዓት በአብዮት በመንቀል በአዲስ መተካት ሲሆን ይህ ሂደት ያለውን ሁሉ በማፍረስ እንደ አዲስ ከዜሮ መጀመርን ያካትታል።
ሁለተኛው ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደሥልጣን እንደመጡ በኢትዮጵያ የታየው ለውጥ ሲሆን ይህ ለውጥ የሪፎርም ለውጥ ሲሆን በዚህ የለውጥ ሂደት ባለው መዋቅር ውስጥ ተጨማሪ ለውጦችን ማድረግን ነው የሚጠይቀው። ዐቢቹም ላለፉት 6 ዓመታት ለእድገትና ብልፅግናችን እንቅፋት የሆኑትን በአዲስ አሰራርና የተቋማዊ ሪፎርሞች እያሻሻለ አዳዲስ እሳቤዎችን ተግባራዊ በማድረግ ማደግ ነው የመረጠው። ይህ መንገድ ለፈፃሚው አካል ከባድ ነው። የተሻለችና የተረጋጋችን ሀገር ለመገንባት ግን ወሳኝ ነው።

#ጴጉሜ 2 የሪፎርም ቀን
#ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት

"እየመዘንን፣ እያነጠርን፣ እየመረመርን የሚበጀንን እንወስዳለን፤ የማይበጀንን እንጥላለን"     ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ አብዮት በጎውን ከክፉው አጃምሎ ጠርጎብናል። ተሻጋሪ ተቋሞች ለመገንባት አ...
07/09/2024

"እየመዘንን፣ እያነጠርን፣ እየመረመርን የሚበጀንን እንወስዳለን፤ የማይበጀንን እንጥላለን"
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አብዮት በጎውን ከክፉው አጃምሎ ጠርጎብናል። ተሻጋሪ ተቋሞች ለመገንባት አላስቻለንም። ለዚህ ነው ሪፎርምን የመረጥነው::እየመዘንን፣ እያነጠርን፣ እየመረመርን የሚበጀንን እንወስዳለን፤ የማይበጀንን እንጥላለን።

በዚህ ዕሳቤ ታላላቅ ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው። የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ ዘርፍ፣ የሕግ፣ የግብርና፣ የትምህርት፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሞችን እያሳካን በመጓዝ ላይ ነን።
#ጴጉሜ 2 የሪፎርም ቀን
#ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት

ዐቢቹ በሁሉም ዘርፎች ላይ ባደረገው ሪፎርም ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋልባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገራችን የለውጥ ብርሃን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአጠቃላይ ዜጎችን የባለቤትነት፣ ተሳታፊነትና...
07/09/2024

ዐቢቹ በሁሉም ዘርፎች ላይ ባደረገው ሪፎርም ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል

ባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገራችን የለውጥ ብርሃን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአጠቃላይ ዜጎችን የባለቤትነት፣ ተሳታፊነትና በሂደቱም ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ታሳቢ ያደረጉ በርካታ ሪፎርሞች ተተግብረዋል፡፡ ዐቢቹ በተለያዩ የሪፎርም ስራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብዙ ተግባራትን አካናውኗል::በተለያዩ ዘርፎች በተላይም በተቋማት:በግብርና, በፀጥታው ዘርፍ:በኢኮኖሚ, በከተማ ልማት, በኢንዱስትሪ, በቱሪዝም ብሎም በሁሉም ዘርፎች የተደረጉ ሪፎርሞች አመርቂ ውጤት ተመዝግበው ለሀገር እድገትና ብልፅግና የበኩላቸውን ከፍተኛ ሚና እየተጫዎቱ ይገኛሉ::
#ጷጉሜን 2


#ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት

በፀጥታ ተቋማት ላይ በተደረገ ሪፎርም በቴክኖሎጂና በሳይንሳዊ ጥበብ የተካነ ሰራዊት ተገንብቷል ዐቢቹ በፀጥታ ተቋማት ላይ ባደረገው ሪፎርም ኢትዮጵያ በማንም የማትበገር ሐያል ክንደ ብርቱ ዘመ...
07/09/2024

በፀጥታ ተቋማት ላይ በተደረገ ሪፎርም በቴክኖሎጂና በሳይንሳዊ ጥበብ የተካነ ሰራዊት ተገንብቷል

ዐቢቹ በፀጥታ ተቋማት ላይ ባደረገው ሪፎርም ኢትዮጵያ በማንም የማትበገር ሐያል ክንደ ብርቱ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የታጠቀ ሰራዊት ባለቤት ለመሆን በቅታለች ባለቤት ሆናለች::
ዐቢቹ ባለፉት 6 ዓመታት በተቋማት ግንባታ ላይ ታላላቅ ሥራዎችን ሰርቷል።የእነዚህ ሥር ነቀል ሪፎርም ተጠቃሚ ከሆኑት ተቋማት መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት የመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም የደህንነት እና የፀጥታ ተቋማት ናቸው።መከላከያ ሰራዊትን ከአንድ ፓርቲ አገልጋይነት እና ከአንድ አካባቢ የመጡ ሰዎች አድራጊ ፈጣሪነት በማላቀቅ ሀገራዊ ቁመና እንዲኖረው ከማስቻሉም፣በላይ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለህገመንግስቱ የሆነ ፤በሞራል፤በቴክኖሎጂ እና ሳይንሳዊ ጥበብ የተካነ ሰራዊት መገንባት ተችሏል።የደህንነት ተቋማትን ዓለማችን በደረሰችባቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች በማስታጠቅ፤ ሙያው የሚጠይቀውን ክህሎት በተላበሱ ወጣቶች በማደራጀት በአዲስ መልክ ተዋቅሯል።የዚህን ተቋማዊ ሪፎርም ውጤት በአጭር ጊዚያት ውስጥ ለማየት የበቃነው የተሰራው ሥራ ጥልቅ መሰረት ያለው በመሆኑ ነው። በመሆኑም አሁን ኢትዮጵያን ከየትም አቅጣጫ ለማጥቃት የሚሻ አካል ደጋግሞ ማሰብ ይኖርበታል።መከላከያ ሰራዊት የመጣው ሪፎርም
#ጷጉሜን 2

#ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት"

ወደ መተማ አካባቢ የሸሸው ፅንፈኛ ቡድን በጀግኖች እየተለበለበ ነው ጀግናው የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የኢትዮ-ሱዳን ድንበር በሆነችው ጋላባት (መተማ) ድንበርን በመቆጣጠር የሳምሪ አራ'ጅ ቡ...
07/09/2024

ወደ መተማ አካባቢ የሸሸው ፅንፈኛ ቡድን በጀግኖች እየተለበለበ ነው

ጀግናው የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የኢትዮ-ሱዳን ድንበር በሆነችው ጋላባት (መተማ) ድንበርን በመቆጣጠር የሳምሪ አራ'ጅ ቡድንን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት የከፈተውን ጥቃት በመቀልበስ ጽንፈኛውን ሃይል የደመሰሰው ሲሆን የጀግኖችን ክንድ መቋቋም የከበደው ጽንፈኛው ኃይል ከሕጋዊ የጸጥታ አባላት መለዮ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ልብስ ለብሶ ወደሱዳን ድንበር በመዝለቅ ትጥቁን በመፍታት ለሱዳን ሰራዊት እጁን ሰጥቷል።ሁለቱ ሃገራት በተፈራረሙት “ሽብርተኝነትን በጋራ የመዋጋት እና ወንጀለኞችን የመለዋወጥ ሥምምነት” መሰረት የሱዳን መንግስት ጽንፈኞችን አሳልፎ እንዲሰጥ ጥያቄ ቀርቦለት አዎንታዊ ምላሽ ሰጥቷል። ግብጽን ጨምሮ የኢትዮጵያ ጠላቶችን አጀንዳ የተሸከመውን ጽንፈኛ የመጥረግ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
#ድል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት

ዐቢቹ በዴሞክራሲ ተቋማት ላይ ባደረገው ሪፎርም ነፃና ገለልተኛ ሆነው ስራቸውን እያከናወኑ ነው በለውጥ ዓመታት ከተደረጉት የተቋማት ሪፎርም አንዱ የዴሞክራሲ ተቋማት ሪፎርም ነው፡፡ በቀደመው ...
07/09/2024

ዐቢቹ በዴሞክራሲ ተቋማት ላይ ባደረገው ሪፎርም ነፃና ገለልተኛ ሆነው ስራቸውን እያከናወኑ ነው

በለውጥ ዓመታት ከተደረጉት የተቋማት ሪፎርም አንዱ የዴሞክራሲ ተቋማት ሪፎርም ነው፡፡ በቀደመው ሥርዓት የዴሞክራሲ ተቋማት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች ከማስከበር ይልቅ የአንድን ቡድን ጠባብ ፍላጎት ለመጠበቅ የተደራጁ የይስሙላ ተቋማት ነበሩ፡፡ በመሆኑም የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ በመመለስና ዘላቂ ሰላም በማስፈን ያጋጠመን የፖለቲካ ስብራታችንን ለማረም እንደ
ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣
የሕዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም፣
ፍርድ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ሪፎርም ተደርጓል፡፡ ምንም እንኳን የነፃነትና ገለልተኝነት አረዳድና ልምምድ ገና ቢሆንም ተቋማቱ ከመንግስት ጫና ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆነው ሥራቸውን ማከናወን ጀምሯል፡፡
#ጷጉሜን 2

#ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት

በ21ኛ ክ/ዘመን ሀብት መፍጠሪያ ዘዴ ምን እንደሆነ ከመሠረቱ የተረዳ መሪጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ 21ኛ ክፍለዘመን ሀብት መፍጠሪ ዜዴ የግድ ነዳጅ ማግኘት፣ ወይንም በትላልቅ ማሺ...
13/07/2024

በ21ኛ ክ/ዘመን ሀብት መፍጠሪያ ዘዴ ምን እንደሆነ ከመሠረቱ የተረዳ መሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ 21ኛ ክፍለዘመን ሀብት መፍጠሪ ዜዴ የግድ ነዳጅ ማግኘት፣ ወይንም በትላልቅ ማሺነሪዎች ከርሰምድርን መቆፈር ሳይሆን ያለንን የተፈጥሮ ሀብት ላይ እሴት ጨምረን በዘመኑ ኑሮ ዘዬ ምክንያት የተጨናነቀን የዓለም ህዝብ ቀልብ የሚስብና የሚያሳርፍ የተፈጥሮ ውበቶችን የሚደነቁበትና በዚያም የውጭ ምንዛሪን አግኝተን ልማትና ዕድጋታችንን የምናፋጥንበት እንደ ጎርጎራ ያሉ በዓለም ላይ ልዩ የሆኑ ቦታዎችን በመገንባት መሆኑን ገብቶት በልዩ ትኩረት ኢንቨስት የተደረገበት ጎርጎራ እነሆ ከፍፃሜ ደርሷል። ጎርጎራን የማይጎበኝ ሰው ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። በዚያ ውስጥ የሚፈጠረው የሥራ ዕድል ደግሞ ሌላ ጸጋችን ነው።



#ጎርጎራ

ጎርጎራ የዐቢቹ ሀሳብ ውጤት፤ የመደመር ትውልድ አሻራ ዐቢቹ የፀናች፣ የበለጸገች፣ ለብዙዎች የሚታጓጓ፣ ለዜጎቿ ደግሞ የኩራት ምንጭ የሆነች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን ለማስረከብ በዚህ መልኩ አገር...
13/07/2024

ጎርጎራ የዐቢቹ ሀሳብ ውጤት፤ የመደመር ትውልድ አሻራ

ዐቢቹ የፀናች፣ የበለጸገች፣ ለብዙዎች የሚታጓጓ፣ ለዜጎቿ ደግሞ የኩራት ምንጭ የሆነች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን ለማስረከብ በዚህ መልኩ አገርን እየገነባ ነው። ጎርጎራ ዓለም አቀፍ የኢኮ-ቱሪዝም መንደር የዚህ ሂደት አንዱ ማሳያ ሲሆን አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ግንባታ ሥራ ተጠናቅቆ እነሆ ለምርቃት በቅቷል።



#ጎርጎራ

ታሪኩን ጠብቆ ዘመኑን ዋጅቶ ለትውልድ የሚሻገር የማይደበዝዝ አሻራ - ጎርጎራ  ለፍፃሜ ደረሰ!  በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጪነት የተገነባው ጎርጎራ እንዲህ ነው ተብሎ አይገ...
13/07/2024

ታሪኩን ጠብቆ ዘመኑን ዋጅቶ ለትውልድ የሚሻገር የማይደበዝዝ አሻራ - ጎርጎራ ለፍፃሜ ደረሰ!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጪነት የተገነባው ጎርጎራ እንዲህ ነው ተብሎ አይገለፅም! የተባበረ ሃሳብ: ያለስስት የተከፈለ ዋጋ!
ጎርጎራ ታሪካዊ ይዘቱን አጉልቶ : ቅርስነቱን አልምቶ : ሁለንተናዊ እሴቱን ከፍ አደርጎ : ውበትን በእርጋታ አልብሶ በልዩ ጥበብ ታነፀ! ጎርጎራን ለመገንባት ያሰቡ አእምሮዎች: የነደፉ እጣቶች: የገነቡ ጉልበቶች: ውበትን ያለበሱ እሳቤዎች ምስጋናና ክብራቸው በትውልድ ሁሉ ውስጥ ያንፀባርቃል:: ጎርጎራ ብዙ ትውልዶችን የሚሻገር: የዚህ ዘመን ስጦታ ነው! በዓይነታቸወው ልዩ ሆነው ደረጃቸውን ጠብቀው የተሰሩ ከአንድ መቶ በላይ ክፍሎች ፤ በሀገራች ለመጀመሪያ የሆነው በውሀ አካል ላይ በጀልባ ቅርፅ የተሰራ ሬስቶራንት ፤ ሁለት ተጨማሪ ሪስቶራንቶች ፤ ሁለት ዘመናዊ አደራሾች ፤ የመዋኛ ገንዳ፤ እጅግ ያማረ ባር ፤ የስፖርት ማዘውተሪያ እና የሄሊኮፍተር ማረፊያ ጨምሮ ይህ ቀረሽ የማይባል የተሟላለት ልዩ መዝናኛ ነው።
ጎርጎራ እንዲህ ነው ተብሎ አይገለፅም! የተባበረ ሃሳብ: ያለስስት የተከፈለ ዋጋ!
ሰማኒያ ሶስት ሜትር ርዝመት ተንሳፋፊ ወደብ: በአንድ ጊዜ ሰላሳ ሁለት ጀልባዎችን ማስተናገድ የሚችል! ዘመን ያፈራውን : አለም የደረሰበትን ቴክኖሎጅ ሁሉ ያቀፈ! በማሪን ዘርፍ አዲስ ከፍታን የፈጠረ! ጎርጎራ!

የኢትዮጵያ መከላከያ ከሀገራችን አልፎ ለጎረቤት አገራት ጭምር አለኝታ የሆነ ጀግና ሰራዊት ነውአይበገሬው መከላከያ ሠራዊታችን፤ እንደ ትናንቱ ዛሬም መንግሥትና ሕዝብ የሰጡትን ተልዕኮ፤ በከፍተ...
13/07/2024

የኢትዮጵያ መከላከያ ከሀገራችን አልፎ ለጎረቤት አገራት ጭምር አለኝታ የሆነ ጀግና ሰራዊት ነው

አይበገሬው መከላከያ ሠራዊታችን፤ እንደ ትናንቱ ዛሬም መንግሥትና ሕዝብ የሰጡትን ተልዕኮ፤ በከፍተኛ የማድረግ አቅም (Doing Capacity)፣ ብቃት፣ ወታደራዊ ጥበብና ክህሎት፣ ዲሲፕሊንና ጨዋነት እንዲሁም በታላቅ ስነ-ልቦናዊና ሞራላዊ ዝግጁነት እየተወጣ ነው::ይህ ዓለም የመሰከረለት የጀግንነት ዳርቻ የሆነ ክንደ ብርቱ ሠራዊት፤ የሀገርና የሕዝብ መከታ፣ ከለላና የማይደፈር አጥር ሆኖ፤ ነገም ሆነ ከነገ በስቲያ ኢትዮጵያን እያፀና ይቀጥላል። አሁን ደግሞ ዘመኑ ባመጣው የወታደራዊና የኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ የበለጠ ጠንክሮ የኢትዮጵን ዳር ድንበርና የህዝብ ሉዓላዊነት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ አገራት አለኝታ ሆነ ሰራዊት ነው።
መከታችን #ሰላም 3ብልፅግና #ኢትዮጵያ #አፍሪካ

አረንጓዴ ዐሻራ ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ ነው!ኢትዮጵያ የበለፀገ ታሪክ፣ ባህልና ብዝሃነት ያላቸው ህዝቦች በጋራ የሚኖሩባት ሀገር ናት። የሀገራችን  ግብርና   በአብዛኛውን  የዝናብ ውሃ ሃብ...
13/07/2024

አረንጓዴ ዐሻራ ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ ነው!
ኢትዮጵያ የበለፀገ ታሪክ፣ ባህልና ብዝሃነት ያላቸው ህዝቦች በጋራ የሚኖሩባት ሀገር ናት። የሀገራችን ግብርና በአብዛኛውን የዝናብ ውሃ ሃብት እና የተፈጥሮ ስነ-ምህዳር ላይ ከፍተኛ ጥገኛ በመሆኑ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ እጅግ ተጋላጭ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያን የልማት ግቦች ፈተና ላይ የሚጥል እና የሚሊዮን ህዝብ መተዳደሪያ የሆነውን ግብርና አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ኢትዮጵያ ለዚህ ዘላቂ መፍትሄ በመቀየስ አረንጓዴ አሻራን ባህሉ ያደረገ ትውልድ እየገነባች ትገኛለች። እድገቷንና ብልፅግናዋን ለመጪዎቹ ትውልዶች ማስቀጠል የሚችል ለአየር ንብረት ለውጥ ተመራጭ የሆነ አረንጓዴ ኢኮኖሚን የመገንባት ራዕይ ሰንቃ ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ስራ እየሰራች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ አረንጓዴ ትለብሳለች!
ከተማችን አረንጓዴ ትለብሳለች!
ኢትዮጵያ ለምለም ምድር ትሆናለች!
መጪው ትውልድ ልምላሜንና ብልፅግናን ይወርሳል!!

የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የፅዳት ባህልን ለማስረፅ ወሳኝ ነው  በዐቢቹ የተጀመረው ፅዱ ኢትዮጵያ ተሳትፎ ጥሪ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰብ መርሃ ግብር የህብረተሰቡ ተሳትፎ እጅጉን ከፍ ብሎ ታይቶ...
13/07/2024

የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የፅዳት ባህልን ለማስረፅ ወሳኝ ነው

በዐቢቹ የተጀመረው ፅዱ ኢትዮጵያ ተሳትፎ ጥሪ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰብ መርሃ ግብር የህብረተሰቡ ተሳትፎ እጅጉን ከፍ ብሎ ታይቶ ነበር። ሊሰበሰብ ከታቀደው 4እጥፍ በአንዲት ጀምበር ብቻ ተሳትፏል። አሁንም ድረስ በርካታ ህዝቦችና የተለያዩ ተቋማት የመፀዳጃ ቤት በመስራትና መዋጮ በማድረግ ድጋፋቸውን ቀጥለዋል። ይህ መልዕክት ተሰራጭቶ የፅዱ ኢትዮጵያ ገቢ ማሰባሰብ ተደርጎ በአጭር ቀናት ውስጥ በተግባር ተገልጦ በርካታ መፀዳጃ ቤቶች በተለያዩ ስፍራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ተሰርቶ የተጠናቀቁም እየተሰሩ ያሉም በተወሰኑ ርቀቶች ላይ በተለይ በዋና ዋና መንገዶች ላይ ይታያሉ። ከሃሳቡ በላይ ተግባሩም አስገርሞን ይህ ንቅናቄ ዋናው አለማ መፀዳጃ ቤት የማስፋት ሳይሆን የፅዳት ባህል ማሳደግ ነው።ዐቢቹ ለሕዝብ የሚጠቅም ነገር ይሰራል ስንል በምክንያት ነው::
#ፅዱ ኢትዮጵያ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awaday Post posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share