Sidama National Regional State Water Mine And Energy Bureau

  • Home
  • Sidama National Regional State Water Mine And Energy Bureau

Sidama National Regional State Water Mine And Energy Bureau ጥራት ያለ ዉሃ ለህብረተሰቡ እናደርሳለን!!

‎Sidaamu dagoomu qoqqowi mootimma sivil seriviisetenna manu jiro latishshi biiro irkotenna harunsote gaamo 2017 M.D  mix...
08/08/2025

‎Sidaamu dagoomu qoqqowi mootimma sivil seriviisetenna manu jiro latishshi biiro irkotenna harunsote gaamo 2017 M.D mixotenna soorrote loosa keentu.

‎ woxawaajje 2-11-2017 M.D S-W-SHi-I-biiro
‎ Hawaasa
‎Sidaamu dagoomu qoqqowi moitimma wayi shiilotenna inrjete biiro uyiitanni no owaante daga mereerissitinota ikkasenna losaasinete injitinota ikkasenni sae losaasinete biifino injo noota buuxinota coyiidhe

‎Xaphooma losaasinete lowo injo nootanna doyiite lau yannara loosu lowota loosamanni noota buuxinoha ikkanna qoqqowu deerrinni woyaawinoha loosu qoxeessa la'a dandiitinota buuxisino.

‎Losaasinete loosoho ikkanno uduune baala wonsha, ilinno amuwira daaimu hoshsho darga qineessa hodhishshu injo dandiinni deerinni tiranni hee'noonita xawisino.

Bare massaginohu biirote layiinki sooreessinna fayiinansetenna gashootu handaari sooreessi kalaa Tsegaye Gabiibibu coyiiraani biiro yanna yannatenni assitanni noonsa irkonna harunso daafo lowota galate

Xaano ikkiro losaasinenkera loosoho hasiissano irko assatenni badhe higanoikkita xawise loosaasinenke halante loosasetenni abitino soorora lowo galati nooe yiinno.

‎ከክልሉ ፐብሊክ ሰርቭስና የስው ሀብት ልማት ቢሮ ከመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን የ2017 የዕቅድ ና የለውጥ ስራዎች አፈፃፃም ገመገሙ ።

‎ኔሐሴ 2/2017 ዓ.ም ውሃ/ማ/ኢ/ቢሮ
‎ ሀዋሳ
‎*********************
‎ቡድኑ በዛሬው ዕለት ባደረገው ግምገማ አመርቂ ስራ እንደተሰራ ባደረጉት ምልከታ የተገነዘቡ መሆኑን ተናግረዋል ።

‎ተገልጋዮችን በአክብሮትና በፍጥነት በማስተናገድ አመርቂ ስራ እንደተሰራ ተገልጋዮችን ዋቢ አድርገው ተናግሯል ።

‎ለሠራተኞች ምቹና ደረጃውን የጠበቀ አከባቢ በመፍጠር እና ለወላድ እናቶች የህፃናት ማቆያ በማዘጋጀት ትልቅ ስራ እንደተሰራ ቡድኑ አንስቶ ከክልሉ ውስጥ የተሻለ እንደሆነ ተናግሯል ።

‎ለሠራተኞች የሚያስፈልጋቸውን የቢሮ ቁሳቁስ በሚያስፈልግ ደረጃ ያሟላ ና ለሠራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት በመስጠት በኩል እየተሰራ ያለው ስራ በቶሎ አልቆ ሠራተኞች ከትራንስፖርት ዕንግልት ማስቀረት ና ሰራተኞቹ ዘግይቶ የመግባት ሕዴትን እንደምታስቀሩ እተማመናለሁ ብለዋል።

‎ቢሮው በየጊዜዉ ለሚያደርግላቸው ድጋፍና ክትትል አመስግነው አሁንም ለሰራተኞቻቸው ድጋፍ ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ ተናግሯል ።
‎Telegram_channal
‎Sidama National Regional State Water Mine And Energy Bureau
https://www.youtube.com/
‎ ሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
‎ channel Sidamu qoqqowi waay shiilotenna enerjete biiro.
‎ .facebook.com

‎Subscribe ያድርጉ መረጃዎችን በትኩሱ ያግኙ



ከነዳጅ ኃይል ወደ ሶላር ኃይል ቴክኖሎጂ የተቀየሩ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ርክክብ ተደረገ፡፡@@@@@@@@@@@@@@@@@ሐምሌ 28/2017 ዓ.ምፕሮጀክቶቹ በመካነ ኢየሱስ ቤተክርስትያን የልማት...
05/08/2025

ከነዳጅ ኃይል ወደ ሶላር ኃይል ቴክኖሎጂ የተቀየሩ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ርክክብ ተደረገ፡፡
@@@@@@@@@@@@@@@@@
ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም
ፕሮጀክቶቹ በመካነ ኢየሱስ ቤተክርስትያን የልማትና ማሕበራዊ አገልግሎት ድርጅት ከኖርዌይ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በሲዳማ ክልል ስር በሚገኙ በቡራ ( የሀማሾ ቄቤና) ፥ በበንሳ ( የጋማጮ )፣ በዳሌ ( የዱባ) ቀበሌዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

የመካነ ኢየሱሱስ ቤተክርስቲያን የልማት፣ ማሕበራዊ አገልግሎት ድርጅት የማዕከላዊ ደቡብ ሲኖዶስ አስተባባሪ አቶ ዳዊት ዮኮና ፡- ቤተክርስቲያኗ ከወንጌል አገልግሎት ጎን ለጎን በመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ሳቴሽንና ሀይጅን ሥራዎች፣ በጤና፣ በትምህርትና ሠላም ግንባታ ላይ ለሁሉም ሕብረተሰብ አገልግሎት እየሰጠች እንደምትገኝ ገልፀው፡- በዛሬው ዕለት ርክክብ የተፈፀመባቸው ፕሮጀክቶች ከዚህ ቀደም በተለያዩ ድርጅቶችና በመንግሥት በጀት ተገንብተው በነዳጅ ኃይል አገልግሎት ይሰጡ የነበሩትን ወደ ፀሐይ ኃይል የሚቀይር መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዚህም ቴክኖሎጂው የተቋማቱ የነዳጅ ወጪንና የአከባቢ ብክለትን በማስቀረት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልፀው:- ተጠቃሚው ሕብረተሰብ ለተቋማቱ ጥበቃና እንክብካቤ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አደራ ብለዋል።

አግሪ ሰን ኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ እና ትሬዲንግ ኃ/የ/የ/ማ ባለቤትና ስ/አስኪያጅ አቶ ይማም ከበደ በበኩላቸው ፦ የሶላር ቴክኖሎጂውን አሰራርና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን አስረድተው፥ ተቋማቱ በማንኛውም ጊዜ ብልሽት ቢገጥማቸው በራሳቸው ወጪ በመጠገን ማሕበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል።
የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና የአከባቢው የሥራ ኃላፊዎች የዋሽኮ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የተቋማቱን ዘላቂነት ለማረጋገጥ ተግተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

‎የአዋዳ - ቦሪቻ ብዘሃ መንደር የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የ 2017 ዓ.ም የሥራ ዕቅድ ክንውንና የ2018 ዓ.ም የሥራ  ዕቅድ  ግምገማ አካሄደ ።‎‎     ሀምሌ 24/2017 ዓ.ም ...
31/07/2025

‎የአዋዳ - ቦሪቻ ብዘሃ መንደር የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የ 2017 ዓ.ም የሥራ ዕቅድ ክንውንና የ2018 ዓ.ም የሥራ ዕቅድ ግምገማ አካሄደ ።

‎ ሀምሌ 24/2017 ዓ.ም ውሃ/ ማ/ኢ/ቢሮ
‎ ሀዋሳ
‎በሲዳማ ብሔራዊ ክልል የአዋዳ -ቦሪቻ ብዘሃ መንደር የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት በራስ አቅም በቦርድ የምተዳደር ስሆን በዛሬው ዕለት የ2017 ዓ.ም የስራ ሪፖርትና 2018 ዓ.ም የስራ ዕቅድ ባለ ድርሻ አካላት ባሉበት ተገምግሟል ።

‎በዕለቱ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአዋዳ-ቦርቻ ብዘሃ መንደር የቦርድ ሰብሳቢና የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የንፁህ የመጠጥ ውሃ ጥናትና ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ኢንጅነር ሀይለኢየሱስ ኤልያስ የአዋዳ ብዘሃ መንደር በየጊዜው ትልቅ መሻሻልና ለህብረተሰቡ የንፁህ መጠጥ ውሃን በማዳረው ረገድ ጉልህ ምና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረው በክልሉ ውስጥም ትልቅ አቅም መፍጠር ችሏል ብለዋል።

‎የአዋዳ - ቦርቻ የብዘሃ መንደር ከ 631 ሺ ሰው በላይ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ ተናግሮ በቅ ውሃ ለህብረተሰቡ ለማዳረስ የባህር ዛፍ ተክል በአከባቢው በስፋት በመኖሩ የውሃ እጥረት እየገጠመው እንደሆነና የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ፍላጎት ማሟላት እንዳልተቻለ አንስተው በቀጣይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን መሰል ችግሮችን በመፍታት የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ፍላጎት እንደሚያሟሉ ገልፀዋል

‎የክልሉ መንግስት ባደረገው ሰፊ ትግል ከዚህ በፍት የምታዩት የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በአንጻሩ መቀረፍ እንደተቻለ ተናግረው አሁንም ህብረተሰባችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ሙሉ በሙሉ እስከሚያገኝ በከፍተኛ ትኩረት እንደምሰሩ ተናግሯል ።

‎የሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታና ዲዛይን ዘርፍ ኃላፊና የአዋዳ ቦርቻ ብዘሃ መንደር ምክትል የቦርድ ሰብሳብ የሆኑት ኢንጂነር ዳዊት በቀለ በበኩላቸው የአዋዳ-ቦርቻ የብዘሃ መንደር ለዛሬው ስከት መነሻ የቅንጅት ስራ እንደሆነ ተናግረው ለዚህም ከክልል እስከ ወረዳ ላደረጉት አመርቂ ተነሳሽነት ምስጋና ካቀረቡ በኃላ ክልሉ በውሃ በመስኖ ዝርጋታ በመንገድ በኢነርጂ በሶላር በሁሉም ረገድ ጉልህ ምና እንደተጫወተ አንስተዋል ።

‎የአዋዳ-ቦርቻ የብዘሃ መንደር የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ስራአስኪያጅ አቶ ማኒቻ ይሳቅ ባቀረቡት ሪፖርት 388 የውሃ ተቋማትን ጥገና እንደተደረገና 36 በቀጣይ እቅዳቸው ውስጥ እንደተካተቱ ተናገረው

‎ተቋማቶቹ ብልሽት በገጠማቸው ጊዜ በፍጥነት በመስራትና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማካተት በቁጥር የማይተመን የመንግሥት ወጭ መቀነስ እንደተቻለ አንስተው

‎በ2017 ዓ.ም 21 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ ይዘው ወደ 23 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር መሰብሰብ እንደተቻለና ከእቅዳቸው በላይ መሆኑ የሁሉም ቅንጅት ስራ እንደሆነ አንስተው

‎የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ያለመሰልቸት ለሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ምስጋና ከቅርበው

‎በሀገር ደረጃ ባለው ምርጥ ተሞክሮ ከኦሮሚያና አማራ ክልልሎች ለልምድ ልዉዉጥ መተው ለድርጅቱ ከፍተኛ አድናቆት እንደቸሩ ተናገረው

‎የተሽከርካሪ እጥረት የነዳጅ ዋጋ መጨመር ጊዜው ክረምት መሆኑና የኃይል መቆራረጥ ለስራቸው መቀላጠፍ ችግር እንደሆነ ተናግሯል ።

‎በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ተሠቶ ስብሰባው ተጠናቋል ።

‎Telegram_channal
‎Sidama National Regional State Water Mine And Energy Bureau
https://www.youtube.com/
‎ ሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
‎ channel Sidamu qoqqowi waay shiilotenna enerjete biiro.
‎ .facebook.com

‎Subscribe ያድርጉ መረጃዎችን በትኩሱ ያግኙ




የማዕድን ዘርፉን የሚያበረታታና ስኬታማነቱን የሚያሳልጥ ድጋፍ!!!
28/07/2025

የማዕድን ዘርፉን የሚያበረታታና ስኬታማነቱን የሚያሳልጥ ድጋፍ!!!

አለታ ወንዶ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የክልሉ ውሃ ቢሮ ሀላፊ፣የዞኑ አስተዳዳሪ፣የከተማው ከንቲባ፣በየደረጃው ያሉ የሚመለከተው አካላት የሥራ ተቋራጭ እና አማካሪ ድርጅቱ ባለበት አፈጻጸምን ...
19/07/2025

አለታ ወንዶ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የክልሉ ውሃ ቢሮ ሀላፊ፣የዞኑ አስተዳዳሪ፣የከተማው ከንቲባ፣በየደረጃው ያሉ የሚመለከተው አካላት የሥራ ተቋራጭ እና አማካሪ ድርጅቱ ባለበት አፈጻጸምን ተገምግሟል።

አፈፃፀሙን በተመለከተ ፕሮጀክቱ በጥሩ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይነት ጠንካራ ክትትል እየተደረገ በውል ስምምነቱ መሠረት ተሠርቶ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ እንደሚደረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል ።

ስራው ያለበት ሁኔታ በጋራ ምልከታ የተደረገ ስሆን ስራውም በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ።

‎Telegram_channal
‎Sidama National Regional State Water Mine And Energy Bureau
https://www.youtube.com/
‎ ሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
‎ channel Sidamu qoqqowi waay shiilotenna enerjete biiro.
‎ .facebook.com

‎Subscribe ያድርጉ መረጃዎችን በትኩሱ ያግኙ




የሲዳማ ክልል ብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም 2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ሐምሌ 12/2...
19/07/2025

የሲዳማ ክልል ብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም 2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም
የቢሮው ዋና ኃላፊ ኢ/ር ከበደ ጋኖሌን ጨምሮ የቢሮው ማኔጅመንትና የዋን ዋሽ ዩኒት ሠራተኞች በተገኙበት በተካሄደው ውይይት ፦ የዋን ዋሽ ፕሮግራም የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር ከበደ ጋኖሌ የፕሮግራሙን የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ፦ የትኛውም ተግባራት ሲከናወኑ የክልሉን ህብረተሰብ ጥቅም ማስቀደም እንደሚገባ ጠቁመው፦ የፕሮግራሙ 2017 ዕቅድ አፈፃፀም መልካም እንደሆነና በቀጣይም በ2018 ዓ.ም ለታቀዱት ተግባራት ተጨማሪ ማችንግ ፈንድ በመመደብ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተጠናቀው የክልሉን ሕብረተሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲቻል ፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በክልሉ ዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ One WaSH National Program ከፍተኛ የፕሮጀክት ክትትልና ግምገማ ስፔሻሊስት አቶ ማጃጃ ማራሳ የፕሮግራሙን አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት :- በፕሮግራሙ በ2017 ዓ.ም ለማከናወን የታቀዱ ተግባራት አፈፃፀማቸው ከ100% በላይ መሆኑ አመላክተዋል።
የፕሮግራሙ 2018 ዕቅድም ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ፥ ማብራሪያና ምላሽ በሚያስፈልጋቸው ሐሳቦች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
( በእስራኤል ንጉሴ)

የሲዳማ ክልል ውሃ ፥ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የ2017 ዕቅድ  አፈፃፀም ከክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ በመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን ተገመገመ።*********************************...
18/07/2025

የሲዳማ ክልል ውሃ ፥ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የ2017 ዕቅድ አፈፃፀም ከክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ በመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን ተገመገመ።
***************************************
ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም
ዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
ሀዋሳ
ቢሮው በ2017 ከውሃ ፣ ማዕድንና ኢነርጂ እንዲሁም ከመስኖ ልማት አኳያ ለማከናወን ያቀዳቸው ተግባራትና አፈፃፀም ተገምግሟል።

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ የቢሮው ዕቅድ አፈፃፀም መሬት ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ለማገናዘብ ችለዋል።

ከዚህም አኳያ የቢሮው ያስመዘገባቸው መልካም አፈፃፀሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የተስተዋሉ ክፍቶች በቀጣይ እንዲስተካከሉ ግብረመልስ ተሰጥቷል።

ለተመዘገበው ጥሩ አፈፃፀም የቢሮው ማኔጅመንትና ባለሙያዎች በተቀናጀ መልኩ በመስራታቸውና እስከታችኛው መዋቅር ተናበው ተግባራትን በየጊዜው እየገመገሙ ማከናወናቸው መሆኑ ተመላክቷል።

የቢሮው ማኔጅመንትም የድጋፍና ክትትል ቡድኑ የቢሮውን እቅድ አፈፃፀም በዝርዝር ተመልክተው ለሰጡት አበረታች ግብረመልስ ምስጋና አቅርበዋል።

‎ የሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በአለታ ጩኮ ከተማ ለሚገነባው የንፁህ የመጠጥ ዉሃ ግንባታ ለማከናወን ከክልሉ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖረሽን ጋር ውል ተፈራረመ ።‎‎   ሐምሌ ...
17/07/2025

‎ የሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በአለታ ጩኮ ከተማ ለሚገነባው የንፁህ የመጠጥ ዉሃ ግንባታ ለማከናወን ከክልሉ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖረሽን ጋር ውል ተፈራረመ ።

‎ ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም ውሃ /ማ/ኢ/ቢሮ
‎ ሀዋሳ
‎ግንባታው ከ15 ወር በኃላ የሚጠናቀቅ ስሆን ለግንባታም 571 ሚሊዮን ብር ወጭ እንደሚሆን ተገልጿል ።

‎ለ10 ዓመት በዘላቂነት የሚያገለግው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታው ስጠናቀቅ 82 ሺ የለታ ጩኮ ከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግና ከዚህ በፊት የሚታየውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር እንደሚያቀርፊ የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ብሮ ኃላፊው ኢንጅነር ከበደ ጋኖለ ተናግሯል ።

‎ግንባታው የ66 KM የቧንቧ ስራ ዝርጋታ የውሃ አገልግሎት መስሪያ ቤት ያካተተ እንደሆነ ተናግሮ ግንባታው በተባለለት ጊዜ እንድጠናቀቅ በከፍተኛ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።

‎የክልሉ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖረሽን ኃላፊው አቶ ኤልያስ ቲሮ በበኩላቸው ግንባታውን በተቀመጠለት ጊዜ ቀድሞው እንደሚያጠናቅቁ ተናግረው ለከተማው ነዋሪዎችም በአጭር ጊዜ ጨርሰን እናስረክባለን ብለዋል።

‎የአለታ ጩኮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሲሳይ ፈተራ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ከዚህ በፊት ያቀረብነውን የንፁ የመጠጥ ውሃ ችግር ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስለመለሰልን እናመሠግናለን ስራው ስጠናቀቅ ከዚህ በፊት ይታይ የነበረው የንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግር እንደሚያቀርፍ ተናግረው የክልሉ መንግስትን ማመስገን እፈልጋለሁ

‎ለአለታ ጩኮ ከተማ ነዋሪዎችም እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል ።

‎Telegram_channal
‎Sidama National Regional State Water Mine And Energy Bureau
https://www.youtube.com/
‎ ሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
‎ channel Sidamu qoqqowi waay shiilotenna enerjete biiro.
‎ .facebook.com

‎Subscribe ያድርጉ መረጃዎችን በትኩሱ ያግኙ




በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አሮሬሣ ወረዳ የመጆ ከተማ የንፅህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ስራው ሙሉ በመሉ  ተጠናቀቀ። በሲዳማ ክልል ዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ  ቢሮ ለበርካታ አመታት የህዝብ ጥያቄ የነበሩ...
11/07/2025

በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አሮሬሣ ወረዳ የመጆ ከተማ የንፅህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ስራው ሙሉ በመሉ ተጠናቀቀ።

በሲዳማ ክልል ዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ለበርካታ አመታት የህዝብ ጥያቄ የነበሩ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ እንዲፋጠንና ለታለመለት አላማ ላይ እንድውል በማድረግ ረገድ ባሳለፈነው አምስት አመት ውስጥ ቢሮ ከክልሉ መንግስት ጋር በማቀናጀት የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እየቀጠለ ይገኛል።

ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ የአሮሬሳ ወረዳ መጆ ከተማ ንፁህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት 18 ሽህ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ከ84 ሚልዮን ብር በላይ ወጭ የወጣበት ይህ ፕሮጀክት ለረጅም አመታት የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየው የዚህ ፕሮጀክት ስራው በአሁኑ ስዓት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቅው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየተሠጠ ይገኛል።

04/07/2025

የሲዳማ ክልል ውሃ ፥ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ለጪሮኔ ከተማና አከባቢው ነዋሪዎች እንኳን ደስስስስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
@@@@@@@@@@@@@@@@@@@
ሰኔ 27/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
በዋን ዋሽ ፕሮግራም እየተከናወነ የሚገኘው የጭሮኔ ከተማ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ በስኬት ተጠናቋል።
19 ሊትር በሰከንድ የሚያመነጨው ይህ ጉድጓድ 180 ሜ ጥልቀት ያለው ሲሆን ከ8000 በላይ የጪሮኔና ዙሪያዋ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ።
የዋን ዋሽ ፕሮግራም በሲዳማ ክልል በ11 ወረዳዎች በንፁህ መጠጥ ውሃ ፣ ሳኒቴሽንና ሀይጅን ላይ የሚሰራና በ100,000 የሚቆጠሩ የክልሉን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ፕሮጀክት ነው።

የገጠር የመጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር  ላይ የተዘጋጀ ስልጠና ተሰጠ ።      የሲዳማ ክልል  ው/ማ/ኢ/ቢሮ  ሰኔ 24/2017 ዓ.ም         ሀዋሳ በሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ...
01/07/2025

የገጠር የመጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር ላይ የተዘጋጀ ስልጠና ተሰጠ ።

የሲዳማ ክልል ው/ማ/ኢ/ቢሮ ሰኔ 24/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
በሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የገጠር የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ላይ የተዘጋጀውን ስልጠና በአለታ ወንዶ ከተማ ለወረዳ ውሃ ጽፈት ቤት ኃላፊዎች ለቀበሌ አስተዳዳርዎች እና ለማህበራት እየተሰጠ ስሆን

በዕለቱ የስልጠናውን መርሃ ግብር በንግግር የከፈቱት የሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የመጠጥ ውሃ ጥገና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ኡራጎ ሀሰን በበኩላቸው በመንግስት ሆነ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የተገነባውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማትን በአባትነትና በሀላፊነት መንፈስ እንድጠቀሙ ተናግረው

በአግባቡ የተያዘ የውሃ ተቋም ለህብረተሰቡ ሰፊ አገልግሎት እንደሚሰጥ አውቀው በሀላፊነት እንድትገለገሉ ስል መልክት አስተላልፈዋል

በተጨማሪም አቶ ኡራጎ መንግስት የንፁህ የመጠጥ ውሃን ለህብረተሰቡ ለማዳረስ ሳይታክት እየሰራ እንደሆነ ተናግረው ገንብቶ ብቻ መተው ሳይሆን በአጠቃቀምና በአያያዝ ዙሪያ እንደዚህ አይነት ስልጠና እንደሚሰጥና

መንግስት የንፁህ የመጠጥ ውሃ ለማህበረሰቡ እየገነባ እያደረሰ ስሆን አሁንም አድርሶ አልጨረሰም በሁሉም ክልሉ አካባቢዎች የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ እየተጋ በለላ ጎኑ ለጥገና ወጭ እያወጣ እንደሆነ ተናገረው አሁን ማህበራት ከተደራጁ በኃላ የተበላሸውን የውሃ ተቋምን የመገንባት አቅም እንድያዳብሩ ተናግሯል ።

በ UNICEF የተዘጋጀውን ስልጠና የሰጡት አቶ ሰይፍ በለጠ ስሆኑ የውሃ ተቋማት መመሰረት ያስፈለገበትን ዓላማ ስገልፁ

ንፀህ በቂ እና ዘላቂ የሆነ የመጠጥ ውሃና የፍሳሽ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ ለማድረግ

ድርጅቶች እና ማህበራት ከአገልግሎት በሚገኘው ገቢ እራሳቸውን ችለው እንድሰሩ ማድረግ እና የውሃ መገኛ ቦታዎችን ለመጠበቅ ለመንከባከብ እንደሆነም ተናግረው በዋነኝነት ጤናማ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሆነም ተናግሯል ።

የስልጠና ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው በጣም አስፈላጊና ጊዜውን የጠበቀ እንደሆነና በወሰዱት ስልጠና መሠረት ወደ ስራ እንደሚገቡ ተናግሯል ።

Telegram_channal
Sidama National Regional State Water Mine And Energy Bureau
https://www.youtube.com/
ሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
channel Sidamu qoqqowi waay shiilotenna enerjete biiro.
.facebook.com

Subscribe ያድርጉ መረጃዎችን በትኩሱ ያግኙ

የባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች በጥራት፣በጊዜና በተያዘላቸው በጀት  እንዲጠናቀቁ ያደርጋል፡፡     ሰኔ 21/2017 ዓ/ምበመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አዘጋ...
29/06/2025

የባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች በጥራት፣በጊዜና በተያዘላቸው በጀት እንዲጠናቀቁ ያደርጋል፡፡

ሰኔ 21/2017 ዓ/ም
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አዘጋጅነት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ባሉባቸው ክልሎችና ዞኖች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተደረገ ውይይት የባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች በጥራት፣በጊዜና በተያዘላቸው በጀት እንዲጠናቀቁ እንደሚያደርግ ተገልፀዋል፡፡

የሚኒስቴር መ/ቤቱና የክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሚኒስቴር መ/ቤቱ መካከለኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያም ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር በሰጡት ማብራሪያና የስራ አቅጣጫ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ተልዕኮ ግልፅ ነው ፤የመስኖ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ማጠናቀቅ፣ ማስተዳደርና ህብረተሰቡ ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው፤ወደ ግንባታ የሚገቡ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች አዋጭነታቸው በደንብ መረጋገጥ አለበት አለበለዚያ የሃብት ብክነት ነው የሚሆነው ብለዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት የተጀመሩት መስኖ ፕሮጀክቶች ከክልሎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተን በመስራት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን፤ህብረተሰቡም ከመስኖ ልማቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ክቡር ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

ክቡር አቶ ተስፋዬ ይገዙ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ያለውን ችግር በመለየት በፌዴራልና በክልል ያለው አመራር መፍትሄ እየሰጠ መሄድ አለበት ፤ በዚህም ሂደት እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ተቀናጅቶ በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የተዘጋጁት የአሰራር ስታንዳርዶች በፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን እንዲሁም ግንባታ ላይ ያለውን ችግር ይፈታል የሚል እምነት አለን ብለዋል።

በአጠቃላይ ሚኒስቴር መ/ቤቱና ክልሎች በጋር ተገናኝተን ስራዎቻችንን መገምገም ቅንጅታዊ አሰራሩን ይበልጥ ያጠናክራል፡፡

ዘገባው :- የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ነው።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama National Regional State Water Mine And Energy Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share