Balageru TV

Balageru TV Balageru television, promotes Ethiopian history, culture, tradition, lifestyle, investment, tourism..
(1)

Our Channel Frequency
NSS12 57 Degree East HD, Freq - 11105, Pol - Horizontal, S/R - 45000
or
DSTV Channel - 484

ኢትዮጵያና አሜሪካ ሕገ ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ለመቆጣጠር መምከራቸው ተገለፀ።(ባላገሩ ቴሌቪዥን ፣ነሃሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም)የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ የአሜ...
11/08/2025

ኢትዮጵያና አሜሪካ ሕገ ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ለመቆጣጠር መምከራቸው ተገለፀ።

(ባላገሩ ቴሌቪዥን ፣ነሃሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም)

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሕገ ወጥ ድንበር ተሻጋር የገንዘብ ማስተላለፊያ ግብይቶችን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህም በገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ላይ በሚደረገው ቁጥጥር ያላቸውን ትብብር ለማጠናክርና የገንዘብ ዝውውሩ በመደበኛ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ መከናወኑን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም ባንኩ አስታውቋል።

ዝነኛዋ አሜሪካዊት የፊልም ባለሙያ እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ አንጀሊና ጆሊ  የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኘች።(ባላገሩ ቴሌቪዥን ነሃሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም)አሜሪካዊት ተዋና...
11/08/2025

ዝነኛዋ አሜሪካዊት የፊልም ባለሙያ እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ አንጀሊና ጆሊ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኘች።

(ባላገሩ ቴሌቪዥን ነሃሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም)

አሜሪካዊት ተዋናይት፣ የፊልም ባለሙያ እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ አንጀሊና ጆሊ በትናንትናው ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎብኝታለች።

የተዋናይቷ ጉብኝት በዋነኝነት ሆስፒታሉ እየሰጠ በሚገኘው መድኃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ሕክምና ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ እንቅስቃሴዎችን፣ የሚታዩ ለውጦችን እንዲሁም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ እንደነበር ሆስፒታሉ አስታውቋል።

በጉብኝቱ ላይ አንጀሊና የሆስፒታሉን የቲቢና መድኃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ሕክምና አገልግሎት መስጫ ዋርድ፣ ላብራቶሪ እንዲሁም ታካሚዎችን ተዘዋውራ መመልከቷ ተገልጿል።

አንጀሊና ወደ ሆስፒታሉ ከረጅም ጊዜያት በፊት መጥታ እንደነበር ያስታወሰች ሲሆን፤ በአሁኑ ጉብኝቷ ላይ ሆስፒታሉ ዘርፈ ብዙ ለውጦች አምጥቶ በመመልከቷ እጅግ ደስተኛ መሆኗን ተናግራለች።

ኢትዮጵያን በአፍሪካ መድረክ የሚወክሉ ክለቦች ተጋጣሚያቸውን ለይተዋል!የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ፣የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ በአፍሪካ መድረ...
09/08/2025

ኢትዮጵያን በአፍሪካ መድረክ የሚወክሉ ክለቦች ተጋጣሚያቸውን ለይተዋል!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ፣የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን ይወክላሉ።

የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን ከዛንዚባሩ ምላንድጌ ክለብ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ያደርጋል።

Eth. Insurance 🇪🇹 🆚 Mlandege (Znz) የሁለቱ አሸናፊ ከኤፒአርና ፒራሚድ አሸናፊ ጋር ይደርሰዋል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ወላይታ ዲቻ ከሊቢያ ክለብ(ያልታወቀ) ጋር ተደልድሏል። የሁለቱ አሸናፊ የግብፁን አልማስሪ ይገጥማል።

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች መስከረም 9-11፤የመልስ ጨዋታዎች በሳምንቱ እንደሚካሄዱ የወጣው መርሀ ግብር ይጠቁማል።

ባላገሩ ስፖርት

ሀይቆቹ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል!የሀዋሳ ስፖርት ክለብ ቦርድ አመራር  ዛሬ  ማምሻውን ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስ...
08/08/2025

ሀይቆቹ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል!

የሀዋሳ ስፖርት ክለብ ቦርድ አመራር ዛሬ ማምሻውን ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።

አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በሀዋሳ ቤት አንድ አመት ውል ማግኘቱ ተገልጿል ። የሀዋሳን የእርከን ቡድኖች ያሰለጠነው ተመስገን ዳና በርካታ ታዳጊዎችን በማፍራት መልካም ስም አግኝቷል።

ወልቂጤ ከተማን ፣ኢትዮጵያ ቡናን በሊጉ ካሰለጠነ በኋላ የቀድሞ ቤቱን በዋና አሰልጣኝነት ተረክቧል። አሰልጣኝ ተመስገን ዳና የዋሊያዎቹ ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ እያገለገለ እንደሆነ ይታወቃል

ባላገሩ ስፖርት

በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታግዷል አለ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፡፡(ባላገሩ ቴሌቪዥን ፣ሀምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም)አገልግሎቱ ሕጋ...
08/08/2025

በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታግዷል አለ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፡፡

(ባላገሩ ቴሌቪዥን ፣ሀምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም)

አገልግሎቱ ሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓትን ወደ ጎን በመተው በሕገ ወጥ እና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል ላይ የተሰማሩ 138 ዋነኛ ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ መደረጉን አመልክቷል፡፡

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት በሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓት በኩል እንዲከናወን በግልጽ የተቀመጠ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ የምንዛሪ አገልግሎት ላይ የተሰማሩት ላይ ጠንካራ የሕግ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን ነው ያስገነዘበው፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በወንጀል ድርጊቱ ላይ ተሰማርቶ መገኘት የንብረት መወረስን ጨምሮ በከፍተኛ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ መደበኛ የባንክ ስርዓትን እንዲጠቀም በመንግስት በኩል ማሳሳቢያ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ሆኖም ግን አንዳንድ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀልን እንደ መደበኛ የንግድ ስራ በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በመሆናቸው ክትትል ሲደረግባቸው መቆየቱን አገልግሎቱ ለኢዜአ ገልጿል፡፡

በዚህ መሠረትም ክትትል ተደርጎ የተደረሰባቸው እና በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ላይ የተሰማሩ 138 ዋነኛ ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ ተደርጓል ነው ያለው፡፡

''እንደ አቶ እዮብ ማሞ ሌሎች ባለሀብቶች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን'' አቶ ባህሩ ጥላሁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሰሜን አሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታ ...
08/08/2025

''እንደ አቶ እዮብ ማሞ ሌሎች ባለሀብቶች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን'' አቶ ባህሩ ጥላሁን

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሰሜን አሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታ መልስ አስተዳደራዊ ጉዳይና ጨዋታውን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን፣የዋሊያዎቹ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በጋራ በሰጡት መግለጫ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

ጉዞው ውጤታማ ነበር ያሉት አቶ ባህሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ እዮብ ማሞ ካቻ በአዲስ አበባ አካዳሚ ለመክፈት በቅርብ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ገልጿል።

ጨዋታውን ለመመልከት በስታዲየም የተገኘው ተመልካች ከኮቪድ በኋላ ትልቁ ቁጥር መሆኑን የተናገሩት አቶ ባህሩ ፣ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራው ማህበረሰብ ለብሄራዊ ቡድኑ ቅርብ እንዲሆን የተለያዩ መልካም አጋጣሚዎች የተፈጠሩበት ነው ብለዋል።

4 ተጨዋቾች የሙከራ እድል እንዳገኙ ሲታወቅ ፣ መጀመሪያ 6 ተጨዋቾች ተመርጠው በእድሜ ምክኒያት የተቀነሱ እንደነበሩ ተነግሯል።

በቀጣይ ስምምነቱን ለማሳደግ እንደሚሰራ፤ በጉዞው አንድ የኪት ማናጀር ከቡድኑ መለየት ውጪ ያገጠመ ችግር አልነበረም ያሉት አቶ ባህሩ እንደ አቶ እዮብ ማሞ ካቻ የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው፤ ሌላ አንድ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ባለሀብት ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸው ግለሰብን ማግኝታቸውን አስታውቀዋል።

ባላገሩ ስፖርት

ሰባት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች  በየመን ባህር ላይ ሲሞቱ 250 የሚሆኑት ከአደጋው ተርፈዋል።(ባላገሩ ቴሌቪዥን ፣ሀምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም)ከ ሶማሊያ ወደ የመን በመጓዝ ላይ ከነበሩ ስደተኞ...
07/08/2025

ሰባት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመን ባህር ላይ ሲሞቱ 250 የሚሆኑት ከአደጋው ተርፈዋል።

(ባላገሩ ቴሌቪዥን ፣ሀምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም)

ከ ሶማሊያ ወደ የመን በመጓዝ ላይ ከነበሩ ስደተኞች መካከል ሰባት ኢትዮጵያውያን በረሃብና በውሃ ጥም መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።

ድርጅቱ፤ 82 ህጻናትን ጨምሮ 250 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነችው ጀልባ፣ ማክሰኞ ዕለት ደቡብ የመን በሚገኘው አርቃህ አካባቢ ደርሳለች ብሏል። ይሁን እንጂ “ሰባት ስደተኞች በመንገድ ላይ በረሃብና በጥም ሞተዋል” ሲል አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርጅቱ ትናንት ረዕብ ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ በየመን የሚገኙ ቡድኖቹ “ከቦሳሶ ሶማሊያ በመነሳት ከሰባት ቀናት አስከፊ ጉዞ የተረፉ ሰዎችን ህይወት አድን እርዳታ” ማድረጋቸውን ገልጿል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።

ከፈረንጆቹ 2025 መጀመሪያ ጀምሮ በምስራቁ መስመር ከ350 በላይ ስደተኞች መሞታቸውን እና ያሉበት አለመገኘቱን ገልጿል።

ከዚህ አደጋ ቀደም ብሎ እሁድ እለት 154 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ ሰጥማ 68 ሰዎች ህይወት አልፏል። 74 የሚሆኑት ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን የተመድ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።

አጫጭር  መረጃዎች...ሲቲ ካፕ መቼ ይካሄዳል ?የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የሲቲ ካፕ የክለቦች ውድድር ከመስከረም 3_18 በአዲስ አበባ ስታዲየም በአማራጭ  አበበ ቢቂላ ...
07/08/2025

አጫጭር መረጃዎች...

ሲቲ ካፕ መቼ ይካሄዳል ?

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የሲቲ ካፕ የክለቦች ውድድር ከመስከረም 3_18 በአዲስ አበባ ስታዲየም በአማራጭ አበበ ቢቂላ ላይ እንደሚደረግ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

6 የአዲስ አበባ ክለቦችና 2 ተጋባዥ ክለቦች እንደሚኖሩ ሲጠበቅ፤
የቀጥታ ስርጭት እንዲኖረው እየተሞከረ እንደሆነ ሰምተናል። ፌዴሬሽኑ በጉዳዩ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ በቅርብ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ቡና.....

ወጣቱ ተስፈኛ የመስመር አጥቂ ዘላለም አባተ ወላይታ ዲቻን ለቆ ለኢትዮጵያ ቡና ፈርሟል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ቡናዎች ኮንኩን ሀፊዝን ሸኝተው ሌላ ጎል አዳኝ አጥቂ ለማስፈረም አማራጮችን እየሞከሩ መሆኑን አውቀናል።

መቻል...

አሰልጣኝ ሙልጌታ ምህረት ሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ለቆ ለመቻል መፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ ፅፏል። ስለመረጃው ክለቡ በይፋ መግለጫ አልሰጠም አላሳወቀም ።

ባላገሩ ስፖርት

ሴናፍ ዋቁማ ከዲሲ ፖወር ክለብ የሙከራ እድል ቀረበላት!የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ  ሴናፍ ዋቁማ በዲሲ ዩናይትድ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ዲሲ ፓወር የሙከራ ጊዜ እንድታሳልፍ ጥሪ እንደቀ...
06/08/2025

ሴናፍ ዋቁማ ከዲሲ ፖወር ክለብ የሙከራ እድል ቀረበላት!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ሴናፍ ዋቁማ በዲሲ ዩናይትድ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ዲሲ ፓወር የሙከራ ጊዜ እንድታሳልፍ ጥሪ እንደቀረበላት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በሰሜን አሜሪካ በዲሲ ፓወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሎዛ አበራ እየተጫወተች እንደምትገኝ ይታወቃል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ የዲሲ ዩናይትድ ክለብ መልማዮች አራት ተጫዋቾች ቢንያም በላይ፣ ከነዓን ማርክነህ፣ ሀብታሙ ተከስተ ፣ ራምኬል ጀምስ በአሜሪካ MLS ፣ USL ለመጫወት የሙከራ እድል ማግኘት እንደቻሉም ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በዲሲ ዩናይትድ ፣ የሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ ክለቦች የሚታዩበትን እድል መፍጠር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ዲሲ ዩናይትድ ክለብ መካከል የተፈፀመው ስምምነት አካል እንደሆነም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

ባላገሩ ስፖርት

ሁለቱ የኢትዮጵያ ሴት ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ለኡጋንዳ ክለብ ፈርመዋል።በኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ፍሬው ሀ/ገብርኤል የሚመሩት የኡጋንዳ ካምፓላ  ኩዊንስ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን  መአድን ሳህሉና...
05/08/2025

ሁለቱ የኢትዮጵያ ሴት ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ለኡጋንዳ ክለብ ፈርመዋል።

በኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ፍሬው ሀ/ገብርኤል የሚመሩት የኡጋንዳ ካምፓላ ኩዊንስ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን መአድን ሳህሉና ቱሪስት ለማን ማስፈረማቸውን ክለቡ ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የዘንድሮ የኡጋንዳ ፉፋ ሱፐር ሊግ ሻምፒዮና የሆኑት ንግስቶቹ ሁለቱን የሉሲዎቹ ተጨዋቾች ያስፈረሙት መስከረም ወር ለሚጀምረው የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ጨዋታዎች ቡድኑን ተፎካካሪ ለመሆን እንደሚያግዙ ተገልጿል ።

ባላገሩ ስፖርት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሩሲያ አውሮፕላኖችን ሊያከራይ ነው በሚል  የተሰራጨውን መረጃ አስተባበለ።(ባላገሩ ቴሌቪዥን ፣ሀምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም)የአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የ...
05/08/2025

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሩሲያ አውሮፕላኖችን ሊያከራይ ነው በሚል የተሰራጨውን መረጃ አስተባበለ።

(ባላገሩ ቴሌቪዥን ፣ሀምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም)

የአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ማዕቀብ ምክንያት የአቪዬሽን ችግር ለገጠማት ሩሲያ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በኪራይ ለማቅረብ ውይይት እያደረገ ነው የሚል መረጃ ከሰሞኑ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲሰራጭ ቆይቷል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖቹን ለሩሲያ ለማከራየት አላሰበም።
ለዚህም ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶችን ሰጥተዋል። የመጀመሪያው፣ አየር መንገዱ ራሱ የአውሮፕላን ፍላጎት ስላለበት፣ ለሌሎች ለማከራየት የሚያስችል አቅም የለውም ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ የአሜሪካን ህግጋትን የማክበር ግዴታ ስላለበት ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።
በዓመቱ 6 ዓለም አቀፍ ጣቢያዎች መክፈት የቻለው አየር መንገዱ፥ 13 የተለያዩ አውሮፕላኖች ወደ ስራ አስገብቷል ብለዋል።
በ2017 በጀት ዓመት 19 ሚሊየን መንገደኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ መጓጓዛቸውን ነው የተናገሩት።
ከመንገደኞችና ዕቃ ጭነት አገልግሎትም 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱንም አመልክተዋል።
በዓመቱ በዘርፉ በርካታ አሉታዊ ክስተቶች መከሰታቸውን አንስተው በተለይም በተለያዩ ሀገራት በተፈጠረው ጦርነት በረራዎች ተስተጓጉለዋል ብለዋል።
አሁን ላይ የአየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎች 21 መሆናቸውን ጠቁመው፥ በቅርቡ የሚጠናቀቁ የ5 መዳረሻዎች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አየር መንገዱ በጭነት አገልግሎት 785 ሺህ 323 ቶን በላይ ካርጎ እንዳጓጓዘ ተናግረዋል።

ሰበር ዜና ...አፄዎቹ ትኩረታቸውን ወደ ካሳዬ አራጌ አድርገዋል !ከወጣቱ አሰልጣኝ አዲስ ወርቁ ጋር ስምምነት ላይ ያልደረሱት ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ አሁን ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ተወዳ...
05/08/2025

ሰበር ዜና ...

አፄዎቹ ትኩረታቸውን ወደ ካሳዬ አራጌ አድርገዋል !

ከወጣቱ አሰልጣኝ አዲስ ወርቁ ጋር ስምምነት ላይ ያልደረሱት ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ አሁን ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ተወዳጁ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ማድረጋቸውን አረጋግጠናል።

ለፋሲል ከነማ ክለብ የረጅም ጊዜ ውጤታማ መሆን በንቃት እተንቀሳቀሰ የሚገኘው የፋሲል ከነማ ስራ አመራር ቦርድ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን እያነጋገረ መሆኑን ባላገሩ ስፖርት አረጋግጧል።

የመጨረሻ ሙሉ ስምምነት ለማድረግ ጥረቶች ቀጥለዋል። በክለቡ ፍላጎትና በአሰልጣኙ ቅድመ ሁኔታዎች መሀል ያለውን አማራጮች አቀራርቦ ወደ ሙሉ ስምምነት ለማምጣት ክለቡ ተስፋ አድርጓል።

በአዲስ ሀይል በአሰልጣኝ ቅጥር ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት አፄዎቹ ካሳዬ አራጌን የግላቸው ለማድረግ የመጨረሻ ንግግሮች ቀርተዋል።

በተጨዋችነት ዘመኑ የጊዜው ድንቅ አማካይ ተጨዋች የነበረው ካሳዬ አራጌ ፣ታሪካዊውን የ1995 ኢትዮጵያ ቡናን ቡድን በማሰልጠን የጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሳክቷል። አሰልጣኝ ካሳዬ ኑሮውን በሰሜን አማሪካ አድርጎ በቅርብ የነገሰበት ኢትዮጵያ ቡና ክለብን ተመልሶ በመረከብ በሊጉ ማራኪ እግር ኳስ የሚጫወት ድንቅ ቡድን ማስተዋወቁ የቅርብ አመት ትውስታ ነው።

አሰልጣኝ ካሳዬ ከሰሜን አሜሪካ እየተመላለሰ በቅርብ የፋስት ትራክ የቢ ላይሰንስ በመውሰድ ራሱን ለክለብ ስራ ማዘጋጀቱ ይታወሳል።

በሊጉ ከፍተኛ የደጋፊዎች ትኩረት ካለባቸው ክለቦች አንዱ የሆነው ፋሲል ከነማ ከአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ጋር የመጨረሻ ስምምነት ለማድረግ ጥረቶቹ ቀጥለዋል ።

ባላገሩ ስፖርት

Address


Opening Hours

Monday 02:30 - 11:30
Friday 02:30 - 01:45

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Balageru TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Balageru TV:

Shortcuts

  • Address
  • Opening Hours
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share

Balageru TV

Balageru television, Television programming that promotes Ethiopian history, culture, tradition, lifestyle, investment, tourism, current affairs, sports, and entertainment.