Andnger አንድነገር

  • Home
  • Andnger አንድነገር

Andnger አንድነገር ጊዜው የመረጃ ነው ! የቴሌግራም እንዲሁም የዩትዩብ ገፃችንን ይከተሉን ።

10/09/2023
09/09/2023
አሳዛኝ ዜና !ከሁለት ሳምንታት ፍለጋ በኋላ ፖሊስ የዮሐንስ ኪዳኔን አስክሬን በሳንፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ ውሀ ላይ ተንሳፎ ማግኘቱን አስታውቋል😭😭😭😭************************...
07/09/2023

አሳዛኝ ዜና !
ከሁለት ሳምንታት ፍለጋ በኋላ ፖሊስ የዮሐንስ ኪዳኔን አስክሬን በሳንፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ ውሀ ላይ ተንሳፎ ማግኘቱን አስታውቋል😭😭😭😭
*******************************************************
ማክሰኞ ነሐሴ 29/2023 ቀን ከሳን ፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ ላይ በውሃ ውስጥ ምላሽ የማይሰጥ ሰው መታየቱን ጥቆማ ለመርማሪዎች ከደረሳቸው በኋላ አስክሬኑን ከውሀ ውስጥ ያወጡት ሲሆን የአስከሬን ምርመራው ውጤት አስከሬኑ የዮሐንስ ኪዳኔ መሆኑን አረጋግጧል።

የሞቱን መንስኤ ራስን ማጥፋት መሆኑን የማሪን ካውንቲ የሸሪፍ ጽህፈት ቤት ዛሬ ያስታወቀ ሲሆን የ22 አመቱ ወጣት የከባድ ጉልበት ጉዳት እና ውሀ ውስጥ መስጠም ለህይወቱ ማለፍ አስተዋፅኦ አድርጓል።

ዮሐንስ በቅርቡ ከኮርኔል ዩኒቨርስቲ ተመርቆ በታዋቂው ኔትፍሌክስ የሶፍትዌር ኢንጂነርነት ተቀጥሮ ለመስራት ከመጥፋቱ ሁለት ሳምንት በፊት ከኒውዮርክ መሄዱ ይታወቃል። ስልኮቹ እና የኪስ ቦርሳው ጎልደን ጌት ድልድይ አካባቢ ከጠፋ በኋላ ተገኝተው የነበረ ሲሆን ለመጨረሻ ግዜ የታየው ከሁለት ሳምንታት በፊት በኡበር ታክሲ ሲሳፈር ነው።

በትልቅ ተስፋ እና ፅናት ሲያፈላልጉት ለነበሩት ቤተሰቦቹ ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጥ።

ሰበር ዜና..!አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)  #ኢትዮሪካ የተሰኘ አዲስ አልበም ሊለቅ ነው!በቅርብ ቀን የሚወጣውን የተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ''ኢትዮሪካ '...
06/05/2023

ሰበር ዜና..!

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) #ኢትዮሪካ የተሰኘ አዲስ አልበም ሊለቅ ነው!

በቅርብ ቀን የሚወጣውን የተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ''ኢትዮሪካ '' አልበም በሰዋሰው መተግበሪያ እንደሚለቀቅ ተገልጿል።

ተደረሰለት! ዛሬ ጠዋት ላይ ራሱን በ Facebook Live ሊያጠፋ ቀጠሮ ይዞ የነበረው    …..ወዳጆቹ ደርሰው ሀሳቡን አስቀይረውታል።
01/05/2023

ተደረሰለት!

ዛሬ ጠዋት ላይ ራሱን በ Facebook Live ሊያጠፋ ቀጠሮ ይዞ የነበረው …..ወዳጆቹ ደርሰው ሀሳቡን አስቀይረውታል።

28/04/2023

😂😂😂😂😂

በታንዛኒያው የ " ሰላም ንግግር " ላይ እነማን እየተሳተፉ ነው ?በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው) መካከል ትላንት የሰላም ንግግር በታንዛኒያ ...
26/04/2023

በታንዛኒያው የ " ሰላም ንግግር " ላይ እነማን እየተሳተፉ ነው ?

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው) መካከል ትላንት የሰላም ንግግር በታንዛኒያ ከፊል ራስ ገዟ ዛንዚባር ተጀምሯል።

ኢጋድ ይሄ የሰላም ንግግር ወደ ፖለቲካ ስምምነት እንደሚያመራ ተስፋ እንዳለው በቃል አቀባዩ በኩል ገልጿል።

ለመሆኑ የታንዛኒያ የሰላም ንግግር ተሳታፊዎች / ተደራዳሪዎቹ እነማን ናቸው ?

ቢቢሲ በድርድሩ ስፍራ ይገኛሉ ያላቸውን ምንጮች ዋቢ በማድረግ ባወጣው ዘገባ ሁለቱም ተደራዳሪ አካላት ስድስት - ስድስት ተወካዮችን ልክው ድርድር እያደረጉ ናቸው።

ከነዚህም መካከል...

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ በፊት የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ለማስቆም ከህወሓት ጋር ሲደራደሩ ከነበሩት መካከል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን (የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ) እና ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (የፍትሕ ሚንስትር) መወከሉን ዘገባው ጠቁሟል።

በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በኩል የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን እና የጦሩ አዛዥ አማካሪ የሆኑት አቶ ጂሬኛ ጉደታ እና አቶ አብዲ ጣሃ የተባሉ ግለሰቦች ይገኙበታል።

በዚሁ ድርድር ላይ የኖርዌይ ፣ የኬንያ ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች እና የኢጋድ ተወካዮች እንደሚገኙ ቢቢሲ ለድርድሩ ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

እነዚህ አገራት በድርድሩ ላይ የሚኖራቸው ሚና እስካሁን ግልጽ አይደለም ።

ሀገሬ ኢትዮጵያ 🇪🇹💚💛❤️የት እንደሆነ የሚያውቅ Credit to
26/04/2023

ሀገሬ ኢትዮጵያ 🇪🇹💚💛❤️
የት እንደሆነ የሚያውቅ Credit to

ይህ የምትመለከቱት አዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ተወልዶ ያደገው ዮሴፍ ነው ዮሴፍ ባለትዳር እና የልጆች አባት ሲሆን  በጣም ጥሩ ኑሮ የሚኖር ብዙ ሀብት  ገልባጭ መኪና የነበረው ባለሀብት ነበ...
24/04/2023

ይህ የምትመለከቱት አዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ተወልዶ ያደገው ዮሴፍ ነው

ዮሴፍ ባለትዳር እና የልጆች አባት ሲሆን በጣም ጥሩ ኑሮ የሚኖር ብዙ ሀብት ገልባጭ መኪና የነበረው ባለሀብት ነበር። ዮሴፍ አንድ ቀን የተለመደ ስራውን ለመስራት መኪናውን ይዞ ለስራ እንደወጣ ሰው ገጭቶ ማረሚያቤት ገባ።

ዮሴፍ ቅጣቱን ጨርሶ ከማረሚያ ቤት ከወጣ በኋላ የነበረው ንብረት ሀብት እንደጠበቀው አላገኘውም። ዮሴፍ በዚህ ተስፋ ሳይቆርጥ ሰፈሩ መገናኛ አካባቢ ስለሆነ ታክሲ ተራ በማስከበር እና የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ቤተሰቡን ማስተዳደር ጀመረ።

ዮሴፍ ከለታት አንድ ቀን የተለመደ ስራውን ለመስራት በጠዋት ከቤት ሲወጣ የሙዝ ልጣጭ አንሸራቶት ለውሀ ታንከር የተቆፈረ ገደል ውስጥ ወድቆ ተሰብሮ ለብዙ ጊዜ ሲሰቃይ ያዩ ሰዎች ወደ መቄዶንያ እንዲገባ ባደረጉት ጥቆማ ወደ መቄዶንያ ሲገባ መንቀሳቀስ መጉረስም ሆነ መፀዳዳት አይችልም ነበር ።

ዮሴፍ የሚመገበው በሰው እጅ የሚፀዳዳው በዳይፐር ነበር። ጆሲ በሁለት አመት በተደረገለት እንክብካቤ፣ ህክምና እና ቤተሰባዊ ፍቅር ከሞት አፋፍ ፈልቅቆ ወደ ቀድሞው ጤንነት በመመለስ በዛሬው ዕለት ወደ ቤተሰቦቹ ተቀላቅሏል።

ዮሴፍ መቄዶንያ በነበረበት ጊዜ እጅግ ለተንከባካቢ ምቹ ባህሪ አመስጋኝ እና የተደረገልኝ ከመጠን ያለፈ ነው ብሎ የሚያስብ ትህትናው ደስ የሚል ወንድማችን ነው።

መልካም የስራ ዘመን ዮሴፈ
መቄዶኒያ

24/04/2023
ኑሮ ገና ብዙ ያስበላናል 20 ብር ነውSource: Dagmawi Belay
23/04/2023

ኑሮ ገና ብዙ ያስበላናል 20 ብር ነው
Source: Dagmawi Belay

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Andnger አንድነገር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share